Waliya Entertainment
ታዋቂው ዘፋኝ ቴዲ አፍሮ ዛሬ የተዘቀዘቀ ልብስ ለብሷል በሚል ከብዙዎቹ ቅሬታ እየደረሰበት ይገኛል በክርስትና እምነት ተከታዮች ዛሬ የሚከበረው በቃና ዘገሊላ ክብረ በአል ላይ ታዋቂው ዘፋኝ ቴዲ አፍሮ የተዘቀዘቀ መስቀል አድርጓል ከሚል ከአብዛኞቹ ተቃውሞ እየደረሰበት ነው። እርሶስ ምን አስተያየት አሎት? Follow us on Social Medias Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt…
ስህተት የመሰለ ፍጹም ልክነት!
ቴዲ አፍሮ ዛሬ ለብሶት በወጣው የሀገር ባህል ልብስ ላይ ያለው ጥልፍ እጅግ የተሳሳተ ነው። ይኼንን መሰል አለባበስ ከዚህ ቀደም የለበሱ ግለሰቦች በይፋ በሚዲያ ሲተቹ እንደነበር እናስታውሳለን። ምክኒያቱም ሰዎቹ በልካቸው የህዝብ ተቀባይነት ያላቸው በመሆናቸው ነው። እንደ ማንኛውም የሀገራችን ማህበረሰብ ቢታዩ ኖሮ ያን ትችት እንደማያስተናግዱ ግልጽ ነው። ምን ጊዜም Public Figure የሆኑ ሰዎች ወደ ሚዲያ ከመውጣታቸው በፊት የጸጉር ቅርጻቸውን እንደሚያሳምሩ ሁሉ የአለባበስ ሁኔታቸውንም መገምገም እንዳለባቸው የሚመክራቸው አካል ያስፈልጋል ብዬም አላምንም። ምክኒያቱም ያሉበት የእድሜ ደረጃ እና የሙያ ዘርፍ ይኼንን ትንሽዬ ነገር ለማገናዘብ ከበቂም በላይ ነው።
በይበልጥ እንደ ቴዲ አፍሮ ያሉ ተጽዕኖ ፈጣሪ ሰዎች ደግሞ እያንዳዱ እንቅስቃሴያቸው በጥንቃቄ የተሞላ መሆን እንዳለበት ግልጽ ነው። ስለሆነም አስቦበት ይኼንን ስህተት የሆነ ነገር እንደማያደርግ ልቤ ቢነግረኝም ስህተቱን ግን አይቶ ማለፍ ለነፍሴ ከስህተቱ ጋ እንደ መተባበር ያለ ውንብድና መስሎ ስለታያት ስህተቱን እንደ ስህተት ለመንቅፍ ፈለኩኝ። ይኼንንም ጽሁፍ እያዘጋጀሁ ባለሁበት ጊዜ ፎቶውን ቀድሜ ልኬለት የነበረ አንድ ወዳጄ ከአሜሪካ ደውሎ ቀጥሎ የጠቀስኩትን እይታ አይ ዘንድ ጠቆመኝ።
ይህ በቴዲ አፍሮ ቲሸርት ላይ የተቀመጠው የመስቀል ጥልፍ በረጅም ክር አንገት ላይ በሚደረግ የመስቀል አይነት የተጠለፈ ሲሆን በምስሉ ላይ እንደሚታየው በአንገቱ ዞሮ ከሚመጣ ቀጭን ጥልፍ ጋ ተያይዞ ወደ ደረቱ ይወርዳል። ከቀጭኑ ጥልፍ ጋ መስቀሉን የሚለዩ ለውበት የተቀመጡት ሁለቱ ዶቃ መሳይ ጥልፎች እንዳበቁ ትንሽዬው የአንገት መስቀል መሳዩ ጥልፍ (መስቀሉ ይጀምራል) ጥቂቶች እንዳሉት የተዘቀዘቀ መስቀል እንዳይሆን ማንጠልጠያ ክር መሳይ ጥልፍ እንጂ በእጅ እንደሚያዝ መስቀል ያለ ወደ ታች የሚወርድ (ወደ ላይ የወጣ) አንዳችም መያዣ የሚመስል ጥልፍ የለውም።
እንደሚታወቀው ክቡር ዶ/ር አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) ከልጅነት እስከ እውቀት ባለው የእድሜ ክፍሉ አስተዋይና ጥንቁቅ፣ ጨዋና ሰው አክባሪ፣ በፍቅርና በይቅርታ የሚያምን ሙሉ ሰው ነው። በግሉ ስህተት ሰርቶ ቢገኝ አይደለም በተለያዩ ጫናዎች ይስተጓጎሉ በነበሩ ስራዎቹ ዙሪ ከሚዲያ ይስሙ አልያም ከዜና አውታሮች መረጃውችን ያግኙ ብሎ ሳይዘናጋ ለአድናቂዎቹ እና ስራውን በቅርበትም ሆነ በርቀት ለሚከታተሉ አካላት፣ ድርጅቶችና ግለሰቦች ትልቅ ይቅርታን በማስቀደም በግልጽ የመስተጓጎሉን ምክኒያቶች ጠቅሶ መረጃ የሚሰጥ እጅግ ጨዋ ሰው ነው። ዛሬም ይኽ እንደኔና እንደመሰሎቼ (ቀድመን እንደሳትን ሰዎች) አረዳድ ነገሩ ስህተት ሆኖ ቢሆን ቴዲ አፍሮ ነገሩን በማስተዋል ባለማድረጉ በይፋ ይቅርታ እንደሚጠይቅ ምንም ጥርጥር የለኝም። ዳሩ ግን ስህተቱ የኔና የመሰሎቼ በጥልቀት ያለማየት ነውና ምንም ይቅርታ የሚያስጠይቅ ጉዳይ አለመሆኑን ሁሉም እንደሚረዳው ግልጽ ነው።
✍#ታታ_አፍሮ (ነፃ ብዕር)
Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt
#Waliya_Entertainemnt #Music