Ethio Job Vacancy
45.1K subscribers
23.2K photos
63 videos
157 files
19K links
አዳዲስ እና ወቅታዊ የሥራ ቅጥር ማስታወቂያዎችን ከተለያዩ ጋዜጦችና ድረ ገጾች ለሥራ ፈላጊዎች መረጃ መስጠት ነው።
Post New Job vacancies to Who are looking jobs.
Group discussion https://t.me/+uGe3tVg5jF4yZjk0
Download Telegram
ክፍት የስራ ማስታወቂያ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ ባለው ክፍት የስራ ቦታ በህግ ትምህርት የመጀመሪያ ዲግሪና ከዚያ በላይ ያላቸውን በዜሮ አመት የስራ ልምድ እና ከአምስት አመት በላይ የስራ ልምድ ያላቸውን ሙያተኞች አወዳድሮ መቅጠር ስለሚፈልግ ተወዳዳሪዎች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 30 ቀናት ልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 ሜክሲኮ ማይጨው ክሊኒክ ጀርባ በሚገኘው ፍትህ ቢሮ አቃብያነ ህግ ጉባኤ 5ኛ ፎቅ በአካል ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው አማካኝነት መመዝገብ ይችላሉ፡፡

#መመዝገቢያ መስፈርቶች
1ኛ ኢትዮጵያዊ የሆነች/የሆነ በኢትዮጵያ የሚኖር
2ኛ ለህገመንግስቱና ለህግ የበላይነት ተገዥ  የሆነ
3ኛ የየትኛውም ፖለቲካ ድርጅት አባል ያልሆነ/ች  እና ወንጀል ቅጣት የሌለበት፡፡
4ኛ በታታሪነቱ/ቷ/ በስነምግባሩ/ሯ መልካም ስም ያተረፈ/ች/ ማስረጃ  ማቅረብ  የሚችል/የምትችል/
5ኛ ከከፍተኛ የትምህርት ተቋም በህግ ትምህርት የመጀመሪያ ዲግሪና ከዚያ በላይ የተመረቀ/ች
6ኛ የስራ ልምድ ዜሮ አመት በ2015 እና በ2016 የትምህርት ዘመን ተመራቂ ሆነው የመውጫ ፈተና ወስደው ያለፉ ለወንዶች የመመረቂያ ነጥባቸው 3.5 እና ከዚያ በላይ ለሴቶችና ለአካል ጉዳተኞች 3.25 እና ከዚያ በላይ
7ኛ ተፈላጊ የሰው ብዛት /15/ አስራ አምስት
8ኛ ከአምስት ዓመት በላይ የስራ ልምድ ላላቸው በአቃቢ ህግነት፣ በዳኝነት ፣ በህግ ምርምር ፣ በመምህርነት እና በተመራማሪነት ያገለገለ/ች/ እንዲወዳደሩ ይጋብዛል፡፡
9ኛ ተፈላጊ የሰው ብዛት ከአምስት ዓመት በላይ ላገለገሉ 10/አስር
10ኛ ደመወዝ በተቋሙ ስኬል መሰረት
11ኛ የስራ ቦታ ቢሮው በሚሰጠው ምደባ ቦታ፣

ተመዝጋቢዎች /ተወዳዳሪዎች/ ለምዝገባ ሲመጡ ሊያሟሏቸው የሚገቡ ሰነዶች   ኢትዮጵያዊ መሆናቸውን የሚገልፅ መታወቂያ ፓስፖርት የትምህርት ማስረጃቸውን ዋና ከማይመለስ ፎቶ ኮፒ ጋር ከምትኖሩበት አካባቢ አግባብነት ካለው አካላት የተፃፈ የስነምግባር ማስረጃ፣
የምዝገባ ቦታ ልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 ሜክሲኮ በሚገኘው ፍትህ ቢሮ አቃብያነ ህግ ጉባኤ 5ኛ ፎቅ በአካል ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው አማካኝነት መመዝገብ ይችላሉ፡፡

ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ እሁድ መስከረም 12ቀን 2017ዓ.ም በሚለው እትም ወጥቷል።

ለተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር ፡- 0115159550 /  0115159548
    
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ