General Wingate Polytechnic college-Official channel
9.96K subscribers
3.37K photos
43 videos
204 files
198 links
ራዕይ:- በ2022 በምስራቅ አፍሪካ ቀዳሚ ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ መሆን።

የአይሶ 9001፡2015 የጥራት አመራር ስርዓት ሰርተፍኬት ባለቤት።
Download Telegram
ሰኞ:- ሐምሌ 1 ቀን 2016 ዓ.ም

ለተመራቂ ሰልጣኞች ሲሰጥ የቆየው የኬፕለር ስልጠና ተጠቀቀ!!

ለአንድ ወር ያህል ቆይታ የነበረው የተመራቂ ሰልጣኞች የኬፕለር ስልጠና ተጠናቀቀ።
                                                                                           ከ200 በላይ የሚሆኑ ተመራቂ ሰልጣኞች የኬፕለር ስልጠና የወሰዱ ሲሆን የስልጠናው መሰረታዊ ዓላማ ተመራቂዎች ወደ ስራ ኢንዱስትሪው ለመግባት የሚያስፈልጋቸውን ክህሎት ለማስጨበጥ እንደሆነ ተገልጿል።

ኬፕለር ተመራቂ ሰልጣኞችን ከኢንዱስትሪዎች ጋር ለማስተሳሰር እየሰራ ያለ ግብረ ሰናይ ድርጅት ሲሆን ለተመራቂዎቹ በስራ ላይ ተግባቦት፣ በጊዜ አጠቃቀም፣ በሲቪ አዘገጃጀት፣  ወዘተ ዙሪያ ትኩረት ያደረጉ የሶፍት ስኪል ስልጠናዎችን እየሰጠ ይገኛል። 

ስልጠናቸውን ላጠናቀቁ ሰልጣኞች በዛሬው ዕለት የማጠናቀቂያ ሰርተፍኬት የተሰጠ ሲሆን በዕለቱ መርሃ ግብር ላይ የኮሌጁ አመራር አካላት፣ የኬፕለር ካንትሪ ዳይሬክተር ሚስተር GMV፣ ከተለያዩ ኢንዱስትሪዎች የተውጣጡ ባለድርሻዎች እና የስልጠናው ተሳታፊ አሰልጣኞችና ሰልጣኞች ተገኝተዋል። 

‹‹በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት››
👍28🙏3👌31
አስቸከይ ይህ የአዲስ አበባ እና የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ የሰራተኞችን እርካታ በመለካታ አሰራሮችን መስተካከል ስለፈለገ ይህንን ፎርም ዛሬ/04-5/11/16 ዓ.ም ድረስ በአስቸከዋይ በመሙላት ሃላፊነታችሁን እንድትወጡ
👍2
ይህ Automotive;Business;ICT;Electrical የ theory ተመዛኞች ዝርዝር ሲሆን የሌሎቹ ዲፓርትመንቶች ተመዛኞች ዝርዝር በየዲፓርትመንታቹ የሚገኝ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
👍1
Forwarded from fikir
👍3🙏1
ሰኞ፡- ሐምሌ 8 ቀን 2016

የኮሌጁ የስነምግባርና ፀረሙስና ዳይሬክቶሬት የ2016 በጀት ዓመት የማጠቃለያ ሪፖርት አቀረበ!!

የስነምግባርና ፀረሙስና ዳይሬክቶሬት በ2016 በጀት ዓመት አቅዶ ያከናወናቸውን ዋና ዋና ተግባራት ለኮሌጁ ማህበረሰብ አቅርቧል።

የእቅዱ አፈፃፀም 3 መሠረታዊ ግቦችን የያዘ ሲሆን እነሱም የሀብት አጠቃቀምና አገልግሎት አሰጣጥ፣ የሞራል እሴቶችና ተቋማዊ አቅም ግንባታ ስራ ማጠናከር እና የሙስና ወንጀልና ብልሹ አሰራርን ለመከላከል ግልጽና ተጠያቂነት ያለው አሰራር ስርዓት ማስፈን የሚሉትን አካቶ በርካታ ተግባራት መከናወናቸው ተገልጿል።

ከዚህ ባሻገር በ2017 በጀት ዓመት በስነምግባር ግንባታና በሙስና መከላከል ዘርፍ ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተገልጸዋል።

‹‹በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት››
👍21