Ethiopian Airlines የኢትዮጵያ አየር መንገድ
82.9K subscribers
2.35K photos
91 videos
2 files
300 links
ይህ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ይፋዊ የቴሌግራም ገፅ ነው።
Download Telegram
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቀዳማዊ መሰረታዊ የሰራተኛ ማህበር ዓለም አቀፉን የሰራተኞች ቀን አከበረ። በክብረ በዓሉ ላይ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው ፣ የአየር መንገዱ አመራር አባላት፣ የሰራተኛ ማህበሩ አመራሮች እና ሰራተኞች ተገኝተዋል። #የኢትዮጵያአየርመንገድ
በኢትዮጵያ ስካይ ላይት ሆቴል በተካሄደው የ #MROAFRICA2024 ኮንፈረንስ እና ኤግዚቢሽን የኢትዮጵያ አየር መንገድን እንደ አውሮፓ አቆጣጠር ከ 1971 እስከ 1975 ዓ.ም የመሩት የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ ዋና ስራ አስፈፃሚ ኮሎኔል ስምረት መድሀኔ በ”አፍሪካ አቪዬሽን ሰርቪስስ” የሕይወት ዘመን ተሸላሚ በመሆን እውቅና ተሰጥቷቸዋል።
እንኳን ደስ አለዎት!
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለስቅለት በዓል በሰላም አደረሳችሁ!
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለትንሳኤ በዓል አደረሳችሁ እያለ በዓሉ የሰላም፣ የጤና እና የፍቅር እንዲሆንላችሁ ልባዊ ምኞቱን ይገልጻል።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
እንኳን ለ83ኛው የኢትዮጵያ አርበኞች ድል መታሰቢያ ቀን አደረሳችሁ!

#የኢትዮጵያአየርመንገድ
ማሕበራዊ ሀላፊነቱን በተለያዩ ግዜያት ዘርፈ ብዙ ተግባራትን በማከናወን የሚወጣው የኢትዮጵያ አየር መንገድ የትንሳኤ በዓልን ምክንያት በማድረግ በ 2015 ዓ. ም በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 ባስገነባው የተስፋ ብርሀን የምገባ ማዕከል የማዕድ ማጋራት ፕሮግራም አካሂዷል።

በማዕድ ማጋራት ፕሮግራሙ ላይ አቶ መስፍን ጣሰው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ አመራር አባላትና ሰራተኞች ፣ የአዲስ አበባ አስተዳደር የስራ ሃላፊዎች እንዲሁም ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

#የኢትዮጵያአየርመንገድ