#እንኳን ለ1442ኛው ኢድ አልፈጥር በአል አደረሳችሁ ፡፡
ለመላው እስልምና እምነት ተከታዮች ለ1442ኛው ኢድ አል-ፈጥር በአል በሰላም አደረሳችሁ የአፋር ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት በዕለቱ የሃይል መቆራረጥ ችግር ለመፍታት የተለያዩ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን አከናውኗል ፡፡
በዋዜማና በበአሉ ወቅት የኤሌክትሪክ ሃይል ሳይቆራረጥ ለደንበኞች ለማቅረብና ችግሩ ከተከሰተ ደግሞ በተገቢው መንገድ ፈጣን ምላሽ ለመስጠት የሚያስችል የዝግጅት ስራ አከናውኗል፡፡
ያልተቆራረጠ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ለማድረስ አስቀድሞ ስራዎች የተሰሩ ቢሆንም ከበአሉ ጋር ተያይዞ የመቆራረጥ ጫናውን ለመቀነስ ተከታታይነት ያላቸው ስራዎችን በመስራት ላይ ይገኛል ፡፡
ሆኖም መሰል ዝግጅቶች ቢደረጉም የሃይል መቆራረጥ ሊያጋጥም ስለሚችል ይህንን ችግር ለመቀነስ ደንበኞች በቤት ውስጥ የሚጠቀሟቸው የኤሌክትሪክ ቁሳቁሶች ሃይል ቆጣቢ ሊሆኑ ይገባል ፡፡
ድንገተኛ የኤሌክትሪክ መቆራረጥ ቢያጋጥ ተቋሙ በስሩ ባሉት የአገልግሎት መስጫ ማዕከላትና በክልል ደረጃ ችግሩ ሊፈቱ የሚችሉ ግብረ ሃይል ያቋመ ሲሆን ደንበኞች በአቅራቢያችሁ ወደሚገኝ አገልግሎት መስጫ ማዕከላት በአካል በመቅረብ ታች በተዘረዘሩት የስልክ ቁጥሮች ጥቆማ ማድረስ የምትችሉ መሆኑን ለመግለፅ እነወዳለን ፡፡
መልካም የኢድ አል-ፈጥር በአል
1. ሠመራ ---------- 0910123048/0913002162
2. ሎጊያ ----------- 0947625666/0913628334
3. ዲችኦቶ --------- 0910221666/0910105630
4. ሚሌ ----------- 0929042401/0914326600
5. ገዋኔ ----------- 0911813394/0913164736
6. አዋሽ 7-------- 0911270506/0914714844
7. አብኣላ -------- 0914045138/0914417912
8. በራሀሌ -------- 0935809972
9. ጭፍራ -------- 0911271135/0913808272
10. ከልዋን -------- 0919101268/0912120347
11. ሱኑታ --------- 0962628866/0953824085
12. ወረር --------- 0931294869/0910385393
13. ኤሊውሃ ------ 0983181211/0964278465
14. ዱብቲ -------- 0972338769/0910470594
15. አይሳኢታ ------ 0920098082/0922615898
16. ተላላክ ------- 0920779957/0921232944
#Via Ethiopian Electric Utility, Afar branch.

#እንኳን ለ 2014 አዲስ አመት በሰላም አደረሳቹህ አደረሰን!
ለመላው የክልላችን ህዝብ እንዲሁም በሀገር ውስጥም ሆነ ውጭ የምትገኙ ኢትዮጵያውያን በሙሉ እንኳን እንደ ኢትዮጵያ አቆጣጠር ለ 2014 አዲስ አመት እንኳን አደረሳቹህ አደረሰን።
አዲሱ አመት የሰላም የብልፅግና የእድገት እንዲሁም የመተሳሰብ እና ሁሉም ዜጋ በጋራ ተሰልፎ ሀገራችንን ወደተሻለ ከፍታ የምናሸጋግርበት አመት እንዲሆንልን እመኛለሁ።
ያሳለፍነው 2013 አመት አሮጌው ተብሎ ቢያልፍም በርካታ መልካም ነገሮችን እንዲሁም በርካታ የሆኑ ችግሮችን ያሳለፍንበት አመት ነበር። በሀገራችን የተጀመረውን ለውጥ በተሻለ ሁኔታ ለማሳለጥና በተለያዩ ዘርፎችም አዎንታዊ ለውጥ ለማምጣት ጥረት ተደርጎ መልካም ውጤት ያስመዘገብንበት አመት ነበር።
በ 2013 የክልላችንን ህዝብ የለውጡ ተቋዳሽ እንዲሆን በተለያዩ መሰረተ ልማት ዘርፎች ተጠቃሚ እንዲሆን በተለይም መንገድ፣ ውሃ፣ የተለያዩ የማህበራዊ አገልግሎት መስጫ ተቋማትን በመገንባት እና ተጀምረው የነበሩትም እንዲጠናቀቁ በማድረግ ለህዝባችን አገልግሎት እንዲሰጥ ተደርጓል።
በክልላችን በተወሰኑ አካባቢዎች ይታይ የነበረው የፀጥታ ችግር ዘላቂ መፍትሄ እንዲያገኝ አርብቶ አደር ህዝባችን ተረጋግቶ በሰላም እንዳይኖር ሰርገው እየገቡ የነበሩ ፀረ ሰላም ሀይሎች ጉዳይ ዘላቂ መፍትሄ እንዲያገኝ ሁሉን አቀፍ የሆነ የህዝባችንን ጥቅም ባስከበረ መልኩ በመንቀሳቀስ በ 2013 አመት አመርቂ ውጤት ሊመዘገብ ችሏል።
በጥቅሉ ሰላምን አስመልክቶ ህዝባችን ለሰላም ያለው ትልቅ ቦታ ክልላችን ሰላማዊ እንዲሆንና የሰላም አምባሳደር እንዲሆን ያስቻለ በዘሩ እና በማንቱ ምክንያት አንድም ሰው ያልተፈናቀለበት ሰላማዊ ክልል መሆኑን ዳግም ማስመስከር ተችሏል።
በኢንቨስትመንት እና በግብርናው ዘርፍም በርካታ ኢንቨስተሮች ወደ ክልሉ እንዲገቡ ተደርጎ በልማት ስራ እየተሳተፉ የሚገኝ ሲሆን የተለያዩ ፋብሪካዎች ተከፍተው ስራ ጀምረዋል በግብርናው ዘርፍ በተለይም የቆላ ስንዴ ምርት በክልላችን እንዲመረት ሆኖ አመርቂ ማግኘት ተችሏል። ለበርካታ ወጣቶች የስራ እድል በመክፈትና ኢንቬስተሮችን መሳብ የሚችለው የሰመራ ኢንዱስትሪ ፓርክ የመጀመሪያ ምዕራፍ ተጠናቆ ለስራ ክፍት መሆኑ ሌላኛው የ 2013 መልካም ስኬት አንዱ ነው።
በጤናው ዘርፍም የጤና አገልግሎት ሰጪ ተቋማት እንዲጠናከሩ ፣ የጤና ኤክስቴንሺን መርሀ ግብር ውጤታማ በሆነ መልኩ ተፈፃሚ እንዲሆን መከላከልን መሰረት ያደረገ የጤና አገልግሎት እንቅስቃሴ በውጤታማ መልኩ ተከናውኗል።
በትምህርት ዘርፍም የክልላችን ትምህርት ስርአት በተሻሻለ መልኩ እንዲካሄድና በሀገር አቀፍ ደረጃ የወጣው የትምህርትና ስልጠና ፍኖተ ካርታን መሰረት ያደረገ ስርአተ ትምህርት ቀረፃ በተሻለ ሁኔታ የሄደበት ትምህርት ጥራት ባለው መልኩ ለሁሉም ዜጎች ተደራሽ ለማድረግ መንግስት ከተለያዪ ግብረ ሰናይ ድርጅቶች ጋር በመተባበር በርካታ ስራዎች ተከናውነዋል።
በዲሞክራሲያዊ ስርአት ግንባታው ዘርፍ በሀገራችን በአይነቱ የመጀመሪያ የሆነው ዴሞክራሲያዊ ምርጫ በክልላችንም ተካሂዶ ዜጎች በሰላማዊ መንገድ ይበጀናል የሚሉትን የመረጡበት ፣ ህዝባችንም ሰላም ወዳድ መሆኑን ዳግም ያስመሰከረበት ሆኖ አልፏል።
በተፃራሪው ደግሞ 2013 አመት በአለም አቀፍ ደረጃ የደረሰው ወርሺኝ ኮሮና፣ በክልላችን ተከስቶ የነበረው የጎርፍ አደጋ፣ አሸባሪው ህወሀት ደግሞ የሀገሪቱን ሰላም የተፈታተነበት እንደ አፋር ክልልም በፈንቲ ረሱ ዞን ሰርጎ በመግባት በርካታ ንፁሀንን በመጨፍጨፍ እንዲሁም ደግሞ በኪልበቲ ረሱ በራህሌ ወረዳ በኩል ወረራ ለማድረግ ሙከራ ያደረገበት አመት ነበር። አሸባሪው ህወሀት በክልላችን በርካቶችን ጨፍጭፎ "የታላቋ ትግራይን" ለመመስረት በርካታ ንብረቶችን በማውደም አውዳሚ አሸባሪ እንዲሁም ለአፋር ህዝብ እና አጠቃላይ ለኢትዮጵያ ህዝብ ያለውን ጥላቻ ያሳየበት እንዲሁም የክልላችን ህዝብም አሸባሪው ህወሀትን ለመመከት ታግሎ ከወረራቸው አካባቢዎች በማስለቀቅ ድል የተመዘገበበት አመት ነበር።
በ2013 አመት የተገኙ መልካም ውጤቶችን በመቀመር እንዲሁም ያጋጠሙን የሆኑ ሰው ሰራሽ እና ተፈጥሯዊ ችግሮችን ትምህርት በመውሰድ 2014 አመትም ህዝባችንን ሰላሙ የተጠበቀ ፣ ለልማት የሚተጋና በመረጠው አስተዳዳሪዎቹ በመተዳደር ወደ ከፍታ ለመውጣት ሁሉም ዜጋ ወንድ ሳይል ሴት ትንሽ ሳይል ትልቅ፣ እንዲሁም አካል ጉዳት ያላቸው እና የሌላቸው ሁሉም በጋራ አሻራቸውን የሚያሳርፉበት እንዲሁም የተለያዩ የመልካም አስተዳደር ችግሮች የሚቀረፉበት፣ መንግስትና ህዝብ በጋራ የሚሰሩበት አመት እንዲሆን እመኛለሁ።
እያንዳንዱ የክልላችን ነዋሪ ለክልሉ ብሎም ለኢትዮጵያ ብልፅግና የሚጠበቅበትን በመወጣት ፣ ሊያገኝ የሚገባው ሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች ተጠብቀውለት አመቱ የሰላም እና የብልፅግና እንዲሆን ጥረት ሊያደርግ ይገባል።
በመጨረሻም በድጋሚ አዲሱ አመት የአሮጌው አመት ችግሮቸና ተግዳሮቶችን አራግፈን አዲስ ተስፋ አዲስ ራዕይ የምንሰንቅበት ብሩህ አመት እንዲሆንልን እመኛለሁ።
መልካም አዲስ አመት!
አቶ አወል አርባ ኡንዴ
የአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ፕሬዝዳንት

#እንኳን ደስ አለን፣፣
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት ምስረታ የእንኳን ደስ አላቹህ መልዕክት
የአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በ 11ኛው አዲሱ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት ምስረታ የተሰማውን ደስታ በአፋር ህዝብ እና መንግስት ስም ይገልፃል።
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች እውነተኛ ዴሞከራሲን መሰረት በማድረግ በተካሄደው የህዝበ ውሳኔ መሰረት በሰጡት ድምፅ 11ኛው ክልል ሊመሰረት ችሏል፣ ይህም በአጠቃላይ እንደ ሀገር በኢትዮጵያውያን የመጣው ለውጥ ፍሬ አንዱ ሲሆን በዚህም የስም ብቻ ሳይሆን እውነተኛ ራስን በራስ የማስተዳደርን መብት ተግባራዊ የተደረገበት ወሳኝ ምዕራፍ ነው።
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ማለትም የምዕራብ ኦሞ፣ የቤንች ሸኮ፣ የከፋ፣ የዳውሮ፣የሸካ ሕዝቦችና የኮንታ ልዩ ወረዳ ነዋሪዎች 11ኛውን ክልል ለመመስረት በተካሄደው ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ ምርጫ ክልሉን ለመመስረት ስለበቃቹህ የተሰማን ደስታ ላቅ ያለ ነውና እንኳን ደስ ያለን እንኳን ደስ ያላቹህ እንላለን።
ሀገራችን ኢትዮጵያ ከየትኛውም ጊዜ በበለጠ ሀገርን የማዳን ዘመቻ ላይ በምትገኝበት በዚህ ወሳኝ ወቅት የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በሰላማዊ መንገድ ተመስርቶ የፌደሬሽኑ 11ኛ አባል ክልል በመሆን እውነተኛ ፌደራሊዝምን እውን ማድረግ መቻሉ ደስ የሚያሰኝ ሲሆን እንደ ሀገር የሚጠበቅብንን ኃላፊነትም ከሌሎች ክልሎች ጋር በጋራ በመሆን በጋራ መንፈስ እንደምንሰራ ተስፋ እናደርጋለን።
የአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስትና ህዝብም አዲስ ከተቋቋመው
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ጋር በተለያዩ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊ እና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች በጋራ በትብብር ለመስራት ዝግጁ መሆኑን እየገለፅን በድጋሚ ለክልሉ ምስረታ ስለበቃቹህ እንኳን ደስ አለን፣ እንኳን ደስ አላቹህ እንላለን።
እውነተኛ ፌደራሊዝም ለወንድማማችነትና ለጋራ እድገት!
የአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት
ሰመራ
ህዳር 14/2014

#እንኳን ለ126ኛው የአድዋ ድል በዓል አደረሰን
አድዋ ለእኛ ኢትዮጵያዊያን ህብረታችንን ያሳየንበት ለአፍሪካውያን ጮራ የፈነጠቅንበት ታሪካዊ በዓላችን ነው!
አድዋ የመላው ኢትዮጵያዊያን ብሎም የአፍሪካውያን የነፃነት ተምሳሌትነት የተረጋገጠበት ታሪካዊ ኩነት ነው።ቀደምት አያቶቻችን የውስጥ ልዩነቶቻቸውን አቻችለው ሽኩቻቸውን ወዲያ አሽንቀጥረው ከፊት ለፊት ሊገዛቸው የመጣውን ወራሪ ሀይል በአንድነት በመሆን አሳፍረው የመለሱበት እና የጥቁር ህዝቦች ማንነትን በደማቸው ጭምር በመሰዋት እንዲረጋገጥ ያደረጉበት ነው ።
የአፋር ህዝብም እንደመላው ኢትዮጵያዊያን ሁሉ ድንበር አልፎ የመጣን ወራሪ ቀድሞ በማሳፈር በሚታወቀው ማንነቱ የውጭ ሀይሎች በመመለስ የአገር ዋልታነቱን ገና በጧቱ ያሳወቀ ህዝብ ነው።፤ከመላ ኢትዮጵያውያን ጋር ሁኖ የአልበገር ባይነት የእምቢተኝነት ድምፁን አሰምቶ ወራሪ ሀይል በመመለስ የኢትዮጵያን ልክ በተግባር ያረጋገጠበት ነው።
አድዋ በህብረት በአንድነትና በመተባበር የአሸናፊነት ስሜትን ማጎልበት እንደሚቻል ያሳወቅንበት ፣በማንነታችን ለመጣ በህብር ተሳስረን ለመመለስ ከቶውንም አንዳች ነገር የማያደናቅፈን የማናገራግር ቁርጠኞች መሆናችንን ያስመሠከርንበት የቃል ኪዳናችን መሰረት ነው።
ድንበር ጠባቂው ህዝባችን በፍጹም ኢትዮጵያዊነት እየተቃኘ ላለፉት በርካታ ዓመታት የውጭ ወራሪ ሀይሎችን አሳፍሮ ስለመመለሱ በታሪክ መዛግብት ተሰንዶ ይገኛል ።ባህር በራችን አልፎ የመጣውን ጠላት ሲመክት ሲከላከል እና ሲቃወም የኖረ ቀዳሚ ህዝብ ነው፤ከነባራዊው መልክዓ ምድራዊ ገፅታ በመነሳት የውጭ ሀይሎች የተለያዩ ጫና ቢፈጥሩበትም ሳይበገር የቆየ ህዝብ መሆኑ እነዚህ መረጃዎች ዛሬም አፍ አውጥተው ይናገራሉ ።
በአገሩ ና በመሬቱ ድርድር የማያውቀው ህዝባችን ከመላ ኢትዮጵያዊያን ጋር በመሆን የኢጣልያ ወራሪ መመከቱ ከቅድመ አያቶቹ የወረሰው የጀግንነት ተጋድሎ ደማቅ ታሪክ ጉልህ ማሣያችን ነው።
አገራችን ኢትዮጵያ በአፋር በኩል ተደፍራም ተወራም እንደማታውቅ የሚናገረው የጎመራ ታሪካችን አፋር በታሪኩ ምዕራፍ ሁሉ እንደ ህዝብ የባንዳነት ሚና ያልነበረውና በምንም ነገር ተደራድሮ አገሩን ለገበያ ያላቀረበ ህዝብ መሆኑን የታሪክ ድርሳናት የሩቁንም የቅርቡንም ዘግበውት ይገኛል ።
አድዋ የማንነታችን ማረጋገጫ የእኛነታችን ማሳያ የሆነው ክቡር ተጋድሎ የተደረገበት ከመሆኑም ባሻገር በዘር በቀለም ላይ ለተመሰረተው ቅኝ ገዥነት ሰብሮ የጥቁር ህዝቦችን የሞራል ከፍታ ያነሳሳ፣ የድል ጮራን የፈነጠቀ ፣የዘር የበላይነት የተቃወመ ና መላ አፍሪካውያን ለነፃነታቸው ተጋድሎ እንዲያደርጉ በር የከፈተ የመስዋዕትነት የአሸናፊነት ደማቅ ገፅ ነው።
አድዋ ትናንት ና ዛሬ ህያው ሁኖ ይኖራል ።ትናንት ጀግኖች አያቶቻችን አባቶቻችን አጥንታቸውን ከስክሰው ደማቸውን አፍስሰው ታላቅ አገር እንድንወርስ አድርገውናል ዛሬ ደግሞ ኢትዮጵያን አፈርሳለሁ ብሎ ለተነሳ ባንዳ ተላላኪ ና ከሀዲ ምን ማድረግ እንደሚገባ በቅጡ በሚገባው ቋንቋ ያናገርንበት በመስዋእትነት የአፋር ልዩ ሀይል፣ ሚሊሺያና ህዝባዊ ሰራዊት ከመላ ኢትዮጵያዊያን ጋር በመተባበር ክንዳቸው ያነሱበት ና ለአገር መሞት ታላቅ ክብር መሆኑን ያረጋገጡበት የአድዋ ሌጋሲ ነው ማለት ይቻላል ።
አድዋ የአሸናፊነት ስነ ልቦና ከፍታ የአልገዛም ባይነት መገለጫ ነው ፣በየትኛውም ቦታ ና ስፍራ የጥቁር ህዝቦች የሚዘምሩት ኢትዮጵያዊያን ሁሉ የሚያቀንቅሉት የሰው ልጆች እኩልነት የተስተጋባበት ታላቅ ድምፅ ነው።
አሁንም ቢሆን ብዙ አድዋዎችን በማህበራዊ፣ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ዘርፎች የምናስመዘግብበት እንዲሁም የሀገራችንን ሰላም ለማናጋት ቆርጠው የተነሱ ሀይሎችን ድል የምንነሳበት በርካታ ዘመቻዎች የሚጠብቀን በመሆኑ ጠላትን የማሳፈር ጀብድን ይህም ትውልድ ዳግማዊ አድዋዎችን ይሰራል።
የአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት
የካቲት 23/2014