አ.አ የህዝብ መዝናኛ ቦታዎች አስተዳደር ኮርፖሬሽን - AACAPRAC 🇪🇹
262 subscribers
580 photos
23 videos
45 links
Download Telegram
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ፈይስል በአዲስ ዙ ፓርክ በebs TV ፓርኩ ለድምጽ ቀረጻ ፣ለፊለም ሰራ በጣም ምቹ
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
አዲስ-ዙ ፓርክ /በተለምዶ አጠራሩ ፒኮክ መናፈሻ /

  በአዲስ አበባ የህዝብ መዝናኛ ቦታዎች አስተዳደር ኮርፖሬሽን ከሚተዳደሩ ፓርኮች  አንዱ አዲስ ዙ  ፖርክ ሲሆን በመሃል አዲስ አበባ ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ አንድ ውስጥ ይገኛል፡፡

  ፓርኩ ከ1957 ዓ.ም ጀምሮ የመናፈሻ አገልግሎት ሲሰጥ የቆየ ሲሆን ከ2005 ዓ.ም ጀምሮ አለም አቀፍ ደረጃውን ወደ ጠበቀ ዙ ፓርክነት ለማሳደግ ‹‹አዲስ ዙ ፓርክ›› የሚለዉን ስያሜ እንዲያገኝ ተደርጓል፡፡

    በዙ ፓርኩ ወሰጥ የእንሳሳቶች ተፈጥሯዊ መኖሪያ ስፍራ  እንዲመስል ተደርጎ በተገነባው  አና  ጥቁር አባይ በሚል ሰያሜ   በሚጠራው ስነ-ምህዳር ውስጥ   አናብስት፣የአፍሪካ ተኩላዎች፣ውድንቢዎች ፣ነብራማ ኤሌዎች፣ጦጣዎች እንዲሁም የተለያዩ አእዋፋት ይኖሩበታል።

  ፓርኩ ለሰርግ፣ለልደት፣ለምረቃ፣ለኮንሰርት፣ለፊልም እና ሙዚቃ ቀረጻ፣ ለኢግዚቢሽን እና ባዛር ወዘተ ምቹ አስተማማኝ እና በቂ ስፍራዎች ያሉት ሲሆን በተለይ በግቢው ውስጥ ዘመናዊ እና ደህንነታቸው የተጠበቁ የህጻናት መጫዎቻዎች ፣ጣፋጭ የህጻናት  ምግቦች፣ የካፍተሪያ አገልግሎቶች ፣ውብ እና ማራኪ የሆኑ አረንጓዴ ስፍራዎች፣በጽሞና ዝግ ብለው በመራመድ ንጹህ አየር የሚወሰዱበት ምቹ የመናፈሻ መንገድ/ወክ ወይ/፣እንደፍላጎትዎ ለተለያዩ ዝግጀቶች የሚያገለግሉ የተለያየ መጠን ያላቸው ደሴቶች፣ዘመናዊ የአውቶብስ አቅርቦት፣ዘመናዊ አዳራሽ፣ሰፊና አስተማማኝ የመኪና ማቆሚያ ስፍራዎች ይገኙበታል፡፡
       
                         YOU GO  PARK!
👍2
የቴያትር ቤቶች  አስተዳደር ድርጅት የኪነ-ጥበብ እና ኘሮሞሽን ሙያተኞች እና ሃላፊዎች ፓርኮችን ዙረው ተመለከቱ።
 
ሰኔ 11/2016  ዓ.ም
      አዲስ አበባ
 
  የአዲስ አበባ ከተማ የህዝብ መዝናኛ ቦታዎች አስተዳደር ኮርፖሬሽን እና  የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቴያትር ቤቶች አስተዳደር ድርጅት  በኮርፓሬሽኑ ስር ያሉ ፓርኮችን በስፋት የማስተዋወቁን ስራ  በጋር ለመስራት ባደረጉት ስምምነት መሰረት ስራውን ለመጀመር የሚያስችል ሃሳብ ለማሰባሰብ የቴያትር ቤቶቹ የኪነጥበብ እና የፕሮሞሽን ሙያተኞች ፓርኮችን ዙረው ተመልክተዋል።

በአሁን ወቅት ኮርፓሬሽኑ 10 ፓርኮችን የሚያስተዳድር ሲሆን እነዚህን ፓርኮች ህዝቡ በሚገባ እንዲያውቃቸው እና እንዱጠቀምባቸው ለማድረግ የፕሮሞሽን  እና የኮሙኒኬሽን ስራ በስፋት መስራት አስፈላጊ መሆኑ ታምኖበት ወደ ስራ እንደተገባ እና በስራውም የአዱስ አበባ ከተማ የቲያትር ቤቶች አስተዳደር ድርጅት ልምድ ያላቸው የኪነጥበብ ሙያተኞች ተሳታፊ እንደሚሆኑበት ታውቋል።
  በዛሬው የመጀመሪያ ምልከታ አዲስ ዙ ፓርክ ፣ብሄረ ጽጌ ፓርክ፣ ሃምሌ 19 እና እንጦጦ ፓርክ ላይ ትኩረት የተደረገ ሲሆን በምልከታው የተሳተፉ የድርጅቱ የኪነጥበብ ሙያተኞች በፓርኮቹ ውስጥ ባዩት ነገር መደነቃቸውን  እና መደሰታቸውን እንዲሁም በቀጣይ ለሚሰሩት ፓርኮችን በጥበብ የማስተዋወቅ ስራ በቂ ግብአት ማግኘታቸውን ገልጸዋል።

  የሕዝብ መዝናኛ ቦታዎችን እና ፓርኮችን በተገቢው መንገድ የማልማቱ ፣ተገቢ አገልግሎት እንዲሰጡ የማድረጉ እና  የማስተዋወቁን ስራ በአዱስ አበባ ከተማ  እየተካሄደ ያለው ሁሉን አቀፍ ልማት እና ገፅታ የመገንባት ስራ አንድ አካል በመሆኑ ኮርፓሬሽኑ የተለየ  ትኩረት ሰጥቶት በስፋት እንደሚሰራበት አሳውቋል።
 YOU GO PARK
* አዲስ ዙ ፓርክ/ 6 ኪሎ አንበሳ ግቢ/

  አዲስ ዙ ፓርክ ሁለት ሳይቶች ያሉት ሲሆን አንዱ ስድስት ኪሎ የሚገኙው በተለምዶ አንበሳ ግቢ ተብሎ የሚጠራው  መዝናኛ ስፍራ ነው ፡፡
  አንበሳ ግቢ በ19 40 ዓ.ም በ1.2 ሄክታር ቦታ ላይ ለአንበሳ እና ለዱር እንስሳቶች መጠለያ ሆኖ ለህብረተሰቡ የመናፈሻነት አገልግሎት እንዲሰጥ ታስቦ የተዘጋጀ ሲሆን ግቢው በወቅቱ ከወለጋ፣ከኢሉአባቦራ(ጎሮ) እና ከሲዳሞ የመጡ ሁለት ጥንድ ማለትም ሁለት ወንድ ሁለት ሴት አንበሶች እንዲሁም ሶስት ደበሎች የነበሩት ሲሆን በሂደትም ሰዎች አንበሶችን መጎብኘት ሲጀምሩ ፓርክ ሆኖ ተመስርቷል፡፡በዚያን ዘመን በግቢው የነበሩት አንበሶች ንጉሱ ለአደንና ለተለያዩ ጉዳዮች ወደተለያዩ ስፍራዎች ሲዘዋወሩ የአካባቢው ሰዎች በስጦታ መልክ የሰጧዋቸው እና ንጉሱ ያመጧቸው እንደነበሩ ይነገራል፡፡

  በአሁኑ ወቅት አንበሳ ግቢ የተለያዩ አገልግሎቶች ተጨምረውበት የመዝናኛ እና የመናፈሸ አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡በተለይ በግቢው ውስጥ በየጊዜው የሚዘጋጁ የቤተሰብ ፌስቲቫሎች፣ የህጻናት ዘመናዊ መጫዎቻ አገልግሎቶች፣ለእይታ የቀረቡ በርካታ ብርቅየ  የዱር እንስሳቶች፣ልዩ ልዩ ባህላዊ እና ዘመናዊ ቁሳቁስ መሸጫ ሱቆች፣ደረጃውን የጠበቀ የካፌና የመናፈሻ አቅርቦቱ …የጎብኝዎችን ቀልብ የሚስብ አድርጎታል፡፡

  6 ኪሎ አንበሳ ግቢን ከሌሎች መዝናኛ ስፍራዎች ለየት የሚያደርገው በርካታ ብርቀየ የዱር እንሳቶች በውስጡ የያዘ መሆኑ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት ከ13 በላይ ዝርያ ያላቸው የዱር እንስሳቶች ይገኙበታለል።
YOU GO PARK