➕ የሠገራ መንሳፈፍ ➕
🖲የመፀዳጃ ሲንክ ላይ የምትጠቀሙ ከሆነ እና ካስተዋላችሁ፣ ሰገራ ከተቀመጣችሁ በኋላ፣ ሰገራው በውሀ አልሄድ ካለ ፣ ወይም እየተንሳፈፈ ካስቸገረ፣ ይህ ሁኔታ በህክምናው Steatorrhea ይባላል።
🖲ከአንድ ጤናማ ሰው፣ ማለትም፣ የሆድ ድርቀት እና ማስቀመጥ በሌለበት ሁኔታ፣ በአማካይ በቀን ማስወገድ የሚቻለው የሠገራ መጠን፣ በ 24 ሰአት ውስጥ 128 ግራም ነው።
🖲ከዚህ ውስጥ 75 በመቶ የሚሆነው ይዘት ውሀ ሲሆን።
🖲የተቀረው ደረቅ ክፍል 25 በመቶ የሚሆነው፣ ከዚህ በታች ያሉትን ተረፈ ምርቶች፣ በተለያየ መጠን ይይዛል፣
👉ሀሞት
👉ባክቴሪያ
👉ያልተብላላ ተረፈ ምርት
👉ስብ
👉ገለባ ወይም ቃጫ (Fiber)
👉የአንጀት ግድግዳ ቅራፊ ህዋስ እና ፈሳሽ
🖲የሰገራው ደረቅ ክፍል የስብ ይዘት ከ 20 በመቶ በላይ ከሆነ፣ ወይም ከሙሉ ሠገራው ይዘት 7 ግራም እና ከዛ በላይ ከሆነ ሠገራው ውሀ ላይ መንሳፈፍ ይችላል።
🖲ይህ ችግር አብዛኛውን ግዜ በበሽታ ሳይሆን፣
👉ከፍተኛ የስብ ይዘት ያላቸውን ምግቦች በማዘውተር እና
👉አልኮል የሚይዙ መጠጦችን ያለልክ በመጠጣት
👉እንዲሁም ከፍተኛ የቃጫ (Fiber) ይዘት ያላቸውን ምግቦች በማዘውተር ምክንያት አልፎ አልፎ ሊታይ ይችላል።
🚩ነገር ግን !
🖲ይህ ችግር በተደጋጋሚ የሚታይና ለረጅም ግዜ የቆየ ከሆነ ግን የበሽታ ምልክት ነው።
👉የጨጓራና የአንጀት የውስጥ ደዌ በሽታዎች
👉በተለያዩ መክንያቶች የአንጀት ባክቴሪያ መብዛት
👉የትንሹ አንጀት ክፍል በቀዶ ህክምና መውጣት
👉የጣፊያ ህመም ጋር ተያይዞ የማብላያ ኢንዛይሞች ማነስ
👉የሀሞት ጠጠር እንዲሁም ውፍረት ለመቀነስ እና ለተጓዳኝ በሽታ የሚሰጡ አንዳንድ መዳኒቶች እና ሌሎችም ለዚህ ችግር ተጠቃሽ ምክኒያቶች ናቸው።
https://t.me/seifemed

👍37❤4👏1
ለህክምና ቀጠሮ ብቻ
ይሄን ተጭናችሁ 👉 @LEKETERO
ስም እና ስልክ አስቀምጡ
📞 ዶ/ር ሰይፈ 0974163424
https://t.me/seifemed
https://t.me/seifemed
ይሄን ተጭናችሁ 👉 @LEKETERO
ስም እና ስልክ አስቀምጡ
📞 ዶ/ር ሰይፈ 0974163424
https://t.me/seifemed
https://t.me/seifemed
👍8
💥Vitiligo ለምፅ💥
✨ ምንም እንኳን የቆዳ ቀለም ተፈጥሮ፣ የፀሃይ ጨረርን ከመከላከል ባሻገር ሌላ ተፈጥሮአዊ ጥቅም ባይኖረውም፣ የቆዳ ቀለም በ ግንዛቤ ላይ ያለው ተፅእኖ ከፍተኛ ነው።
✨ ለምፅ የሚመጣበት አንድ ወጥ የሆነ ምክንያት የለውም። ነገር ግን ብዙ ምክንያቶች ለምፅን እንደሚያመጡ ይገመታል
✨ ለምፅን ሊያስነሱ የሚችሉ ምክንያቶች
👉 የ ቫይረስ ኢንፌክሽን
👉 የ ሆርሞን መለዋወጥ
👉 ቆዳን የሚጎዱ ኬሚካሎች
👉 ጭንቀት እና
👉 ቆዳ ላይ የሚደርሱ አደጋዎች
ተጠቃሾች ናቸው።
✨ ለምፅ በዋነኝነት ሊመጣ የሚችለው፣ የሰውነት የበሽታ ተከላለይ ህዋሶች፣ በቀለም አምራች ህዋሶች ላይ በሚያስከትሉት ጉዳት ነው።
🔴ለምፅ ከሰው ወደሰው በንክኪ አይተላለፍም 🔴
✨ ከዚህም ምክንያት ጋር ተያያዥነት ያላቸው፣ የተለያዩ የውስጥ ደዌ ህመሞች ፣ በለምፅ ታካሚዎች ላይ ሊያጋጥሙ ይችላሉ።
ለምሳሌ ያህል፣
👉 የ እንቅርት ህመም
👉 የስኳር በሽታ
👉 የደም ማነስ አይነት
👉 የ ላሽ በሽታና፣ እንዲሁም ሌሎች ከሰውነት ቁጣ ጋር የተያያዙ ተጓዳኝ በሽታዎች ሊኖሩ ስለሚችሉ፣ የለምፅ ታካሚዎች አስፈላጊውን ምርመራና ክትትል ማድረግ ይጠበቅባቸዋል

👍14❤2👏1
🖲 ደርማ ሮለር ሲባል ሰምታችሁ ታቃላችሁ?
Micro needling ይባላል በሌላ ስሙ።
🟢የሚያገለግለው 🟢
👉ስስ የቆዳ መጨማደድ ካለ
👉የብጉር ጠባሳን ለመቀነስ (ሙሉ ለሙሉ አያጠፋም)
👉ለራሰ በርሀነት (ከፀጉር ማሳደጊያ ጋር ቢሆን)
🖲የላይኛው የቆዳ ክፍል ላይ ከፍተኛ ጉዳት ሳይደርስ የስረኛውን የቆዳ ክፍል ለማነቃቃት የተዘጋጀ መንገድ ነው።
🖲የቆዳ መጨማደድ እንዲሁም የብጉር ጠባሳ ባለበት ቦታ፣ የስረኛው የቆዳ ክፍል መዋቅር የሆኑት ንጥረነገሮች ይኮማተራሉ።
🖲እነዚህን የተኮማተሩ የቆዳ ስር መዋቅሮች በመበተን የስረኛው የቆዳ ክፍል ላይ የሚገኙ ጥቃቅን ህዋሳት አዲስ መዋቅር እንዲያመርቱ ይረዳቸዋል
🖲 ለዚህ ተግባር እነዚህ ህዋሳት የሚያመርቱት ንጥረ ነገር የከሰመ የፀጉር ስርንም የማነቃቃት አቅም አለው።
🖲ደርማ ሮለር ብቻውን ከመጠቀም ይልቅ፣ እንደታሰበለት አላማ፣ ከተጨማሪ የሚቀቡ አንቲ ኦክሲዳንቶች፣ የፀጉር ማሳደጊያዎች፣ የፀሀይ መከላከያዎች ጋር ቢሆንና እንዲሁም የቆዳ ሀኪምን አማክራችሁ ብትጠቀሙ የበለጠ ለውጥ ልታገኙበት ትችላላችሁ።
🔴መጠቀም የሌለባቸው ሰዎች 🔴
👉ብጉር፣ ብጉንጅ እና ማንኛውም የቆዳ ኢንፌክሽን ያለበት ሰው
👉በቀላሉ የሚቆጣ ቆዳ ያላቸው ሰዎች
👉ቆዳቸው የሚያብጥ ጠባሳ የሚፈጥር ሰዎች
Telegram 👉https://t.me/seifemed
Facebook 👉https://fb.me/seifemedfb

👍15
መመረዝ
👉በአቅራቢያወ ያለ ሰዉ መርዝ ቢጠጣ፣መድሀኒት አብዝቶ ቢወስድ ወይም በእባብ ቢነደፍ ምን ያደርጋሉ!!!!
👉መመረዝ(poisning) አንድ ሰዉ በሚጠጣ መልክ፣ በሚዋጥ መልክ በህክምና ያልታዘዙ መድሀኒቶችን አብዝቶ መዉሰድ፣ለፅዳት አገልግሎት የምንጠቀምባቸዉን ኬሚካሎች:እንደ በረኪና ና ሌሎችን መጠጣት ወይም በእባብ መነደፍ ሊሆን ይችላል።።
👉መመረዝ በትንፋሺ (በአየር )የሚገባም ሊሆን ይችላል
🎇🎇በትንፋሺ የሚከሰት መመረዝ
👉በአየር የሚከሰት መመረዝ ምሳሌ የከሰል ጮስ፣ከጋዝ ሞተሮች የሚወጣ ጭስ፣ከእሳት አደጋ የሚወጣ ጭስ ወዘተ ሊሆኑ ይችላሉ
👉ይህ በሚያጋጥም ጊዜ ቶሎ ወደ ንፁህ አየር መዉሰድ ያስፈልጋል።
👉አፍ ዉስጥ ወይም ወደ ጉሮሮዉ ና አየር መተላለፊያዉ የዘጋዉ ባዕድ ነገር ካለ ቀስ ብሎ ማዉጣት ና ቶሎ ወደ ህክምና ቦታ መዉሰድ ይመከራል
👉አንዳንድ ጊዜ ተጎጂዉ ራሱን የሳተ ከሆነ አንዳንድ ሰወች እንዲነቃ በማሰብ ክብሪት መለኮስ እና እንዲያሸተዉ ማድረግ ሲያደርጉ ይስተዋላል: ይህ የሚመከር ተግባር አይደለም ።
👉ምንም የባሰ ምልክት ባያሳይም እንኳ ቶሎ ወደ ህክምና ቦታ መዉሰድ ያስፈልጋል
👉ቤት ዉስጥ ከሰል አያይዞ የቤት በርና መስኮት ዘግቶ መቀመጥም ለዚህ ያጋልጣል።
🎇🎇በሚጠጡ ወይም ሚዋጡ ነገሮች መመረዝ
👉ይህ ፀረ ተባይ፣ፀረ አረም፣በረኪና ወይም ሌላ ማንኛዉም መድሀኒት ወይም መርዝ በመዉሰድ ሊከሰት ይችላል
👉በዚህ ጊዚ በሺተኛዉን ህክምና ቦታ እስኪደርስ ድረስ በግራ ጎኑ ያስተኙ።
👉እንዲያስመልሰዉ ብለዉ ምንም ነገር አይስጡ
👉አፉ ዉስጥ የቀረ መርዝ ካለ ያስወግዱ፣ሆስፒታል ደርሶ በሀኪም ካልታዘዘ በስተቀር መርዙን ለማርከስ ብለዉ ሎሚ፣ወተት ወይም ሌላ ነገር አይሰጡ
👉ራሱን የሳተ ከሆነ ምንም ነገር በአፋ አይስጡ
👉የጠጣዉ (የወሰደዉ)ነገር የሚታወቅ ከሆነ መድሀኒቱን ወይም እቃዉን አብረዉ ወደ ሆስፒታል በመዉሰድ ለሀኪም ያሳዪ፣ማርከሻ መድሀኒቱን ለመስጠት ለሀኪሞች ስለሚያግዝ።።።
ዶ/ር ዮርዳኖስ
ክፍል ሁለት ይቀጥላል።።።።

👍19😱1
➕ አምሮትና እርግዝና ➕
🖲 አንዳንድ ሴቶች አማረኝ የሚሉት ነገር ሲበዛ፣ በእርግዝና ግዜ እንዲሁም የተለያዩ ባእድ ነገሮችን መመገብ ሲመኙ ካጋጠማችሁ።
🖲 PICA ይባላል በስነአእምሮ ህክምና
🖲ከማህበረሰቡ ስርአተ አመጋገብ የወጣ እና ከምግብ ዘርፍ የማይመደብ ባእድ ነገር መመገብን ያመላክታል
🖲በምን መልኩ እንደሚመጣ የሚያሳውቅ ግልፅ የሆነ አንድ መንገድ ባይኖርም ነገር ግን አፈር መቃም በረዶ ማኘክ የመሳሰሉ በህሪዎችን የሚያሳዩ ነብሰ ጡሮች አብዛኛውን ግዜ በእርግዝናቸው ወቅት በቂ የሆነ ክብደት የማይጨምሩ እና እንዲሁም የ iron zink እና calsium የመሳሰሉ ጥቃቅን ንጥረ ነገሮች እጥረት የሚታይባቸው ናቸው።
🖲 ይህ ሁኔታ ከፍ ያለ የኑሮ ደረጃ ካላቸው ይልቅ ዝቅ ያለ የኑሮ ደረጃ የሚመሩ ማህበረሰቦች ላይ ያመዝናል።
🖲አፈርን እንዲሁም ባእድ ነገርን መመገብ፣ ለተጓዳኝ በሽታ አጋላጭ ከመሆኑ ባሻገር ምንም ጥቅም የለውም።
👉በእርግዝና ወቅት በቂ የሆነ እና የተመጣጠነ ምግብ መመገብ
👉ከጤና ባለሞያ የሚሰጡ ምክሮችን እንዲሁም
👉የቅድመወሊድ ክትትል ማድረግ ተያያዥነት ያላቸውን ችግሮች በቶሎ ለመፍታት ያስችላል።
🖲በዚህ እና በማህፀን እና ፅንስ ህክምና ጉዳይ ከዶ/ር ቤቴል ደረጄ ( የማህፀን እና ፅንስ ስነ ካንሰር ሀኪም) የበለጠ መረጃና ተጨማሪ ህክምና በዊኬር አፕሊኬሽን ላይ ማግኘት ትችላላችሁ።
👇👇👇👇👇👇
🖲መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ! https://play.google.com/store/apps/details?id=com.icare.patient
ሐኪሞችን ለማግኘት መተግበሪያውን በመጫን ቀጠሮ ይያዙ።
telegram 👉https://t.me/seifemed
Facebook 👉https://fb.me/seifemedfb
ዶ/ር ሰይፈ

👍23❤1🥰1
➕➕ ቀድሞ የመጨረስ ችግር ➕➕
🖲አስቀድሞ የመጨረስ ችግር፣ በስነ እምሮ ህክምና መስፈርት ያለው ትርጓሜ
▶አንድ ወንድ በተሳተፈባቸውን ግንኙነቶች ለይ ፣ 75 በመቶ እና ከዛ በላይ የሚሆኑት የተጠናቀቁት ከ 1 ደቂቃ በታች ከሆነ።
▶ይህ ችግር በጌዜ ሂደት ሳይሻሻል 6 ወር እና ከዛ በላይ ከቆየ ከሆነ እና የስነልቦናዊ ጫና ካሳደረ።
▶እንዲሁም ከተጓዳኝ መዳኒቶች የጎንዮሽ ጉዳት፣ የስነ አእምሮ ፣ እና የውስጥ ደዌ በሽታዎች ጋር የማይገናኝ ሲሆን።
👉ቶሎ የመጨረስ ችግርን ያመላክታል።
🖲የግንኙነት ቆይታ ግዜን መስፈርት በማረግ ከፍተኛ፣ ዝቅተኛ ና መለስተኛ ተብሎ በሶት ደረጃዎች ይከፈላል።
▶ከፍተኛ፣- ግንኙነት ሳይጀመር፣ ወይም ግንኙነት በተጀመረ በ 15 ሰከንድ ውስጥ የሚያልቅ።
▶መለስተኛ፣ ግንኙነት ተጀምሮ ከ 15 እስከ 30 ሰከንድ ውስጥ ሲጠናቀቅ።
▶ዝቅተኛ፣- ግንኙነቱ ከ 30 ሰከንድ እስከ 1 ደቂቃ ባለው ግዜ ውስጥ ሲጠናቀቅ።
🖲ቀድሞ የመጨረስ ችግር፣ ከመጀመሪያ ግንኙነት ጀምሮ አብሮ የነበረ ወይም ፣ከግዜ በኋላ የመጣ ሊሆን ይችላል
🖲ለዚህ ችግር መፍትሔ የሚሆኑ ፣ በግንኙነት ግዜ የሚደረጉ ተግባሮች
👇👇👇 👇👇👇

👍96❤27😱14🙏1
በግንኙነት ግዜ የሚደረጉ ተግባሮች.pdf
2.3 MB
👍29❤5😍4🥰3
ይቅርታ፣ ይህ 👉 @LEKETERO የክሊኒክ አድራሻ ነው ለቀጠሮ ብቻ ምልክቱን ተጭነው ስም እና ስልክ ያስቀምጡ
ለጥያቄ ይሄን ይጠቀሙ👉https://t.me/seifemedask
በስልክ ለማግኘት ከሆነ ለ ዶ/ር ሰይፈ +251974163424 ይደውሉ፣ ማታ ከ 12 ሰአት በኋላ እና ስራ ላይ ከሆነ ስልክ ስለማያነሳ በሌላ ግዜ ደግመው ይደውሉለት።
telegram 👉https://t.me/seifemed
Facebook 👉https://fb.me/seifemedfb
ለጥያቄ ይሄን ይጠቀሙ👉https://t.me/seifemedask
በስልክ ለማግኘት ከሆነ ለ ዶ/ር ሰይፈ +251974163424 ይደውሉ፣ ማታ ከ 12 ሰአት በኋላ እና ስራ ላይ ከሆነ ስልክ ስለማያነሳ በሌላ ግዜ ደግመው ይደውሉለት።
telegram 👉https://t.me/seifemed
Facebook 👉https://fb.me/seifemedfb
👍100❤33😱10🥰9🤔7🙏7👏6🎉3🤩2🏆1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
➕➕ የአይን መርገብገብ ➕➕
🖲 የላይኛው ወይ የታችኛው የአይን ክዳን ሲንቀጠቀጥ፣ ማንን ልናይ ነው ወይ በምን ልናለቅስ ነው ይባላል በተለምዶ
▶eyelid myokemia ይባላል በህክምናው።
🖲በአይን ክዳን ዙሪያ የሚገኙ ጡንቻዎች፣ ከቁጥጥር ውጪ ስስ የሆነ እንቅስቃሴ ሲኖራቸው የሚፈጠር ሁኔታ ነው።
🖲አብዛኛውን ግዜ በአንድ አይን ብቻ የተገደበ ሆኖ ከላይኛው ይልቅ የታችኛው የአይን ክዳን ላይ አዘውትሮ የሚታይ፣ በራሱ ግዜ የሚጠፋ እና ከምንም ተጓዳኝ ህመም ጋር ያልተገናኘ ሁኔታ ነው።
🖲አንዳንድግዜ ቡና በተደጋጋሚ ከመጠጣት ጋር ተያይዞ፣ እንዲሁም ጭንቀት እና ድካም ባለበት ሁኔታም ሊታይ ይችላል
🖲ነገር ግን፣ ለረጅም ግዜ የቆየ ከሆነ እና እንዲሁም አይን በተደጋጋሚ የማስጨፈን ጥንካሬ ካለው፣ የአይን መቅላት እና
ከአይን አልፎ የፊት ጡንቻዎች ላይ የሚታይ ከሆነ ሀኪምጋ መቅረብ ያስፈልጋል።
telegram 👉https://t.me/seifemed
Facebook 👉https://fb.me/seifemedfb
🖲 የላይኛው ወይ የታችኛው የአይን ክዳን ሲንቀጠቀጥ፣ ማንን ልናይ ነው ወይ በምን ልናለቅስ ነው ይባላል በተለምዶ
▶eyelid myokemia ይባላል በህክምናው።
🖲በአይን ክዳን ዙሪያ የሚገኙ ጡንቻዎች፣ ከቁጥጥር ውጪ ስስ የሆነ እንቅስቃሴ ሲኖራቸው የሚፈጠር ሁኔታ ነው።
🖲አብዛኛውን ግዜ በአንድ አይን ብቻ የተገደበ ሆኖ ከላይኛው ይልቅ የታችኛው የአይን ክዳን ላይ አዘውትሮ የሚታይ፣ በራሱ ግዜ የሚጠፋ እና ከምንም ተጓዳኝ ህመም ጋር ያልተገናኘ ሁኔታ ነው።
🖲አንዳንድግዜ ቡና በተደጋጋሚ ከመጠጣት ጋር ተያይዞ፣ እንዲሁም ጭንቀት እና ድካም ባለበት ሁኔታም ሊታይ ይችላል
🖲ነገር ግን፣ ለረጅም ግዜ የቆየ ከሆነ እና እንዲሁም አይን በተደጋጋሚ የማስጨፈን ጥንካሬ ካለው፣ የአይን መቅላት እና
ከአይን አልፎ የፊት ጡንቻዎች ላይ የሚታይ ከሆነ ሀኪምጋ መቅረብ ያስፈልጋል።
telegram 👉https://t.me/seifemed
Facebook 👉https://fb.me/seifemedfb
👍50❤4🙏2
poisining
መመረዝ
ክፍል 2
👉በእባብ መነደፍ (በእባብ መመረዝ)
👍የእባብ መርዙን በአፍ መጦ ለማዉጣት አይሞክሩ።
👍መርዙ በፍጥነት በደም ስርጭት ወደ ተለያዩ የሰዉነት ክፍሎች እንዳይዛመት የሚከተሉትን ያድርጉ።
🎇 የተመረዘዉን የሰዉነት ክፍል ከልብ በታች ያድርጉ።
🎇 የሰዉነት እንቅስቃሴ ና በፍጥነት መንቀሳቀስን ይቀንሱ።
🎇ከቻሉ በጎን በኩል በመተኛት እረፍት ያድርጉ
👍ከተነከሰዉ አካል በላይ ያለዉን የሰዉነት ክፍል ማሰር የራሱ ጉዳት ያለዉ ቢሆንም ህክምና ቦታ ለመድረስ ከ 3 ሰዓትበላይ የሚፈጅ ከሆነ የመርዙን ስርጭት ለመቀነስ ይረዳል።
👍ከተነከሰዉ አካል በላይ ያለዉን ክፍል ጥብቅ አድርገዉ አይሰሩ።ይህ የደም ዝዉዉርን ሊጎዳ ይችላል።
👍እንደ ቀለበት ጌጣጌጥ ያሉ ነገሮች ካሉ ያዉልቁ ።
👉እብጠት ካለ የደም ዝዉዉርን ሊቀንሱ ይችላሉና ከቻሉ ወደ ሆስፒታል ሲመጡ የነደፈወትን እባብ ይዘዉ ይምጡ ።
👉መርዛማ መሆን አለመሆኑን ለመለየት ለሀኪሞች እገዛ ስለሚያደርግ ነዉ።
👉መርዛማ ከሆኑ እባብ መለያወች ዉስጥ የሶስት ማዕዘን ጭንቅላት ና ሞላላ የአይን ብሌን(pupil) ያላቸው ጥቂቶቹ ናቸዉ።
ዶ/ር ዮርዳኖስ.መ

👍31🥰2❤1
ቃጠሎ(BURN)
👉ቃጠሎ ሰዉነታችን በእሳት ሲያያዝ የሚከሰት ነገር ብቻ አይደለም።በኬሚካል፣በጨረር ወይም በኤሌክትሪክም ሊከሰት ይችላል።።
✍️ቃጠሎዉን ባስከተለዉ መንስኤ እንደሚከተለዉ ይከፈላል።።
🎇የእሳት ቃጠሎ..dry heat (የሚነድ እሳት)ወይም scald(ምሳሌ የፈላ ዉሃ)
🎇የኤሌክትሪክ ቃጠሎ
🎇የኬሚካል ቃጠሎ..አሲድ ወይም ቤዝ ሲደፋ የሚከሰት
🎇የጨረር ቃጠሎ..ሰዉነታችን ከሚችለዉ በላይ እንደ x.rayላሉ ጨረሮች ሲጋለጥ የሚከሰትነዉ።
👉በሚደርሰዉ የቃጠሎ ደረጃ እንዲህ ይከፈላል።
ሀ..አንደኛ ደረጃ ቃጠሎ-ይህ የቆዳ የላይኛዉ ክፍል በከፊል ሲጠቃ የሚከሰት ነዉ።
ለ..ሁለተኛ ደረጃ ቃጠሎ..ይህ ደረጃ የላይኛዉ የቆዳ ክፍልና ዉስጠኛዉ የቆዳ ክፍል በከፊል ሲያጠቃ የሚከሰት ነዉ።
ሐ..ሦስተኛደረጃ ቃጠሎ..ይህ ዉጨኛዉና ዉስጠኛዉ የቆዳ ክፍል በሙሉ ሲያጠቃ የሚከሰት ነዉ።
መ..አራተኛ ደረጃ ቃጠሎ.ይህ ሁሉንም የቆዳ ክፍሎች አልፎ ጡንቻና ሌሎች ክፍሎችን ሲያጠቃ የሚከሰት ነዉ።።
👉ቃጠሎ ሲከሰትምን ማድረግ አለብን።
✍️ከቃጠሎዉ ቦታ ቶሎ አንስተን ንፁህ አየር ወዳለበት ቦታ መዉሰድ።
✍️የተቃጠለዉ ቦታ ላይ ሊጥ ቭዝሊን ና ሎሎች ቅባቶች አለማድረግ።
✍️አሲድ ወይም ቤዝ የተደፋበትን በዉሃ ብቻ አጥቦ(Irigate with water)ሆስፒታል መዉሰድ።
✍️ኤሌክትሪክ ለያዘዉ ሰዉ ደግሞ ቶሎ ኤሌክትሪኩ እንዲቋረጥ ማድረግ ና ቶሎ ሆስፒታል መዉሰድ ናቸዉ።።
👍👍ህክምናዉ እንደቃጠሎዉ ደረጃ ና አንደተቃጠለዉ የሰዉነት ክፍል ብዛት ይወሰናል ።ስለዚህ ቶሎ ሆስፒታል መወለሰድ ያስፈልጋል።
ዶ/ር ዮርዳኖስ.

👍33❤1👏1😱1😢1🤩1
➕➕ ቁንጭር(የቆዳ ሌሽማኒያሲስ)➕➕
🖲 ቁንጭር ሌሽማኒያ በሚባል ጥገኛ ተውሳክ ዝርያ የሚመጣ በሽታ ሲሆን በሴቷ የአሸዋ ትንኝ sand fly አማካኝነት ይተላለፋል።
🖲በሽታው በሰውነት ውስጥ እና በቆዳ ላይ የሚከሰት ሲሆን የውስጥ አካል ሌሽማኒያሲስ በቆላ አካባቢ የሚታይና በአግባቡና በቶሎ ካልታከሙት ጉበትን በመጉዳት እስከ ሞት የሚያደርስ ነው።
🖲 የውስጥ አካል ሌሽማኒያስስ ትንኟ ከተናደፈች ከወራቶች በኋላ የሚጀምር ሲሆን ምልክቶቹም
👉 ለረጅም ግዜ የቆየ ትኩሳት
👉የሰውነት መጥቆር
👉ድካም ድካም ማለት
👉የሆድ እብጠት የመሳሰሉት ይገኙበታል
🖲ሌላኛው አይነት የቆዳ ላይ የአፍ፤ አፍንጫ ህብረ ህዋስ ሽፋን ሌሽማኒያሲስ በወይናደጋማና ደጋማ አካባቢዎች የሚታይ ሲሆን በተለይም ስስ የሰውነት ክፍል ላይ እየሰፋ የሚሄድ ቁስል በመፍጠር ዘላቂ የአካልና የስነ ልቦና ጉዳት ያስከትላል
🖲 ይሁን እንጂ እንዳገኘሁት መረጃ በዚህ በሽታ ተጠቂ የሆኑ የአዲስ አበባ ነዋሪዎችም (በሳሪስ እና በመገናኛ) አካባቢ የሚኖሩ ግለሰቦች በ አለርት ሆስፒታል የህክምና ክትትል ሲያደርጉ እየታዩ ነው።
🖲ይህ በሽታ ሰዎችን የሚይዘው ከ20 አይነት በሚበልጡ ጥገኛ ተውሳክ ዝርያዎች አማካኝነት ሲሆን በሀገራችን ከ99.9% በላይ የሚሆነው ጥገኛ ተውሳክ ሌሽማኒያ ኢቶፒካ በመባል ይታወቃል።
🖲የቁንጭር መተላለፊያ ዑደት እና መንገዶች አሁንም በመጠናት ላይ ሲሆኑ እስካሁን ያሉት የቅርብ ጥናቶች በሽታውን አምጭ ጥገኛ ተውሳክ ተሸካሚ ናቸው ተብለው ከሚታሰቡት በድንጋያማ እና ገደላማ ቦታዎች የሚኖሩት አሽኮኮ(hyraxes) እና ሌሎች አጥቢዎች በሴቷ አሸዋ ዝንብ ንክሻ አማካኝነት ይተላለፋል።
🖲 ህክምናው አስቸጋሪ ስለሆነ ከላይ በምስሉ ላይ የሚታየውን አይነት የቆዳ ለውጥ ሲመለከቱ በቶሎ የቆዳ ሀኪምን እንዲያማክሩ አሳስባለሁ

👍16
🥰3
➕➕ የመሀፀን ፈሳሽ ➕➕
🖲 አንድ ለ አቅመ ሄዋን የደረሰች ሴት፣ በአማካይ በቀን አንድ የሻይ ማንኪያ (1.5 g) የሚሆን ጤናማ የመሀፀን ፈሳሽ ሊኖራት ይችላል።
🖲ጤናማ የመሀፀን ፈሳሽ የወር አበባ ኡደትን ተከትሎ መጠኑና ይዘቱ ይቀያየራል። ይዘቱም ቀጭን ውሀ መሰል አንዳንዴ ነጣ ያለ መጥፎ ጠረን የሌለው መሆን አለበት።
🖲ይህ ፈሳሽ መነሻው መሀፀን በር ላይ ከሚገኙ ሙከስ አመንጪ ጥቃቅን እጢዎች እና የተቀረው ደሞ በመራቢያ አካል ግድግዳ ላይ ከሚገኙ ፈሳሽ አመንጪ እጢዎች ሲሆን፣ አብዛኛው የፈሳሹ ይዘት በመሀፀን በር አካበቢ ይጠራቀማል።
🖲የጤናማ ፈሳሽ ባህሪዎች
👉የወር አበባ እንዳለቀ የሚያጣብቅ እና ወፍራም ይዘት አለው
👉ከ ሁለት ሳምንት በኋላ እንቁላል ወደመሀፀን ሲለቀቅ መጠኑ ይበዛና ይዘቱም ውሀ መሰል፣ የሚሳብ አይነት በህሪ ይኖረዋል
👉ቀጣይ የወር አበባ ሲሰናዳ ደሞ ቀድሞ የነበረውን አይነት እና መጠን ተመልሶ ይይዛል።
👉በግንኙነት ግዜ እና ተነሳሽነት ሲኖር፣ የዚህ ፈሳሽ መጠን ይጨምራል።
🖲 ጤናማ ያልሆነ የመሀፀን ፈሳሽ ምልክቶች
👉ይዘቱ ቀለሙና ጠረኑ የተለወጠ ከሆነ
👉ማሳከክ እና ከ እንብርት በታች ህመም ካለ፣
👉በግንኙነት እና ከወር አበባ ጋር ተያይዞ ከግዜ በኋላ የመጣ ህመም ካለ።
🚩 ሀኪምን ማማከር ግድ ይላል።

👍60❤3😱1
➕➕ ፈለግ ➕➕
🖲ፈለግ በዋነኝነት የሚከሰተው በቆዳ ድርቀት ምክኒያት ነው፣ ፈለግ በተደጋጋሚ የሚያስቸግረው ሰው ካለ በዋነኝነት የእጅ ድርቀትን መከላከል ይኖርበታል
🖲ፈለግ የሚያስከትሉ ምክኒያቶች
👉እጅን በተደጋጋሚ ግዜ በልብስ ሳሙና መታጠብ
👉የቆዳ ቁጣ፣ የምግብ እጥረት
👉ቅዝቃዜ፣ዲተርጀንት፣ ኬሚካሎች እና ከመሳሰሉት ጋር
👉ለረጅም ግዜ የቆዳ ንክኪ ማረግ አጋላጭ ምክኒያቶች ናቸው
🖲 Vit C እና Vit C በውስጣቸው የሚይዙ የቆዳ ማርጠቢያ (moisturizer) ክሬሞችን አዘውትሮ በመጠቀም እና ለአጋላጭ ምክኒያቶች ትኩረት በመስጠት ይህን ችግር በቀላሉ ማስወገድ ይቻላል።
🖲 ነገር ግን በቦታው ላይ ከፍተኛ እብጠት ካለ እንዲሁም መግል የያዘ ከሆነ ተጓዳኝ የቆዳ ኢንፌክሽን መኖሩን ስለሚያመላክት ሀኪምን ማማከር ያስፈልጋል።
Telegram 👉https://t.me/seifemed
Facebook 👉https://fb.me/seifemedfb
YouTube
👇 https://youtube.com/channel/UCYypDej8w4sAcILX3PcGXUw
Tiktok
👇
https://vm.tiktok.com/ZM8cRdRTQ/

👍26😱1
በዚህ ሳምንት ከተጠየቁት ጥያቄወች ዉሰጥ
'መጥፎ ሺታ ያለዉ የማህፀን ፈሳሺ አለኝ '
የሚለዉ በብዛት ቀርቧል።
✍️ስለ አባላዘር በሺታ ከአሁን በፊት የቀረበ ቢሆንም በድጋሜ አቅርበናል።
✍️የአባላዘር በሺታ የሴትን ወይም የወንድን የመሪቢያ አካል የሚያጠቃ ተላላፊ በሺታ ኘዉ።
✍️መተላለፊያዉ በንክኪ ሲሆን ዋነኛ የመተላለፊያ መንገድ የግብረ ስጋ ግንኙነት ነዉ።
* ምልክቶች*
👉ከማህፀን የሚወጣ መጥፎ ሺታ ያለዉ ፈሳሺ።ፈሳሹ ነጭ ወይም ቢጫ ሊሆን ይችላል።
👉የሚፈረፈር አይነት ነጪ ፈሳሺ
👉የብልት ማሳከክ፣ሺንት ሲሸና ማቃጠል ፣በግንኙነት ጊዜ ህመም
👉ብልት ላይ የሚከሰት መሰነጣጠቅ ወይም ቁስለት
👉ከወንድ ብልት የሚወጣ ነጭ ፈሳሺ
👉ታችኛዉ የሆድ ክፍል ላይ ህመም
👉የወንድ ልጅ ፍሬን የሚሸፍነዉ ክፍል ላይ እብጠት(scrotal swelling)
👉የአባላዘር በሺታ ካለባት እናት የተወለደ ህፃን ላይ ደግሞ የህፃኑ አይን ላይ የሚታይ ከፍተኛ የሆነ እብጠት :መቅላት እና አይን አር(Neonatal conjunctivites)
**በምን ምክንያት ይመጣል**
👉ባክቴሪያ፣ቫይረሶች፣ፓራሳይት ዋናዎቹ ናቸዉ።
**ህክምናዉ**
✍️በደምስር (በመርፌ የሚሰጥ) መድሀኒት cefttiaxone
👉የሚዋጥ መድሀኒት
👉ታይቶ እንደአስፈላጊነቱ በሴት ልጅ ብልት ዉስጥ የሚገባ ክኒን.....
✍️✍️✍️✍️መረሳት የሌለበት ነገር አንድ ሰዉ የአባላዘር በሺታ በሚታከምበት ጊዜ የትዳር ጎደኛዉን አብሮ ማሳከም ይኖርታል።የትዳር ጎደኛዉ ምልክት ቢያሳይም ባያሳይም።ይህ የሚሆንበት ምክንያት አብዛኛዉ ተጠቂወች በሺታዉ ቢኖርባቸዉም ምልክት ላያሳዩ ስለሚችሉ ነዉ።የትዳር ግደኛ ካልታከመ በሺታዉ በተደጋጋሚ በመከሰት ይመላለሳል ማለት ነዉ።
ካልታከም ምን ያስከትላል**
👉PID(pelvic inflamatory desease )
👉የእንቁላል መተላለፊያ ቱቦዉ ላይ ጠባሳ በመፍጠር የእንቁላል መጎጎዝን በማስተጎጎል መዉለድ አለመቻል (መሀንነት)
👉ከማህፀን ዉጭ ርግዝና
👉ለማህፀን ጫፍ ካንሰር ተጋላጭነትን መጨመር
👉የመራቢያ አካል ኪንታሮት (Genital wart)
👉ወንዶች ላይ የሺንት ቧንቧ ጥበት(urethral stricture)...
👉👉👉👉ምልክቶቹ እንደታዩ ቶሎ ህክምና ማግኘት ይመከራል👈👈👈👈👈👈

👍49❤3👌1
➕➕ የእርዳታ ጥሪ ➕➕
ስሜ ተማም ጀማል ይባላል
ተወለጄ ያደኩት በባሌ ጎባ ስለሴ ቤ/ክሪስቲያን አከባቢ ነው ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በሚድዋይፈሪ ሞያ ተመርቄ
ላለፉት 8 አመታት በባሌ ሮቤ ሆስፒታል ህብረተሰቡን ሳገለግል ቆይቻለሁ ከሁለት አመት በፊት ባደረብኝ ከፍተኛ የኩላሊት ህመም ምክንያት ሁለቱም ኩላሊቶቼ ተጎድተው
ላለፉት ሁለት አመታት የኩላሊት እጥበት እየተደረገልኝ እገኛለሁ
ዉድ ወገኖቼ ከዚህ ህመም ለመዳን የኩላሊት ንቅለ ተከላ ማድረግ ያስፈልገኛል
የኩላሊት ንቅለ ተከላ በሀገራችን እየተሰጠ ስለ ማይገኝ
ዉጭ ሀገር ሄዶ ማሰራት ግድ ሆኖብኛል
እኔም ሆንኩ ቤተሰቦቼ ወደ ዉጭ ሀገር ሄጄ ምታከምበት ገንዘብ ስለሌለን ሁላቹም አቅማቹ የቻለዉን ያክል ከታች በተጠቀሰው የባንክ አካውንት እንድትረዱኝ ስል በፈጣሪ ስም እጠይቃለሁ ።
ስለበጎነታችሁ በፈጣሪ ስም ከልብ አመሰግናለሁ ።
ተማም ጀማል አህመድ 📞 091 179 1452
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
1000040276053
አዋሽ ባንክ
01425154552700265
አቢሲኒያ ባንክ 54375816

👍31
➕➕ የሴት ልጅ ዳሌ ➕➕
🖲የሴት ልጅ ዳሌ ለውበት ብቻ የተፈጠረ እንዳይመስላችሁ በስነተዋልዶ ህክምናም ራሱን የቻለ ጠቀሜታ አለው። አመቺ ዳሌ ያላት ሴት በወሊድ ግዜ አትቸገርም
🖲የሴት ዳሌ ብዙ አይነት አፈጣጠር ያለው ቢሆንም ነገርግን
መደበኛ የሴት ልጅ የዳሌ አጥንት አይነት ፣ (Gynacoid) ጋይናኮይድ በመባል የሚታወቅ ሲሆን፣ በምጥ ለመውለድ ምቹ የሆነ እና 50 በመቶ የሚሆኑ ሴቶች የሚይዙት የዳሌ አጥንት አይነት ነው።
🖲ይህም ሲባል ሰፊ ዳሌ ያላት ሴት በምጥ ግዜ የሚደርስ መስተጓጎል አይፈጠርባትም ማለት አይደለም
🖲በምጥ ግዜ የሚከሰት መስተጓጐል ከዳሌ አፈጣጠር ውጪ የሚመጣበት መንስኤ ብዙ ነው
👉የፅንስ ክብደት ከ 4.5 ኪሎ በላይ መሆን
👉በምጥ ግዜ ያለው የፅንስ አቀማመጥ
👉ተጓዳኝ የውስጥ ደዌ ህመሞች እና
👉የ ስነፅንስ ተኮር ችግሮች መኖር
🖲አንድ ሴት በምጥ ከመውለድ ውጪ በቀዶ ጥገና (Cesarean Section (CS)) እንድትወልድ የምትገደድባቸው ምክኒያቶች ናቸው።
🖲ከዛ ውጪ የዳሌ አጥንት በምጥ ለመውለድ አመቺ መሆኑን ለማወቅ የህክምና ምዘና ይደረጋል
👉Pelvimetry
👉Obstetric ultrasound
👉Biophysical Profile
👉 የደም የሽንት እንዲሁም እንዳስፈላጊነቱ ተጨማሪ ምርመራዎች
🖲 እነዚህን ምዘናዎች እና ተጓዳኝ የምርመራ ውጤቶችን በማገናዘብ በምጥ የመውለድ እድልን አስቀድሞ መተንበይ ያስችላል።
🖲ለዚህ ሁሉ ስኬት በግዜ የሚጀመር የቅድመ ወሊድ ክትትል ወሳኝነት አለው።
ለህክምና ቀጠሮ ብቻ
ይሄን ተጭናችሁ 👉 @LEKETERO
ስም እና ስልክ አስቀምጡ።
ዶ/ር ሰይፈ 0974163424

👍39
➕ የማይግሬን ራስ ምታት (Migraine Headache) ➕
🖲ማይግሬን ከፍተኛ እና በተደጋጋሚ ግማሽ ከፈሎ የሚከሰት ራስ ምታት ነው። ህመሙ ከአራት ሰአት እስከ ሁለት እና ሶስት ቀናት የሚቆይ ሲሆን ከጭንቅላት እንቅስቃሴ ጋር ተያይዞ ይባባሳል፡፡
👉👉ለማይግሬን አጋላጭ ሁኔታዎች👉👉
✍️ በፆታ ሴት መሆን
✍️በቤተሰብ ተመሳሳይ ችግር ካለ
🎇🎇የማይግሬን ምልክቶች🎇🎇
👉ማቅለሽለሽ እና ማስመለስ
👉ከፍተኛ የድካም ስሜት
👉ብርሐን፣ ድምፅ እና ሽታ መጥላት
👉 የምግብ ፍላጎት ማጣት
👉ዉሃ መጠማት/የከንፈር መድረቅ
👉የስሜት መዋዠቅ
👉ድርቀት ወይም ተቅማጥ
👉 ቅዠት(የሌለ ብርሐን፣ ጥቋቁር ነጠብጣብ መታየት)
👉ጣዕም እና ሽታ ለመለየት መቸገር
👉የእይታ መደብዘዝ
👉በግማሽ በኩል የሰዉነት መዛል/አለመታዘዝ
👉እግር እና እጅ ላይ የመክበድ ስሜት/መደንዘዝ
👉ጆሮ ላይ የደዉል ድምጽ መሰማት
😺😺ማይግሬንን የሚያባብሱ ሁኔታዎች😺😺
👉በወር አበባ ጊዜ የሚከሰት ህመም እና የሆርሞን መለዋወጥ
👉ጭንቀት
👉ምግብ አለመብላት/ርሀብ
👉የአየር ንብረት መቀያየር
👉ምግቦች (እንደየሰዉ ይለያያል) አልኮል
👉የእንቅልፍ መዛባት
✍️✍️✍️የማይግሬን ህክምና✍️✍️✍️
👉የህመም ማስታገሻ እና እንደደረጃው የህመም መከላከያ መድሓኒቶች በሀኪም ክትትል የሚወሰድ
👉ጨለማ እና ፀጥ ያለ ክፍል ዉስጥ በቂ እረፍት ማድረግ
👉በቂ ዉሃ መጠጣት
👉የዝንጅብል ሻይ ፣አፕል እንዲሁም
👉ፎጣ በቀዝቃዛ ዉሃ ነክሮ ወይም በረዶ ጭንቅላት ላይ ማድረግ
👉ጭንቅላት እና የእጅ መዳፍን ማሸት
👉 ቋሚ የሆነ ሰዉነትን የማሳሳብ እንቅስቃሴ እና አርማሞ መስራት :ቋሚ የሆነ መመገቢያ እና የሚተኛበት ግዜ መኖር
👉 የሚያባብስብንን ነገር ለይቶ ማስወገድ ችግሩ እንዳይከሰት ይረዳል።
✍️✍️ዶ/ር ዮርዳኖስ.መ

👍61😢7❤3🥰1