Dr. Seife | ዶ/ር ሰይፈ
47.7K subscribers
178 photos
2 videos
6 files
130 links
የዚህ ቻናል አላማ፣ ለህብረተሰቡ አስፈላጊውን የህክምና አስተምሮት እና መልእክቶች ማስተላለፍ ነው።
📞 0974163424
ለህክምና ቀጠሮ ብቻ ይሄን 👉 @LEKETERO ወይም @Apointment1
ተጭነው ስም እና ስልክ አስቀምጡ።

ዶ/ር ሰይፈ (ጠቅላላ ሐኪም)
Download Telegram
Live stream started
Live stream finished (26 minutes)
Live stream started
Live stream finished (35 minutes)
ከፍተኛ የደም ስብ መጠን የጤና ጠንቅ መሆኑን የማያውቅ የለም።

🚩 ልብ ማለት ያስፈልጋል 🚩

ደረቅ ዘይት ወይም ከእንስሳት ምርት የሚወጣ ስብን አብዝቶ በመመገብ የምንሸምተው።

🖲 ውፍረት
🖲 የደም ግፊት
🖲 የ ስኳር በሽታ
🖲 የልብ ህመም
🖲 ስትሮክ

እና ሌሎችም የስነልቦና ችግሮች ተጠቃሾች ናቸው።

የደም ስብ ምርመራ የሚያካትተው

🖲 LDL
🖲 HDL
🖲 Total Cholesterol
🖲 Triglyceride

ይባላሉ።
እነዚህን ምርመራዎች ከየትኛውም ላቦራቶሪ ማግኘት ይቻላል
ለምርመራ በጠዋት ምግብ ከመበላቱ በፊት ሲሆን ትክክለኛ ውጤት ይሰጣል።

ውጤቱም ለጤነኛ ሰው።
🖲 Total cholesterol ከ 200 በታች
🖲 LDL ከ 100 በታች
🖲 HDL ከ 50 በላይ
🖲 Triglyceride ከ 150 በታች መሆን አለበት

።።።።።ይቀጥላል ።።።።
👍11
👉 ስፖርትን ሳያቋርጡ አዘውትሮ መስራት
👉 የ አታክልት ፣ ፍራፍሬ ፣ እና ከእፅዋት የተውጣጡ ምግቦችን መመገብ
👉 ከ ጥብሳጥብስ ምግቦች ይልቅ፣ የተቀቀሉ ምግቦችን መምረጥ
👉አልኮል የሚይዙ መጠጦችን በጣም መቀነስ

የደም ስብ መጠንን በደምብ አርገው የቀንሳሉ።

💥 ከዚህ ውጪ በሀኪም ትእዛዝ የሚሰጠው የ ደም ስብ መቀነሻ መዳኒት ግዜአዊ በሆነ መልኩ ብቻ የደም ስብን የመቀነስ እገዛ ያደርጋል።
👍62
💥የዐይን መንሸዋርን በህክምና ማስተካከል ይቻላል💥

👉 የመጀመሪያው የህክምና እርምጃ የዐይን መንሸዋረሩ በምን ምክንያት አንደመጣ መረዳት ነው።

ይሄን ማድረግ የሀኪም ስራ ይሆናል ማለት ነው።

ምክንያቱ ከታወቀ፣ እንዳስፈላጊነቱ የተለያዩ የህክምና አማራጮች ይኖሩታል።

🖲 በመነፅር
🖲 በአይን መሸፈኛ
🖲 በቀዶ ህክምና
🖲 የአይን ጡንቻ ላይ በሚወጋ መዳኒት እና
🖲 ለተጓዳኝ ህመሞች አስፈላጊውን ህክምና በማድረግ ይሆናል።

።።።።።ይቀጥላል ።።።።።
👍6
Forwarded from Dr. Seife | ዶ/ር ሰይፈ (Dr. Seife)
💥የዐይን መንሸዋርን በህክምና ማስተካከል ይቻላል💥

👉 የመጀመሪያው የህክምና እርምጃ የዐይን መንሸዋረሩ በምን ምክንያት አንደመጣ መረዳት ነው።

ይሄን ማድረግ የሀኪም ስራ ይሆናል ማለት ነው።

ምክንያቱ ከታወቀ፣ እንዳስፈላጊነቱ የተለያዩ የህክምና አማራጮች ይኖሩታል።

🖲 በመነፅር
🖲 በአይን መሸፈኛ
🖲 በቀዶ ህክምና
🖲 የአይን ጡንቻ ላይ በሚወጋ መዳኒት እና
🖲 ለተጓዳኝ ህመሞች አስፈላጊውን ህክምና በማድረግ ይሆናል።

።።።።።ይቀጥላል ።።።።።
👍81
💥ዉርጃ 💥


👉 ዉርጃ ፅንስ ከተፈጠረበት ጊዜ ጀምሮ ከ 28 ሳምንት በፊት የሚያጋጥም የፅንስ መጨናገፍ ነዉ።

👉ይህም በራሱ ወይም ሆን ተብሎ ሊከናወን ይችላል።

👉 በኢትዮጵያ ህግ ነባራዊ ሁኔታ መሰረት ዉረጃየሚፈቀደዉ ፣

ከ 18 አመት በታች ለሆነች ሴት

*ፅንሱ በህይወት ለመቀጠል የማያሰቺል መሰረታዊ የአፈጣጠር ችግር ካለበት፣

*እናትዮዋ ከባድ የሆነ የልብ ፡ የሳንባ ወይም አዕምሮ ህመም ያለባት እንደሆነ፣

*እርግዝናዉ የተፈጠረዉ ተደፍራ ከሆነ ነዉ።

ዶ/ር ዮርዳኖስ
👍72
💥Vitiligo ለምፅ💥

ምንም እንኳን የቆዳ ቀለም ተፈጥሮ፣ የፀሃይ ጨረርን ከመከላከል ባሻገር ሌላ ተፈጥሮአዊ ጥቅም ባይኖረውም፣ የቆዳ ቀለም በ ግንዛቤ ላይ ያለው ተፅእኖ ከፍተኛ ነው።

ለምፅ የሚመጣበት አንድ ወጥ የሆነ ምክንያት የለውም። ነገር ግን ብዙ ምክንያቶች ለምፅን እንደሚያመጡ ይገመታል

ለምፅን ሊያስነሱ የሚችሉ ምክንያቶች
👉 የ ቫይረስ ኢንፌክሽን
👉 የ ሆርሞን መለዋወጥ
👉 ቆዳን የሚጎዱ ኬሚካሎች
👉 ጭንቀት እና
👉 ቆዳ ላይ የሚደርሱ አደጋዎች
ተጠቃሾች ናቸው።
ለምፅ በዋነኝነት ሊመጣ የሚችለው፣ የሰውነት የበሽታ ተከላለይ ህዋሶች፣ በቀለም አምራች ህዋሶች ላይ በሚያስከትሉት ጉዳት ነው።

ከዚህም ምክንያት ጋር ተያያዥነት ያላቸው፣ የተለያዩ የውስጥ ደዌ ህመሞች ፣ በለምፅ ታካሚዎች ላይ ሊያጋጥሙ ይችላሉ።

ለምሳሌ ያህል፣
👉 የ እንቅርት ህመም
👉 የስኳር በሽታ
👉 የደም ማነስ አይነት
👉 የ ላሽ በሽታና፣ እንዲሁም ሌሎች ከሰውነት ቁጣ ጋር የተያያዙ ተጓዳኝ በሽታዎች ሊኖሩ ስለሚችሉ፣ የለምፅ ታካሚዎች አስፈላጊውን ምርመራና ክትትል ማድረግ ይጠበቅባቸዋል ።
👍6😢1
💥ይህ አይነቱ የቆዳ ለውጥ አብዛኛውን ግዜ እንደ ቀቁቻ እና ጭርት ተደርጎ ይታያል፣

⭐️ ነገር ግን ቋቁቻም ጭርትም አይደለም

በተለያዩ ምክንያቶች ቆዳ ለረጅም ግዜ ሲታከክ የሚፈጠር ነው።

⭐️ ከሰው ወደሰው በንክኪ አይተላለፍም

👉ህክምናው

ኮሌታ ያላቸውን ልብሶች አለማረግ

እከክ ሊያስነሱብን የሚችሉ ማናቸውንም ነገሮች ከመጠቀም መቆጠብ

በሀኪም ትእዛዝ የሚሰጡ የሚቀቡ የስቴሮይድ መዳኒቶችን በአግባቡ መጠቀም

ከጭንቀት ጋር ተንተርሶ ለሚመጣ ማሳከክ ተጨማሪ የስነልቦና ምክር እና ህክምና ያስፈልገዋል ።
👍2
***የአባላዘር በሺታ********

*የአባላዘር በሺታ የመራቢያ አካላትን የሚያጠቃ በሺታ ነዉ።።።።

*አብዛኛዉን ጊዜ የሚተላለፈዉ በግብረ ስጋ ግንኙነት አማካኝነት ነዉ።።።።።።

*ሴቶች ከወንዶች የበለጠ ተጋላጭ ናቸዉ ።።።።

*ሺንት ሺሸኑ ማቃጠል ወይም መቆጥቆጥ፣ከሴትም ወይም ወንድ ብልት የሚወጣ ነጭ ወይም ቢጫ ፈሳሺ፣የብልት ማሳከክ፣ብልት አካባቢ የሚፈጠርቁስለት ዋና ዋና ምልክቶች ናቸዉ።።

*ልቅ የሆነ የግብረ ስጋ ግንኙነት፣ከ1በላይ የፆታ ጓደኛ መያዝ ና ሌሎችም ለአባላዘር በሺታ የሚያጋልጡ ነገሮች ናቸዉ።።።

*ህክምና ያለዉ በመሆኑ ምልክቶች ሲታዩ ቶሎ ህክምና ማግኘት ያስፈልጋል።።።

*የአባላዘር በሺታ አንድ ሰዉ በሚታከምበት ጊዜ የትዳር ጓደኛዉ ምልክት ባይኖረዉም መታከም ይኖርበታል።
👍4
👍3
*🌴🌴🌴🌴🌴🌴**
ይህ ሶኳር ህመም ከሚያስከትላቸዉ
የጤና ችግሮች አንዱ ነዉ።

ስኳር ከፍተኛ ደረጃ ላይ ሲደርስ ትናንሽ የደም ስሮች ላይ በሚያሰከትለዉ ተፅዕኖ ከፍተኛ ነዉ።

በወቅቱ ህክምና ካላገኘ ጋንግሪን ወደ ተባለ ችግር ብሎም እግር እሰኸመቆረጥ ሊያደርስ ይችላል።።።

ሰፋ ያሉ እና ጥብቅ የማያደርጉ ጫማዎችን መጠቀም ይመከራል
👍5