GDG On Campus AASTU
4.83K subscribers
861 photos
52 videos
24 files
603 links
Google Developers Group On Campus for Addis Ababa science and Technology University.

Discussion group: @DSCAASTUCHAT
twitter handle: @gdscaastu
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/gdgaastu
Download Telegram
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA
#የኢትዮጵያልጆች👏

ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች በቻይና የሁዋዌ " ቴክፎርጉድ ግሎባል " ውድድርን #አንደኛ በመሆን አሸነፉ።

የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የሁዋዌ ሲድስ ፎር  ዘ ፊውቸር ቴክ ፎር ጉድ ግሎባል ውድድርን አንደኛ በመሆን አሸንፈዋል።

ውድድሩ ከመጋቢት 29 እስከ ሚያዝያ 9 ቀን 2017 ዓ.ም የቆየ ሲሆን በቻይና ቤጂንግ እና ሼንዘን የሚገኙ የቴክኖሎጂ ማዕከሎችን ጉብኝትና የተግባር ስልጠናዎችን ካካተተው ዝግጅት ጋር የተካሄደ ነው።

በስድስት ተማሪዎች የተወከለው የኢትዮጵያ ቡድን ተማሪዎቹን ፦
➡️ ከአዲስ አበባ፣
➡️ ከሐረማያ፣
➡️ ከጅማ፣
➡️ ከወልቂጤ 
➡️ ከአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ (AASTU) ዩኒቨርስቲዎች ነው ያሰባሰበው።

ቡድኑ በውድድሩ ከሞሮኮ፣ ደቡብ አፍሪካ፤ አርጀንቲና አየርላንድ፣ ማላዊ፣ ቬትናም፣ አረብ ኤምሬትስና ሌሎችን ጨምሮ ከዓለም ዙሪያ ከተውጣጡ 12 ልዩ ቡድኖች ጋር ተወዳድሯል።

የሲድስ ፎር ዘ ፊውቸር ግሎባል አምባሳደር የሆነችው ኢትዮጵያዊቷ ተማሪ አሲያ ከሊፋም በዝግጅቱ በእንግድነት ተገኝታለች።

ተማሪዎቹ በምን ፕሮጀክት አሸነፉ ?

ተማሪዎቹ የእንስሳትን ህመሞች አስቀድሞ ለመለየት በተዘጋጀውና በአርተፊሻል አስተውሎት (AI) በጎለበተው ኤርሊ ቬት (EarlyVet) በተሰኘው ፕሮጀክታቸው ነው የተወዳደሩት። በዚህም ትኩረት ለመሳብ ችለዋል።

ይህ የፈጠራ ፕሮጀክት ከተባበሩት መንግስታት የዘላቂ ልማት ግቦች (SDGs) በተለይም ግብ 2 " ዜሮ ርሃብ " እና ግብ 15 " ህይወት በምድር " ከሚለው ጋር የተጣጣመ መሆኑና በግብርና እና በእንስሳት ጤና ላይ ያሉ ወሳኝ ተግዳሮቶችን ይፈታል ተብሎ እንደሚታመን በውድድሩ ተብራርቷል።

የሁዋዌ ኢትዮጵያ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ሚስተር ሊሚንግ ዬ ምን አሉ ?

ዳይሬክቱ ፥ በቡድኑ ስኬት የተሰማቸውን ደስታ ገልጸው " ድሉ የኢትዮጵያውያን ወጣቶች ልዩ ችሎታ እና ፈጠራ የታየበት ነው " ብለዋል።

መጪው ትውልድ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ በመጣው የቴክኖሎጂ ገጽታ ውስጥ እንዲበለጽግ በሚያስፈልገውን ድጋፍ እና እድሎች ማመቻቸቱን ለማስቀጠል ሁዋዌ ቁርጠኛ መሆኑን ገልጸዋል።

ቡድኑ ለዓለም አቀፋዊ ውድድር እድል ያገኘው  በግንቦት 2016 ዓ.ም በኤሳውራ ሞሮኮ በተካሄደው የክፍለ አህጉራዊ የቴክፎርጉድ (Tech4Good) ውድድር ወቅት ከ17 የአፍሪካ ሀገራት ከተውጣጡ 28 ቡድኖች ጋር ተወዳድሮ አንደኛ በመውጣቱ ነው።

መረጃው ከሁዋዌ ኢትዮጵያ የተላከ ነው።

@tikvahethiopia