Dr. Seife | ዶ/ር ሰይፈ
47.7K subscribers
178 photos
2 videos
6 files
130 links
የዚህ ቻናል አላማ፣ ለህብረተሰቡ አስፈላጊውን የህክምና አስተምሮት እና መልእክቶች ማስተላለፍ ነው።
📞 0974163424
ለህክምና ቀጠሮ ብቻ ይሄን 👉 @LEKETERO ወይም @Apointment1
ተጭነው ስም እና ስልክ አስቀምጡ።

ዶ/ር ሰይፈ (ጠቅላላ ሐኪም)
Download Telegram
የተረከዝ ህመም

🖲 የተረከዝ ህመም ሁሉ፣ አንድ አይነት በሽታ ነው ማለት አይደለም 🚩

🖲የውስጥ እግር ማቃጠል እና መቆጥቆጥ ሲኖር አብዛኛውን ግዜ የስኳር በሽታ ምልክት ነው የሚል ስጋት በታካሚዎች ላይ ይስተዋላል፣

🖲ምንም እንኳን የስኳር በሽታ የነርቭ ጉዳትን ከማስከተል ጋር ተያይዞ የእግር ህመምን ቢያስከትልም ፣ነገር ግን፣ የውስጥ እግር እና የተረከዝ ህመም በተደጋጋሚ ግዜ ሲያጋጥም ፣እንደ ህመሙ አይነት እና ባህሪ የተለያየ  አይነት መንስኤ አለው።

🖲ለምሳሌ፣ ብዙ ሰዎች ላይ የሚያጋጥም አንድ የተረከዝ ህመም አይነት አለ በህክምናው ( Plantar Faciitis ) በመባል ይታወቃል፣

🖲አብዛኛውን ግዜ ፣ሰዎች በዚህ ህመም ሲጠቁ በየህክምና ተቋሙ ይመላለሳሉ።

🖲ነገር ግን፣ ይህን አይነቱን የተረከዝ ህመም፣  ያለ መዳኒት ፣በቤት ውስጥ በሚደረግ ቀላል እንቅስቃሴ ብቻ ማዳን የሚቻልበትም መንገድም አለ።

🖲ይህ ችግር ያለባቸው ሰዎች፣ አብዛኛውን ግዜ ጠዋት ላይ ከእንቅልፋቸው ሲነሱ ፣ወይም ደሞ ረዘም ላለ ግዜ እረፍት አድርገው ለመንቀሳቀስ ሲሞክሩ፣ ከስር ተረከዛቸው ላይ ፣የውጋት ስሜት ይሰማቸዋል።

🖲አንዳንዴ የህመም ስሜቱ ከበድ ያለ ሲሆን፣ ከተረከዝም አልፎ እስከ ቁርጭምጭሚት ድረስ የሚደርስ የውጋት ስሜት ይኖራል።

🖲በዚህን ግዜ ታዲያ፣ እግርን ማንቀሳቀስ የውጋት ስሜት ስለሚፈጥር ፣ በተቀመጡበት አንኳን እግርን እንደልብ ለማንቀሳቀስ ያስቸግራል፣ እንደውም ብዙ ሰዎች በህመማቸው ግዜ፣ ቁርጭምጭሚታቸው ላይ እብጠት እንዳለ ያህል ይሰማቸዋል፣

🖲በተለይ ደሞ ፣ጠዋት ላይ ከአልጋ ሲወረድ፣ ሙሉ እግር መሬት ሲነካ ህመሙ ስለሚብስ፣ በእንቅስቃሴ ግዜ፣ የማስነከስ ባህሪ ሊኖረው ይችላል፣

🖲ወይም ደሞ፣ አብዛኛውን ግዜ ፣ ይህ ችግር ያለባቸው ሰዎች፣ ህመሙን ለመቋቋም ሲሉ፣ ጠዋት ጠዋት ላይ ተረከዝን መሬት ሳያስነኩ በጣታቸው መራመድን ይመርጣሉ።

🖲ታዲያ፣ የተረከዝ አጥንት ላይ ከሚደርስ አደጋ አንስቶ፣ የቁርጭምጭሚት፣ የጡንቻ እና የጅማት አካሎችን የሚያጠቃ ችግር ሲኖር ፣የውስጥ እግርን እና፣ የተረከዝ ህመምን ይፈጥራል።

🔴የተረከዝ ህመም አይነቶችን እና ከተረከዝ ጅማት ቁጣ የተነሳ የተረከዝ ህመምን በቤት ውስጥ ማከም የሚቻልበትን መንገድ በተመለከተ፣ ሰፋ ያለ መረጃ በ YouTube ላይ አስቀምጫለሁ።

🔴ከታች ያለውን አድራሻ ተጭናችሁ መመለክት ትችላላችሁ፣ መልካም ግዜ።
👇👇👇👇👇

https://youtu.be/4vBtJmJ0De4
👍25297🙏20🏆15🥰12👏12🎉4👌2
Channel photo updated
31👍17🙏8
መጥፎ የአፍ ጠረን

🖲 ጠዋት ላይ ብዙ ሰው ከእንቅልፉ ሲነሳ መጥፎ የአፍ ጠረን ያጋጥመዋል።

🖲 ከ 85 በመቶ በላይ የሚሆነው መጥፎ የአፍ ጠረን፣  በድድ በጥርስ እና በአፍ ዙሪያ ባለ ችግር ይጀምራል።

🖲 ከዛውጪ የሳይነስ ፣የቶንሲል፣ የሳምባ ፣ የጨጓራ እና  እንዲሁም፣ የጉበት እና የኩላሊት ድክመትን ጨምሮ በተለያዩ የውስጥ ደዌ ህመሞች ምክኒያት፣ አንድ ሰው ላይ መጥፎ የአፍ ጠረን ሊጀምር ይችላል።

🖲 መጥፎ የአፍ ጠረን በህክምናው( Halitosis) በመባል ይታወቃል።

🖲 ይህ ችግር በተለያየ እድሜ ክልል ሊጀምር ይችላል፣ እንዲሁም ደሞ ፣ እድሜ እየገፋ ሲሄድ፣ አንድ ሰው ላይ መጥፎ የአፍ ጠረን የሚከሰትበት እድል እየጨመረ ይሄዳል።

🖲 አንድ ሰው ፣በህክምና የተረጋገጠ ፣ምንም አይነት መጥፎ የአፍ ጠረን ሳይኖረው፣ ነገር ግን፣ መጥፎ የአፍ ጠረን እንዳለው በማሰብ ብቻ ወደህክምና የሚመጣ ከሆነ፣ የስነልቦና ችግር እንዳለ ያመላክታል።

🖲 ይህ አይነቱ ችግር ሲኖር በህክምናው (Delusional halitosis) በመባል ይታወቃል

🖲 በተፈጥሮ ወይም በተጓዳኝ በሽታ ምክኒያት፣ አንድ ሰው ላይ በህክምና የተረጋገጠ መጥፎ የአፍ ጠረን ሲኖር ደሞ፣ በህክምናው (Genuine halitosis) በመባል ይታወቃል

🖲 ምንም አይነት የጥርስ እና የድድ ችግር ሳይኖር፣ ወይም ደሞ ምንም አይነት ተጓዳኝ የውስጥ ችግር በሌለበት ሁኔታ፣ መጥፎ የአፍ ጠረን የሚፈጠር ከሆነ ተፈጥሮአዊ ሊሆንም ይችላል።

🖲 ይህ አይነቱ ችግር በህክምናው (Phyisiological halitosis) በመባል ይታወቃል፣ ይህ የሚመጣበት ሁለት አይነት ምክኒያት አለው

👉 የመጀመሪያው፣ በአንድ ጤናማ ሰው አፍ ውስጥ፣ በተፈጥሮ የሚኖሩ ጥቃቅን ተህዋሶች ፣አንድ ሰው ከተመገበ በኋላ በምላስ እና በጥርስ መሀል የሚቀር ጥቃቅን የምግብ ትርፍራፊን ወደ መጥፎ ጠረን ወዳለው ተረፈ ምርት ሲቀይሩት ነው።

👉 ሌላው ምክኒያት ደሞ ፣የምራቅ መጠን እና የምራቅ ዝውውር መቀነስ ነው፣ በአፍ ውስጥ በቂ የምራቅ መጠን የማይኖር ከሆነ ፣በአፍ ውስጥ ያሉ ጥቃቅን ተህዋስያን ፣ አፍ ውስጥ የቀረ ምግብን የበለጠ እንዲያብላሉ ስለሚያስችላቸው፣ መጥፎ የአፍ ጠረንን ይፈጥራሉ።

🖲 አንድ ሰው እርግጠኛ የሆነ መጥፎ የአፍጠረን እንዳለው ለማወቅ በሀኪም እገዛ ፣ወይም ደሞ በቤት ውስጥ የተለያዩ መንገዶችን በመጠቀም ማወቅ ይቻላል።

👉 ለምሳሌ፣ መጥፎ የአፍ ጠረን አለብኝ የሚል ሰው፣ ለ 12 ሰአት ያህል ምንም አይነት ቅመማ ቅመም የበዛባቸውን ምግቦች ሳይመገብ እና ለ 6 ሰአት ያህል ጥርስ ሳይቦረሽ ፣ የእጁን ጀርባ አንድ ግዜ በመላስ በምራቁ ካረጠበ በኋላ፣ ምራቁ ሲደርቅ በቦታው ላይ ያለ መጥፎ ጠረን መኖሩን ማረጋገጥ ነው።

👉 ሌላው ደሞ ፣ ንፁህ መጥረጊያን በመጠቀም፣ ምላስን በመፈግፈግ እና ፣ ወይም ደሞ፣ በጥርስ መሀል በሚገባ ገመድ ፣  ወይም dental flos በመጠቀም ፣የጥርስ መሀልን ፈግገፍጎ ገመዱ ላይ መጥፎ ጠረን መኖሩን አሽትቶ በማረጋገጥ ነው።

🔴 መጥፎ የአፍ ጠረንን የሚያስከትሉ በሽታዎችንን እና ህክምናቸውን በተመለከተ፣ እንዲሁም በቤት ውስጥ መደረግ ያለበትን ሁኔታ በተመለከተ፣ በ 🚩 YouTube🚩 ቻናሌ ላይ ሰፋ ያለ መረጃ አስቀምጫለሁ።

❤️የሚቀጥለውን ማስፈነወጠሪያ በመጫን መመልከት ትችላላችሁ፣ መልካም ግዜ።
👇👇👇👇👇👇👇

https://youtu.be/6stDN6haWac
👍20453🙏48👏2💯1
👍185
ቋቁቻ

🖲 ቋቁቻ እና ጭርት ሊመሳሰሉ ይችላሉ ፣ ነገር ግን፣ ሁለቱም  የተለያየ ዝርያ ባለው ተህዋስ የሚፈጠሩ የቆዳ በሽታዎች ናቸው፣

🖲 ቋቁቻ ከሰው ወደሰው አይተላለፍም፣ ጭርት ከሆነ ግን ከሰው ወደሰው ብቻ ሳይሆን ከእንስሳት ወደሰውም ጭምር በንክኪ መተላለፍ ይችላል።

🖲 ቋቁቻን የሚያስከትለው ተህዋስ፣  አንድ ጤናማ ሰው ቆዳ ላይ፣ ምንም አይነት ቋቁቻን ሳያስከትል ፣ ልከኛ በሆነ መንገድ በተፈጥሮ የሚኖር ተህዋስ ነው፣በህክምናው malassezia ተብሎ ይጠራል።

🖲በተለያዩ ምክኒያቶች ፣ይህ ተህዋስ ከልክ ባለፈ መልኩ ቆዳ ላይ ማደግ ሲጀምር እና የላይኛውን ቆዳ ሲያጠቃ፣ በቦታው ላይ ቋቁቻን ይፈጠራል።

🖲 ይህ ቋቁቻን የሚያስከትል ተህዋስ፣ የተለያዩ ዝርያዎች ያሉት ቢሆንም፣ ነገር ግን፣ አንድ ሰው ላይ ቋቁቻን ሊፈጥሩ የሚችሉት በዋነኝነት 3 አይነት ዝርያዎች ናቸው።

እነዚህ ዝርያዎች፣ አንድ ሰው ቆዳ ላይ ፣ ቋቁቻን የሚያስከትሉበት የተለያየ ምክኒያት አላቸው፣

👉 ወዛም የሆኑ ሰዎች፣ ሞቃታማ ቦታ የሚኖሩ ከሆነ እና ፣ የንፅህና ጉድለት ካላቸው
👉ዘይታማ ቅባቶችን ቆዳ ላይ አዘውትሮ በመቀባት
👉የአንድ ሰው የበሽታ መከላከል አቅም ሲቀንስ
👉እንደ ደርሞቬት ፣ቤትኖቬት፣ ቤታሴት የመሳሰሉትን መዳኒቶች ፣ ከሀኪም ትእዛዝ ዉጪ ለረጅም ግዜ አዘውትሮ በመቀባት
👉ጥራታቸውን ያልጠበቁ እና ፊትን የሚያቀሉ ክሬሞችን ማዘውተር የመሳሰሉት፣ አንድ ሰው ላይ በተደጋጋሚ ግዜ ቋቁቻ እንዲወጣ የሚያደርጉ ምክኒያቶች ናቸው።

🖲 ቋቁቻ በቆዳ ላይ ሲወጣ፣ ነጣ ያለ ወይም ደሞ ጠቆር ያለ ገፅያን ሊይዝ ይችላል፣ አብዛኛውን ግዜ ደሞ፣ ከሌላው የሰውነት ክፍል ይልቅ፣ ወዝ በበዛበት የቆዳ ክፍል ላይ የመውጣት ባህሪ አለው።

🖲 ፊት ላይ የሚወጣ ቋቁቻ ፣ አብዛኛውን ግዜ በአዋቂዎች ላይ የተለመደ አይደለም፣ ነገር ግን፣ ካዋቂዎች ይልቅ አንዳንዴ የልጆች ፊት ላይ ሊያጋጥም ይችላል።

🖲 ቋቁቻ መሆኑን ለመለየት ፣ አንድ ሰው ከታጠበ በኋላ ምንም አይነት ቅባት ሳይቀባ፣ ቋቁቻው በወጣበት ዙሪያ ያለውን ቆዳ በመለጠጥ ፣ወይም ደሞ ፣ቋቁቻው ሲታከክ፣ አመድ የመምሰል ገፅታን ይሰጣል።

🖲 እየከሰመ ያለ ቋቁቻ ሲሆን ደሞ፣ አብዛኛውን ግዜ አመድ የመምሰል ባህሪ ላይኖረው ይችላል።

⭕️ታዲያ ቋቁቻን ለማጥፋት የሚያስፈልገው መዳኒት ምንድነው? በቤት ውስጥ ቀምሞ መጠቀም የሚቻል ውህድስ አለ?

🔴የቋቁቻ ህክምናን በተመለከተ ሰፋ ያለ መረጃ በ YouTube ላይ አስቀምጫለው። ከዚህ በታች ያለውን ማስፈንጠሪያ በመጫን መመልከት ትችላላችሁ። መልካም ግዜ።
👇👇👇👇👇👇👇
https://youtu.be/44WovKjIg_E
👍16855💯10👏9
271👍84🥰34🙏31🤩4
34👍8🏆2
የነርቭ ህመም

🖲የነርቭ ህመም፣  በአንድ የህመም ምልክት ብቻ የሚገለፅ ህመም አይደለም፣ እንደ ቦታው እና እነደ ነርቭ ጉዳቱ ደረጃ፣ በተለያየ አይነት የህመም ምልክቶች ይገለፃል።

🖲መቆጥቆጥ፣ ማቃጠል፣ መለብለብ ፣መደንዘዝ ፣መዛል ፣ እና ከአቅም ማጣት ጀምሮ እስከ ራስ መሳት ድረስ ሁሉ ያሉ የህመም ምልክቶች ፣በነርቭ ህመም ተጠቂዎች ሊገለፁ ይችላሉ።

🖲ነርቭ ላይ ከፍተኛ ጉዳት ከደረሰ፣ አንዳንዴ፣ በህክምና እንኳን መመለስ ስለማይቻል ፣ ብዙ ሰዎችን ዘላቂ ለሆነ የአካል ጉዳት ይዳርጋል።

🖲ጉዳቱ አነስተኛ ከሆነ ደሞ፣ እንደ ተጎዳው ነርቭ  እና፣ ጉዳቱን እንዳስከተለው በሽታ፣ በህክምና ፣ ወደነበረበት መመለስም ይቻላል።

🖲አንድ ሰው ላይ፣ ባጋጣሚ ከሚደርስ አደጋ አንስቶ በቂ ክትትል በሌላቸው ስር ሰደድ በሽታዎችም ጭምር የነርቭ ህመም ሊጀምር ይችላል።

🖲አንድ ጤናማ ሰው ላይ ያለ የነርቭ አካል አፈጣጠር በአቀማመጡ በሁለት ይከፈላል፣  ማእከላዊ የነርቭ አካል እና ውጫዊ የነርቭ አካል።

🖲ማእከላዊ የነርቭ አካል ማለት፣ አይምሮ እና ሀብለ ሰረሰር ናቸው። ውጫዊ የነርቭ አካሎች ደሞ፣ ከአይምሮ እና ከ ሀብለ ሰረሰር የሚነሱ የነርቭ መስመሮች ናቸው።

🖲አይምሮ ውስጥ ያሉ የነርቭ ህዋሶች በከፍተኛ ደረጃ ሲጎዱ ራሳቸውን መልሶ የማደስ ብቃታቸው አነስተኛ ስለሆነ አይምሮ ላይ የሚደርስ ጠንከር ያለ የነርቭ ጉዳት ሲኖር ዘላቂ ለሆነ ወይም በህክምና ለማይመለስ የአካል ጉዳት ሊዳርግ ይችላል።

🖲ከአይምሮ እና ከሀብለሰረሰር ውጪ ያሉ የነርቭ መስመሮች ደሞ፣ እንደ ጉዳት ደረጃቸው ራሳቸውን የማደስ የተወሰነ አቅም አላቸው።

🖲አብዛኛውን ግዜ፣ ቀለል ያለ እና መካከለኛ የጉዳት ደረጃ የደረሰባቸው ከሆነ በግዜ ሂደት ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ የሚያገግሙ ይሆናሉ።

🖲ነገር ግን፣ አንዳንዴ እነዚህ የነርቭ መስመሮች ላይ የሚደርሰው አደጋ ከፍተኛ ከሆነ፣ ጉዳቱ የነርቭ መስመሮቹ ራሳቸውን ከሚያድሱበት አቅም በላይ ስለሚሆን ዘላቂ ለሆነ የአካል ጉዳት ሊዳርጉ ይችላሉ።

🖲የነርቭ ህመም በተለያዩ አደጋዎች እና የውስጥ ደዌ በሽታዎች ምክኒያት ሊከሰት ይችላል፣ የነርቭ ህመሙ በአደጋ ምክኒያት ሲጎዳ፣ ነርቩ ሊጨፈለቅ፣ በከፍፊል ወይም ሙሉ በሙሉ ሊቆረጥ ይችላል።

🖲ስርሰደድ በሽታዎችን ተከትለው የሚመጡ የነርቭ ህመሞች፣ ለምሳሌ፣ የስኳር በሽታን ተከትሎ የሚመጣ የነርቭ ህመም፣ ከእይታ ድክመት ጀምሮ እንደ ደረጃው በብዙ መንገድ ሊገለፅ ይችላል፣

🖲ነገር ግን አብዛኛውን ግዜ ፣ ከጉልበት በታች በሁለቱም እግር ላይ የሚሰማ የመለብለብ እና የማቃጠል ስሜት በተለይ ከመሀል እግር ጀምሮ ወደላይ ከፍ እያለ የሚሄድ የህመም አይነት ይሰማቸዋል።

🖲ከዚህ ውጪ ፣ ለምሳሌ፣ በአልኮል ጥገኝነት፣ በቫይታሚን ቢ እጥረት፣ በመመረዝ፣ በታይሮይድ ህመም እና በተለያዩ ኢንፌክሽኖችም ጭምር የሚመጡ ሌሎች አሳሳቢ የሆኑ የነርቭ ህመም አይነቶችም አሉ።

⭕️የነርቭ ህመምን በተመለከተ፣ ሰፋ ያለ መረጃ በ YouTube ቻናሌ ላይ አስቀምጫለሁ፣ የሚቀጥለውን ማስፈንጠሪያ ተጭናችሁ መመልከት ትችላላችሁ። መልካም ግዜ!!
👇👇👇👇👇👇👇
https://youtu.be/ASL4flPnaU4
👍19965🥰29🙏27
296🙏121👍71🥰40👏24👌14🤩10🕊10🎉9
👍288
የእግር እብጠት

🖲 ሁለት እግር አንድ ላይ የሚያብጥ ከሆነ አንዳንዴ ጥሩ ምልክት አይደለም፣

🖲 ለወራት የሚቆይ ተቅማጥ ፣ የጉበት ችግር፣ የኩላሊት በሽታ፣ እና የልብ ድክመት ሲኖር፣  ከተለያዩ ተጓዳኝ ምልክቶች ጋር ሁለቱም እግር ሊያብጥ ይችላል።

🖲 እብጠቱ በኩላሊት ድክመት ምክኒያት የመጣ ከሆነ፣ በእግር ላይ እብጠት ከመጀመሩ በፊት፣ የአይን ዙሪያ እብጠት ይኖራል

🖲 በልብ ህመም ምክኒያት የሚመጣ የእግር እብጠት፣ እንደ ደረጃው ራስ መሳት፣ አቅም ማነስ፣ ሳል እና አየር ማጠር ሊኖረው ይችላል

🖲 የእግር እብጠት በጉበት ድክመት ምክኒያት የመጣ ከሆነ ደሞ፣ ሆድ ማበጥ እና የአይን ቢጫ መሆን ሊከሰት ይችላል።

🖲 አንዳንዴ ደሞ፣ የከፋ የጤና ችግር በሌለበት ሁኔታም፣ አንድ ሰው ላይ የእግር እብጠት ሊያጋጥም ይችላል።

🖲 ለምሳሌ፣ ነብሰጡር ሴት ላይ እርግዝናው እየገፋ ሲሄድ፣ ሁለቱም እግር ሊያብጥ ይችላል፣

🖲 ውፍረት የሚታይበት ሰው በቀን ውስጥ ረጅም ሰአት የሚቆም ከሆነም፣ እግር ሊያብጥ ይችላል።

🖲 አብዛኛውን ግዜ እድሜያቸው ከ 50 በላይ የሆኑ ሰዎች ላይ፣ ከደም ስር ድክመት ጋር በተያያዘ ሁኔታ፣ ሁለቱም እግር ላይ እብጠት ሊፈጠር ይችላል።

⭕️ ታዲያ አንድ ሰው ላይ የሚታይ የእግር እብጠት ፣ በምን ምክኒያት እንደመጣ እንዴት መለየት ይቻላል

👉የእግር እብጠትን በተመለከተ ከነህክምናው ሰፋ ያለ መረጃ ዩቲዩብ ላይ አስቀምጫለሁ።

▶️የሚቀጥለውን ማስፈንጠሪያ በመጫን መመልከት ትችላላችሁ።
👇👇👇👇👇
https://youtu.be/KeBT-mfwqiQ
👍321104🥰39🙏35🤩23👏16
243🙏79👍44🥰24
266🙏108👍67🥰25👏9👌9