የርእሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ትምህርቶች የሚተላለፉበት Aba Gebrekidan sibket
6.52K subscribers
171 photos
7 videos
858 links
የርእሰ ሊቃውንት አባ ገብረኪዳን ትምህርቶች
Download Telegram
ሰላም ለእናንተ ይሁን የርእሰ ገዳማት ወአድባራት ጣና ቅዱስ ቂርቆስ አንድነት ገዳም የ፬ቱ ጉባኤያተ መጻሕፍት ምስክር ት/ቤት የፈውስ መንፈሳዊ ሚዲያ ተከታታዮች፤ ከቀን ፲፩-፯-፳፲፯ ሐሙስ ጀምሮ "ፈውስ መንፈሳዊ ሚዲያ -youtube " በሌሎች ሰዎች ስለተጠለፈ እኛ መግለጫ እስክንሰጥ ድረስ በሚዲያው የሚተላለፉ መልእክቶች ቢኖሩ የጉባኤ ቤቱ አለመሆናቸውን አውቃችሁ እንድትጠነቀቁ በጉባኤ ቤቱ ስም እንገልጻለን።
አምላከ ጉባኤ እግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያናችንን ይጠብቅ።
ሰላም ለእናንተ ይሁን የርእሰ ገዳማት ወአድባራት ጣና ቅዱስ ቂርቆስ አንድነት ገዳም የ፬ቱ ጉባኤያተ መጻሕፍት ምስክር ት/ቤት የፈውስ መንፈሳዊ ሚዲያ ተከታታዮች፤  "ፈውስ መንፈሳዊ ሚዲያ -youtube " በሌሎች ሰዎች ተጠልፎ የነበረ ቢሆንም በእግዚአብሔር ቸርነት በእመቤታችን ተራዳኢነት በቅዱስ ቂርቆስ አጋዥነት በአባቶቻችን ጸሎት በእናንተም ጸሎት እንዲሁም በወንድሞቻችን ረዳትነት ወደ ጉባኤ ቤታችን የተመለሰ መሆኑን ልንናሳውቃችሁ እንወዳለን።
አምላከ ጉባኤ እግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያናችንን ይጠብቅ።
https://youtube.com/@fewus_menfesawi_aba_gebrekidan?si=yoiBv0sUl7cZ6oXL
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ፩ዱ አምላክ ዘለዓለም ሥላሴ።

በኢትዮጵያና በመላው ዓለም ለምትገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች፣ የጉባኤ ቤታችን ቤተሰቦች በሙሉ ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን እንደምን ሰነበታችሁ? እኛ አምላከ አበው እግዚአብሔር ይመስገን ደኅና ነን።
የርእሰ ገዳማት ወአድባራት ጣና ቅዱስ ቂርቆስ የአባቶችና የእናቶች ገዳም የ፬ቱ ጉባኤያተ መጻሕፍት የምስክር ት/ቤት በእሳት እንደተቃጠለ በማኅበራዊ መገናኛ መረቦች እየተላለፈ እንደሆነ ብዙዎቻችሁ ተጨንቃችሁ ደውላችሁልናል።
በመሆኑም ከጉባኤ ቤቱ ሐሙስ ግንቦት ሰባት ቀን እሳት ከቤት ተነሥቶ ለደቀ መዛሙርቱ ተሠርቶ የነበረ ቆርቆሮ በቆርቆሮ ጊዚያዊ መጠለያና የግማሾቹ ደቀ መዛሙርት ልብስና መጻሕፍቶቻቸው ተቃጥለዋል። ነገር ግን በሰማዕቱ በቅዱስ ቂርቆስና በእመቤታችን ጸሎት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጠብቆን ጉባኤ ቤታችንና መጻሕፍቶቻችን ደኅና ናቸው።

እኛም ደቀመዛሙርቱና ዋናው ጉባኤ ቤት፣ እንዲሁም ገዳማችን ደኅና ስለሆነ፣ ጊዜው የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ የተጀመረበት በመሆኑ ለቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ተጨማሪ ርእሰ ጉዳይ ላለመጨመር ለሚዲያ ሳንገልጽ ቆይተናል።በመሆኑም አሁን ግን ስለወጣ ይህንን መግለጫ ለተጨነቃችሁ ወገኖቻችን ልንገልጽ ፍቅር ያገብረናል።

ለጉባኤ ቤቱ የሚያስፈልጉን ጉዳዮች ቢኖሩ እኛ በፈወስ መንፈሳዉ የጉባኤ ቤታችን ሚዲያ በምስል የምንገልጽ መሆናችንን እየገለጽን ፣ ለተጨነቃችሁልን፣ለጸለያችሁልን፣ላሰባችሁልን፣ለረዳችሁን የቅድስት ቤተ ክርስቲያን ልጆች ኦርቶዶክሳውያን ሁሉ የጉባኤ አምላክ በምሕረቱ ያስብልን።

አምላከ ጉባኤ እግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያናችንንና ሀገራችንን ይጠብቅ።
የርእሰ ገዳማት ወአድባራት ጣና ቅዱስ ቂርቆስ  የአባቶችና እናቶች አንድነት ገዳም የ፬ቱ ጉባኤያተ መጻሕፍት ምስክር ቤተ ጉባኤ
ግንቦት፳፫-፳፻፲፯ ዓም