የርእሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ትምህርቶች የሚተላለፉበት Aba Gebrekidan sibket
6.51K subscribers
171 photos
7 videos
858 links
የርእሰ ሊቃውንት አባ ገብረኪዳን ትምህርቶች
Download Telegram
🌌 መጽሐፈ አቡሻክር 🌌
(በአዲሱ ዓመት ፳፻፲፯)

አዘጋጅ፦ በኢ/ኦ/ተ/ቤተ ክርስቲያን፥ በጎንደር መንበረ መንግሥት መድኀኔ ዓለም፥ የ፬ቱ መጻሕፍተ ትርጓሜ መምህርና የሊቀ ሊቃውንት ዕዝራ ሐዲስ ምክትል የሆኑት የኔታ ዘለዓለም ሐዲስ ናቸው!

የክቡር ሊቀ ሊቃውንት የኔታ ዕዝራ ሐዲስ ምክትል መምህር በሆኑት በየኔታ ዘላለም ሐዲስ ተዘጋጅቶ ቀርቦልናል።
መምህር ዘላለም ሐዲስ
በጎንደር መንበረ መንግሥት መድኃኔዓለም የ ፬ቱ መጻሕፍተ ትርጓሜ ምክትል መምህር ሲሆኑ መጽሐፉን ለሊቃውንት እና ለምዕመናን ተስማሚ አድርገው አቅርበውልናል ።

ይህንን መጽሐፍ በቅርብ ቀን ይጠብቁ !
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!

“አሐቲ ድንግል”

በፈውስ መንፈሳዊ የዩቲዩብ ቻናል የህይወትን ቃል በሚመግቡን በርእሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ ተጽፎ በ628 ገጾችና በ12 ምዕራፎች የተሰነደ
መጽሐፍ ነው፡፡

ከኅሊና አምላክ እስከ ዕርገቷ ድረስ ያለውን የእመቤታችንን ሙሉ የሕይወት ጉዞና በርካታ ምሥጢራት የያዘ ድንቅ መጽሐፍ ነው፡፡

እመቤታችን በነገረ ድኅነት ያላት ድርሻ ምን ይመስላል? ስለ እመቤታችን የሚነሡ ጥያቄዎች በመጽሐፍ ቅዱሳዊ የአበው ትምህርት እንዴት ተዳሰሰ? እንዴትስ በፍቅሯ ማደግና መጽናት ይቻላል? ሌሎችም መልሶችን የያዘው ይህ ግዙፍ መጽሐፍ አበው ሊቃነ ጳጳሳትን ጨምሮ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን በተገኙበት የፊታችን ቅዳሜ ጥቅምት 2/2017 ዓ.ም ከቀኑ 7 ሰዓት ተኩል ጀምሮ በቦሌ ደብረ ሳሌም መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን አዳራሽ ይመረቃል፡፡  ሁላችሁም እንድትገኙ በአክብሮት ተጠርታችኋል።

የምርቃት መርሐ ግብሩ በ ፈውስ መንፈሳዊ የዩቲዩብ ቻናል በቀጥታ ሥርጭት ይተላለፋል።


https://t.me/Fewus_Menfesawi
አሐቲ ድንግል - በርእሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ

የሚያረካ የመጻሕፍት ፊት አውራሪ ፤ የነገረ ማርያም ጥም ቆራጭ ፤ የትርጓሜ ድግስ ፤ የምሥጢራት ዝናም ፣ ያለ ስስት በፍቅር የተጻፈ ቅኔ መወድስ ፤ እንደ ሊቅ በምሥጢር እየተራቀቁ እንደ መናኝ በፍቅር እሳት እየተማወቁ የጻፉት በጸዳለ ምሥጢር የተጽደለደለ መጽሐፍ ተከስቶአል:: እመቤታችንን የሚወድ ሁሉ በፍቅርዋ ባሕር ለመዋኘት የሚችልበት እጅግ እጅግ እጅግ ውብ መጽሐፍ ፤ በጸሎት መንፈስ ለብቻ ተኾኖ ካልሆነ ሊነበብ የማይችል በዕንባ የሚያሰጥም መጽሐፍ ፤ ሌላ ነገር አንብበህ በዚያው ዓይንህ ልታነበው የማይገባ ዓይኖች ጾመው ሌላ ከማየት አክፍለው ሊያነቡት የሚገባ የወላዲተ አምላክ የቀሚስዋን ዘርፍ በፍቅር የሚያስነካ መጽሐፍ እነሆ ከደጃችን ነው::

እንደ ቃና ሊቀ ምርፋቅ መልካም የወይን ጠጅ "አሐቲ ድንግል" እያለች በመናኛ መጻሕፍት ለምን ሰከርን የሚያሰኝ የመጽሐፍ ወይን ታዩ ዘንድ ኑ! !
ነገ ቅዳሜ ከሰዓት በቦሌ መድኃኔዓለም ካቴድራል

ሥዕል :- ሠዓሊ ዲ/ን ዮርዳኖስ ዘሪሁን (ገብረ ኪዳን) እንደሣለው

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ እንደጻፈው
https://t.me/Fewus_Menfesawi
ትላንት ቦሌ መድኃኔዓለም የነበረው የአሐቲ ድንግል የመጽሐፍ ምረቃ መርሐግብር እጅግ አስደሳች ቢሆንም በሰው ብዛት እና በነበረው መጨናነቅ ምክንያት መጽሐፉን ማግኘት ያልቻላችሁ በሙሉ ዛሬ ቅድስት ሥላሴ ባለው መርሐግብር ላይ መጽሐፉን ማግኘት ትችላላችሁ !
📍ከቀኑ 8:00 ጀምሮ ቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ አዳራሽ
ለበለጠ መረጃ 0906654465 / 0931675567