General Wingate Polytechnic college-Official channel
9.96K subscribers
3.37K photos
43 videos
204 files
198 links
ራዕይ:- በ2022 በምስራቅ አፍሪካ ቀዳሚ ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ መሆን።

የአይሶ 9001፡2015 የጥራት አመራር ስርዓት ሰርተፍኬት ባለቤት።
Download Telegram
በሚኒስቴሩ የለሙ መተግበሪያዎች አጠቃቀም ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ

በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የለሙ የቀጠሮ ማስያዣ እና ቅሬታ እና አስተያየት ማቅረቢያ መተግበሪያዎች አጠቃቀም ላይ ያተኮረ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ለሚኒስቴሩ አመራርና ሰራተኞች ተሰጥቷል፡፡

ሚኒስቴሩ አገልግሎት ሰጪ ተቋም እንደመሆኑ የአገልግሎት አሰጣጡን ለማቀላጠፍ እና በተቋሙ የሚቀርቡ አቤቱታ እና ቅሬታዎችን መቀበል እና ፈጣን ምላሽ መስጠት የሚያስችሉ የቀጠሮ ማስያዣ(appointment system) እና አስተያየት እና ቅሬታ መቀበያ(public feedback system) በአግባቡ እንዲጠቀሙ ታሳቢ ተደርጎ መድረኩን መዘጋጀቱ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የኢንፎርሜሽን ኮሙዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ ስራ አስፈጻሚ አቶ ኃ/እየሱስ ደምሴ ገልጸዋል፡፡

ሀገራት አገልግሎታቸውን ለማዘመን ወደ ዲጃታል ዓለም እየገቡ መሆኑ የገለጹት ሥራ አስፈጻሚው ሚኒስቴሩም ዘመኑና ጊዜውን የሚመጥን አገልግሎት መስጠት የሚያስችሉትን ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚውሉ መተግበረያዎችን በማልማት ወደ ሥራ እያስገባ ቆይቷል ብለዋል፡፡

በመድረኩ የተቋሙ ሠራተኞች መረጃ መለዋወጥ የሚያስችላቸውን አፕሊኬሽን( MOLS Family chat application) እና የተቋሙ ሰራተኞች የሀሳብ ባንክ(Idea bank) ሲስተሞች አጠቃቀም አስመልክቶ ገለጻ ተደርጓል፡፡

ባለጉዳዮች ወይም ተገልጋዮች ወደ ሚኒስቴሩ ለመምጣት ቢፈልጉ አስቀድመው ቀጠሮ ለማስያዝ appointment.mols.gov.et እና አስተያየት እና ቅሬታ ለማቅረብ ደግሞ pfs.mols.gov.et በመግባት መስተናገድ እና አገልግሎቱን ማግኘት እንደሚችሉ ተገልጿል፡፡

ሰኔ 14/2016 ዓ.ም
ለወቅታዊ ትኩስ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር
በድረገጽ፡- http://mols.gov.et/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/MolsFDRE
ቴሌግራም፦https://t.me/fdre_mols
ቲክቶክ:- tiktok.com/@mols_official
የኢትዮጵያ የሥራ ገበያ መረጃ ሥርዓት https://lmis.gov.et
👍5
ቅዳሜ፡- ሰኔ 15 ቀን 2016 ዓ.ም

14ኛው የቴክኒክ እና ሙያ ሳምንት ዐውደ ርዕይ ተጀመረ፡፡

14ኛው የቴክኒክ እና ሙያ ሳምንት ዐውደ ርዕይ ዛሬ ሰኔ 15 ቀን 2016 ዓ.ም በአዲስ አበባ ኤግዚቪሸን ማዕከል ለጎብኝዎች እይታ ክፍት ተደረገ፡፡

በመክፈቻ መርሃ ግብሩ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ክብርት ወ/ሮ አዳነች አቤቤ፣ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጥራቱ በየነን ጨምሮ የፌደራል እና የከተማ አስተዳደር የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

በዕለቱ የመዲናይት ከንቲባ በመልዕክታቸው የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ተቋማት ኢንተርፕራይዞቻችን እንዳይከስሙ፣ ይልቁኑ  በስራ ባህልና ክህሎት እየታነጹ ከራሳቸው አልፈው ለሌሎች የስራ ዕድል በመፍጠር ተኪ ምርት ለገበያ እንዲያቀርቡ ትርጉም ያለው አስተዋፅኦ አበርክተዋል። ብለዋል።

በዚህ ኤግዚቪሽን ላይ በ15 የመንግስት እና በ6 የግል ኮሌጆች የተሰሩ አስደናቂ የማምረቻ እና የምርት ፈጠራ ስራዎች ለተመልካቾች ቀርበዋል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ በጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ የተሰሩ 3 የማምረቻ እና 4 የምርት ውጤቶች ለእይታ ቀርበው የተመልካችን ቀልብ መሳብ ችለዋል፡፡

በተጨማሪም በኮሌጁ የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን ድጋፍ የሚደረግላቸው ኢንተርፕራይዞች የፈጠራ ምርታቸውን ይዘው ተገኝተዋል፡፡

ኤግዚቪሽኑ ''ቴክኒክና ሙያ ለዘላቂ ልማት'' በሚል መሪ ሃሳብ እየተካሄደ የሚገኝ ሲሆን ለ6 ተከታታይ ቀናት ለጎበኝዎች ክፍት ተደርጎ እንደሚቆይ ታውቋል።

‹‹በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት››
👍213
ረቡዕ፡- ሰኔ 19 ቀን 2016 ዓ.ም

              ኮሌጁ የፋሽን ሾው ትርኢቱን ዛሬ አቀረበ!!

የ14ኛው ቴክኒክ እና ሙያ ሳምንት ዐውደ ርዕይ አካል የሆነውን የፋሽን ሾው ትርኢት ውድድር የጀነራል ዊንጌት ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ዛሬ ሰኔ 19 ቀን 2016 ዓ.ም አቀረበ፡፡

ከባለፈው ቅዳሜ ጀምሮ በአዲስ አበባ ኤግዚቪሸን ማዕከል ለጎብኝዎች እይታ ክፍት የተደረገው 14ኛው የቴክኒክ እና ሙያ ሳምንት ዐውደ ርዕይ የማምረቻ እና የምርት ፈጠራ ስራዎችን ለተመልካቾች ከማቅረብ ባሻገር በልዩ ልዩ ትርኢቶች እና አዝናኝ ውድድሮች እየተከበረ ይገኛል፡፡

በዛሬው ዕለትም በተካሄደው የፋሽን ሾው ትርኢት በኮሌጆች የተሰሩ የፋሽን ዲዛይኖች የተመልካቾችን ቀልብ የሰረቁ አስደማሚ ስራዎች የታዩ ሲሆን የጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ቴክስታይ ሌዘር ጋርመንት ዲፓርትመንት አሰልጣኞች እና ሰልጣኞች እጃችሁ ይባረክ ያስባለ ፈጠራዎችን ለመድረክ አብቅተዋል፡፡

ዲፓርትመንቱ በጋርመንት እና በሌዘር ዘርፎች ያዘጋጃቸውን ቅንጡ የወንድ እና የሴት ፋሽን ልብሶች እና መዋቢያዎች ለታዳሚዎች እና በመድረኩ ለተሰየሙት ዳኞች በማራኪ አቀራረብ አሳይቷል፡፡

ከዲዛይነሮቹ ፍሸና ጋር የሞደሎቹ ውብ አቀራረብ ተዳምሮ የመድረኩን ታዳሚ ቀልብ በመግዛት እውነትም ዊንጌት ብቸኛው የአይ ኤስ ኦ ባለቤት አስብሎታል።

በቴክኖሎጂ ረገድ በከተማ ደረጃ በዚህ ዐውደ ርዕይ በተለያዩ የሙያ ዓይነቶች 99 የማምረቻ፣ የምርት፣ የሀገር በቀል እና የኢንፎርሜሽን ኮሙዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ ፈጠራዎች ተሰርተው ለጎብኝዎች መቅረባቸው ታውቋል፡፡

             ‹‹በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት››
👍38🏆4👏32
ረቡዕ፡- ሰኔ 19 ቀን 2016 ዓ.ም

ኮሌጁ ዛሬ ባቀረበው የፋሽን ሾው ውድድር የአሸናፊዎች አሸናፊ ተፋላሚ ኮሌጆች ጋር ተቀላቀለ!!

ፋሽን እንደተመልካቹ ሳይሆን እንደሰሪው ነው በተባለላቸው ዲዛይነሮች ተጌጠው ያሸበረቁ ቄንጠኛ አልባሳትን በውብ ተክለሰውነታቸው አዋህደው ባስተዋወቁ እንቁ ሞደሊስቶች ሲታዩ የዳኞችን ዐይን በመስረቃቸው ነገም በአሸናፊዎች አሸናፊ ሜዳ ላይ ደግመን እንያችሁ ተብለዋል።

ስለሆነም የዊንጌት ቆንጃጅቶች ነገ 5:30 ላይ በድጋሜ ከአቻዎቻቸው ጋር በመድረኩ ይወረገረጋሉ።

መቼም ከዐይን ያውጣችሁ አንልም ከዳኞች ዐይን ይጣላችሁ እንጂ ዳግመኛ መልካም ዕድል ተመኘን።

             ‹‹በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት››
🏆22👍124
ሐሙስ፡- ሰኔ 20 ቀን 2016 ዓ.ም

በአዲስ አበባ ኤግዚቪሽን ማዕከል ሲካሄድ የቆየው የቴክኒክና ሙያ ሳምንት ዐውደ ርዕይ ተጠናቀቀ!!

ቴክኒክና ሙያ ለዘላቂ ልማት በሚል መሪ ቃል ለ6 ቀናት ሲካሄድ የቆየው 14ኛው የቴክኒክና ሙያ ሳምንት ዐውደ ርዕይ በዛሬው ዕለት ተጠናቋል።

በዕለቱ በክህሎት ውድድር፣ በጥናትና ምርምር፣ በቴክኖሎጂ፣ በፋሽን ሾው ትርኢትና በስፓርታዊ ጨዋታዎች ከአንደኛ እስከ ሶስተኛ ደረጃ  ለያዙ ኮሌጆች፣ አሰልጣኞች እና ሰልጣኞች የዋንጫ፣ የሰርተፍኬትና የገንዘብ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

በአጠቃላይ በቴክኖሎጂ ዘርፍ ውድድር ጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ 2ኛ ደረጃን ይዞ ሲያጠናቅቅ ተግባረ-ዕድ እና አቃቂ ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጆች አንደኛና ሶስተኛ ደረጃ ሆነዋል።

በሌላ በኩል  በፋሽን ሾው ትርኢት ምስራቅ፣ እንጦጦ እና ተግባረ ዕድ ከአንደኛ እስከ ሶስተኛ ያለውን ደረጃ በመያዝ ጨርሰዋል።

በማጠቃለያ መርሃ ግብሩ ላይ ተገኝተው የመዝጊያ ንግግር ያደረጉት በቢሮ ኃላፊ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስራና ክህሎት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ መክብብ ወልደሐና ሲሆኑ የቴክኒክና ሙያ ሳምንት የቴክኖሎጂ ዐውደ ርዕይ አጠቃላይ ዘርፉን ለህብረተሰቡ ለማስገንዘብ እና የተሰሩ የምርትና የማምረቻ ቴክኖሎጂዎች ወደ ኢንዱስትሪዎች ተሸጋግረው ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ ዕድል ይፈጥራል ብለዋል።

‹‹በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት››
👍244