✝️✝️✝️በመጋቤ ብሉይ ወሐዲስ አባ ገብረኪዳን ግርማ✝️✝️✝️
ዛሬ #ሊቀ_ሰማዕታት ቅዱስ ጊዮርጊስ የከበረ ዐፅሙ ተቃጥሎ የተበተነበት (ውእየተ ዐፅሙ ወዝርወቱ) የሚታሰብበት ከበረ ዕለት ነው!
መ
"የትዕግስት ጽዋ"
የጦሩን አንደበት የእሳቱን ወላፈን
የመጋዙን ስለት የመንኮራኩሩን
እንዲያ ፋት እንዳልከው ፍጹም በመታመን፡
እኛም እንድንወደው አንተን ተከትለን
የትዕግስትን ጽዋ ለእኛም አቀብለን።
ባለቤቱ እንዳለ ይች ጽዋ ትለፍ
ብርሐኑን ገልጦ ጨለማን ለመግፈፍ
የተጋድሎን ማዕድ ከእርሱ ለመሳተፍ
ፍጹም ደስ እንዳለህ ብዙ ስትገረፍ
ጊዮርጊስ አስታጥቀኝ አብሬህ ልሰለፍ
በብረት ሊፈጩሕ ሊወጉህ በካራ
ወደ እሳት ሲወስዱሕ ደግሰው መከራ
እንደ ሸለሙት ሰው ሠርግ እንደተጠራ
ለምን ነው ደስ ያለህ እንኳን ልትፈራ
ስለምታይ ነዋ የሰማዩን ጌራ!
በጦር አልተወጋሁ ስለት አላገኘኝ
እሳት አልነደደ ሾተል አልጎሰመኝ
ኧረ እኔን ምኑ ነው የሚያነጫንጨኝ?
አክሊለ ሰማዕታት ትርጉሙ እንዲገባኝ
የሰማዩን ምስጢር ለእኔ ሹክ በለኝ።
የመበለቷን አምድ አንተ ስትጠጋው
ሥር እንደሰደደ እንዳለመለምከው
መሶቡን በኅብስት ቶሎ እንደ መላኸው
ደረቁን ሕይወቴን ለፍሬ ክብር አብቃው
ቀዝቃዛውን ልቤን ምውቅ ጽዋ ምላው።
ጽንዓ ሰማዕታትን ያድለን !በሰማዕትነት ዘመን ሰማዕት ከጠፋ የቤተክርስቲያን ሕመሟ ያን ጊዜ ነው።
ዛሬ #ሊቀ_ሰማዕታት ቅዱስ ጊዮርጊስ የከበረ ዐፅሙ ተቃጥሎ የተበተነበት (ውእየተ ዐፅሙ ወዝርወቱ) የሚታሰብበት ከበረ ዕለት ነው!
መ
"የትዕግስት ጽዋ"
የጦሩን አንደበት የእሳቱን ወላፈን
የመጋዙን ስለት የመንኮራኩሩን
እንዲያ ፋት እንዳልከው ፍጹም በመታመን፡
እኛም እንድንወደው አንተን ተከትለን
የትዕግስትን ጽዋ ለእኛም አቀብለን።
ባለቤቱ እንዳለ ይች ጽዋ ትለፍ
ብርሐኑን ገልጦ ጨለማን ለመግፈፍ
የተጋድሎን ማዕድ ከእርሱ ለመሳተፍ
ፍጹም ደስ እንዳለህ ብዙ ስትገረፍ
ጊዮርጊስ አስታጥቀኝ አብሬህ ልሰለፍ
በብረት ሊፈጩሕ ሊወጉህ በካራ
ወደ እሳት ሲወስዱሕ ደግሰው መከራ
እንደ ሸለሙት ሰው ሠርግ እንደተጠራ
ለምን ነው ደስ ያለህ እንኳን ልትፈራ
ስለምታይ ነዋ የሰማዩን ጌራ!
በጦር አልተወጋሁ ስለት አላገኘኝ
እሳት አልነደደ ሾተል አልጎሰመኝ
ኧረ እኔን ምኑ ነው የሚያነጫንጨኝ?
አክሊለ ሰማዕታት ትርጉሙ እንዲገባኝ
የሰማዩን ምስጢር ለእኔ ሹክ በለኝ።
የመበለቷን አምድ አንተ ስትጠጋው
ሥር እንደሰደደ እንዳለመለምከው
መሶቡን በኅብስት ቶሎ እንደ መላኸው
ደረቁን ሕይወቴን ለፍሬ ክብር አብቃው
ቀዝቃዛውን ልቤን ምውቅ ጽዋ ምላው።
ጽንዓ ሰማዕታትን ያድለን !በሰማዕትነት ዘመን ሰማዕት ከጠፋ የቤተክርስቲያን ሕመሟ ያን ጊዜ ነው።