ቅዳሜ ፡- ግንቦት 24 ቀን 2016 ዓ.ም
የኮሌጁ EASTRIP ፕሮጀክት የስራ አፈፃፀም ግምገማ ውይይት ተካሄደ!!
የጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ EASTRIP ፕሮጀክት የ9 ወር የስራ አፈፃፀም ግምገማ በአዳማ ከተማ ሂልሳይድ ሆቴል ተካሄደ፡፡
በዚህ የስራ አፈፃፀም ግምገማ ውይይት ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስራ እና ክህሎት ቢሮ የስራ ኃላፊዎች፣ የከተማው ኮንስትራክሽን ቢሮ ተወካዮች፣ የአስተዳዳሩ ፋይናንስ ቢሮ ተጋባዦች፣ ከተለያዩ ኢንዱስትሪዎች የተውጣጡ የኢንዱስትሪ አድቫይዘሪ ቦርድ አባላት እና የኮሌጁ ዲኖች ተገኝተዋል፡፡
በዕለቱ በኮሌጁ ዲን አቶ መለሰ ይግዛው አማካኝነት የእንኳን ደህና መጣችሁ የመግቢያ ንግግር ከተደረገ በኋላ ተቋማዊ የፕሮጀክቱ አጠቃላይ የስራ አፈፃፀም ሪፓርት በፕሮጀክት ጽ/ቤቱ አስተባባሪ አቶ ጀማል ሐሰን አማካኝነት ቀርቧል፡፡
አጠቃላይ የኮንስትራክሽን ስራው ሂደት ምን ይመስላል የሚለው መረጃ ደግሞ በኮንስትራክሽን አማካሪ ድርጅቱ መሀንዲስ ቢኒያም አለማየሁ አማካኝነት በዝርዝር ቀርቧል።
በሌላ በኩል ለኮሌጁ አመራር እና ባለሙያዎች በተለያየ ጊዜ የተሰጡ ልዩ ልዩ ስልጠናዎች በተቋሙ ላይ ያመጡት ፋይዳና የነበረባቸው ክፍተቶችን የሚያሳይ ጥናታዊ ጽሑፍ በዶ/ር ፍስሐ ማሞ ቀርቧል።
በመጨረሻም በቀረቡት የስራ አፈፃፀም ሪፖርት እና ጥናታዊ ጽሑፍ ሰነዶች መሠረት ከተሳታፊዎች ጥያቄ ተነስቶ እና ገንቢ አሰተያየት ተሰጥቶ የዕለቱ መድረክ ተጠናቋል።
‹‹በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት››

👍13
ማክሰኞ፡- ግንቦት 27 ቀን 2016 ዓ.ም
ኮሌጁ ከአጠቃላይ ትምህርት የስራ ኃላፊዎች ጋር ውይይት አካሄደ!!
የጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ከ18 ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች እና ከ3 ክፍለ ከተሞች ማለትም ከአዲስ ከተማ፣ ከኮልፌ ቀራንዮ እና ከጉለሌ ክፍለ ከተሞች ትምህርት ጽ/ቤቶች ጋር ግንቦት 27 ቀን 2016 ዓ.ም ውይይት አካሄደ፡፡
የውይይቱ መሰረታዊ ዓላማ የኢንዱስትሪውን ፍላጎት ከግምት ያስገባ ብቁ፣ ተወዳዳሪና ስራ ፈጣሪ የሆነ የሰለጠነ የሰው ሃብት ገበያው ላይ ለማቅረብ የባለ ድርሻ አካላት ሚና ከፍተኛ በመሆኑ የአጠቃላይ ትምህርት እና የቴክኒክና ሙያ ስልጠናው ዘርፍ በተመጋጋቢነት ይሄድ ዘንድ ትብብር ለመፍጠር ታቅዶ ነው፡፡
በውይይቱ ላይ የተገኙት የትምህርት ቤቶቹ ርዕሳነ መምህራን እና የጽ/ቤቶቹ ትምህርት አመራር ከኮሌጁ ጋር ተቀናጅተው ዘመኑን የዋጅ ሀገር ተረካቢ ኃይል ለማፍራት ይረዳ ዘንድ ቁሳዊ እና ሰብዓዊ ግብዓቶችን በጋራ ለመጠቀም እንዲሁም ለተማሪዎች ግንዛቤ በመፍጠር የአመለካከት ለውጥ ለማምጣት ምን ማድረግ አለብን በሚለው ጉዳይ ላይ ሰፊ ሀሳብ ተነስቷል፡፡
በዕለቱ ከውይይት ባሻገር በኮሌጁ ውስጥ ያሉ የተለያዩ የማሰልጠኛ ወርክሾፖችን ጎብኝተዋል፡፡ የአጠቃላይ ትምህርት ዘርፍ አመራር የሆኑት ተሳታፊዎች በተሰጣቸው ማብራሪያ እና በጉብኝት ወቅቱ ባዩት የስራ እንቅስቃሴ በጣም እንደተደሰቱ ገልፀው ቀጣይ የተጠናከረ ትስስር በመፍጠር ስራዎችን በጋራ ለመስራት ተስማምተዋል፡፡

👍5❤1
በአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ አስተባባሪነት ሲካሄድ የቆየው ከተማ አቀፍ የተግባራዊ ጥናትና ምርምር ውድድር በጄነራል ዊንጌት ፖሊ-ቴክኒክ ኮሌጅ አሸናፊነት ተጠናቀቀ።
ግንቦት 27 ቀን ፤ 2017 ዓ.ም
የአዲስ አበባ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ 14ኛውን የቴክኒክና ሙያ ሳምንት ምክንያት በማድረግ ከሚያከናውናቸው ሁነቶች አንዱ የሆነው <<ሙያና ክህሎት ለዘላቂ ልማት>>በሚል መሪ ቃል ሲያካሂድ የቆየው የተግባራዊ ጥናትና ምርምር ከተማ አቀፍ ውድድር በዛሬው ዕለት ተጠናቋል።
በማጠቃለያ ውድድሩ በክላስተር ደረጃ በተካሄደው ውድድር የተሻለ ውጤት ያስመዘገቡ የጥናትና ምርምር ስራዎች የቀረቡ ሲሆን ከፌዴራል ቴክኒክና ሙያ ኢንስቲትዩት የተውጣጡ ምሁራን ደግሞ በዳኝነት ተሳትፈ ውበታል።
በዚህ መሰረት #ጄኔራል ዊንጌት ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በአንደኝነት ሲያጠናቅቅ #ተግባረ-ዕድ ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ እና ንፋስ ስልክፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ሁለተኛና ሶስተኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቀዋል ።
በማጠቃለያ ውድድሩ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት በቢሮ ኃላፊ ደረጃ የኢንተርፕራይዝና ቴክኖሎጂ ልማት ዘርፍ ኃላፊ #አቶ መክብብ ወልደሃና የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጆች በስልጠና ወቅት የሚያጋጥሟቸውን ችግሮች እና በማህበረሰቡ የሚስተዋሉ ችግሮችን በጥናት በመለየት እና ችግሮቹ በዘላቂነት እንዲፈቱ ለማድረግ ተግባራዊ ጥናትና ምርምሮች ድርሻቸው የጎላ መሆኑን ገልጸዋል።
#አቶ መክብብ ወልደሃና አያይዘውም ቢሮው በተግባራዊ ጥናትና ምርምር የተገኙ ግኝቶችን በተግባር ለመለወጥ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ አረጋግጠዋል።

🏆7❤2👍2👎1
ሐሙስ:- ግንቦት 29 ቀን 2016 ዓ.ም
የቀንድ ከብት ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ
ኮሌጁ በእርባታ ጣቢያው የሚገኙ 4 ላሞችና 3 ጊደሮችን በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ አቅዷል፡፡ ስለሆነም በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ አካላት የጨረታው ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ማለትም ከግንቦት 28 እስከ ሰኔ 6 ቀን 2016 ዓ.ም በኮሌጁ ንብረት እና ጠቅላላ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ቢሮ በመገኘት የመወዳደሪያ ሰነዱን መሙላት እንደምትችሉ እያሳወቅን ዝርዝር መረጃውን ከላይ አያይዘናል፡፡
"በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት"

👍10❤1😢1
ሐሙስ:- ግንቦት 29 ቀን 2016 ዓ.ም
ማስታወቂያ
ለተመራቂ #ሰልጣኞች በሙሉ!!
ኮሌጁ ቀጣይ ሰኞ ማለትም ሰኔ 3 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ለተከታታይ #20 ቀናት ለተመራቂ ሰልጣኞች በልዩ ሁኔታ ያዘጋጀውን የሶፍት ስኪል ስልጠና ለመውሰድ የሚያስችላችሁን መመዝገቢያ ሊንክ ከላይ ያያዝን ስለሆነ በዚህ መተግበሪያ ላይ ፈጥናችሁ እንዲትመዘገቡ እናሳስባለን፡፡

👏5👍4