Afar Mass Media Agency (AFMMA)
1.09K subscribers
3.65K photos
161 videos
2 files
655 links
This channel is an official channel of Afar Mass Media Agency (AFMMA).
AFMMA is an autonomous government organization accountable to the regional Council of the Afar region.
Download Telegram
#የአክሱም እና ሽሬ ከተሞች ማምሻውን የኤሌክትሪክ አገልግሎት አገኙ ።

አፋር ብዙሃን መገናኛ ድርጅት-ጥር 10 /2013

በትግራይ ክልል በጁንታው ጉዳት ደርሶበት የነበረው የኤሌክትሪክ መስመር ተጠግኖ የአክሱም እና ሽሬ ከተሞች እና አካባቢያቸው ዛሬ የኤሌክትሪክ አገልገሎት ማግኘታቸውን የኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ኃይል አስታውቋል።

መሠረተ ልማቱን ለመጠገን በተደረገው ከፍተኛ ጥረት ቀደም ሲል አብዛኞቹ የትግራይ አካባቢዎች የመብራት አገልግሎት ማግኘታቸውንና የአድዋ ከተማ ደግሞ ዛሬ ከሰዓት በፊት ኤሌክትሪክ ማግኘቱን አስታውሷል።

በጁንታው ጉዳት ደርሶበት ከጥቅም ውጭ ሆኖ የቆየው የአክሱም እና ሽሬ ከተሞች እና አካባቢያቸው የኤሌክትሪክ መስመር በመጠገኑ ማምሻውን ከተሞቹ የመብራት አገልግሎት አግኝተዋል ብሏል።

የሑመራ እና ወልቃይት ከተሞች እና አካባቢያቸውን ኤሌክትሪክ ለማገናኘትም ርብርብ እየተደረገ መሆኑን ጠቅሷል።

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ አሸብር ባልቻ፣ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ በመሆን የጥገና ሥራውን በሓላፊነት ለተወጡ የተቋሙ ሠራተኞች ምስጋና አቅርበዋል።

#Addis Media Network