የርእሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ትምህርቶች የሚተላለፉበት Aba Gebrekidan sibket
6.5K subscribers
172 photos
7 videos
858 links
የርእሰ ሊቃውንት አባ ገብረኪዳን ትምህርቶች
Download Telegram
#የሐዲስ_ኪዳን_ጉባኤ_ተዘክሮ

#የቅዱስ ጳውሎስ መልዕክት ወደ ዕብራውያን ሰዎች_ ትርጓሜ

#መግቢያ ክፍል 5


#"እኔ ክርስቶስን እንደምመስል እናንተም እኔን ምሰሉ (1ኛ ቆሮ 11፥1)"

"አይነኩ ቢነኩ ያድሯል ሲታወኩ"
👉የክርስቲያኖች ደም ሁለት ነገር ያደርጋል።
1. የክርስቲያን ደም ዘር ነው ክርስቲያን ያበቅላል፤ ክርስቲያንን ገድሎ መጨረስ አይቻልም። ዘር ሲዘራ 100 እንደሚሆን ክርስቲያንን መግደል ክርስቲያንን ለማብዛት ይጠቅማል ።
2.#የክርስቲያንን ደም ማፍሰስ የክርስቶስን ደም ማፍሰስ ነው። ይበቀላል❗️
👉ክርስቲያኖች የሚበቀሉት በስጋቸው ሳይሆን በሞታቸው ነው።
👉ስንሞት ሞታችን እሳት ሆኖ ያቃጥላል ፤ኃይል ሆኖ ሰራዊትን ያሰድዳል ፤ጦር ሆኖ ይዋጋል ፤ሰይፍ ሆኖ ይቆራርጣል ፤ የክርስቲያን ሞት እረፍት ይነሳል ለክርስቲያኖች ግን እረፍት ይሰጣል።
"አይነኩ ቢነኩ ያድሯል ሲታወኩ"
👉ሰው በነፍሱ ሥላሴን ይሰብካል።
👉ሰው በስጋውና በነፍሱ የክርስቶስን ሰው መሆን ይሰብካል።
👉መጽሐፍ አልተማርኩም ፣ ሰባኪ አላገኘሁም ፣ ንስሐ አባት አላስተማረኝም ብሎ ከፍርድ ማምለጥ አይቻልም። ተፈጥሮ ሃይማኖትን ይሰብካልና።
👉ኃጢአት የምትሰራ ስጋችን ናት ወይስ ነፍሳችን
👉"ምንም እውነት ቢሆን ሰይጣን ተናግሮት እውነት አይሆንም"

በመጋቤ ብሉይ ወሐዲስ ቆሞስ አባ ገብረ ኪዳን


በዮቱብ የምትከታተሉ የዮቱብ ቻናሉ ይህ ነው::!!
https://youtu.be/dPmq2mhulXs