የርእሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ትምህርቶች የሚተላለፉበት Aba Gebrekidan sibket
6.49K subscribers
173 photos
7 videos
861 links
የርእሰ ሊቃውንት አባ ገብረኪዳን ትምህርቶች
Download Telegram
✝️✝️✝️በመጋቤ ብሉይ ወሐዲስ አባ ገብረኪዳን ግርማ✝️✝️✝️

ዛሬ #ሊቀ_ሰማዕታት ቅዱስ ጊዮርጊስ የከበረ ዐፅሙ ተቃጥሎ የተበተነበት (ውእየተ ዐፅሙ ወዝርወቱ) የሚታሰብበት ከበረ ዕለት ነው!


 "የትዕግስት ጽዋ"
የጦሩን አንደበት የእሳቱን ወላፈን
የመጋዙን ስለት የመንኮራኩሩን
እንዲያ ፋት እንዳልከው ፍጹም በመታመን፡
እኛም እንድንወደው አንተን ተከትለን
የትዕግስትን ጽዋ ለእኛም አቀብለን።

ባለቤቱ እንዳለ ይች ጽዋ ትለፍ
ብርሐኑን ገልጦ ጨለማን ለመግፈፍ
የተጋድሎን ማዕድ ከእርሱ ለመሳተፍ
ፍጹም ደስ እንዳለህ ብዙ ስትገረፍ
ጊዮርጊስ አስታጥቀኝ አብሬህ ልሰለፍ

በብረት ሊፈጩሕ ሊወጉህ በካራ
ወደ እሳት ሲወስዱሕ ደግሰው መከራ
እንደ ሸለሙት ሰው ሠርግ እንደተጠራ
ለምን ነው ደስ ያለህ እንኳን ልትፈራ
ስለምታይ ነዋ የሰማዩን ጌራ!

  በጦር አልተወጋሁ ስለት አላገኘኝ
 እሳት አልነደደ ሾተል አልጎሰመኝ
ኧረ እኔን ምኑ ነው የሚያነጫንጨኝ?
አክሊለ ሰማዕታት ትርጉሙ እንዲገባኝ
 የሰማዩን ምስጢር ለእኔ ሹክ በለኝ።

የመበለቷን አምድ አንተ ስትጠጋው
ሥር እንደሰደደ እንዳለመለምከው
መሶቡን በኅብስት ቶሎ እንደ መላኸው
ደረቁን ሕይወቴን ለፍሬ ክብር አብቃው
ቀዝቃዛውን ልቤን ምውቅ ጽዋ ምላው።              

ጽንዓ ሰማዕታትን ያድለን !በሰማዕትነት ዘመን ሰማዕት ከጠፋ የቤተክርስቲያን ሕመሟ  ያን ጊዜ ነው።
እንኳን ለጌታችን እና ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የትንሳኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን !
Audio
ዓይኖቹ እንደወይን ቀይ ጥርሶቹ እንደወተት ነጭ ናቸው

#Share / #subscribe / #Like

በመጋቤ ብሉይ ወሐዲስ አባ ገብረ ኪዳን ግርማ

በዩቱብ ለምትከታተሉ
👉https://youtu.be/RXbo0YCNPyg
የብሉያት እና የሐዲሳትን መጻሕፍት ከምንጩ ይማሩ።

🛑የዩቲዩብ ሊንክ 👉https://youtube.com/channel/UCUC5SLeTiPLbN8iA4E3bBgw
🛑የቴሌግራም ሊንክ 👉@AbaGebrekidangubaetezekro
🛑የዋትሳፕ ሊንክ 👉https://chat.whatsapp.com/G5sQlltWryQ2pPkU9RDeVt
Audio
ዕለተ ዓርብ


#Share / #subscribe / #Like

በመጋቤ ብሉይ ወሐዲስ አባ ገብረ ኪዳን ግርማ

በዩቱብ ለምትከታተሉ
👉https://youtu.be/zkZlNpycXjY
የብሉያት እና የሐዲሳትን መጻሕፍት ከምንጩ ይማሩ።

🛑የዩቲዩብ ሊንክ 👉https://youtube.com/channel/UCUC5SLeTiPLbN8iA4E3bBgw
🛑የቴሌግራም ሊንክ 👉@AbaGebrekidangubaetezekro
🛑የዋትሳፕ ሊንክ 👉https://chat.whatsapp.com/G5sQlltWryQ2pPkU9RDeVt
Audio
እግዚአብሔርን የሚፈልግ ልብ ደስ ይበለው

#Share / #subscribe / #Like

በመጋቤ ብሉይ ወሐዲስ አባ ገብረ ኪዳን ግርማ

በዩቱብ ለምትከታተሉ
👉https://youtu.be/WtuXh1e8irI
የብሉያት እና የሐዲሳትን መጻሕፍት ከምንጩ ይማሩ።

🛑የዩቲዩብ ሊንክ 👉https://youtube.com/channel/UCUC5SLeTiPLbN8iA4E3bBgw
🛑የቴሌግራም ሊንክ 👉@AbaGebrekidangubaetezekro
🛑የዋትሳፕ ሊንክ 👉https://chat.whatsapp.com/G5sQlltWryQ2pPkU9RDeVt
Audio
ሰሎሞን ለራሱ ዙፋን ሰራ


#Share / #subscribe / #Like

በመጋቤ ብሉይ ወሐዲስ አባ ገብረ ኪዳን ግርማ

በዩቱብ ለምትከታተሉ
👉https://youtu.be/V_JfuqsM7oM
የብሉያት እና የሐዲሳትን መጻሕፍት ከምንጩ ይማሩ።

🛑የዩቲዩብ ሊንክ 👉https://youtube.com/channel/UCUC5SLeTiPLbN8iA4E3bBgw
🛑የቴሌግራም ሊንክ 👉@AbaGebrekidangubaetezekro
🛑የዋትሳፕ ሊንክ 👉https://chat.whatsapp.com/G5sQlltWryQ2pPkU9RDeVt
ጾሙስ አበቃ.....?
በአባ ገብረ ኪዳን

ጾሙስ አበቃ የነፍስ ረሃባችን መቼ ያበቃ ይሆን? ነፍሳችን ሥጋውን ደሙን እስከመቼ ነው የምትጾመው? ጾሙስ ተደመደመ። የእኛ በደል መቼ ይሆን የሚቋጨው? ስግብግብነታችን መቼ ነው ዳር የሚደርሰው? በዚህ ጾም መጨረሻ የአብ አንድያ ልጁ ተወልዶ መለያየት ተወገደ ሰውና መላእክት አንድ ሆኑ፤ መቼ ይሆን ጎጠኝነታችን የሚጠፋው? መቼ ይሆን ሰማያዊ ዘመድ የምናበጀው። ጾም ተፈጽሟልና ለሥጋ ሥጋ ተገዛለት። ለዚህ ጾሞ ፋሲካ ለነፍስ ምን ቅመም ተቀመመላት? ምን ንብረት ተመደበላት? ምን ሙክት ተገዛላት? ምን ወይን ተጠመቀላት? ምን ልብስ ተሠራላት? ምን ድግሥ ተደገሠላት? እነማንን ድግሥ ጠራንላት? አጋንንትን ወይስ መላእክትን? ዛሬ ዛሬ የጾም መግቢያና መውጫ ይገርማል። የጾም መግቢያ ሥጋ ይበላል የጾም ፍጻሜ ሥጋ ይበላል። በሥጋ ጀምረን በሥጋ መጨረስን ተያይዘነዋል! ሥጋው በደል ሆኖ አይደለም መጀመሪያችን መፈጸሚያችን የሥጋ ብቻ መሆኑ ግን የነፍስ ያለህ ያሰኛል!

አንዳንድ ሰው የዘንድሮው በዓል ልዩ የሚያደርገው ዓመቱ ፳፻፲፩ መሆኑ ይመስለዋል። ልዩ የሚያደርገው ከአምናው በተለየ ነፍስ ያገኘችው ነገር ሲኖር ነው። ለሥጋ ተበድሮ ሳይቀር ይደገሳል። ቢያንስ ድኃ ቢያጣ ያለችውን አጥቦ ለብሶ ከጎረቤት ሥጋ እየሸተተው ይውላል። ነፍሳችንስ ቢያንስ የሚቆርቡትን እያየች የክርስቶስ መዐዛ ቢናፍቃትም ባይሆን ተናዝዘን ታጥበን ብንውል ምን አለ?

የጸሎት ረሀብ መቼ ነው የምንፈስከው? የንጽሕና ረሀብ መቼ ነው የምንገድፈው? መፈሰክ ማለት መሻገር ነው? ዝሙትን የተሻገርን ዕለት ያን ጊዜ ነበር ፋሲካ!

ሱባኤው ደረሠ ቀጠሮው ተፈጸመ ጌታ ተወለደ። የእኛ ቀጠሮ መቼ ነው የሚደርሰው? በዚህን ጊዜ...ን አደርጋለሁ ብቻ! ጸሎቱ ቀጠሮ ጾሙ ቀጠሮ ትጋቱ ቀጠሮ አሥራቱ ቀጠሮ ኑዛዜው ቀጠሮ መታረቁ ቀጠሮ ቁርባኑ ቀጠሮ ሁሉ ቀጠሮ!ማን አለ የእኛስ ቀጠሮ ቢደርስ ምን አለ ጽኑዕ ቀጠሯችን ሳይደርስ እኛ የቀጠርነውን ጽድቅ ብንጀምረው! ምን አለ የእኛም ሱባኤ አብቅቶ የእግዚአብሔርና የቅዱሳን ልጆች ሆነን በምግባር ብንወለድ!

የጾመ ነቢያት ፍጻሜ ጌታ ተወለደ። እኛም ከንስሐ ማኅፀን እንድንወለድ ይርዳን። ከጾሙ መጨረሻ ክርስቶስ ከእነርሱ በሥጋ መጣ። ከጾማችን ፍጻሜ ጌታ በሰውነቴችን እንዲያድር ንስሐ ብንገባ ይህ ነው የጾም ፍጻሜ። ጌታ ሲወለድ አሮጌው ዘመን አበቃ። ሐዲስ ሕይወት፡ተወጠነ። እኛም ኃጢአታችን በንስሐ አልቆ አዲስ ከዘንድሮው ልደት ጀምሮ አዲስ ሕይወት ለመኖር ያብቃን። ኃጢአታችን ይለቅልን!
ታህሳስ 2012ዓ.ም ተጻፈ
👉@AbaGebrekidangubaetezekro
"አቤቱ ጌታችን ስምህ በምድር ዅሉ እጅግ ተመሰገነ" የቅዱስ ዳዊት መዝሙር ጥናት ክፍል #33 በመጋቤ…
ጉባኤ ተዘክሮ ዘብሉይ ኪዳን
መዝሙረ ዳዊት ማብራሪያ
👉ክፍል 33

""አቤቱ ጌታችን ሰምህ በምድር ሁሉ እጅግ ተመሰገነ::""


መጋቤ ብሉይ ወሐዲስ አባ
ገብረኪዳን

በዩቱብ ለምትከታተሉ
👉
https://youtu.be/bLEFhookmz0

የብሉያት እና የሐዲሳትን መጻሕፍት ከምንጩ ይማሩ።

http://t.me/AbaGebrekidangubaetezekro
Audio
🛑በክፉ ቀን መልካም ቀን ትዝ አይልም::

መጋቤ ብሉይ ወሐዲስ አባ
ገብረኪዳን

🛑በዩቱብ ለምትከታተሉ
👉
https://youtu.be/JiTZRJfT0QU

የብሉያት እና የሐዲሳትን መጻሕፍት ከምንጩ ይማሩ።

http://t.me/AbaGebrekidangubaetezekro
💠💠💠💠" ዕለተ ኃይል - የኃይል ቀን " መዝ፻፱ ፥ ፫ 💠💠💠

ትንቢተ ነቢያትን ስብከተ ሐዋርያትን መሠረት ፥ ክርስቶስን የማዕዘኗ ራስ ያደረገች ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የኃይል ቀን ብላ የምትጠራቸው ዕለታት አሉ።

ኃይል ስንል ኃይል ሥጋዊ ፥ ኃይል መንፈሳዊ ፥ ኃይል መልአካዊ አሉ። ኃይል ሥጋዊ እንደ ሶምሶን ያለው ነው። መንፈሳዊ እንደ አብርሃም ያለው ነው። መልአካዊ ደግሞ ቅዱሳን መላእክት ከጊዜ ውጭ ፈጣኖች ናቸው። ለምሳሌ በተመሳሳይ ጊዜ አንድ መልአክ ለረድኤት ቢጠራ ሁሉም ቦታ ላይ በተመሳሳይ ጊዜ የሚገኝበት ፍጥነት አለው። የነደደ እሳት ውስጥ የተጣለን ሰው እሳቱ መብላት ሳይጀምር እሳትን ቀድመው ይገኛሉ። አስተውሉ ይህ ምልዐት አይደለም። በሁሉም ቦታ መልቶ ያለ ያለቦታም መልቶ ያለ ምሉዕ በኩለሄ እግዚአብሔር ብቻ ነው።

የመላእክት ግን በተለያየ ጌዜ በአንድ ቦታ ቢገኙ ከጊዜ ውጭ የሆነ ፍጥነት ይባላል። "ዘይሬስዮሙ ለመላዕክቲሁ መንፈሰ - መላእክቱን መንፈስ የሚያደርግ " ያለው ነቢዩ ይህንን ነው። ይህ የመላእክቱ አንዱ ኃይላቸው ነው። ለምሳሌ ፦ ቅዱሰ ገብርኤል ለቂርቆስና ኢየሉጣ እሳቱን ባበረደበት ሰአት ሌላም ቦታ እንዲሁ የሚያደርግበት ፍጥነት አለው ማለት ነው። ከፍጥነታቸውም የተነሣ ዓይንን ጨፍነን እስንገልጥ ባለችው ቅጽበት ከላይኛው ሰማይ ተነሥተው ሐኖስን ፣ ጠፈርን ፥ አየራትን ፣ ምድርን ፣ ዓለመ ማይን ፥ ዓለመ እሳትን ፣ ዓለመ ነፋሳትን አልፈው ወርደው በርባሮስ ደርሰው መልሰው እነዚህን አልፈው ወጥተው ከላይኛው ሰማይ ይደርሳሉ።

ሁለተኛው የመላእክት ኃይላቸው ረቂቅነት ነው። ረቂቅነታቸው ደግሞ ተራራ አይጋርዳቸውም። ሰማይ አይከለክላቸውም ፤ ውኃ አይቀዘቅዛቸውም፥ እሳት አይሞቃቸውም ምንም የሚከለክላቸው የለም። ከሰማይ ወደ ምድር ሲወርዱ ወይም ሲያደርጉ መስኮት አያሻቸውም። እንኳንስ እነርሱን ሊጋርዳቸው ሊረዱት የመጡትን ሰው እንኳን ቦታ አይከለክለውም። ቅዱስ ጴጥሮስን ከተዘጋ ወህኒ ገብቶ ሳይከፍት እንዳወጣው መልአክ ቅዱስ እንደ ሚካኤል ማለት ነው። በሐዋርያት ሥራ እንደተጻፈው።

ከርቀታቸውም የተነሣ እንኳን ግዙፉ ረቂቁ አካል አይጋርዳቸውም። ከዚህም ኃይላቸውም የተነሣ አንዱ መልአክ በአንዱ መልአክ ሲያልፍ ፈቀቅ በልልኝ አይለውም። " ወኃለፈ መልአክ በመልአክ -መልአኩ በመልአክ ያልፋል " እንጅ። የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር በላያቸው ከሳለባቸው ግርማ መብረቅ የተነሣም አንዱ መልአክ ብቻ ብርሃነ መብረቁን ሰይፈ መቅሰፍቱን ጋት ስንዝር ሙሉ ብቅ ቢያደርግ ሕያዋንን ሁሉ ከምድረ ገጽ ማጥፋት ይቻለዋል። በእግዚአብሔር ላይ ሲመካ የነበረው የሰናክሬም 185, 000 ወታደሮችን ቅዱስ ሚካኤል ጋት ሙሉ የብርሃን ሰይፉን መዞ ቢያሳያቸው በአንድ ቀን እንደ ቅጠል ረግፈው እንዳደሩ በትንቢተ ኢሳይያስ እንደተጻፈው ማለት ነው። በእነዚህ ኃያላን የሚጠብቀን አምላከ ኃያላን ክብር ምስጋና ይግባው።

በጥቂቱ ስለ ኃያላኑ ይህን ያህል ከተነጋገርን ወደ ቀድሞ ርዕሳችን እንመለስና ቤተክርስቲያን የኃይል ቀን የምትላቸው እነማንን ነው? እነዚህ ደግሞ ሕያው የሠራዊት አምላክ ጌታ እግዚአብሔር ኃይሉን የገለጠባቸው ናቸው።

፩. ዓለምን ካለመኖር ወደ መኖር አምጥቶ የፈጠረበት ቀን ፦ ይህ ዓለም አልነበረም ፤ ጥንተ አካልም መነሻም አልነበረውም። ዓለምን ቀድሞ የተፈጠረ ዓለምም አልነበረም። ዓለምን ለመፍጠር የተፈጠረ መሣሪያ የሚሆን ዓለምም አልነበረም። ዓለም የሚዘጋጅበት ጠጣርም ሆነ ፈሳሽ ወይም አየር ወይም ጋዝ ወይም ትነት ወይም ቅንጣት ወይም ብናኝ ምንም አልነበረም ። እግዚአብሔር ብቻ ያለ ዓለም በራሱ ዓለምነት በመንግሥቱ አለ እንጅ ። መዝ ፸፫ ፥ ፲፫
ፈቀዱን የሚገልጥበትን ጊዜም ያለ ጊዜ ሆኖ ወሰነ። ጊዜን ራሱንም ፈጠረው። ይህን ዓለምም ይገኝ ሲል ተገኘ። ከየት አመጣው አይባልም "የት -ቦታ " ራሱ አልነበረምና። ያልነበረው ፍጥረት ካለና ከሚኖር እግዚአብሔር ከኢምንት ወደ ምንት - ከምንም ወደ ምንነት መጣ እንጅ። በዚህም ሦስት የእግዚአብሔር ኃይሉን እናስተውላለን።
ሀ. አይመረመሬነቱን ፦ እንኳን እርሱን የእርሱ ሥራ የሆነው ዓለም እንዴት ካለመኖር ወደ መኖር ማወቅ አልተቻለነምና።

ለ. ባዕለጸግነቱን ፦ ፍጥረት ባዕለ ጸጋ ቢሆን የሌለውን ካለው ወስዶ ነው። " ምንት ብከ ዘኢነሣእከ እምካልእከ - ከሌላ ያላገኘኸው ምን አለ " እንዳለ ቅዱስ ጳውሎስ ። እግዚአብሔር ግን በባሕርይው የሌለው የሌለ በባሕርዩ ሙሉዕነት ባዕለ ጸጋ ነው። ስለዚህ የሌለ ዓለምን ባለና በሚኖር ባሕርይው ባዕለጸግነቱ አመጣ።

ሐ. ከሃሊነቱ ፍጥረትን ከፍጥረት እያጣመሩ አዳዲስ ግኝቶችን ያመጡ ጠበብተ ዓለም አሉ። ግን የሚያደርጉት ሁሉ በተደረገ ነገር ላይ ነውና አዲስ አይባልም። "የሆነው ነገር እርሱ የሚሆን ነው፥ የተደረገውም ነገር እርሱ የሚደረግ ነው፤ ከፀሐይም በታች አዲስ ነገር የለም። " (መክ፩፥ ፱) ይልባቸዋልና ጠቢቡ። እንዲህም ሆኖ እግዚአብሔር ከፈጠረው ፍጥረት ለአንዱ እንኳን በቂ የዕውቀት ፍጻሜ ያገኘ ሊቅ የለምና። እርሱ ግን የሌለን ዓለም በከሃሊነቱ አመጣ። የሚታየውን ዓልም ካለመኖር በማይመረመር ከሃለነቱ አስገኝቷልና ከሃሌ ኩሉነቱን እናስተውላለን። " ዓለሞች በእግዚአብሔር ቃል እንደ ተዘጋጁ፥ ስለዚህም የሚታየው ነገር ከሚታዩት እንዳልሆነ በእምነት እናስተውላለን። " እንዳለ ቅዱስ ጳውሎስ ( ዕብራውያን ፲፩ ፥ ፫)

ፍርሃት የሚያናውጸው ሰው ይህን ሲያስብ ፍጹም ይበረታል። ያልነበረውን ዓለም ያመጣ ያለውን መጠበቅማ እንዴታ! ... ይቀጥላል ይቆየን!
" ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን በዓቢይ ኃይል ወደሥልጣን...
አባ ገብረ ኪዳን
ሚያዚያ ፲፭ - ፳፻፲፪ ዓም
የመጋቤ ብሉይ ወሐዲስ አባ ገብረ ኪዳን ትምህርቶች የሚተላለፉበት ጉባኤ ተዘክሮ ዘጎንደር
የብሉያት እና የሐዲሳትን መጻሕፍት ከምንጩ ይማሩ
https://t.me/AbaGebrekidangubaetezekro
እንኳን አደረሳችሁ!!

የቅዱስ ያሬድን ዓመታዊ ክብረ በዓል ምክንያት በማድረግ ልዩ ትምህርት በሊቀ ሊቃውንት እዝራ ሐዲስ እንዲሁም ያሬዳዊ አኮቴት ዝማሜ፣ ወረብ እና ምልጣን በመምህር ልሳነወርቅ ሞላ ተዘጋጅቷል። ይህ መንፈሳዊ እና በአይነቱ ለየት ያለ ዝግጅት እንዳያመልጥዎ፣ ወዳጅ ዘመድዎን ይጋብዙ፤ Subscribe በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ።


ግንቦት ፲፩ በልሳኑ-ዘያሬድ መንፈሳዊ የዩትዩብ ቻናል

#Like #Share #Subscribe
አዲስ አበባ ፒያሳ ዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ ቤ/ክ ጸበል ቤት አዳራሽ