አ.አ የህዝብ መዝናኛ ቦታዎች አስተዳደር ኮርፖሬሽን - AACAPRAC 🇪🇹
262 subscribers
580 photos
23 videos
45 links
Download Telegram
አዲስ-ዙ ፓርክ /በተለምዶ አጠራሩ ፒኮክ መናፈሻ /
  በአዲስ አበባ የህዝብ መዝናኛ ቦታዎች አስተዳደር ኮርፖሬሽን ከሚተዳደሩ ፓርኮች  አንዱ አዲስ ዙ  ፖርክ ሲሆን በመሃል አዲስ አበባ ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ አንድ ውስጥ ይገኛል፡፡
  ፓርኩ ከ1957 ዓ.ም ጀምሮ የመናፈሻ አገልግሎት ሲሰጥ የቆየ ሲሆን ከ2005 ዓ.ም ጀምሮ አለም አቀፍ ደረጃውን ወደ ጠበቀ ዙ ፓርክነት ለማሳደግ ‹‹አዲስ ዙ ፓርክ›› የሚለዉን ስያሜ እንዲያገኝ ተደርጓል፡፡
    ዙ ፓርኩን ለማሳደግ ባለፉት ጥቂት አመታት ብቻ በከተማ አስተዳደሩ በጀት የተለያዩ ግንባታዎች የተሰሩ ሲሆን በተለይ የሃገራችንን ሰነ-ምህዳር እንዲወክሉ ተደርገው እንዲሰሩ ከታቀዱ ስድስት የስነ-ምህዳር አምሳያዎች መካከል በ2013 ዓ.ም ግንባታው ተጠናቆ የተመረቀው እና የእንሳሳቶች ተፈጥሯዊ መኖሪያ /መገኛ/ ስፍራ  እንዲመስል ተደርጎ የተገነባው ጥቁር አባይ በሚል የሚታወቀው  ስፍራ ተጠቃሽ ነው፤በዚህ ስነ-ምህዳር ውስጥ   አናብስት፣የአፍሪካ ተኩላዎች፣ውድንቢዎች ፣ነብራማ ኤሌዎች፣ጦጣዎች እንዲሁም የተለያዩ አእዋፋት ይኖሩበታል፣ በግልጽም ይታዩበታል፡፡

    ከዚህ በተጨማሪ ፓርኩ ለመዝናናት፣ለሰርግ፣ለልደት፣ለምረቃ፣ለኮንሰርት፣ለፊልም እና ሙዚቃ ቀረጻ፣ ለኢግዚቢሽን፣ለባዛር ወዘተ ምቹ አስተማማኝ እና በቂ ስፍራዎች ያሉት ሲሆን በተለይ በግቢው ውስጥ ዘመናዊ እና ደህንነታቸው የተጠበቁ የህጻናት መጫዎቻዎች እና ጣፋጭ የህጻናት  ምግቦች፣ የካፍተሪያ አገልግሎቶች ፣ውብ እና ማራኪ የሆኑ አረንጓዴ ስፍራዎች፣በጽሞና ዝግ ብለው በመራመድ ንጹህ አየር የሚወሰዱበት ምቹ የመናፈሻ መንገድ/ወክ ወይ/፣እንደፍላጎትዎ ለተለያዩ ዝግጀቶች የሚያገለግሉ የተለያየ መጠን ያላቸው ደሴቶች፣ዘመናዊ የአውቶብስ አቅርቦት፣ዘመናዊ አዳራሽ፣ሰፊና አስተማማኝ የመኪና ማቆሚያ ስፍራዎች ይገኙበታል፡፡
         ርስዎ በማንኛውም ጊዜ  መጥተው አዲስ ዙ ፓርክን እንዲጎበኙ ተጋብዘዋል!!
                                 YOU GO PARK!
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የህዝብ መዝናኛ ቦታዎች አስተዳደር ኮርፖሬሽን አመራር እና ሰራተኞች  በአደባባይ በዓላት አከባበር ዙሪያ ውይይት አካሄዱ።
            
         መስከረም  8/2017 ዓ.ም

  በያዝነው አመት የሚከበሩ የመስቀል እና የእሬቻ የአደባባይ በዓላት ፍፁም ሰላማዊ ሆነው እንዲከበሩ እንዲሁም  የሃገራችንን መልካም ገጽታ ለመገንባት በሚያስችሉ ጉዳዮቾ ዙሪያ በዛሬው ዕለት ውይይት ተካሂዷል።

   የውይይት መነሻ ሰነዱን  የኮርፖሬሽኑ ዋና አማካሪ ዶ/ር ግርማ መንገሻ  ያቀረቡ ሲሆን መድረኩን የኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስኪያጂ ወ/ሮ ነጻነት ዳባ መርተውታል። ሁለቱም በዓላት በሰላም ተከብረው እንዲጠናቀቁ ሁሉም ሰራተኞች የጎላ ሚናቸውን መወጣት እንደሚጠበቅባቸው  እና በዓላቱ ለሀገራችን ያላቸውን ሁለንተናዊ ፋይዳ  ተገንዝቦና የበዓሉን  ድባብ የሚያጠለሹ የፀጥታ ስጋቶችን ለይቶ በተቀናጀ እና በተደራጀ አግባብ ማክሸፍ ከሰራተኛው የሚጠበቅ ተግባር ሊሆን እንደሚገባ በመድረኩ ተገልጿል።

     በአላቶቻችን የመልካም እሴቶቻችን ማንጸባረቂያ  ከመሆናቸውም በላይ ለፓርኮቻቸን  የገቢ ምንጭ መሆናቸውን ተገንዝበን እንግዶችን በአግባቡ ለማስተናገድ ከወዲሁ ልንዘጋጀባቸዉ እንደሚገባ ተጠቁሟል ።
በተለይ በእለቱ የበአሉ ታዳሚዎች ወደ መናፈሻዎቻችን እንዲመጡ ፣ በአግባቡ እንዲስተናገዱ እና ረክተዉ እንዲመለሱ የፖርኮቻቸንን ጽዳት መጠበቅ፣ጥበቃዉን ማጠናከር እና እንግዳ አቀባበላችንን ከወትሮው በተለየ ሁኔታ ማሻሻል  እና  የተሟላ ዝግጅት ማድረግ ይጠበቅብናል ሲሉ የኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ ነጻነት ዳባ ገልጸዋል።