#የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የከተማዋን የመንገድ መብራት የሚያስተዳድር ኤጀንሲ ማቋቋሙን አስታወቀ
አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ ትላንት ሰኔ 11 ቀን 2016 ዓ.ም ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ የከተማዋን የመንገድ መብራት የሚያስተዳድር ኤጀንሲ ማቋቋሙን አስታውቋል።
ለኤጀንሲው መቋቋም ዋነኛ ምክንያቶች ብሎ የከተማ አስተዳደሩ ከዘረዘራቸው ጉዳዮች መካከልም የከተማዋ ነዋሪዎችን የማታ እንቅስቃሴ ከአደጋ እና ከወንጀል ድርጊት ተጠብቆ የሚንቀሳቀሱበት ምቹ ሁኔታ መፍጠር፣ ከተማዋ የቀን ብቻ ሳትሆን ሌሊትም የሚሰራባት ከተማ እንድትሆን ማስቻል የሚለው ይገኝበታል።
በተጨማሪም በከተማ አስተዳደሩ የሚገኙ የመንገድ ላይ መብራቶች አለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ እና ለከተማዋ ውበት በሚፈጥር መልኩ ማሻሻል አስፈላጊ በመሆኑ ነው ብሏል።
አዳዲስ ቴክኖሎጂዎች በመተግበር፣ በመቆጣጠር፣ የጥገና ሥራዎችን በማከናወን የመንገድ ዳር መብራት የሚያስተዳደር ተቋም ማቋቋም አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ነው ኤጀንሲው የተቋቋመውም ሲል ገልጿል።
እንዲሁም ለተደጋጋሚ ብልሽት የመጋለጥ እና ለብልሽት በሚዳረጉበት ወቅት ሥራውን በባለቤትነት ይዞ የሚጠግን አካል እንዲኖር ማድረግ በደንቡ ውስጥ መደንገጉን ጠቁሟል።
ኤጀንሲው ከተሰጡት ሥልጣንና ተግባራት መካከል በህብረተሰቡ፣ በቡድን፣ በግል ወይም በመንግስታዊና መንግስታዊ ባልሆኑ ድርጅቶች አማካኝነት ለሚሰሩ የመንገድ ላይ መብራቶች ስታንዳርድ ማውጣት ይገኝበታል።
================
@አዲስ ስታንዳርድ
የእኛ አገር
ቴዘርን የመኪና መቆጣጠሪያ GPS ሲያስገጥሙ የ5 ዓመት ዋስትና እንሰጣለን!
ለበለጠ መረጃ +251906550011
መተግበሪያውንም አውርደው ይሞክሩ !
https://tinyurl.com/tethereth