#ሠመራ ዩኒቨርሲቲ እና አዋሽ ባንክ በጋራ ለመስራት የሚያስችል ስምምነት ተፈራረሙ፣፣
ሰመራ-ግንቦት 09/2014 (አፋ.ብ.መ.ድ)
ሠመራ ዩኒቨርሲቲ እና አዋሽ ባንክ በጋራ ለመስራት የሚያስችል ስምምነት ተፈራረሙ፣፣
ሠመራ ዩኒቨርሲቲ ለምምህራን ለቤት ግንባታ፣ ለመኪና እና ለቤት እቃዎች ግዥ የሚሆን ብድር ለማመቻቸት የሚያስችል ስምምነት ግንቦት 10/2014 ከአዋሽ ባንክ ጋር ተፈራርሟል፡፡
የጋራ ስምምነቱ የዩኒቨርሲቲውን መምህራን የቤት እና የተሽከርካሪ ባለቤት የሚያደርግ ብድር የሚያመቻች እና ዩኒቨርሲቲው ለሚሰራቸው ሰፋፊ የገቢ ማመጫ ስራዎች የሚያግዝ እንደሆነ ታውቋል፡፡
በስምምነቱ ላይ ንግግር ያደረጉት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር መሀመድ ኡስማን ስምምነቱ ለረጅም ጊዜ የመምህራን ጥያቄ የነበረውን የመኖሪያ ቤት እና የተሸከርካሪ ፍላጎት ለመፍታት የታለመ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
ፕሬዝዳንቱ አያይዘውም መምህራን ትኩረታቸውን በምርምር እና በማስተማር ላይ እንዳደርጉ ለማሽቻል ዩኒቨርሲቲው ካቀዳቸው ምቹ የስራ አካባቢ የመፍጠር እቅዶች አንዱ አካል ነው ብለዋል፡፡ በቀጣይም ለአስተዳደር ሰራተኞች ቤት መስሪያ የሚሆን ቦታ ለማግኘት ከከተማ አስተዳደሩ ጋር እየተነጋገሩ እንደሆነ ገልፀዋል፡፡
የአዋሽ ባንክ የደሴ ሪጅናል ዳይሬክተር አቶ ኤልያስ እሸቱ በበኩላቸው ባንኩ ስምንት ከሚሆኑ ተመመሳሳይ የመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጋር እንደዚሁ አይነት ስራ እየሰራ ስለሆነ ለሠመራ ዩኒቨርሲቲም ከነበረው በተሻለ ለመስራት እንደሚፈልጉ ገልፀዋል፡፡
ስራውን ሲያስተባበሩ የነበሩት አቶ ዳውድ አህመድ በበኩላቸው ይህ ስምምነት ለሠመራ ዩኒቨርሲቲ መምህራን መልካም አጋጣሚ ነው ብለዋል፡፡ ስራውን ለመስራት በተደረገላቸው ግብዣ በርካታ ባንኮች ቢቀርቡም አዋሽ ባንክ በወለድ አልባም በወለድም ያቀረበው አማራጭ የተሻለ ስለነበር አሸናፊ ሆኖ ለስምምነት ተደርሷል ብለዋል፡፡ ይህ ስምምነት ዩኒቨርሲቲው እና ባንኩ ዋናውን ፊርማ ከተፈራረሙ ብኋላ በፍጥነት ወደተግባር ይገባል የሚል ተስፋ እንዳላቸው ተናግረዋል፡፡
የዩኒቨርሲቲ የኢንተርፕራይዝ ዳይሬክተር ዶ/ር አህመድ አብዱለጢፍ በበኩላቸው የዛሬው ፊርማ ዩኒቨርሲቲው ላቀደው ዘርፈብዙ የገቢ ማመንጫ ስራዎች አጋዥ ሃይል የሚሆን እና ሁለቱንም የሚጠቅም ስምምነት ነው ብለዋል፡፡ አያይዘውም የመኖሪያ ቤት እና ተሸከርካሪ ለመምህራኑ መሰረታዊ ፍላጎት በመሆኑ እድሉን መጠቀም አለበት ሲሉ አደራ ብለዋል፡፡
#ምንጭ: በሰመራ ዩኒቨርሲቲ የህዝብና አለም አቀፍ ግንኙት ዳይሬክቶሬት