Afar Mass Media Agency (AFMMA)
1.09K subscribers
3.65K photos
161 videos
2 files
655 links
This channel is an official channel of Afar Mass Media Agency (AFMMA).
AFMMA is an autonomous government organization accountable to the regional Council of the Afar region.
Download Telegram
#የአዋሽ ወንዝ በአፋር ክልል እና በአጎራባች ክልሎች የሚያስከትለውን የጎርፍ አደጋ በተመለከተ በገንዘብ ሚኒስቴር ውይይት ተካሄደ::

ሰመራ-የካቲት 09/2013 (አፋ.ብ.መ.ድ)

የአዋሽ ወንዝ በአፋር ክልል እና በአጎራባች ክልሎች የሚያስከትለውን የጎርፍ አደጋ በተመለከተ በገንዘብ ሚኒስቴር ውይይት ተካሄደ::

የገንዘብ ሚኒስትር ክቡር አቶ አህመድ ሽዴ ከአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳደር ከክቡር አቶ አወል አርባ ጋር የአዋሽ ወንዝ የሚያስከትለውን የጎርፍ አደጋን በመከላከልና በመቆጣጠር ላይ ያተኮረ ውይይት ዛሬ የካቲት 10/2013 ዓ.ም በሚኒስቴሩ ጽ/ቤት አካሄዱ፡፡

ክቡር ሚኒስትሩና የክልሉ ርእሰ መስተዳድር የአዋሽ ወንዝ ቀደም ባሉት ዓመታት በተደጋጋሚ ጊዚያት በከፍተኛ ሁኔታ በመሙላት በአካባቢው ነዋሪዎች፣ በቁም እንስሳት እና በንብረት ላይ የሚያደርሰውን ጉዳት ለመቀነስ እየተሰሩ ባሉ ስራዎች ላይ ተወያይተዋል፡፡

ችግሩን ለመከላከል ክልሉ ከፌዴራል መንግስት እና ከልማት አጋሮች ጋር ተቀናጅቶ እየሰራ መሆኑን ክቡር አቶ አወል አርባ አመልክተው፣ ከዚህ ቀደም ጉዳቱ የደረሰባቸውን ነዋሪዎች በዘላቂነት የማቋቋም ስራዎችም መልካም ውጤት እንዳስገኙ አስረድተዋል፡፡

ክቡር አቶ አህመድ በበኩላቸው የአዋሽ ወንዝ በተደጋጋሚ ጊዚያት የሚያደርሰውን ጉዳት ለመቀነስ የቅድመ መከላከል ስራዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ አሳስበው የፌዴራል መንግስት ከክልሉ ጋር በመተባበር ከአዋሽ ወንዝ ጋር በተያያዘ የሚደርሰውን የጎርፍ አደጋ ለመከላከል አስፈላጊው ድጋፍ ሁሉ እንደሚያደርግ አመልክተዋል፡፡

#Source: Ministry Of Finance-Ethiopia Facebook Page