የርእሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ትምህርቶች የሚተላለፉበት Aba Gebrekidan sibket
6.51K subscribers
171 photos
7 videos
858 links
የርእሰ ሊቃውንት አባ ገብረኪዳን ትምህርቶች
Download Telegram
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!

“አሐቲ ድንግል”

በፈውስ መንፈሳዊ የዩቲዩብ ቻናል የህይወትን ቃል በሚመግቡን በርእሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ ተጽፎ በ628 ገጾችና በ12 ምዕራፎች የተሰነደ
መጽሐፍ ነው፡፡

ከኅሊና አምላክ እስከ ዕርገቷ ድረስ ያለውን የእመቤታችንን ሙሉ የሕይወት ጉዞና በርካታ ምሥጢራት የያዘ ድንቅ መጽሐፍ ነው፡፡

እመቤታችን በነገረ ድኅነት ያላት ድርሻ ምን ይመስላል? ስለ እመቤታችን የሚነሡ ጥያቄዎች በመጽሐፍ ቅዱሳዊ የአበው ትምህርት እንዴት ተዳሰሰ? እንዴትስ በፍቅሯ ማደግና መጽናት ይቻላል? ሌሎችም መልሶችን የያዘው ይህ ግዙፍ መጽሐፍ አበው ሊቃነ ጳጳሳትን ጨምሮ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን በተገኙበት የፊታችን ቅዳሜ ጥቅምት 2/2017 ዓ.ም ከቀኑ 7 ሰዓት ተኩል ጀምሮ በቦሌ ደብረ ሳሌም መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን አዳራሽ ይመረቃል፡፡  ሁላችሁም እንድትገኙ በአክብሮት ተጠርታችኋል።

የምርቃት መርሐ ግብሩ በ ፈውስ መንፈሳዊ የዩቲዩብ ቻናል በቀጥታ ሥርጭት ይተላለፋል።


https://t.me/Fewus_Menfesawi
አሐቲ ድንግል - በርእሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ

የሚያረካ የመጻሕፍት ፊት አውራሪ ፤ የነገረ ማርያም ጥም ቆራጭ ፤ የትርጓሜ ድግስ ፤ የምሥጢራት ዝናም ፣ ያለ ስስት በፍቅር የተጻፈ ቅኔ መወድስ ፤ እንደ ሊቅ በምሥጢር እየተራቀቁ እንደ መናኝ በፍቅር እሳት እየተማወቁ የጻፉት በጸዳለ ምሥጢር የተጽደለደለ መጽሐፍ ተከስቶአል:: እመቤታችንን የሚወድ ሁሉ በፍቅርዋ ባሕር ለመዋኘት የሚችልበት እጅግ እጅግ እጅግ ውብ መጽሐፍ ፤ በጸሎት መንፈስ ለብቻ ተኾኖ ካልሆነ ሊነበብ የማይችል በዕንባ የሚያሰጥም መጽሐፍ ፤ ሌላ ነገር አንብበህ በዚያው ዓይንህ ልታነበው የማይገባ ዓይኖች ጾመው ሌላ ከማየት አክፍለው ሊያነቡት የሚገባ የወላዲተ አምላክ የቀሚስዋን ዘርፍ በፍቅር የሚያስነካ መጽሐፍ እነሆ ከደጃችን ነው::

እንደ ቃና ሊቀ ምርፋቅ መልካም የወይን ጠጅ "አሐቲ ድንግል" እያለች በመናኛ መጻሕፍት ለምን ሰከርን የሚያሰኝ የመጽሐፍ ወይን ታዩ ዘንድ ኑ! !
ነገ ቅዳሜ ከሰዓት በቦሌ መድኃኔዓለም ካቴድራል

ሥዕል :- ሠዓሊ ዲ/ን ዮርዳኖስ ዘሪሁን (ገብረ ኪዳን) እንደሣለው

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ እንደጻፈው
https://t.me/Fewus_Menfesawi
ትላንት ቦሌ መድኃኔዓለም የነበረው የአሐቲ ድንግል የመጽሐፍ ምረቃ መርሐግብር እጅግ አስደሳች ቢሆንም በሰው ብዛት እና በነበረው መጨናነቅ ምክንያት መጽሐፉን ማግኘት ያልቻላችሁ በሙሉ ዛሬ ቅድስት ሥላሴ ባለው መርሐግብር ላይ መጽሐፉን ማግኘት ትችላላችሁ !
📍ከቀኑ 8:00 ጀምሮ ቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ አዳራሽ
ለበለጠ መረጃ 0906654465 / 0931675567
ትላንት ቦሌ መድኃኔዓለም የነበረው የአሐቲ ድንግል የመጽሐፍ ምረቃ መርሐግብር እጅግ አስደሳች ቢሆንም በሰው ብዛት እና በነበረው መጨናነቅ ምክንያት መጽሐፉን ማግኘት ያልቻላችሁ በሙሉ ዛሬ ቅድስት ሥላሴ ባለው መርሐግብር ላይ መጽሐፉን ማግኘት ትችላላችሁ !
📍ከቀኑ 8:00 ጀምሮ ቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ አዳራሽ
በአካል መገኘት ለማትችሉ ከታች ባለው ሊንክ ይጠቀሙ።
https://tally.so/embed/mOJbok?transparentBackground=1&dynamicHeight=1

ለበለጠ መረጃ 0906654465 / 0931675567 ይደውሉ ።
የተወደዳችሁ ኦርቶዶክሳውያን ምእመናን በያላችሁበት ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችን ጋር ይሁን። አሐቲ ድንግል ከታተመችበት ጊዜ ጀምሮ መጽሐፉን ለማግኘት በምታደርጉት ርብርብ ለእመቤታችን ያላችሁን ፍቅርና ለኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮ ያላችሁን ቅናት አሳይታችኁናል። በመሆኑም መጽሐፉ በተፈለገው ቁጥር መጠን መድረስ ባለመቻሉ
አንዳንድ ሰዎች ከዋጋው በላይ እንደሚሸጡት ከወንድሞቻችንና እኅቶቻችን ጥቆማ ደርሶናል። በመሆኑም መጽሐፉ እየታተመ ስለሆነ ከዋጋው በላይ በመግዛት እንዳትጎዱ ለመጠቆም እንወዳለን።

©አባ ገብረ ኪዳን ግርማ
https://t.me/Fewus_Menfesawi