Afar Mass Media Agency (AFMMA)
1.09K subscribers
3.65K photos
161 videos
2 files
655 links
This channel is an official channel of Afar Mass Media Agency (AFMMA).
AFMMA is an autonomous government organization accountable to the regional Council of the Afar region.
Download Telegram
#ባቲ፣ አቀስታ፣ መሀል ሳይንት እና ሳይንት አጅባር ከተሞች የኤሌክትሪክ አገልግሎት አገኙ

ሰመራ-ታህሳስ 02, 2014 (አፋ.ብ.መ.ድ)

ባቲ፣ አቀስታ፣ መሀል ሳይንት እና ሳይንት አጅባር ከተሞች የኤሌክትሪክ አገልግሎት አገኙ

አሸባሪው ሕወሃት ቡድን ባደረሰው የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት ጉዳት አገልግሎት ተቋርጦበቸው የነበሩ ባቲ፣ አቀስታ፣ መሀል ሳይንት እና ሳይንት አጅባር ከተሞች በዛሬው ዕለት ኤሌክትሪክ ማግኘታቸውን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታወቀ፡፡

አሸባሪው ቡድን ባደረሰው የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት ጉዳት ምክንያት የተጎዱ የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ መስመሮች የመጠገንና መልሶ የማገናኘት ስራው ተጠናክሮ እየተሰራ ሲሆን፣ የክልሉ ሰራተኞችና ማኔጅመንት አባላት እያደረጉት ባለው ከፍተኛ ትብብር ኤሌክትሪክ ተቋርጦባቸው የነበሩ ከተሞችን ኤሌክትሪክ መልሶ እንዲያገኙ መደረግ ተችሏል፡፡

በዛሬው ዕለት ጠዋት ማጀቴ ከተማ ኃይል ያገኘች መሆኗን የገለፀው አግልግሎቱ፣ ከሰዓት በኋላ ደግሞ ባቲ፣አቀስታ፣መሀል ሳይንት እና ሳይንት አጅባር ከተሞች የኤሌክትሪክ አገለግሎት እንዲያገኙ መቻሉን የአገልግሎቱ የደሴ ዲስትሪክት ዳይሬክተር አቶ ሀብቱ አበበ አሳውቀውናል ብሏል፡፡

በደሴ ዲስትሪክት ስር አገልግሎት የሚያገኙት ከሚሴ፣ኮምቦልቻ፣ደሴ እና ጨፋ ሮቢት ከተሞች የኤሌክትሪክ አገልግሎት ማግኘታቸውን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታውቋል፡፡

#EBC