የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የህዝብ መዝናኛ ቦታዎች አስተዳደር ኮርፖሬሽን አመራር እና ሰራተኞች በአደባባይ በዓላት አከባበር ዙሪያ ውይይት አካሄዱ።
መስከረም 8/2017 ዓ.ም
በያዝነው አመት የሚከበሩ የመስቀል እና የእሬቻ የአደባባይ በዓላት ፍፁም ሰላማዊ ሆነው እንዲከበሩ እንዲሁም የሃገራችንን መልካም ገጽታ ለመገንባት በሚያስችሉ ጉዳዮቾ ዙሪያ በዛሬው ዕለት ውይይት ተካሂዷል።
የውይይት መነሻ ሰነዱን የኮርፖሬሽኑ ዋና አማካሪ ዶ/ር ግርማ መንገሻ ያቀረቡ ሲሆን መድረኩን የኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስኪያጂ ወ/ሮ ነጻነት ዳባ መርተውታል። ሁለቱም በዓላት በሰላም ተከብረው እንዲጠናቀቁ ሁሉም ሰራተኞች የጎላ ሚናቸውን መወጣት እንደሚጠበቅባቸው እና በዓላቱ ለሀገራችን ያላቸውን ሁለንተናዊ ፋይዳ ተገንዝቦና የበዓሉን ድባብ የሚያጠለሹ የፀጥታ ስጋቶችን ለይቶ በተቀናጀ እና በተደራጀ አግባብ ማክሸፍ ከሰራተኛው የሚጠበቅ ተግባር ሊሆን እንደሚገባ በመድረኩ ተገልጿል።
በአላቶቻችን የመልካም እሴቶቻችን ማንጸባረቂያ ከመሆናቸውም በላይ ለፓርኮቻቸን የገቢ ምንጭ መሆናቸውን ተገንዝበን እንግዶችን በአግባቡ ለማስተናገድ ከወዲሁ ልንዘጋጀባቸዉ እንደሚገባ ተጠቁሟል ።
በተለይ በእለቱ የበአሉ ታዳሚዎች ወደ መናፈሻዎቻችን እንዲመጡ ፣ በአግባቡ እንዲስተናገዱ እና ረክተዉ እንዲመለሱ የፖርኮቻቸንን ጽዳት መጠበቅ፣ጥበቃዉን ማጠናከር እና እንግዳ አቀባበላችንን ከወትሮው በተለየ ሁኔታ ማሻሻል እና የተሟላ ዝግጅት ማድረግ ይጠበቅብናል ሲሉ የኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ ነጻነት ዳባ ገልጸዋል።

ጽዱ ፣ውብ እና ማራኪ መዝናኛ ስፍራ ለሁላችን!
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የህዝብ መዝናኛ ቦታዎች አስተዳደር ኮርፖሬሽን አመራር አና ሰራተኞች በሁሉም ፓርኮች የጽዳት ዘመቻ አካሄዱ።
በቀጣይ ቀናቶች የሚከበሩ የመስቀል እና እሬቻ በአል ታዳሚዎች ወደ ፓርኮቻችን እንዲመጡ እና በአግባቡ እንዲስተናገዱ ለማድረግ የሚደረግ ቅድመ ዝግጅቶች እካል የሆነው በተለይ ፓርኮችን ጽዱ ውብ አና ማራኪ የማድረግ የጽዳት ዘመቻ በሁሉም ፓርኮች ዛሬ ተካሄዷል።
በኮርፓሬሽኑ ስር ያሉ ፓርኮች በሙሉ ለመዝናናት፣ለሰርግ፣ለልደት፣ለምረቃ፣ለኮንሰርት፣ለኢግዚቢሽን.ለባዛር ወዘተ ምቹ አስተማማኝ እና በቂ ስፍራዎች ያሏቸው ሲሆን ዘመናዊ እና ደህንነታቸው የተጠበቁ የህጻናት መጫዎቻዎች፣ውብ እና ማራኪ የሆኑ አረንጓዴ ስፈራዎች፣በጽሞና ዝግ ብለው የሚራመዱበት እና ንጹህ አየር የሚወሰዱበት ረጅም ፣የአማረና ምቹ የመናፈሻ መንገድ/ወክ ወይ/፣ ፋውንቴን ...ያሏቸውን መዝናኛ ስፍራዎች ለጎብኝዎች ዝግጁ አድርጎ የሚጠብቃችሁ በመሆኑ በማንኛውም ጊዜ መጥታችሁ እንድትገለገሉባቸው ኮርፖሬሽኑ ግብዣውን ያስተላልፋል።
የህዝብ መዝናኛ ቦታዎች አስተዳደር ኮርፖሬሽን 🇪🇹
🌐 Website
AACAPRAC.gov.et
👉FaceBook
fb.com/AACAPRAC
👉Instagram
instagram.com/AACAPRAC
👉Telegram
t.me/AACAPRAC
👉Titkok
Tiktok.com/@AACAPRAC
👉YouTube
youtube.com/@AACAPRAC
👉Twitter( X )
twitter.com/AACAPRAC