አ.አ የህዝብ መዝናኛ ቦታዎች አስተዳደር ኮርፖሬሽን - AACAPRAC 🇪🇹
263 subscribers
580 photos
23 videos
45 links
Download Telegram
ጽዱ  ፣ውብ እና ማራኪ መዝናኛ ስፍራ ለሁላችን!
       የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር  የህዝብ   መዝናኛ ቦታዎች አስተዳደር ኮርፖሬሽን  አመራር አና ሰራተኞች በሁሉም ፓርኮች የጽዳት ዘመቻ አካሄዱ።
      በቀጣይ ቀናቶች የሚከበሩ የመስቀል እና እሬቻ በአል ታዳሚዎች ወደ ፓርኮቻችን እንዲመጡ እና በአግባቡ እንዲስተናገዱ ለማድረግ የሚደረግ ቅድመ  ዝግጅቶች  እካል የሆነው  በተለይ ፓርኮችን  ጽዱ ውብ አና ማራኪ  የማድረግ  የጽዳት ዘመቻ በሁሉም ፓርኮች ዛሬ ተካሄዷል።
       በኮርፓሬሽኑ ስር ያሉ ፓርኮች በሙሉ ለመዝናናት፣ለሰርግ፣ለልደት፣ለምረቃ፣ለኮንሰርት፣ለኢግዚቢሽን.ለባዛር ወዘተ ምቹ አስተማማኝ እና በቂ ስፍራዎች ያሏቸው ሲሆን  ዘመናዊ እና ደህንነታቸው የተጠበቁ የህጻናት መጫዎቻዎች፣ውብ እና ማራኪ የሆኑ አረንጓዴ ስፈራዎች፣በጽሞና ዝግ ብለው የሚራመዱበት እና ንጹህ አየር የሚወሰዱበት ረጅም ፣የአማረና ምቹ የመናፈሻ መንገድ/ወክ ወይ/፣ ፋውንቴን ...ያሏቸውን  መዝናኛ ስፍራዎች ለጎብኝዎች ዝግጁ አድርጎ የሚጠብቃችሁ በመሆኑ በማንኛውም ጊዜ መጥታችሁ እንድትገለገሉባቸው ኮርፖሬሽኑ ግብዣውን ያስተላልፋል።
የህዝብ መዝናኛ ቦታዎች አስተዳደር ኮርፖሬሽን 🇪🇹

🌐 Website
                  AACAPRAC.gov.et
👉FaceBook
                 fb.com/AACAPRAC
👉Instagram
                 instagram.com/AACAPRAC
👉Telegram
                 t.me/AACAPRAC
👉Titkok
                 Tiktok.com/@AACAPRAC
👉YouTube
                 youtube.com/@AACAPRAC
👉Twitter( X )
                 twitter.com/AACAPRAC