የርእሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ትምህርቶች የሚተላለፉበት Aba Gebrekidan sibket
6.46K subscribers
181 photos
7 videos
863 links
የርእሰ ሊቃውንት አባ ገብረኪዳን ትምህርቶች
Download Telegram
Audio
🔴 እጅግ አስቸኳይ እና ወቅታዊ መልዕክት

ከመጋቤ ብሉይ ወሐዲስ አባ ገብረኪዳን ግርማ


የብሉያት እና የሐዲሳትን መጻሕፍት ከምንጩ ይማሩ።
@AbaGebrekidangubaetezekro
Audio
🔴 እጅግ አስቸኳይ እና ወቅታዊ የወርሃ ጳጉሜን መልዕክት

ከመጋቤ ብሉይ ወሐዲስ አባ ገብረኪዳን ግርማ

🔴 ሁላችንም በያለንበት ልንተገብረው የሚገባ !

የብሉያት እና የሐዲሳትን መጻሕፍት ከምንጩ ይማሩ።
@AbaGebrekidangubaetezekro
#ዕንቈ_ሥላሴ_Tube #እንቁጣጣሽ ብላለች !
እንኳን አደረሳችሁ
"በቸርነትህ አመታትን ታቀዳጃለህ፥ ምድረ በዳውም ሰብን ይጠግባል፥ የምድረ በዳ ተራሮች ይረካሉ፥ ኮረብቶችም በደስታ ይታጠቃሉ" መዝ 64:11-12

የብሉያት እና የሐዲሳትን መጻሕፍት ከምንጩ ይማሩ።

@AbaGebrekidangubaetezekro
ዘለዓለም ባለና በሚኖር በሕያው ክርስቶስ፤ በአዲሲቱ እንቦሳ በድንግል ማርያም ላመን ሁሉም ዘመን አዲስ ዓመታችን ነው።💠🌿💠
አባ ገብረ ኪዳን

የብሉያት እና የሐዲሳትን መጻሕፍት ከምንጩ ይማሩ።
@AbaGebrekidangubaetezekro
ወደ እኔ ብረሪ

በርግብ ክንፎችሽ ከአውሬው ስትሸሽ፣
በጸዳል እግሮችሽ ስትንከራተቺ
በበረሃዉ ጉያ ስትመላለሽ
ከአህያይቱ ጀርባ ጫማ ተሸክሜ
ምነው በነበርኩኝ እኔ እንደ ሰሎሜ።

ከሄሮድስ ዱላ ከሳለው ጋሻ ጦር
ፈጥነሽ እንደበረርሽ ልጅሽን ለመሰወር
እኔም እንድሰደድ ከኃጢአቴ መንደር
ለጽድቅ እንድፋጠን በሰማይ እንድበር
ደግፊኝ እመ አምላክ ክንፌ እንዳይሰበር።
የቀላያት ጌታ ውኃ እንደተጠማ
በነፋስ የሚበርር በደመናው ማማ
ውኃ ስትለምኚ ጫማ እንደተቀማ
እኔን ድርቅ ያርገኝ ከኃጢአት ልጠማ
ደረቄን እንዳልቀር ከፍሬው አውድማ።

ምድርንም ያጸና ሰማይን የታታ
ግሩም እምግሩማን ያኀያላን ጌታ
ለሰው ፍቅር ብሎ ብዙ ሲንገላታ
በዉኃ እንዳጠብሽው ኃይሉ እንዲበረታ
በእንባሽ እጠቢችኝ ኃጢአቴ በርትቶ የተረታሁ ለታ።
ጸሐይን ያዘልሽው ደመና መፍጠኒት
የወርቅ ሐመልማል ርግብየ ኅሪት
አክናፍኪ መስቀል የሕይወት መሠረት
ሄሮድስ ሳይውጠኝ ሳልቀሰፍ በሞት፤ ወደ እኔ ብረሪ አዝለሽልኝ ምሕረት።

የግብጽን በረሃ የጎበኘሻቸው
አድባረ አግአዚትን ዞረሽ ያየሻቸው
የሕይወትን ውኃ ያዘነብሽላቸው
ሐሩሩ ሕይወቴን ፍጹሙን በረሀ
ታስትይዮ ስቴ እሴፎ አሜሃ።

ነውር የሌለብሽ መልካም ጸጌረዳ
በመንከራተትሽ ውስተ ምድረበዳ
ሸክም ቀለለልን ከፈልሽልን እዳ
በምጽአቱ ጌዜ ፍቁርሽ እንግዳ
ቅርጫፍሽ ልሁን አይብላኝ አንጋዳ።

👉በመጋቤ ብሉይ ወሐዲስ አባ ገብረ ኪዳን

https://t.me/joinchat/-oBrjmN9Hsc3MTA0
🥰1
Audio
እንደ ዕባብ ብልህ እንደ ርግብ የዋህ ሁኑ
ማቴ 10÷16
ወቅታዊና ሊደመጥ የሚገባው


በመጋቤ ብሉይ ወሐዲስ አባ ገብረኪዳን ግርማ

በዩቱብለምትከታተሉ
👉https://youtu.be/kd43QPX3iD8

የብሉያት እና የሐዲሳትን መጻሕፍት ከምንጩ ይማሩ።
@AbaGebrekidangubaetezekro
Audio
መልዕክት ለወጣቶች መስቀል ስታከብሩ ...

በመጋቤ ብሉይ ወሐዲስ አባ ገብረኪዳን ግርማ


የብሉያት እና የሐዲሳትን መጻሕፍት ከምንጩ ይማሩ።
@AbaGebrekidangubaetezekro
https://youtu.be/V7xmIwb9Aes
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆
ከላይ ባለው ሊንክ ያገኙታል ።
" ✝️ መስቀል ከሁሉም ነገር በላይ ነው ✝️ "
✝️ በመጋቤ ብሉይ ወሐዲስ አባ ገብረ ኪዳን
እግዚአብሔር ምድርን በታች መሠረት ሁኖ ያጸና በላይ በሰማያት ጠፈር ሁኖ ያለ እርሱ እርጥብ መስቀል መሸከም ያቅተዋል ?
👉አያቅተውም። መስቀልን #ለስምኦን_ቀሬናዊ እንዲያግዘው የሰጠበት ምክንያት ለእኛ መስቀሉን በስምኦን በኩል ሲሰጠን ነው።

🔆 መስቀልን በስምኦን
🔆ድንግል ማርያምን በዮሐንስ
🔆ንስሐን በፈያታዊ ዘየማን
🔆ክህነትን በቅዱስ ጴጥሮስ

አድርጎ ሰጦናል ። እነዚህ ፀጋዎቻችን ናቸው።
https://t.me/Enqosilassie
Forwarded from Samuel
💠መስቀል💠

ነደ እሳትን የተሸከመ የኪሩቤልም ባልንጀራ የሆነ እንደ ድንግል ማርያም ስም አራት ፊደል ያለው ነበልባላዊ የእሳት መንበር።

✣✣✣ አዳምን ከሞት ያወጣው የሕይወት ዛፍ።

✥✥✥ የኃጢአትን ቀላይ የገታ መርከብ።

❖❖❖ ባሕረ እሳትን ያሻገረ የድኅነት ትርክዛ።

✞✟✟ነፍሳት የሕይወት እንጀራን የጠገቡበት ማዕድ!

✟✟✟ክርስቶስና ቤተክረስተያን የተሞሸሩበት የሠርግ ቦታ።

ምእመናን የተጸነሱበት መካነ ክርስትና።

🔸🔸🔸 ቤተክርስቲያን የጸናችበት መሠረተ ሃይማኖት።

🔹🔹🔹የፍስሐ ኩሉዓለም ክርስቶስ ደም የፈለቀበት ሙሐዘ ትፍሥሕት!

🔶🔶🔶 ከሕይወት ውኃ ከክርስቶስ የተተከለ ሁል ጊዜ የሚያፈራ የሕይወት ዛፍ።

🔷🔷🔷 የንጉሥ ልጅ በአባቱ ኅልቀተ ወርቅ ማኅተም እንዲመካ፥ የንጉሠ ነገሥት ክርስቶስ ልጆች የምንለይበት የምንመካበት ትእምርተ ድኂን።

🔹 የጨለማውን አበጋዞችን ድቅድቅ የምንገፍበት
ጸዳለ ኩሉ ዓለም።

🔹🔹🔹 የሚወረወረውን ፍላጻ የምንሰብርበት ልብሰ ሃይማኖት ጥሩር።

✟✟✟ጦር ከነቀነቀ ጋሻ ከታጠቀ ከቀን ወራሪ ከሌሊት ሰባሪ የምንመክትበት ንዋየ ሐቅል።

🔷 ቢዋጉ ማሸነፊያ ቢሸሹ መጠጊያ ጸወነ ሥጋ ወነፍስ ወልታ ጽድቅ።
መስቀል መልዕልተ ለኩሉ ነገር
መጋቤ ብሉይ ወሐዲስ አባ ገብረ ኪዳን ግርማ

የብሉያት እና የሐዲሳትን መጻሕፍት ከምንጩ ይማሩ።
@AbaGebrekidangubaetezekro
👍1
እንኳን ደስ አላችሁ !
ለ ሁለት ወራት ተቋርጦ የነበረው የቅዱስ ዳዊት መዝሙር ማብራሪያ ተጀምሯል።