Afar Mass Media Agency (AFMMA)
1.09K subscribers
3.65K photos
161 videos
2 files
655 links
This channel is an official channel of Afar Mass Media Agency (AFMMA).
AFMMA is an autonomous government organization accountable to the regional Council of the Afar region.
Download Telegram
#የገንዘብ ሚኒስቴር ከዓለም ባንክ ጋር የ405 ሚሊዮን ዶላር የድጋፍ ስምምነት ተፈራረመ

ሰመራ-ሰኔ 10, 2014 (አፋ.ብ.መ.ድ)

የገንዘብ ሚኒስቴር ከዓለም ባንክ ጋር የ405 ሚሊዮን ዶላር የድጋፍ ስምምነት ተፈራረመ፡፡

ስምምነቱን የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ ከዓለም ባንክ የኢትዮጵያ ተወካይ ኦስማን ዲዬ ጋር ተፈራርመዋል፡፡

ገንዘቡ ለአርብቶ አደርና ደረቃማ አካባቢ የከርሰ ምድር ውሃ ልማት እንዲሁም የኮቪድ 19 ወረርሽኝን ለመከላከል እንደሚውል ነው የተገለጸው፡፡

በዚህም 210 ሚሊዮን ዶላሩ በአርብቶ አደርና ደረቃማ አካባቢ የከርሰ ምድር ውሃ ልማት የሚውል ሲሆን ቀሪው ደግሞ የኮቪድ 19 ቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከል ይውላል መባሉን ኢዜአ ዘግቧል።