🛑❌እነዚህን አጭበርባሪ ሌቦች ለፖሊስ በማጋለጥ ተባበሩኝ።🔴❌❌❗️❗️
ከዚህ በታች ያለው ምስል የምታዩት በኔ ስም የተከፈተ ሀሰተኛ የፌስቡክ አካውንት ነው።
🔴ህገወጥ መዳኒቶችን ለህብረተሰቡ እየሸጡ እና እያታለሉ ይገኛሉ፣ በምስሉ ላይ ያስቀመጥኩት፣ ብዙ ሰዎችን የሚያጭበረብሩበት የባንክ አካውንት እና ስም ነው።
🟢የኔ ትክክለኛው የፌስቡክ አካውንት ይሄ ነው
https://fb.me/seifemedfb
🔴እኔ አሁንም ወደፊትም ምንም አይነት መዳኒት አልሸጥም፣ በኔ ስም እና ፎቶ መዳኒት ሲሸጥ ካያችሁ እባካችሁ በቶሎ ለፖሊስ አመልክቱ።
ዶ/ር ሰይፈ
🔴🔴🔴እባካችሁ ሼር ሼር ሼር ሼር
ከዚህ በታች ያለው ምስል የምታዩት በኔ ስም የተከፈተ ሀሰተኛ የፌስቡክ አካውንት ነው።
🔴ህገወጥ መዳኒቶችን ለህብረተሰቡ እየሸጡ እና እያታለሉ ይገኛሉ፣ በምስሉ ላይ ያስቀመጥኩት፣ ብዙ ሰዎችን የሚያጭበረብሩበት የባንክ አካውንት እና ስም ነው።
🔴እኔ አሁንም ወደፊትም ምንም አይነት መዳኒት አልሸጥም፣ በኔ ስም እና ፎቶ መዳኒት ሲሸጥ ካያችሁ እባካችሁ በቶሎ ለፖሊስ አመልክቱ።
ዶ/ር ሰይፈ
🔴🔴🔴እባካችሁ ሼር ሼር ሼር ሼር
Facebook
Log in or sign up to view
See posts, photos and more on Facebook.
👍122❤9🙏8👌5🥰4👏4🤩4
🛑❌እነዚህን አጭበርባሪ ሌቦች ለፖሊስ በማጋለጥ ተባበሩኝ።🔴❌❌❗️❗️
ከዚህ በላይ ያለው ምስል የምታዩት በኔ ስም የተከፈተ ሀሰተኛ የፌስቡክ አካውንት ነው።
🔴ህገወጥ መዳኒቶችን ለህብረተሰቡ እየሸጡ እና እያታለሉ ይገኛሉ፣ በምስሉ ላይ ያስቀመጥኩት፣ ብዙ ሰዎችን የሚያጭበረብሩበት የባንክ አካውንት እና ስም ነው።
🟢የኔ ትክክለኛው የፌስቡክ አካውንት ይሄ ነው https://fb.me/seifemedfb
🔴እኔ አሁንም ወደፊትም ምንም አይነት መዳኒት አልሸጥም፣ በኔ ስም እና ፎቶ መዳኒት ሲሸጥ ካያችሁ እባካችሁ በቶሎ ለፖሊስ አመልክቱ።
ዶ/ር ሰይፈ
🔴🔴🔴እባካችሁ ሼር ሼር ሼር ሼር
ከዚህ በላይ ያለው ምስል የምታዩት በኔ ስም የተከፈተ ሀሰተኛ የፌስቡክ አካውንት ነው።
🔴ህገወጥ መዳኒቶችን ለህብረተሰቡ እየሸጡ እና እያታለሉ ይገኛሉ፣ በምስሉ ላይ ያስቀመጥኩት፣ ብዙ ሰዎችን የሚያጭበረብሩበት የባንክ አካውንት እና ስም ነው።
🔴እኔ አሁንም ወደፊትም ምንም አይነት መዳኒት አልሸጥም፣ በኔ ስም እና ፎቶ መዳኒት ሲሸጥ ካያችሁ እባካችሁ በቶሎ ለፖሊስ አመልክቱ።
ዶ/ር ሰይፈ
🔴🔴🔴እባካችሁ ሼር ሼር ሼር ሼር
👍132🥰18❤14👏5👌4
➕➕ የጨጓራ ህመም ➕➕
🖲የጨጓራ በሽታ ያለበት ሰው ላይ፣ የደም ማነስ ካለ እና የሚከሳ ከሆነ፣ ጥሩ ምልክት አይደለም።
🖲የጨጓራ ህመም ያለበት ሰው ሁሉ፣ ደሞ የጨጓራ ቁስለት አለበት ማለት አይደለም።
🖲የጨጓራ ቁስለት ሲኖር ፣ የህመም ስሜቱ እና የጉዳት ደረጃው፣ ቁስለቱ እንደወጣበት ቦታ እና እንደ ይዘቱ የተለያየ ነው።
🖲 አንድ ሰው ላይ፣ የጨጓራ ቁስለት ባይኖር እነኳን፣ የጨጓራ ህመም ሊፈጠር ይችላል።
🖲 የጨጓራ ቁስለት ደሞ፣ ባጣዳፊ መልኩ የሚፈጠር ሳይሆን አብዛኛውን ግዜ ስር ሰዶ የሚፈጠር ቁስለት ነው።
🖲 አንዳንዴ ፣የጨጓራ ቁስለት ያለባቸው ሰዎች፣ የህመም ስሜት ላይሰማቸው ይችላል፣ በተቃራኒው ደሞ፣ የጨጓራ ህመም ስሜት የሚሰማቸው አብዛኛዎቹ ታካሚዎች፣ በምርመራ ግዜ የጨጓራ ቁስለት ላይኖራቸው ይችላል።
🖲 አንድ ሰው ላይ የጨጓራ ህመም እና የጨጓራ ቁስለት ሊፈጠር የሚችለው፣ በተለያዩ ምክኒያቶች፣ ሆድ የሚያመርተው የአሲድ መጠን የበዛ ከሆነ እና የሆድ ግድግዳ ራሱን ከዚህ አሲድ የሚከላከልበት መንገድ የተዳከመ ከሆነ ነው።
🖲 አብዛኛውን ግዜ ፣ በህክምናው አንድ ሰው ላይ የጨጓራ ህመም መኖሩን ለማወቅ አዳጋች አይደለም፣ የህመም ስሜቶቹን በማገናዘብ የጨጓራ በሽታ መኖሩን ለመተንበይ ያስችላል።
🖲 ምግብ ከተበላ በኋላ አለመስማማት፣ በተደጋጋሚ ግዜ ማግሳት ፣ ቃር ወይም የደረት ማቃጠል እና ማቅለሽለሽ ፣ የመሳሰሉ የህመም ስሜቶች፣ የጨጓራ ህመም መኖሩን የሚገልፁ ምልክቶች ናቸው።
🖲 ከእንብርት በላይ የሚሰማ የሚጎትት የሆድ ህመም መኖር፣ ማቅለሽለሽ እና በተደጋጋሚ ማስመለስ፣ በተለይ ደሞ ደም የሚያስመልስ ከሆነ እና ከፍተኛ እና አጣዳፊ የሆነ የሆድ ህመም ካለ፣ 🚩ይህ አይነቱ የህመም ስሜት ጠንከር ያለ የጨጓራ ቁስለት መኖሩን የሚያመላክት ስለሆነ እና፣ እንዲሁም ወዲያውኑ ካልታከመ ለከፋ ጉዳት ስለሚዳርግ፣ በቶሎ ወደ ህክምና ተቋም መሄድ ያስፈልጋል።
🖲 እድሜያቸው 45 እና ከዛበላይ የሆኑ ሰዎች፣ የጨጓራ ህመም ስሜት ከታየባቸው፣ እንዲሁም ደሞ ፣በየትኛውም የእድሜ ክልል ላይ ያሉ ሰዎች፣
👉 በተደጋጋሚ ግዜ የሚመጣ ማስመለስ ካላቸው፣
👉ለመዋጥ የሚቸገሩ እና ሲውጡ ህመም የሚሰማቸው ከሆነ፣
👉 መክሳት ወይም ክብደት መቀነስ ካላቸው፣ እና፣
👉እንዲሁም የደማነስ የሚታይባቸው ከሆነ፣ የኢንዶስኮፒ ምርመራ የሚያስፈልጋቸው ይሆናል።
🖲 ህክምናውን እና በቤት ውስጥ መደረግ ስላለበት የጨጓራ ህመም እንክብካቤ በተመለከተ፣ ሰፋ ያለ መረጃ በ Youtube ቻናሌ ላይ አስቀምጫለሁ። ከዚህ በታች ያለውን ሊንክ ተጭናችሁ መመልከት ትችላላችሁ።
🚩 ጥያቄ ለመጠየቅ፣ ዘወትር ቅዳሜ ከ 9 እስከ 11 ሰአት ድረስ ብቻ መደወል ትችላላችሁ።📞 0974163424 ዶ/ር ሰይፈ ወርቁ
🚩ለህክምና ቀጠሮ ብቻ ይሄን 👉 @LEKETERO ወይም @Apointment1
ተጭነው ስም እና ስልክ በማስቀመጥ ቀጠሮ መያዝ ይችላሉ። መልካም ግዜ
👇👇👇
https://youtu.be/q1qpUlChfxo

YouTube
የጨጓራ በሽታ ህክምና (መፍትሄ) | Dyspepsia and PUD | Dr. Seife | ዶ/ር ሰይፈ #drseife #medical
ለህክምና አገልግሎት እኔን በስልክ ለመሰግኘት፣ ዘወትር ቅዳሜ ከ ሰዓት ከ9 እስ 11 ባለው ግዜ ብቻ በ 0974163424 መደወል ይችላሉ
ለህክምና ቀጠሮ በአካል ለማግኘት ከፈለጉ የቴሌግራም ቻናሌ ላይ አድራሻ አስቀምጫለሁ።
የቴሌግራም አድራሻ 👉https://t.me/seifemed

👍232❤64🙏36🥰12🏆11👏8🤩5👌5
➕➕ የጥፍር መሰባበር ➕➕
🖲 በተደጋጋሚ ግዜ የጥፍር ቀለምን መቀባት እና ጠንካራ በሆነ የጥፍር ቀለም ማስለቀቂያ በተደጋጋሚ ጥፍርን መፈተግ አንዳንዴ፣ የጥፍርን ተፈጥሮአዊ ገፅታ ሊቀይር እና ጥፍር አንዲሳሳ እንዲሁም በቀላሉ እንዲሰባበር ምክኒያት ሊሆን ይችላል።
🖲አንዳንዴ፣ ጥፍር ላይ ከወትሮው ለየት ያሉ ገፅታዎች ሲታዩ፣ የበሽታ ጠቋሚ ምልክቶች ሊሆኑ ይችላሉ
🖲ከጥፍር መሳሳት መሰነጣጠቅ እና መሰባበር ጋር ተያይዘው፣ አንድ ሰው ጥፍር ላይ የሚታዩ ምልክቶች፣ የራሳቸው የሆነ ባህሪዎች እና የራሳቸው የሆነ የህክምና ስያሜዎች አሏቸው
🖲ታዲያ፣ ጠቅለል ባለ መልኩ ለመግለፅ ያህል፣ የጥፍር መሰነጣጠቅ ፣ የጥፍር በቀላሉ ተሰባሪ መሆን እንዲሁም ጥፍር የተፈጥሮ አቅሙን ሲያጣ፣ ምክኒያቱ፣ ከተጓዳኝ የጤና ችግሮች የተነሳ ሊሆን ይችላል፣ ወይም ደሞ ፣ ምንም አይነት ተጓዳኝ የጤና ችግር በሌለበት ሁኔታ፣ በራሱ ግዜ ሊፈጠርም ይችላል።
🖲በተጓዳኝ በሽታ ምክኒያት ሊከሰት የሚችል የጥፍር መሰባበር እና መሰነጣጠቅ ሲኖር ፣ አብዛኛውን ግዜ፣ የእግር እና የእጅ ጥፍርን አብሮ ሊያጠቃ የሚችልበት አጋጣሚ ሊፈጠር ይችላል።
🖲 በዚህን ግዜ ለተጓዳኝ የጤና ችግሮች የሚሰጥ ህክምና፣ ለችግሩ ዋነኛ መፍትሄ ይሆናል።
🖲 ከዛ ውጪ፣ ለጤናማ የጥፍር እድገት መሰረታዊ የሆኑ እንደ ባዮቲን፣ አይረን እና ዚንክ የመሳሰሉ ጠቃሚ ንጥረ ነገሮችን በውስጣቸው የሚይዙ ምግቦችን ማዘውተር፣ ለጥፍር ጤንነት ጉልህ ሚናን ይጫወታሉ።
🖲 ለምሰሌ፣ የዶሮ ወይም የከብት ጉበት፣ እንቁላል፣ አቮካዶ፣ አተር፣ ለውዝ ፣ ሱፍ፣ አጃ፣ ብሮኮሊ የመሳሰሉት ምግቦች በባዮቲን፣ በዚንክ እና በአይረን የበለፀጉ ምግቦች ናቸው።
🖲 ይህ የማይቻል ከሆነ ደሞ፣ እንዚህን ጠቃሚ ንጥረነገሮች በበቂ ሁኔታ የሚይዙ የቫይታሚን ሰፕልመንቶችን በቀን 1 ፍሬ ከ 3 እስከ 6 ወር ያህል መጠቀም ይቻላል።
🖲ይህን በተመለከተ፣ በምስል የተደገፈ ተጨማሪ መረጃ በዩቲዩብ ቻናሌ ላይ አስቀምጫለሁ። የሚቀጥለውን አድራሻ በመጫን መመልከት ትችላላችሁ።
🚩 ጥያቄ ለመጠየቅ፣ ዘወትር ቅዳሜ ከ 9 እስከ 11 ሰአት ድረስ ብቻ መደወል ትችላላችሁ።📞 0974163424 ዶ/ር ሰይፈ ወርቁ
🚩ለህክምና ቀጠሮ ብቻ ይሄን 👉 @LEKETERO ወይም @Apointment1
ተጭነው ስም እና ስልክ በማስቀመጥ ቀጠሮ መያዝ ይችላሉ። መልካም ግዜ
👇👇👇👇👇👇👇
https://youtu.be/x2Z178dYa7Y

ለተሰባበረ ጥፍር መፍትሄው | Nail fragility | Dr. Seife | ዶ/ር ሰይፈ #drseife #medical #habesha
ለህክምና አገልግሎት እኔን በስልክ ለመሰግኘት፣ ዘወትር ቅዳሜ ከ ሰዓት ከ9 እስ 11 ባለው ግዜ ብቻ በ 0974163424 መደወል ይችላሉ
ለህክምና ቀጠሮ በአካል ለማግኘት ከፈለጉ የቴሌግራም ቻናሌ ላይ አድራሻ አስቀምጫለሁ።
የቴሌግራም አድራሻ 👉https://t.me/seifemed
ለህክምና ቀጠሮ በአካል ለማግኘት ከፈለጉ የቴሌግራም ቻናሌ ላይ አድራሻ አስቀምጫለሁ።
የቴሌግራም አድራሻ 👉https://t.me/seifemed
👍150❤44🙏15🥰12
Forwarded from Hakim
ለወንድማችን እንድረስለት
ይህ በፎቶ የምታየው ዶ/ር ያዕቆብ ጨመረ ይባላል። በሰሜን ሸዋ ዞን በሞረትና ጅሩ ወረዳ በእነዋሪ ሚሊኒየም ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ከፍተኛ ውጤት በማስመዝገብ በወቅቱ ሜዲስን (medicine) ትምህርት እንዲያጠና በሃረማያ ዩኒቨርስቲ ገብቶና ትምህርቱን በከፍተኛ ውጤት በማጠናቀቅ በድሬደዋ ዮኒቨርስቲ በሌክቸርነትና በሆስፒታሉ በህክምና ዶክተርነት ሲያገለግል ቆይቷል።
አሁን ላይ በሃዋሳ ዩኒቨርስቲ በዐይን ህክምና ስፔሻላይዜሽን ትምህርት ክፍል የሶስተኛ አመት ተማሪ እያለ በጭንቅላት እጢ ታሞ የሀኪሞች ቦርድ ሕንድ ሄዶ እንዲታከም ጽፈውለታል። ለሕክምናው የሚያስፈልገው ከ1ሚሊየን ብር በላይ በመሆኑ ተቼግሯል::
1000474028864
Dr. YAKOB CHEMERE
Phone 0910144989
[Medical document will be provided upon request]
@HakimEthio

👍223❤56🥰9
➕➕ የፀጉር እንክብካቤ ➕➕
➕➕(Shampoo & Conditioner)➕➕
🖲 የፀጉር እንክብካቤ ፣ የፀጉር ንፅህናን ከመጠበቅ ይጀምራል።
🖲ፀጉር ከቆዳ በበለጠ መልኩ በተለያዩ ምክኒያቶች ሊቆሽሽ ይችላል፣ ደረቅ ፀጉር እርስ በእርሱ ሲፋተግ የኤሌክትሪክ ቻርጅ ስለሚያጠራቅም፣ በቀላሉ ብናኝን የመሳብ አቅም አለው።
🖲በተጨማሪም የራስ ቅል ቆዳ ፍርፋሪ ፣ከፀጉር ስር የሚመነጭ የተፈጥሮ ወዝ እና ላብ ከልክ ያለፈ ሲሆን፣ እንዲሁም ለፀጉር ውበት በምንጠቀማቸው፣ ዘመናዊ እና ባህላዊ ቅባቶች ምክኒያት ፀጉር በቀላሉ ሊቆሽሽ ይችላል።
🖲ታዲያ፣ ፀጉር ሲታጠብ፣ ከትኩስ ውሀ ይልቅ፣ በመጠኑ ለብ ያለ ውሀን መጠቀም ተመራጭ ነው ። ፀጉር እርጥብ እንደሆነ ማበጠር ደሞ፣ የፀጉርን ሰበቃ ስለሚጨምር ፀጉር ከልክ በላይ ሊሳሳብ እና ሊሰባበር ይችላል።
🖲 ፀጉር እርጥብ እንደሆነ ለማበጠር ከተፈለገ፣ ለዚህ ተብለው የተዘጋጁ ለየት ያሉ ኮንዲሽነሮችን መጠቀም ያስፈልጋል።
🚩 ስለነዚህ ምርቶች በቪዲዮው ላይ አይነታቸውን አብራርቻለሁ።
🖲ፀጉር ላይ የምንጠቀማቸው ሳሙናዎች፣ ጥንካሬያቸው፣ የፀጉሩን አይነት ያማከለ ካልሆነ፣ የፀጉር ቅርፊትን እና የፀጉር ተፈጥሮአዊ ወዝን ከልክ ባለፈ መልኩ ስለሚያነሱ፣ ፀጉርን ሊያገረጡና ውበቱን ሊያሳጡት ይችላሉ።
🖲በተለይ ጨዋማ የሆነ ወይም ፣የጉድጓድ ውሀ ባለበት ቦታ የሚኖር ሰው፣ ለፀጉር ንፅህና፣ የገላ ወይም የልብስ ሳሙናን ባይጠቀም ተመራጭ ነው።
🖲ከዛ ይልቅ ፣ እንደ ፀጉሩ አይነት በተለያየ ጥንካሬ የተዘጋጁ የፀጉር ሻምፖዎችን መጠቀም ይመረጣል።
🖲ገበያ ላይ 11 አይነት የፀጉር ሻምፖዎችን ልታገኙ ትችላላችሁ። እነዚህ ሻምፖዎች በውስጣቸው የሚጨመርባቸው ግብአት፣ የተጠቃሚውን ትኩረት ለመሳብ ሲባል፣ ከፋብሪካ ፋብሪካ ወይም ከምርት ምርት የተለያዩ ሊሆኑ ይችላሉ።
🖲ነገር ግን፣ የትኛውም ፋብሪካ ቢሆን፣ አንድን ሻምፖ ለገበያ ሲያቀርብ፣ በዋነኝነት 5 የዲተርጀንት አይነቶችን ይጠቀማል።
🖲ከነዚህ ውስጥ፣ አንድን ሻምፖ ጠንካራ የሚያስብለው፣ በውስጡ በሚይዘው የ ሰልፌት አዘል ዲተርጀንት ፣አይነት እና መጠን ይሆናል።
🖲 ስለተለያዩ የሻምፖ እና የኮንዲሽነር አይነቶች፣ እንዲሁም የትኞቹ ምርቶች ለየትኛው የፀጉር አይነት ተስማሚ እንደሆኑ፣ በቪዲዮው ላይ በምስል የታገዘ መረጃ አስቀምጫለሁ።
🖲 ከዚህ በታች ያለውን ሊንክ በመጫን ፣ ቪዲዮውን መመልከት ይችላሉ 👇👇👇
https://youtu.be/5lX5lmp2u9Q
ጥያቄ ለመጠየቅ፣ ዘወትር ቅዳሜ ከ 9 እስከ 11 ሰአት ድረስ ብቻ መደወል ትችላላችሁ።📞 0974163424 ዶ/ር ሰይፈ ወርቁ

ሻምፖ እና ኮንዲሽነር (Shampoo & Conditioner | የፀጉር እንክብካቤ | ዶ/ር ሰይፈ | Dr.Seife #drseife #medical #habesha
ለህክምና አገልግሎት እኔን በስልክ ለመሰግኘት፣ ዘወትር ቅዳሜ ከ ሰዓት ከ9 እስ 11 ባለው ግዜ ብቻ በ 0974163424 መደወል ይችላሉ
ለህክምና ቀጠሮ በአካል ለማግኘት ከፈለጉ የቴሌግራም ቻናሌ ላይ አድራሻ አስቀምጫለሁ።
የቴሌግራም አድራሻ 👉https://t.me/seifemed
ለህክምና ቀጠሮ በአካል ለማግኘት ከፈለጉ የቴሌግራም ቻናሌ ላይ አድራሻ አስቀምጫለሁ።
የቴሌግራም አድራሻ 👉https://t.me/seifemed
👍211❤65👌21🏆16💯14👏9🥰2🙏2🎉1🤩1
Forwarded from Dr Haileleul | ዶ/ር ኃይለልዑል 🩺
🙏 ለጤና ባለሙያዉ እንድረስለት 🙏
🔹ከታች የምትመለከቱት ወንድማችን ተሾመ አበራ ይባላል። ተወልዶ ያደገው በደምቢ ዶሎ ከተማ ሲሆን የአንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን እዛው በማጠናቀቅ ወደ አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በመሄድ በህብረተሰብ ጤና ት/ት ክፍል በጥሩ ዉጤት ተመርቆ ህብረተሰቡን እያገለገለ ለተወሰነ ጊዜ ቢቆይም በአዕምሮ ህመም ምክንያት እንደቀድሞዉ መስራት አልቻለም።
🔹በአካባቢው ባለ ሆስፒታል ቢታከምም ህመሙ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን እና ወደ አማኑኤል ሆስታፒል ሪፈር ቢፃፍለትም ወላጅ እናቱ ብቻቸውን በመሆናቸው እሱን ለማሳከም ከአቅማቸው በላይ ሆኖባቸዋል ።
🔸አቅማችንሁ በፈቀደ መጠን በእናቱ ስም በተከፈተ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካዉንት እጃችሁን እንድትዘረጉ በፈጣሪ ስም እንጠይቃለን።
# 1000527420265(CBE-አያሉ)
ለብዙዎች እንዲደርስ ሼር ያድርጉ::
ዶ/ር ኃይለልዑል-ሀኪሙ

👍278🏆13🙏8👏3👌2
➕➕የፀጉር ቅባት ➕➕
🖲የትኛውም የፀጉር ቅባት ፣ ከተፈጥሮ ውጪ የፀጉር ርዝመትን አይጨምርም። ነገር ግን፣ እንክብካቤ የጎደለው ፀጉር ጥንካሬውን ስለሚያጣ ከእድሜው በፊት ይሰባበርና የፀጉርን ርዝመት ያሳጥራል።
🖲 አንዳንድ ሴቶች፣ ለፀጉራቸው እንክብካቤ፣ ከቅባት ይልቅ ቅቤ መቀባትን ይመርጣሉ። አንዳንድ ሴቶች ደሞ፣ ቅቤ የሚፈጥረውን መጥፎ ጠረን በመጥላት እና የቀለጠው ቅቤ ፊታቸውን ሲነካ ስለማይወዱ፣ ቅቤ ከመቀባት ይልቅ የፀጉር ቅባትን ይመርጣሉ።
🖲 አንድ ሰው፣ ውብ የሆነ የፀጉር ገፅታ እንዲኖረው መጀመሪያ የፀጉሩን ተፈጥሮአዊ ባህሪ ማወቅ አለበት።
🖲 የፀጉሩን አይነት ባማከለ መልኩ በቂ የሆነ የፀጉር እንክብካቤ ሲኖር እና ፣ፀጉር ልከኛ በሆነ መንገድ የሚዋብ ከሆነ ጥንካሬውን እና ውበቱን እንደጠበቀ መቆየት ይችላል።
🖲 በቂ እንክብካቤ የሌለው ፀጉር ፣ ለማስዋብ ሲባል ከልክ ባለፈ መልኩ የሚንገላታ ከሆነ፣ ፀጉሩ በግዜ ሂደት በቀላሉ የሚበላሽ እና በተፈለገው መንገድ ለማስዋብም አስቸጋሪ እየሆነ ይሄዳል።
🖲 ፀጉር በተፈጥሮው አንዴ ከተበላሸና ፣ተፈጥሮአዊ ገፅታውን ካጣ በኋላ፣ የተበላሸውን የፀጉር ከመቁረጥ ውጪ፣ ፀጉሩን በቋሚነት ወደነበረበት ገፅታው ለመመለስ የሚያስችል የፀጉር ቅባት የለም።
🖲 ነገር ግን፣ የተበላሸው ፀጉር ከተቆረጠ በኋላ፣ ከስር በአዲስ መልክ የሚበቅለውን ፀጉር ተፈጥሮአዊ ገፅታውን ሳይለቅ ለረጅም ግዜ እንዲቆይ የሚረዱ የተለያዩ የፀጉር ቅባቶች አሉ።
🖲 አንድ የፀጉር ቅባት፣ ለፀጉር እንክብካቤ ተመራጭ የሚሆነው፣ የፀጉርን ዘለላ በደምብ የማራስ ባህሪ ሲኖረው እና የፀጉሩን ተፈጥሮአዊ ይዘት የሚያጎላ ሆኖ ሲገኝ ነው።
🖲ገበያ ላይ የተለያዩ የፀጉር ቅባት አይነቶች ይገኛሉ፣ ከምርቶች ውስጥ ለአፍሪካዊ ፀጉር ተስመማሚ የሚሆኑት የተፈጥሮ እና የመአድን ዘይት መጠናቸው ከፍ ያሉ ቅባቶች ናቸው።
🖲ገበያ ላይ የፀጉር ዘይቶች ለብቻቸው እንዲሁም ከተለያዩ ጠቃሚ ንጥረ ነገሮች ጋር ተቀላቅለው ለተጠቃሚው ይቀርባሉ።
🖲 አብዛኛውን ግዜ በተጠቃሚዎች ዘንድ የሚታወቁት፣ የ Olive Oil እና Shea Butter ናቸው። እነዚህ ቅባቶች ሁለቱም ለአፍሪካዊ ፀጉር እንክብካቤ ጠቃሚ ናቸው። በተለይ Shea Butter, ከርዳዳ ፀጉር ላለው ሰው የፀጉርን እርጥበት እና ወዛማ ገፅታን ይጠብቃል።
🖲 ከነዚህም ውጪ፣ እንደ Coconut Oil, Jojoba Oil, Argan Oli, እና Tea Tree Oil የመሳሰሉ ለአፍሪካዊ የፀጉር አይነት ተመራጭ የሆኑ ቅባቶችም አሉ።
🚩 ስለነዚህ ቅባቶች ጠቀሜታ እና አይነታቸውን በተመለከተ በዩቲዩብ ቻናሌ ላይ ሰፋ ያለ መረጃ አቅርቤያለሁ።
🚩የሚቀጥለውን Link በመጫን መመልከት ትችላላችሁ። አመሰግናለሁ ።
👇👇👇👇👇
🛑ለህክምና ቀጠሮ ብቻ ይሄን 👉 @LEKETERO ወይም @Apointment1
ተጭነው ስም እና ስልክ በማስቀመጥ ቀጠሮ መያዝ ይችላሉ። መልካም ግዜ
https://youtu.be/H2ALiwlnXH0

የፀጉር ቅባት |Hair oils (coconut, jojoba, argan.. etc ) | Dr. Seife | ዶ/ር ሰይፈ #drseife #medical #habesha
ለህክምና አገልግሎት እኔን በስልክ ለመሰግኘት፣ ዘወትር ቅዳሜ ከ ሰዓት ከ9 እስ 11 ባለው ግዜ ብቻ በ 0974163424 መደወል ይችላሉ
ለህክምና ቀጠሮ በአካል ለማግኘት ከፈለጉ የቴሌግራም ቻናሌ ላይ አድራሻ አስቀምጫለሁ።
የቴሌግራም አድራሻ 👉https://t.me/seifemed
ለህክምና ቀጠሮ በአካል ለማግኘት ከፈለጉ የቴሌግራም ቻናሌ ላይ አድራሻ አስቀምጫለሁ።
የቴሌግራም አድራሻ 👉https://t.me/seifemed
👍285❤106🥰22🙏21🤩11🎉8👏6👌6
➕➕የዓይን ዙሪያ ጥቁረት➕➕
🖲 የዓይን ዙሪያ ጥቁረት፣ አብዛኛውን ግዜ በቀላሉ የሚጠፋ ጥቁረት አይደለም
🖲አንዳንዴ ፣እንደ ጥቁረቱ ይዘት እና እንደ መጣበት ምክኒያት ህክምና ሲደረግ፣ አንዳንዱ ሙሉበሙሉ የሚጠፋ፣ አብዛኛው ደሞ፣ በከፊል ወይም በመጠኑ ብቻ የሚደበዝዝ ሆኖ ይገኛል።
🖲ምክኒያቱም፣ በዓይን ዙሪያ ያለ ቆዳ ከሌላው ቆዳ የበለጠ ስስ ከመሆኑ የተነሳ፣ ቆዳው ላይ የሚፈጠር ጥቁረት አብዛኛውን ግዜ ከቆዳው ስር ስለሚጠራቀም ነው።
🖲 የዓይን ዙሪያ ጥቁረት፣ አራት መነሻ መሰረቶች አሉት፣ የመጀመሪያው በዓይን ዙሪያ ላይ ያለው ቆዳ ፣ በተፈጥሮም ሆነ በተለያዩ ምክኒያቶች ቀለሙ ከልክ ያለፈ ሆኖ ሲገኝ ነው።
🖲 ሁለተኛው መነሻ መሰረት ደሞ ፣ከቆዳው ስር ያሉ ደም ስሮች ገነው በሚታዩበት ግዜ ነው። የዚህ አይነቱ ሁኔታ፣ በተለይ ቀላ ያለ የቆዳ ቀለም ያላቸው ሰዎች፣ በዓይናቸው ዙሪያ ያለው ቆዳ የሳሳ ይሆንና አንዳንዴ በዙሪያው ያለው ደምስር ጎልቶ ሲወጣ በዓይናቸው ዙሪያ ጥቁረትን ሊፈጥርባቸው ይችላል።
🖲 ሶስተኛው መነሻ መሰረት ፣ በዓይን ዙሪያ የሚፈጠር እብጠት ወይም መሰርጎድ ሲኖር ፣ በቦታው ላይ የሚፈጥረው ጥላ የዓይን ዙሪያ ጥቁረት ሆኖ ሊታይ ይችላል።
🖲 አራተኛው እና የመጨረሻው ምክኒያት ደሞ፣ አንድ ሰው ላይ እነዚህ ሶስት መነሻ መሰረቶች ተደራርበው በሚከሰቱበት ግዜ ነው። ለምሳሌ፣ በዓይን ዙሪያ ገኖ የሚታይ ደምስር ያለበት ሰው፣ በተጨማሪም የዓይን ስር እብጠት ወይም መሰርጎድ ሲኖረው የጥቁረቱ መነሻ የተደራረበ ይሆናል ማለት ነው።
🖲 ታዲያ፣ አንድ ሰው የዓይን ዙሪያ ጥቁረትን ለመቀነስ መጀመሪያ የዓይን ዙሪያ ጥቁረቱ የተፈጠረው ከተጓዳኝ የቆዳ ችግር አለመሆኑን ሀኪም ጋር ቀርቦ ማረጋገጥ አለበት።
🖲 ማድያትም ሆነ፣ ማንኛውም ቁጣን የሚፈጥር የቆዳ ችግር ካለ፣ ጥቁረትን የሚጀምር እና የሚያባብስ ምክኒያት ስለሚሆን ህክምና ማድረግ ያስፈልጋል።
🖲 ከዛ ውጪ፣ እንደ እንቅልፍ ማጣት፣ ከፍተኛ የህይወት ጫና መኖር፣ የአልኮል መጠጦችን ከልክ ባለፈ መልኩ መጠጣት፣ እና፣ ራስን ለከፍተኛ የፀሀይ ጨረር ማጋለጥ የመሳሰሉ ምክኒያቶች፣ የአይን ዙሪያ ጥቁረትን የሚያባብሱ ናቸው፣
🖲 ለዚህም ሲባል፣ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎችን ማዘውተር ፣ በቂ እረፍት እና በቂ ውሀ መጠጣት፣ እንዲሁም ደሞ፣ ወደፀሀይ ሲወጣ ዓይንን በአግባቡ የሚሸፍን የፀሀይ መከላከያ መነፅሮችን መጠቀም ያስፈልጋል።
🖲 በተጨማሪም፣ ከተቻለ፣ የሚኒራል ይዘት ያላቸውን፣ ለዓይን ዙሪያ ቆዳ የተዘጋጁ የፀሀይ መከላከያ ክሬሞችን ብቻ መጠቀም እና ፀሀይ ላይ ከ ሁለት ሰአት በላይ መቆየት ግዴታ ከሆነ ፣ ደግሞ መቀባት ያስፈልጋል
🖲 ከዛ ውጪ፣ የአይን ዙሪያ ጥቁረትን ለመቀነስ የሚረዱ ፣በሚቀባ መልክ የተዘጋጁ የተለያዩ ክሬሞች አሉ። እነዚህ ክሬሞች ያላቸው አቅም እና ውጤታማነታቸው ከሰው ሰው የተለያየ ነው።
🖲 ታዲያ፣ አብዛኛውን ግዜ፣ የዓይን ዙሪያ ጥቁረትን ለመቀነስ ሲታሰብ፣ አንድ ክሬም ብቻ መጠቀም ያንን ያህል አጥጋቢ ለውጥን አያስገኝም። በተለያየ መንገድ ጥቁረቱን ለመቀነስ እንዲያስችል ከ አንድ በላይ ክሬሞችን መጠቀም ተመራጭ ነው።
🔵 ስለነዚህ ክሬሞች አይነት እና አጠቃቀማቸውን በተመለከተ፣ የበለጠ መረጃ በ YouTube ቻናሌ ላይ አስቀምጫለሁ። የሚቀጥለውን አድራሻ ተጭናችሁ ማግኘት ትችላላችሁ። አመሰግናለሁ።
👇👇👇👇👇👇
https://youtu.be/8weptclRps4

የአይን ስር ቅባቶች | Topicals for Dark Circle | Dr. Seife | ዶ/ር ሰይፈ | #medical #habesha #drseife
ለህክምና አገልግሎት እኔን በስልክ ለመሰግኘት፣ ዘወትር ቅዳሜ ከ ሰዓት ከ9 እስ 11 ባለው ግዜ ብቻ በ 0974163424 መደወል ይችላሉ
ለህክምና ቀጠሮ በአካል ለማግኘት ከፈለጉ የቴሌግራም ቻናሌ ላይ አድራሻ አስቀምጫለሁ።
የቴሌግራም አድራሻ 👉https://t.me/seifemed
ለህክምና ቀጠሮ በአካል ለማግኘት ከፈለጉ የቴሌግራም ቻናሌ ላይ አድራሻ አስቀምጫለሁ።
የቴሌግራም አድራሻ 👉https://t.me/seifemed
❤143👍132💯14🏆14🥰13🙏10👏8🤩5🕊2
➕➕ የፀጉር ቀለም ➕➕
🖲 አብዛኛውን ግዜ፣ አንድ ሰው የፀጉር ቀለምን የሚጠቀምበት አንደኛው ምክኒያት፣ ያለግዜው የሚመጣ ሽበትን ለመሸፈን ነው።
🖲ያለግዜው የሚመጣ ሽበት ደሞ፣ በጣም ጥቂት ከሚባሉ የጤና ችግሮች በስተቀር፣ አብዛኛውን ግዜ በተፈጥሮ የሚመጣ ሁኔታ ነው።
🔴 እርጉዝ ሴት የፀጉር ቀለም መቀባት ትችላለች እንዴ? ለካንሰር በሽታ አጋላጭ የሆነው የፀጉር ቀለምስ የትኛው ነው?
🖲 ከአንድ የፀጉር ዘለላ ተፈጥሮአዊ ክብደት ውስጥ ፣97 % የሚሆነው የፀጉር ይዘት፣ ቀለም አልባ ተፈጥሮ ነው። የፀጉር ቀለም፣ የተቀረውን 3 % ብቻ የሚሆነውን የክብደት ድርሻ ይይዛል።
🖲 ታዲያ፣ ምንም እንኳን ተፈጥሮ ለፀጉር ቀለም ያደለው ክብደት በጣም አነስተኛ ቢሆንም፣ ከስነውበት አንፃር በማህበረሰብ ዘንድ የሚሰጠው ድርሻ ግን ቀላል የሚባል አይደለም
🖲 የአንድ ሰው ተፈጥሮአዊ የፀጉር ቀለም፣ አብዛኛውን ግዜ ከ ሁለት መሰረታዊ የተፈጥሮ ቀለሞች የተገነባ ነው። እነዚህ ቀለሞች፣ በህክምናው " eumelanin "እና "pheomelanin " በመባል ይታወቃሉ። አንዳንድ ሰው ላይ "oximelanin " በመባል የሚታወቅ ሶስተኛ የቀለም አይነት ሊኖር ይችላል።
🖲 አንድ ሰው፣ ምንም አይነት ተጓዳኝ የጤና ችግር ሳይኖርበት በተፈጥሮ ብቻ የመጣ ሽበትን ግዜያዊ በሆነ መልኩ ለመቀነስ ካሰበ፣ ሁለት አይነት አማራጮችን መጠቀም ይችላል።
🖲 አንደኛው መንገድ፣ የሽበት መጠኑ 10 % እና ከዛ በታች ከሆነ፣ ሽበቱን መንቀል ይቻላል። ወይም ደሞ የዛ ሰው የሽበት መጠን ከ 10 % በላይ ከሆነ፣ የፀጉር ቀለምን መጠቀም ሌላኛው አማራጭ ነው
🖲 ሽበትን ለመሸፈን፣ ወይም ለማቅለም የተዘጋጁ የፀጉር ቀለሞች፣ በሁለት አይነት መንገድ ፀጉሩን ሊያቀልሙት ይችላሉ፣
👉 አንደኛው መንገድ፣ የፀጉሩን ዘለላ የላይኛውን ሽፋን ብቻ በቀለም በመሸፈን ሲሆን፣
👉 ሁለተኛው መንገድ ደሞ፣ ቀለሙ ከፀጉር ዘለላው ውስጥ ገብቶ እንዲቀመጥ በማድረግ ነው።
🖲 ፀጉር ውስጥ ሳይገቡ የፀጉሩን ሽፋን ብቻ የሚያቀልሙት የፀጉር ቀለሞች፣ ግዚያዊ ቀለሞች ናቸው፣ በተደጋጋሚ ግዜ በመታጠብ ግዜያቸውን ጠብቀው ከፀጉር ላይ ይነሳሉ።
🖲የፀጉር ዘለላው ውስጥ የሚገቡት ቀለሞች ደሞ፣ በቋሚ መልክ የተዘጋጁ ቀለሞች ናቸው፣ ማስለቀቂያ ኬሚካሎችን በመጠቀም እና ፀጉሩን በመቁረጥ ካልሆነ በቀር፣ ፀጉሩን በተደጋጋሚ ግዜ በማጠብ ብቻ ቀለሙን ማስለቀቅ አይቻልም።
▶️በዚህ መሰረት ታዲያ፣ አራት አይነት የፀጉር ቀለሞችን ገበያ ላይ ታገኛላችሁ
⭕️ስለነዚህ የፀጉር ቀለም አይነቶች እና አንዳንዶቹ ቀለሞች የሚያስከትሉትን የጎንዮሽ ጉዳት በተመለከተ አጠር ያለ መረጃ በ YouTube ቻናሌ ላይ አስቀምጫለሁ።
⭕️ለመመልከት ከፈለጋችሁ የሚቀጥለውን አድራሻ ተጭናችሁ ማግኘት ትችላላችሁ።
👇👇👇👇👇👇👇👇
https://youtu.be/kpcAbBIFXmk
መልካም ግዜ።

የፀጉር ቀለም | Hair dye | Dr. Seife | ዶ/ር ሰይፈ #drseife #habesha #medical
ለህክምና አገልግሎት እኔን በስልክ ለመሰግኘት፣ ዘወትር ቅዳሜ ከ ሰዓት ከ9 እስ 11 ባለው ግዜ ብቻ በ 0974163424 መደወል ይችላሉ
ለህክምና ቀጠሮ በአካል ለማግኘት ከፈለጉ የቴሌግራም ቻናሌ ላይ አድራሻ አስቀምጫለሁ።
የቴሌግራም አድራሻ 👉https://t.me/seifemed
ለህክምና ቀጠሮ በአካል ለማግኘት ከፈለጉ የቴሌግራም ቻናሌ ላይ አድራሻ አስቀምጫለሁ።
የቴሌግራም አድራሻ 👉https://t.me/seifemed
👍259❤81🙏16👏13🏆10👌9🎉6💯6🥰4🤩4