Dr. Seife | ዶ/ር ሰይፈ
47.7K subscribers
178 photos
2 videos
6 files
130 links
የዚህ ቻናል አላማ፣ ለህብረተሰቡ አስፈላጊውን የህክምና አስተምሮት እና መልእክቶች ማስተላለፍ ነው።
📞 0974163424
ለህክምና ቀጠሮ ብቻ ይሄን 👉 @LEKETERO ወይም @Apointment1
ተጭነው ስም እና ስልክ አስቀምጡ።

ዶ/ር ሰይፈ (ጠቅላላ ሐኪም)
Download Telegram
Neo hair lotion ታውቁታላችሁ?

🖲ፀጉር ማብቀያ ተብሎ ሶሻል ሚዲያዎች ላይ ሲተዋወቅ ያያችሁት ይመስለኛል።

🖲Neo hair lotion በመባል የሚታወቀው የ ታይላንድ ምርት ከዘመናዊ የፀጉር ማሳደጊያ መዳኒቶች የተሰራ ቅባት ሳይሆን፣ ፀጉርን ያሳድጋሉ ከሚባሉ ፣የእፅዋት ወጤቶች የተቀመመ ስለመሆኑ በምርቱ ላይ የተገለፀ ነው።

🖲ታዲያ በውስጡ የያዛቸው ንጥረነገሮች፣ ራሰ በርሀነት ሲጀምር፣ እየከሰመ ያለ ፀጉርን የመመለስ የተወሰነ አቅም እንዳላቸው ጥናቶች ይደግፋሉ።

🖲ነገር ግን፣ እነዚህን ምርቶች፣ ማለትም፣ በዘመናዊም ሆነ በባህላዊ የተቀመጡ የፀጉር ማብቀያዎችን ተጠቅማችሁ  ለውጥ ለማየት በአማካይ ከ4 እስከ 6 ወር በቀን በቀን መጠቀም ያስፈልጋል ።

🖲ሁሉም ሰው ላይ  ተመሳሳይ የሆነ እና የሚፈለገውን ያህል ለውጥ አያስገኝም። ለውጥ ከታየ ደሞ፣ መጠቀም ስታቆሙ  ፣በግዜ ሂደት ፀጉር ወደቀድሞ ይዞታው ይመለሳል

🖲ለማንኛውም Neo hair lotion ለመጠቀም ከመወሰናችሁ በፊት፣ ማወቅ ያለባችሁን ነገር ዩቲዩብ ላይ በሰፊው አስቀምጫለሁ ።

🖲የሚቀጥለውን ማስፈንጠሪያ ተጭናችሁ በቀላሉ መመልከት ትችላላችሁ።

👇👇👇👇👇👇👇👇

https://youtu.be/Tfe7OG2Ftg0
👍26684🥰27🤔22👏20
የወር አበባ በሄደ በሚቀጠለው ቀን ግንኙነት ባደርግ ርግዝና ይፈጠራል?


🖲አንድ ቋሚ የወር አበባ ያላት ሴት የወር አበባ በአማካይ በየ 28 ቀኑ ይመጣል ተብሎ ይታሰባል

🖲ነገር ግን ከ21 እሰከ 35 (ሲፈጥን በየ 21 ቢበዛ ደግሞ በየ 35 ቀን ሊመጣይችላል) ማለት ነው

🖲ስለዚህ ርግዝና የሚፈጠረው መቸ ነው የማይፈጠረውስ መቸ ነው ?

🖲በአማካይ መደበኛ የሚባለውን ወስደን ስናይ የወር አበባ በየ 28 ቀን ይመጣል::

🖲የወር አበባ በጀመረ የመጀመሪያወቹ 5 ቀናት በአማካይ የወር አበባ የሚፈሰባቸው ቀናት ናቸው።

🖲ከ 6ኛው እስከ 14 ኛው ቀን ያለው Follicular phase ይባላል።ይህም ኢስትሮጂን :FSH የሚባሉት ሆርሞኖች የሚጨምሩበትና የማህፀን ግድግዳ እየወፈረ የሚሄድበት ጊዜ ነው

🖲14 ኛው ቀን ውፃት(ovulation) ይባላል። እንቁላል ለፅንሰት ዝግጁ ሆኖ ይወጣል ማለት ነው።

🖲በዚህ ግዜ የግብረ ስጋ ግንኙነት ከተፈፀመ ርግዝና የመፈጠር እድሉ በጥም ከፍተኛ ነው፣ ከ 14 _28ኛው ያለው ቀን lutheal phase ይባላል።ርግዝና ከተፈጠረ ማህፀን ፅንሱን ለማሳደግ ዝግጁ የሚሆንበት ጊዜ ካልተፈጠረ ደሞ የዳበረው የማህፀን ወለል በመፈራረስ በወር አበባ መልክ የሚፈስበት ጊዜ ነው።

🖲ሰለዚህ 14 ኛው ቀን ላይ ርግዝና ይፈጠራል።ነገር ግን የወንድ ስፐርም የሴትብልት ላይ እስከ 5 ቀን ድረስ ሳይሞት ይጠብቃል እንቁላልም ከወጣ ጀምሮ እስከ 24 ሰዓት ይጠብቃል

🖲 ስለዚህ ከ 14 ኛው ቀን 5 ቀን ወደ ፊት ና 3 ቀን ወደ ሗላ ርግዝና የሚፈጠርባቸው ቀናት ናቸው።

🖲የወር አበባ በየ 28 ቀን የማይመጣ ከሆነ ና ቋሚ ከሆነ ከ14 ኛው ቀን እሰከ 28 lutheal phase ያልነው ቋሚ 14 ቀን ስለሆነ ተመሳሳይ ሰሌት በመጠቀም ማወቅ ይቻላል።

ዶ/ር ዮርዳኖስ
👍496128👏67😱6🎉2🙏2
የፊት ክሬሞችን ከመምረጣችሁ በፊት

🖲 መቼም ግዜ ቢሆን የፊት ቅባቶችን ከገበያ ስትገዙ: ለምን እንደምትገዙ እና የገዛችሁት ቅባት ከቆዳችሁ ጋር እንደሚሄድ እና እንደማይሄድ ካላወቃችሁ: እንዲሁም ደሞ የገዛችሁአቸው ቅባቶች: ጥራት የሌላቸው እና ይዘታቸው የማይታወቅ ከሆነ:

🖲 አንዳንዴ ሊመልስ ለማይችል የቆዳ ጠባሳ ከመጋለጥ ባሻገር: አንዳንድ ቅባቶች በድብቅ ከሚይዙት መዳኒት የጎንዮሽ ጉዳት የተነሳ: ለአንዳንድ የውስጥ ደዌ በሽታዎችም የመጋለጥ እድል አለ::

🖲እዚህ ቪዲዮ ላይ የቀረበው መረጃ አንዳንድ የፊት ቅባቶች ውስጥ ሊጨመሩ የሚችሉ መዳኒቶችን እና: ሊያስከትሉ የሚችሉትን የጎንዮሽ ጉዳት ማስተማሪያ ነው::

አመሰግናለሁ

እነዚህን የፊት ክሬሞች እባካችሁ አትጠቀሟቸው
https://youtu.be/kzdE58BkHiA
👍331142🥰52👏51😢8🙏1
👍5239🥰9
የትኛው ሳሙና ይሻላል?

🖲 በልብስ ሳሙና መታጠብ ቆዳን አመድ ያስመስላል።

🖲ከገላ ሳሙናዎች ውስጥ ለደረቅ እና ለሚቆጣ ቆዳ Dove የተሻለ ሳሙና ነው።

🖲 አንድ ሳሙና ሲሰራ ቁሻሻን የማስለቀቅ አቅሙ ከፍተኛ በሆነ መጠን፣ ቆዳን የማድረቅ መጠኑም በዛውልክ ይጨምራል፣

🖲አብዛኞቹ የገላ ሳሙናዎች ከ 9 እስከ 11 የሚደርስ የ ph ልኬት አላቸው።

🖲የገላ ሳሙናዎች እንደ ምርታቸው፣ አይነታቸው እና ጥቅማቸው ተጨማሪ መዳኒቶች፣ ቫይታሚኖች ፣ የቆዳ ማርጠቢያዎችን እና ማኣዛዎች ይጨመርባቸዋል።

🖲ታዲያ፣ በተለምዶ ሳሙና ተብለው ይጠሩ እንጂ፣ አንድአንድ ሳሙናዎች መደበኛ የሳሙና ይዘት የላቸውም

🖲ይዘታቸው (Synthetic Detergent) የሆነ፣ ወይም ስማቸው ሲያጥር ( Syndet ) በመባል የሚታወቁት መታጠቢያዎች፣ አብዛኛወን ግዜ ለቆዳ ተስማሚ ናቸው።

🖲ስለቆዳ አይነቶች እና ስለ ተስማሚ የሳሙና አይነቶች በሰፊው ዩቱዩብ ላይ አስቀምጫለሁ።  አመሰግናለሁ።

👇👇👇👇👇

https://youtu.be/r1-mJhp-ahQ
👍29299🥰51👏27😱11🙏2
👍6115🥰11🤔6😢3👏2🙏1
የማድያት እውነታዎች

🖲ማድያትን ለመለየት ቀላል ቢሆንም ነገርግን ፊት ላይ የሚወጣ ጥቁረት ሁሉ ማድያት አይደለም።

🖲ማድያትን በወጣበት ቦታ እና በያዘው የቆዳ ክፍል መሰረት ይከፋፈላል።

🖲አብዛኛውን ግዜ ከህክምና በኋላ እየተመላለሰ የመለያስቸግረው ማድያት የስረኛውን የቆዳ ክፍል የያዘ ከሆነ ነው።

🖲ማድያት የያዘው የቆዳ ክፍልን ለመለየት በቆዳ ሀኪም መታየት ያስፈልጋል።

🖲ማድያት የሚመጣበት አንድ ብቻ ምክኒያት የለውም፣ የተለያዩ ምክኒያቶች ማለትም፣

👉በተፈጥሮ
👉ለፀሀይ ጨረር መጋለጥ
👉ባለ ሁለት ሆርሞን የእርግዝና መከላከያ
👉እርግዝና
👉ከታይሮይድ ሆርሞን ማነስ እና ምክኒያቱ በማይታወቅ ሁኔታም ሊመጣ ይችላል።

🖲በእርግዝና ምክኒያት የመጣ ማድያት ከወሊድ በኋላ እየደበዘዘ ይጠፋል፣ ነገር ግን ከ ወሊድ በኋላ ከ 8 ወር በላይ ከቆየ እና እየሰፋ ከመጣ ህክምና ያስፈልገዋል።

🖲ማድያትን ሙሉ በሙሉ እንዳይመለስ አድርጎ የሚያጠፋ አንድ ብቻ የሆነ የሚቀባ መዳኒት የለም።

🖲ነገር ግን በተለያየ መንገድ የማድያት ጥቁረትን የሚያጠፉ፣ በሚቀባ መልክ የተዘጋጁ መዳኒቶች በሀኪም ትእዛዝ ይሰጣሉ።

🖲በዚህ መልኩ ማድያቱ ሲጠፋ፣ ተመልሶ እንዳይመጣ እና በህክምና ግዜ የሚሰጡ መዳኒቶች የቆዳ ቁጣ እንዳያስከትሉ ረዘም ላለ ግዜ ክትትልን ይፈልጋል።

🖲 ተጨማሪ መረጃ በ YouTube ላይ አስቀምጫለሁ ፣ አመሰግናለሁ ።

     👇👇👇👇👇
https://youtu.be/KXS9zzDVH-g
👍201125🥰41🤔18😱5👏4
ለማድያት እና ለጥቋቁር ነጠብጣቦች

🖲ማድያት እየተመላለሰ የሚታስቸግረው የስረኛውን የቆዳ ክፍል የያዘ ከሆነና ከህክምና በኋላ ማድያትን ለሚያስከትሉ እና ለሚያባብሱ ምክኒያቶች ተጋላጭነት ከቀጠለ ነው።

🖲እነዚህ ምክኒያቶች

👉ምግብ ከማብሰል ጋር ተያይዞ እና በተለያዩ ምክኒያቶች ለከፍተኛ ሙቀት መጋለጥ

👉የፀሀይ መከላከያዎች ባግባቡ ባለመጠቀም እና፣ ለፀሀይ ጨረር መጋለጥ

👉ጭንቀት እና ድባቴ መኖር እና ቆዳ ላይ ቁጣ ሊያስከትሉ የሚችሉ ቅባቶችን ወይም በቤት የሚዘጋጁ ቅመሞችን በመጠቀም

🖲ማድያት ሊባባስ እንዲሁም ሊመላለስ ይችላል።

🖲ይህ እንዳይሆን ታድያ፣ በህክምና ማድያቱ ከጠፋም በኋላ፣ ከሀኪም ትእዛዝ ውጪ በቅባት መልክ የሚገኙ የጥቁረት ማደብዘዣዎችን እና የፀሀይ መከላከያዎችን አዘውትሮ በመቀም ማድያቱ እንዳይመለስ ይረዳል።

🖲ከዛ ውጪም በብጉር እና በአንዳንድ የቆዳ ቁጣዎች ምክኒያት የሚመጣን ጥቋቁር ነጠብጣብ ማደብዘዝም ያስችላል።

🖲እነዚህን የጥቁረት ማደብዘዣ ቅባቶችን እና የፀሀይ መከላከያ አይነቶችን፣ በ youtube ላይ አስቀምጫለሁ።

👇👇👇👇👇👇👇👇

https://youtu.be/KDy5sHrAhfA
👍21384🥰21🤔13😱5🙏3😢2
👍5514🥰13🤔8
የፊት መታጠቢያዎች

🖲ከደረቅ ሳሙና ይልቅ የፊት ቆዳን ለማፅዳት የተዘጋጁ ብዙ አይነት መታጠቢያዎች አሉ።

🖲በጠቅላላው Cleanser ተብለው ይጠራሉ፣ አይነታቸው እና አሰራራቸው፣ እንደታሰበላቸው አላማ ይለያያሉ። ለምሳሌ፣

👉ቆሻሻን ለማስለቀቅ
👉የፊት ወዝን ለመቀነስ
👉የብጉር ጥቃቅን ሽፍታን ለመቀነስ
👉የቆዳ ቅርፊትን ለማንሳት
👉ሜካፕን ለማስለቀቅ ፣ እንደ ቆዳው ይዘት ተቀምመው ለገበያ ይቀርባሉ።

🖲ከነዚህም ውስጥ በብዛት የሚታወቁት የ መታጠቢያ አይነቶች

👉ባለ አረፋ መታጠቢያ ( Foaming Cleanser )
👉ዘይት አዘል መታጠቢያ (Oil based Cleanser)
👉የቆዳ ቅርፊት ማንሻ ( Scrub )
👉ውሀ የማያስፈልገው የፊት ማፅጃ ( Milk Cleanser, Toner)
👉ደረቅ እና እርጥብ የፊት መጥረጊያ ጨርቆች ( Substrate Cleansers) በመባል ይታወቃሉ።

🖲ከነዚህ ውስጥ፣ ለወዛም ቆዳ ተስማሚ የሚሆኑት መታጠቢያዎች፣ ባለ አረፋ እና በውስጣቸው Salicylic Acid የሚይዙ ቢሆኑ ተመራጭ ነው።

🖲ለደረቅ እና ለሚቆጣ ቆዳ ደሞ፣ ውሀ የማያስፈልገው የፊት ማፅጃ (Milk Cleanser) በውስጡ የሚይዛቸው ንጥረ ነገሮች፣ ለቆዳ ተስማሚ ናቸው።

🖲ስለ ሁሉም የክሊንዘር አይነቶች በሰፊው ማብራሪያ YouTube ላይ አስቀምጫለሁ። አመሰግናለሁ።

👇👇👇👇👇👇

https://youtu.be/pLn8A8ynlxI
👍26596🥰32👏5😍1
29👍15😢6
ተደጋጋሚ የሽንት ቱቦ ኢንፌክሽን

🖲 የሽንት ቱቦ ኢንፌክሽን በግብረስጋ ግንኙነት አይተላለፍም፣ ነገር ግን፣ በአንድ ጓደኛ ያልተወሰነ እና ተደጋጋሚ የግብረስጋ ግንኙነት፣ ለሽንት ቱቦ ኢንፌክሽን አጋላጭ ነው።

🖲በአመት ሶስት ግዜ እና ከዛ በላይ የሚመጣ የሽንት ቱቦ ኢንፌክሽን፣ በተደጋጋሚ ግዜ የሚመጣ የሽንት ቱቦ ኢንፌክሽን ወይም በህክምናው (Recurrent UTI) ይባላል።

🖲ከ 50 እስከ 80 በመቶ የሚሆኑ ሴቶች በህይወት ዘመናቸው አንድ ግዜ የሽንት ቱቦ ኢንፌክሽን ያጋጥማቸዋል። ከነዚህም ውስጥ ከ 20 እስከ 30 በመቶ የሚሆኑት ደሞ በድጋሚ ሊታመሙ ይችላሉ።

🖲ከወንዶች ይልቅ በሴቶች ላይ አብዝቶ ይከሰታል፣ ነገር ግን ከ 50 አመት የእድሜ ክልል በኋላ በወንድም በሴትም እኩል ሊከሰት ይችላል።

🖲አንድ ሴት ለመጀመሪያ ግዜ የሽንት ቱቦ ኢንፌክሽ የታመመችው ከ 15 አመቷ በፊት ከሆነ፣ በቀጣይ እድሜዋ ተደጋጋሚ የሽንት ቱቦ ኢንፌክሽን ሊያጋጥማት ይችላል።

ከግንኙነት በኋላ ቶሎ ሽንት አለመሽናት
መሀፀን በሚታጠብበት ግዜ ውሀ እና ሳሙናን እንዲሁም ጣትን ወደውስጥ አስገብቶ መታጠብ
ሽንት በመጣ ግዜ ቶሎ አለመሽናት
ጥብቅ ያሉ ልብሶችን ማዘውተር
የመታጠቢያ ገንዳ ውስጥ ለረጅም ሰአት መዘፍዘፍ
ሴቶች ሰገራ ከተቀመጡ በኋላ ከኋላ ወደፊት ማፅዳት የመሳሰሉት ድርጊቶች

🛑 ለሽንት ቱቦ ኢንፌክሽን አጋላጭ ምክኒያቶች ናቸው።

🖲የሽንት ቱቦ ኢንፌክሽን ሲኖር ጥብቅ ክትትል እና የህክምና ትኩረት ሊሰጣቸው የሚገባ ሰዎች፣

👉እርጉዝ ሴቶች
👉የስኳር በሽታ ያለባቸው፣
👉የስተሮክ እና በአደጋ ወይም በበሽታ ምክኒያት የማይንቀሳቀሱ ታካሚዎች፣
👉የHIV እና የካንሰር ታካሚዎች እና እድሜ ጠገብ አዛውንቶች ናቸው።

ሙሉ መረጃውን በ YouTube ቻናሌ ላይ አስቀምጫለሁ።
👇👇👇👇👇👇👇👇

https://youtu.be/Add7eDCFq50
👍33294🥰15👏13😱7
344👍180
👍85😢10🙏1
ቆዳ ማርጠቢያ (Moisturizers )

🖲ጥርት ያለ እርጥብ ገፅታ ያለው ቆዳ እንዲኖር እንጂ የቆዳው ቀለም መቅላቱ ግዴታ አይደለም

🖲አንድ ሰው ያለው የቆዳ ይዘት እንጂ፣ የተፈጥሮ ቆዳ ቀለም የቆዳውን ጤንነት አይወስነውም።

🖲የቆዳን ጤንነት ለመጠበቅ ሶስት መሰረታዊ የቆዳ ጤንነት አጠባበቅ መንገዶች ያስፈልጋሉ

👉የቆዳ ንፅህናን መጠበቅ
👉ቆዳን ከፀሀይ ጨረር መከላከል እና
👉የቆዳን እርጥበት በጠበቅ ናቸው።

🖲ቆዳ ሁሌ የሚደርቅ ከሆነ፣ የቆዳው ጤንነት ይዛባል እንዲሁም ከእድሜ በፊት ቶሎ ያረጃል።

🖲የቆዳን እርጥበት ለመጠበቅ የሚያስፈልጉት ዋነኛ ተግባሮች ውስጥ፣

👉በቂ ውሀ መጠጣት
👉ሲጋራ አለማጨስ
👉ሰውነትን በቀን ውስጥ በተደጋጋሚ ግዜ አለመታጠብ
👉የልብስ ሳሙናን ለቆዳ ንፅህና አለመጠቀም
👉ከታጠቡ በኋላ የቆዳ ማርጠቢያዎችን መጠቀም የመሳሰሉት ይገኙበታል።

🖲የቆዳ ማርጠቢያ ቅባቶች በ 4 አይነት መልኩ ይገለፃሉ፣ ዝርዝራቸውን በቪዲዮው ላይ አስቀምጫለሁ።

🖲ለማንኛውም ግሊስሪንን የሚይዙ የቆዳ ማርጠቢያዎች ፣ እንዲሁም በውስጣቸው የፀሀይ መከላከያ እና ቪታሚን E የሚይዙ የቆዳ ማርጠቢያዎች፣ ለሁሉም አይነት የቆዳ ይዘት ተስማሚ ናቸው።

🖲ስለነዚህ ምርቶች አይነት በዝርዝር YouTube ላይ አስቀምጫለሁ ። አመሰግናለሁ

👇👇👇👇👇👇👇👇
https://youtu.be/3PSI8aAaWKQ
👍202194👏41🥰34
ያልተፈለገ ቦታ ላይ ፀጉር ሲበቅል

🖲ሴቶች ልክ እንደ ወንዶች ከንፈር እና ደረት እንዲሁም በብልት አካባቢ የተጋነነ ፀጉር የሚያበቅሉ ከሆነ በህክምናው Hirsutism ይባላል።

🖲ምክኒያቱም በነዚህ የሰውነት ክፍል ላይ ያሉ ፀጉሮች በ ወንዴ ሆርሞን ስለሚታዘዙ ነው።

🖲ነገር ግን ከሆርሞን ጋር ባልተገናኘ መልኩ ወንዶችም ሴቶችም ከልክ ያለፈ ወይም በሰውነታቸው ላይ የተጋነነ የፀጉር አበቃቀል ሲኖር ደሞ በህክምናው Hypertrichosis በመባል ይጠራል።

🖲የስሙ ልዩነት ያስፈለገው፣ አመጣጡ እና የህክምና ምርመራ አማራጮችን ለመለየት ነው።

🖲ስለነዚህ 2 ችግሮች በምስል የተደገፈ መረጃ እና የህክምና አማራጮቻቸውን በ YouTube ላይ አስቀምጫለሁ።ትምህርት እንደምታገኙበት ተስፋ አደርጋለሁ። አመሰግናለሁ

  ለመመልከት ይሄን ይጫኑ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇

https://youtu.be/lXW2ZVdxrHA
👍23789🥰13👏4😱2
ሬንጅ መድሀኒት ይሆናል?

🖲ሬንጅ መዳኒት ሊሆን ይችላል፣ አዎ አብዛኞቻችን የምናቀው አስፋልት ሲሰራበት ነው።  Coal Tar ወይም ሬንጅ።

🖲በህክምናው ዘርፍ፣ በዋነኝነት ለፎረፎር እና ሶርያስስ ለተባለ ስር ሰደድ የቆዳ በሽታ ህክምና፣ በሻምፖ፣ በሳሙና እና በክሬም መልክ ተቀላቅሎ ህክምና ላይ ይውላል።

🖲አንዳንዴ ጥራታቸውን ያልጠበቁ የመዋቢያ ግብአቶች ውስጥ፣ ለማቅለሚያነት ተብሎ በድብቅ ሊጨመር ይችላል።

🖲ለምሳሌ አንዳንድ የጥቁር ሂና አይነቶች በውስጣቸው ይሄንን ሬንጅ ይይዛሉ ፣ነገር ግን በላያቸው ላይ ሬንጅ ወይም Coal Tar እንደሚይዙ አይፃፍባቸውም።

🖲ይህ Coal Tar ታዲያ አደገኛነቱ፣ አንዳንድ ሰዎች ላይ የፀሀይ ንክኪ ሲኖረው ቆዳን በከፍተኛ ሁኔታ ሊያስቆጣ ይችላል።

🖲ይህም የሆነበት ምክኒያት፣ አንዳንድ ንጥረ ነገሮች የፀሀይ ንክኪ ሲኖራቸው፣ ይዘታቸው ይቀየር እና ቆዳን እንዲቆጣ ያደርጉታል።

🖲ስለዚህም ከዚህ በፊት ተጠቅማችሁ የማታቋቸውን የመዋቢያ ግብአቶች ከመጠቀማችሁ በፊት፣ ቅድሚያ በትንሽ ቆዳ ላይ አስቀድሞ መሞከር ያስፈልጋል።

🖲ከዚህ ባለፈ መልኩ ደሞ ፀሀይ በብዙ መልኩ ቆዳን ሊጎዳ እንደሚችል ግልፅ ነው።

🖲ከፀሀይ ንክኪ ጋር በተያያዘ መልኩ የሚመጡ የቆዳ ጉዳቶችን፣ እንዲሁም የፀሀይ መከላከያ አጠቃቀም ላት የሚታዩ ጉድለቶችን በተመለከተ ሰፋ ያለ መረጃ YouTube ላይ አስቀምጫለሁ።
👇👇
https://youtu.be/KkV-tlknCEo

መልካም ግዜ።
👍23969🥰18🤩3
👍65😢6👏5
ቫይታሚን ዲ

🖲ለረጅም ግዜ የቆየ ካልሆነ በቀር ወዲያውኑ የሚታይ የህመም ምልክት የለውም።

🖲ከፍተኛ የቫይታሚን ዲ እጥረት ያለባቸው ሰዎች  የደረት እና የቋንጃ አጥንትታቸው ላይ ጫን ተብሎ ሲነካ ህመም ይሰማቸዋል

🖲አንዳንዴ ደሞ የትከሻ እና ክንድ መዛል ይኖራቸዋል። እንዲሁም አልፎ አልፎ የመሚመጣ የእግር ህመምም ሊያጋጥማቸው ይችላል።

🖲የእጅ እና የትከሻ መዛል ካለ፣ ከቫይታሚን ዲ እጥረት ባሻገር በተለያዩ፣ የጡንቻ ፣የነርቭ እና የደምስር ችግሮች ምክኒያትም ሊፈጠር ይችላል።

🖲ከሌላ ተጌዳኝ ችግር የመጣ ካልሆነ በቀር፣ ከፍተኛ መጠን ያለው ቫይታሚን ዲ ከካልሲየም ጋር በመዳኒት መልኩ ሲሰጥ፣ ወዲያውኑ በተወሰነ ግዜ ውስጥ ፈውስ ይኖረዋል።

🖲የፀጉር መነቃቀል ያለባቸው ሰዎች እንዲሁም አንዳንድ የውስጥ ቁጣን ተከትለው የሚመጡ በሽታዎች ያሉባቸው ሰዎች ላይ፣ አንዳንዴ የቫይታሚን ዲ እጥረት ይታያል።

🖲የቫይታሚን ዲ ይዘት የሚለካው IU በሚባል ልኬት ነው፣
(1 mg) ቫይታሚን ዲ ከ (40,000 IU) ጋር እኩል ነው።

👉ከአንድ አመት በታች ያሉ ህፃናቶች በቀን 400 IU ወይም(0.001 mg ) ቫይታሚን ዲ በቂያቸው ነው።

👉ከ 1 አመት እስከ 70 አመት ላሉ ሰዎች በቀን 600 IU ወይም (0.0015 mg) ቫይታሚን ዲ በቂያቸው ነው።

👉ከ 70 አመት በላይ ያሉ አዛውንቶች  በቀን 800IU ወይም (0.002 mg) ቫይታሚን ዲ ያስፈልጋቸዋል።

🖲ልብስን አውልቆ 30 ደቂቃ ያህል የጠዋት ፀሀይ ላይ የተቀመጠ ሰው ፣ ቀይ ከሆነ ከ 20 እስከ 30ሺ IU የሚሆን ቪታሚን ዲ፣ እንዲሁም ጠይም የሆነ ሰው ላይ ደሞ ከ 8 እስከ 10ሺ IU የሚሆን  ቪታሚን ዲ በ 24 ሰአት ውስጥ ሰውነት ማዘጋጀት ይችላል።

🚩እድሜ ጠገብ አዛውንቶች ሰውነታቸው በፀሀይ ጨረር ቫይታሚን ዲን የማምረት አቅሙ ይቀንሳል

🚩ህፃናቶች ከተወለዱ ከ 2 ሳምንት በኋላ በቀን ከ15 እስከ 20 ደቂቃ የጠዋት ፀሀይ ያስፈልጋቸዋል።

🚩ታዲያ ፣ለህፃንም ሆነ ላዋቂ ፣ፀሀይ በሚሞቅበት ግዜ ማናቸውንም ቅባቶች  መቀባት ፈፅሞ አስፈላጊ አይደለም

🖲ከዚህ ውጪ ቫይታሚን ዲን ከምግብ ማግኘትም ይቻላል።

🖲ቫይታሚን ዲ እንደሌላው በብዙ የምግብ ዘርፎች ውስጥ አይገኝም፣

🖲የአሳ ዘይት፣ የአሳ ስጋ፣ ቱና ፣ ጉበት እና እንቁላል የመሳሰሉት ምግቦች በደረጃ የተቀመጠ የ ቫይታሚን ዲ ይዘት አላቸው።

👉አንድ የሻይ ማንኪያ የአሳ ዘይት አንድ ሰው በቀን ውስጥ የሚያስፈልገውን 2 እጥፍ ቫይታሚን ዲ ይይዛል።

👉100 ግራም የአሳ ስጋ ወይም ቱና ደሞ ከ 70 እስከ 90 በመቶ የሚሆነውን በቀን ውስጥ የሚያስፈልገውን የቫይታሚን ዲ መጠን ይይዛል።

👉ጉበት፣እና እንቁላል ደሞ አነስተኛ መጠን ያለው ቫይታሚን ዲ በውስጣቸው ይይዛሉ።

🖲የታሸጉ ምግቦች ላይ በተለይ ለህፃናት እንዲሁም ላዋቂ የሚዘጋጁ የዱቄት ወተቶችን ጨምሮ፣ አንድ ሰው በቀን ውስጥ ሊያስፈልገው የሚችለውን የቫይታሚን ዲ መጠን በውስጣቸው ይጨመርባቸዋል።

🖲ከዛ ባለፈ ደሞ፣ ቫይታሚን ዲ በእንክብል እና በሽሮፕ መልክ በተለያየ መጠን ይገኛል

🖲ከፍተኛ የቫይታሚን ዲ  እጥረት የተገኘበት ሰው በ 50ሺ IU የተዘጋጀውነን ቫይታሚን ዲ 1 ፍሬ በሳምንት አንድ ግዜ እንደ እጥረቱ ደረጃ ከ 3 ሳምንት እስከ 3 ወር ሊሰጠው ይችላል

🖲ከቫይታሚን ዲው ጋር አብሮ እንዲሰራ ካልሲየምም አብሮ ይታዘዛል

🖲የአጥንት መሳሳት ላለባቸው አዛውንቶች ደሞ በቀን 1000 IU ቫይታሚን ዲ ከካልሲየም ጋር እስከ 3 ወር ድረስ ሊሰጥ ይችላል።

🚩በ 50ሺ IU የተዘጋጀው ቫይታሚን ዲ በቀን በቀን አይወሰድም።

🖲ምክኒያቱም ይህ ከፍተኛ መጠን ያለው ቫይታሚን ዲ በቀን በቀን የሚወሰድ ከሆነ፣ ከልክ ላለፈ የቫይታሚን ዲ ችግር ሊያጋልጥ ይችላል

🖲ከልክ ያለፈ መጠን ያለው ቫይታሚን ዲ የተወሰደ ከሆነ በደም የሚገኘው የካልሲየም መጠን ከልክ ያለፈ ሰለሚሆን፣ ከዚህ ጋር ተያትዘው የሚመጡ የተለያዩ የህመም ስሜቶች ለምሳሌ

🖲ድካም ድካም ማለት፣ በውሀጥም መቸገር እና ሽንት በተደጋጋሚ ግዜ መሽናት፣ የሆድ ድርቀት፣ ማቅለሽለሽ፣ ማስመለስ የመሳሰሉ የህመም ምልክቶች ይኖራሉ።

🖲እንዲህ አይነቶቹ የህመም ምልክቶች ሲያጋጥሙ ታዲያ፣ የካልሲየም ይዘት ያላቸውን ምግቦች ባለመመገብ እንዲሁም በህክምና እና በመዳኒት እገዛ፣ በእንድ ወር ግዜ ውስጥ እነዚህን ችግሮች መመለስ ይቻላል።

የበለጠ መረጃ YouTube ላይ አስቀምጫለሁ

👇👇👇👇👇👇
https://youtu.be/SlD6HeKj_jI
👍42081🥰22😢8🙏8😱6🤩6
የሽንት እርግዝና ምርመራ

🖲በሽንት የሚደረግ የእርግዝና ምርመራ Urin HCG Test ይባላል።

🖲ይህ የምርመራ መንገድ፣ እርግዝና መፈጠሩን ማሳየት የሚችለው፣ የወር አበባ ከቆመ ከ2 ሳምንት በኋላ ምርመራ የተደረገ ከሆነ ነው።

🖲አብዛኛውን ግዜ የሽንት እርግዝና ምርመራ ሲደረግ፣ የጠዋት ሽንት ላይ ቢሆን ይመረጣል።

🖲ምርመራው እርግዝና ከሌለ 1 መስመር ያሳያል እርግዝና የተፈጠረ ከሆነ ደሞ 2 መሰረመር ያሳያል።

🖲በቅርቡ ወደሀገራችን የገባ፣ የሽንት እርግዝና ምርመራ መሳሪያ አለ፣ ዋጋው ርካሽ ከመሆኑም ባሻገር አጠቃቀሙም በአማርኛ የተፃፈ ነው። ቲና ይባላል። በየተኛውም ፋርማሲ ይገኛል

🖲ጤና ተቋም ሳትሄዱ በቤታችሁ መጠቀም ትችላላችሁ

🖲የዋና አከፋፋዮች አድራሻ
👉Company : Labora International Trading Plc
👉Tele:0911104930
👍33585🥰38🤔23👏20🙏16