የርእሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ትምህርቶች የሚተላለፉበት Aba Gebrekidan sibket
6.48K subscribers
173 photos
7 videos
861 links
የርእሰ ሊቃውንት አባ ገብረኪዳን ትምህርቶች
Download Telegram
ሶስት ሽህ ደርሰናል !
#ሌሎች ወንድም እህቶችን በመቀላቀል የእግዚአብሔርን ቃል በጋራ እንመገብ ።
#ለወንድሞች እና #ለእህቶች ያጋሩ
http://t.me/AbaGebrekidangubaetezekro
Audio
አቤቱ በሰላም እተኛለሁ በሰላም አንቀላፋለሁ
መዝ4፥7
መጋቤ ብሉይ ወሐዲስ አባ ገብረ ኪዳን ግርማ✝️

#የብሉይ_ኪዳን_ጉባኤ_ተዘክሮ

#የቅዱስ_ዳዊት_መዝሙር_ጥናት

👉 #ክፍል_24

👉https://youtu.be/-sdJoGNL6N8 በዩቱብ ለምትከታተሉ::
የጉባኤ ተዘክሮ የዩቱብ ሊንክ
👉
https://youtube.com/channel/UCUC5SLeTiPLbN8iA4E3bBgw

የብሉያት እና የሐዲሳትን መጻሕፍት ከምንጩ ይማሩ።

http://t.me/AbaGebrekidangubaetezekro
✝️ልዩ የበዓለ ጥምቀት ትምህርት በመጋቤ ብሉይ ወሐዲስ አባ ገብረ ኪዳን
ዕንቈ ሥላሴ Tube Enqo silasse Tube
"ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ መጣ::"

የበዓለ ጥምቀት ትምህርት


በመጋቤ ብሉይ ወሐዲስ አባ ገብረ ኪዳን ግርማ

በዩቱብለምትከታተሉ👉
https://youtu.be/9dyBwMfjmEc


የብሉያት እና የሐዲሳትን መጻሕፍት ከምንጩ ይማሩ።

http://t.me/AbaGebrekidangubaetezekro
ንስሐ ክፍል 5 በመጋቤ ብሉይ ወሐዲስ አባ ገብረ ኪዳን ግርማ /Aba G
ዕንቈ ሥላሴ Tube Enqo silasse Tube
ንስሐ እንዴት መግባት እንችላለን?
ክፍል፭ (5)

መጋቤ ብሉይ ወሐዲስ አባ
ገብረኪዳን
👉
https://youtu.be/jhDXOJm93fU በዩቱብለምትከታተሉ

የብሉያት እና የሐዲሳትን መጻሕፍት ከምንጩ ይማሩ።

http://t.me/AbaGebrekidangubaetezekro
የመጽሐፍ ዳሰሳ

ርዕስ:- ጸያሔ ፍኖት
ገጽ :- 495
ጸሐፊ:-አባ ገብረ ኪዳን ግርማ (መምህረ ብሉይ ወሐዲስ)

ሰሞኑን ለአንድ ሳምንት ያክል ስለ ጥምቀት ምስጢር ለመረዳት ስድስት መጻሕፍትን ከማገላበጥ አልተቆጠብኩም።

ጸያሔ ፍኖት በሦስት ክፍል በዐሥር ምዕራፍ ተከፍሎ የተጻፈ ሲሆን መጽሐፉ ዋና ይዘቱ የመጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስን ሕይወቱንና ትምህርቱን መተንተን ማራቀቅ ላይ አተኩሮ የተጻፈ ድንቅ መጽሐፍ ነው።

የቅዱስ ዮሐንስን ታሪክ በመጽሐፍ ቅዱስ አራቱም ወንጌላውያን በመግቢያቸው ጠቅሰውታል። ቅዱስ ዮሐንስ የብሉይ ማብቂያ የሐዲስ ኪዳን መግቢያ ላይ በመነሳቱ የነቢያቱ ትንቢት መፈጸሚያ ከሌሎቹ ነቢያት ጭምር በሁለንተናው ላቅ ያለ ነበር። ብዙዎች ስለ መድኃኒት ክርስቶስ መምጣት ተነበዩ ዮሐንስ ግን በዓይኑ አይቶ መስክሮም ወደ ፍጻሜ ያደረሰ ነው። ትምህርትም በይዘቱ በምስጢሩ በዓላማው ከሌሎቹ ይለያል።

መጽሐፉን ምዕራፍ በምዕራፍ መዳሰስ ይቻላል። ነገር ግን መጽሐፉ በምስጢር የታጨቀ የሊቁ የአዕምሮ ጭማቂ የፈሰሰበት በመሆኑ ምንም የሚጣል የሌለው ስለሆነ ጥቅል ዳሰሳ መጻፉ ይቀላል። ቅዱስ ዮሐንስን ከልደቱ የጀመረው መጽሐፉ አንዲት ቃል ሳትባክን ተጽፋለች ሳይሆን ተተንትናለች ማለት ይቻላል። በዚኽም የቅዱሱን ልደት ብቻ ሳይሆን ከልደቱ ከካህንነቱ እንዲሁም ከሕይወቱ ጋር የሚዛመዱ የነገረ መለኮት ትምህርቶች ተሰግስገውበታል።

የቅዱስ ዮሐንስ አባት ዘካርያስ እናቱ ኤልሳቤጥ መነሳታቸው ግድ ነውና ጽንሰቱ ልደቱ እድገቱ በተጻፈበት አንቀጽ በብስራት ጊዜ ስለነበረው መጽሐፉ በጥሩ ትምህርት ይገልጻል።

የመጽሐፉ ከፍታችሁ በበር ከገባችሁ በኋላ እፍታውን የያዘው ምዕራፍ ሰባት ነው "ትምህርቱ ለዮሐንስ" ይላል። በብዙ መምህራን ሳይቀር (ሰባኪያን አላልኩም) ትርጉሙን ጠለቅ አድርጎ ያለማስተማር ችግር የጎላ ነው። ገጸ ንባቡ የሚሰጠን ስሜት ብቻ ሳይሆን የወቅቱን ኁኔታና ሕዝቡ ምን አይነት ኁኔታ ላይ እንደነበረ ስንረዳ የመልእክት ዓላማና ጥንካሬ ይረዳናል። መጽሐፉ ገለባ ገለባውን ለይቶ ኩልል ያለ ፍሬውን ሳይቆረቁረን የምስጢር አጥንት ያስቆረጥማል።

መጽሐፍት እንዲኽ ቋሚ ምስክር ሆነው ሲጻፉ የትውልድን ረሃብ ይቀንሳሉ (ተመጋቢ ካለ) ክሕደት ጥርጥር ሲነሳ ማጣቀሻ ሆነው እንደ መከታ ያገለግላሉ። ለመምህራንም ጥሩ ስንቅ ያቀብላል፣ ሃይማኖት ያጸናል፣ ምስጢር ያሰፋል።

ጸያሔ ፍኖት መጽሐፍ ትልቅ የነገረ መለኮት ትንታኔ የያዘ መጽሐፍ ነው። ትምህርተ ሃይማኖት በእጅጉ የተጫነው መጽሐፍ በመሆኑ ሃይማኖትን ምግባርን፣ መንፈሳዊ ሕይወትን የሚዳስስ ነው።

አባ ገብረ ኪዳን የትምህርታቸው አንድ ስብከት መስማት የዓመት ስንቅ ነው። ሰምቼ አልጠግበውም ጥቅጥቅ ነው። ሰማእያን ሲቸገሩ እሳቸውም መላልሰው መላልሰው እንዲረዱት ሲናገሩ ስሰማ ልቤ በሐሴት ይሞላል። ትውልድ ማነጽ መቅረጽ የሚቻለው እንዲህ ነው። ጧፍ እየለኮሱ ምርኩዝ የሌለው ነገር አስይዞ መስደድ ከውድቀት አያተርፍም።
መጽሐፉ አልፎ አልፎ የፊደላት እርምት ይፈልጋል። ከመጽሐፉ ያልተመቸኝ እና ቅር ያለኝ የመጽሐፉ የሽፋን ገጽ የቅዱስ ዮሐንስ ስእል በቢዛንታይን አይነት መሆኑ ብቻ ነው። በእኛው አሳሳል ዘይቤ ቢሆን ጥሩ ነበር እላለሁ። እንዲመች እንጅ ስህተት ሆኖ አይደለም።

ሊቃውንት የመጽሐፍና የቃል ተብለው ይከፈላሉ። አባ ገብረ ኪዳን የቃልም የመጽሐፍም ሊቅነታቸው ግልጽ ነው። ትውልዱን ቀድመው የሚመሩ ናቸው። መጽሐፉን ብታነቡ ትጠቀማላችሁ። አስበ መምህራንን ይክፈልልን።

መ/ር ንዋይ ካሳሁን
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆
ይሄን የታላቅ ወንድማችንን ምክር እና አስተያየት ተቀብለው የመጽሐፉን የሽፋን ገጽ የቅዱስ ዮሐንስ ስእል በቢዛንታይን አይነት የነበረውን በእኛው አሳሳል ዘይቤ አዘጋጅተው እና የፊደላት እርምት አድርገው ለአንባቢያን እነሆ አቅርበውልናልና የአባታችን መጽሐፍ እንብበን የህይወት ስንቅ እንሰንቅ።
"ያንብቡ ያስነብቡ"
"ጸያሔ ፍኖት ወመጥምቀ መለኮት"
http://t.me/AbaGebrekidangubaetezekro
Audio
ንስሐ እንዴት መግባት እንችላለን?
ክፍል፬ (4)

መጋቤ ብሉይ ወሐዲስ አባ
ገብረኪዳን
👉https://youtu.be/wdCc08CQ0ms
በዩቱብ(በቪዲዮ) ለምትከታተሉ

የብሉያት እና የሐዲሳትን መጻሕፍት ከምንጩ ይማሩ።

http://t.me/AbaGebrekidangubaetezekro
ንስሐ ክፍል 5 በመጋቤ ብሉይ ወሐዲስ አባ ገብረ ኪዳን ግርማ /Aba G
ዕንቈ ሥላሴ Tube Enqo silasse Tube
ንስሐ እንዴት መግባት እንችላለን?
ክፍል፭ (5)

መጋቤ ብሉይ ወሐዲስ አባ
ገብረኪዳን
👉
https://youtu.be/jhDXOJm93fU በዩቱብለምትከታተሉ

የብሉያት እና የሐዲሳትን መጻሕፍት ከምንጩ ይማሩ።

http://t.me/AbaGebrekidangubaetezekro
Audio
የብሉይ ኪዳን ጉባኤ ተዘክሮ
መዝሙረ ዳዊት ማብራሪያ

ክፍል 25
🛑ጸሎቴ እንዲሰማ ምን ላድርግ ? "አቤቱ ቃሌን ስማ ጩኸቴንም አስተውል" መዝ 5:1
✝️በመጋቤ ብሉይ ወሐዲስ አባ ገብረ ኪዳን ግርማ
👉https://youtu.be/x4XrM81qvvA
በዩቲዩብ(በቪዲዮ) ለመከታተል

የብሉያት እና የሐዲሳትን መጻሕፍት ከምንጩ ይማሩ።

http://t.me/AbaGebrekidangubaetezekro
"ታላቅ መዳን" ወቅታዊ ትምህርት የዕብራውያን መልዕክት ማብራሪያ ክፍል 16 በመጋቤ ብሉይ ወሐዲስ አባ ገብረኪዳን ግርማ New Sbket Aba Gebrekidan
https://youtu.be/IWISldo1FLQ