ቄድሮን • qedron
448 subscribers
264 photos
32 videos
3 files
497 links
ተሽከርካሪ፡በስልክ፡መከታተያ፡እና፡መቆጣጠሪያ።
Tracking and security for your vehicles.
Download Telegram
3 people died in a traffic accident.
May 13, 2016 in Jimma zone Sokoru woreda Abelti kebele three people died.

In the accident that happened at 7.30 in the morning, seven people were seriously injured in addition to three people who died.
🙏🙏🙏🙏

Let's drive carefully.
በምሽት ተገቢ የተሽከርካሪ መብራት በማይጠቀሙ አሽከርካሪዎች ላይ ቁጥጥር ተደረገ:: *54 አሽከርካሪዎች ተቀጥተዋል -----
- (ት/ማ/ባ/ ግንቦት 8/2016 ዓ.ም) በአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለሥልጣን የየካ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በትናንትናዉ እለት በምሽት የሌሎች አሽከርካሪዎችን እይታ በማወክ ለትራፊክ ግጭት እና ለትራፊክ ፍሰት መስተጓጎል ምክንያት በሆኑ አሽከርካሪዎች ላይ በልዩ ኦፕሬሽን ቁጥጥር አድርጓል።

በክፍለከተማዉ በተመረጡና እግረኞች በሚበዙባቸው ቦታዎች ከምሽቱ 1 ሰዓት ጀምሮ በተቀናጀ መልኩ ጥብቅ ቁጥጥር ተካሂዷል።

በቁጥጥሩም ረጅም መብራት እያላቸው በማብሪያ ጊዜ ያላበሩ፣ መብራት የሌላቸው፣ እያላቸዉ ያላበሩ፣ ከስታንዳርዱ ውጪ ተጨማሪ መብራት የገጠሙ በድምሩ 54 አሽከርካሪዎች በደንብ 395/2009 በእርከን 1/21 እና በእርከን 4/5 መሰረት የገንዘብ ቅጣት ተጥሎባቸዋል።

ይኸዉ ቁጥጥር ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም በቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የመንገድ ትራፊክ የግንዛቤና ደንብ ማስከበር ዳይሬክተር አቶ ሀገሬ ኃይሉ አስታዉቀዋል።
👍1
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
" ሲጀመር ‘የኮቴ’ ክፍያ አገር ውስጥ መጠየቅ አግባብ አይደለም " - ጣና የከባድ ተሽከርካሪ አሽከርካሪዎች ማኀበር

የከባድ ተሽከርካሪ አሽከርካሪዎች ፣ ሞጆ መግቢያ ‘ #የኮቴ ’ በሚል ታጣቂዎች አስቁመው 2,000 ብር እያስከፈሏቸው መሆኑን እየገለጹ ይገኛሉ።

ካሁን ቀደም ገንዘቡን ሲጠየቋቸው የነበረው አንዳንድ ጊዜ በቀን እንደነበር ፣ ከሰሞኑን ግን ቀንም ሌሊትም እየጠየቋቸው ከመሆኑም ባሻገር ድብደባና እንግልት እያደረሱባቸው መሆኑን አስረድተዋል።

ሰሞኑን አንዱን ሹሬር ሞጆ መግቢያ ከሌሊቱ 6 ሰዓት አስቁመው ገንዘብ እንደጠየቁት፣ ‘የለኝም’ ሲላቸው እንዳንገላቱት ገልጸዋል።

ሌላኛው ሹፌር ክፉኛ መመታቱን አመልክተዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ስለ “ ኮቴ ” ክፍያው ምንነት ያውቅ እንደሆን የጣና የከባድ ተሽከርካሪ አሽከርካሪዎች ማኀበርን ጠይቋል።

ማኀበሩ ፤ " አሁን #ጂቡቲ ስንደርስ የሌላ አገር መሬት ስለምንረግጥ ‘ የኮቴ ’ እንከፍላለን። የተለመደ ነው። እዚህ ግን ‘የኮቴ’ እያሉ 2,000 ነው የሚጠይቁት። ይሄ ደግሞ ተገቢም አይደለም " ብሏል።

" ሞጆ ብቻ ሳይሆን በተለያዩ የኦሮሚያ ክልል ከተሞች ድርጊቱ አለ " ያለው ማኀበሩ ፣ አንድ ጊዜም ቢሆን መከፈሉ ከህግ አግባብ ውጪ ሆኖ ሳለ በድጋሚ ሌላ ቦታ ላይ እንደሚያስከፍሏቸው አስረድቷል።

ማኀበሩ ፤ " ሲጀመር ‘ የኮቴ ’ ክፍያ በአገር ውስጥ መጠየቅ አግባብ አይደለም " ብሎ፣ ከክፍያው ባሻገር አሽከርካሪዎቹ ገንዘቡን በሚጠይቁ መሳሪያ የታጠቁ ታጣቂዎች ድብደባ እንደሚፈጸምባቸው፣ የክልሉ አካላት ድርጊቱን ቢያውቁም መፍትሄ እንዳልሰጡ ገልጿል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ፤ ቅሬታውን በተመለከተ ምላሽ ለማግኘት ወደ ክልሉ ባለስልጣናት ያደረገው ሙከራ ለጊዜው አልተሳካም።

Video Credit - ኪያ

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
👍1
ከመገናኛ አዲሱ ገበያ አገልግሎት ይሰጡ የነበሩ 19 ሚኒባስ ታክሲዎች ስራቸው እንዲያቆሙ ማድረጉን የከተማው ትራንስፖርት ቢሮ ተናገረ
ጥንቃቄ
ጭሮ (አሠበ ተፈሪ ) መግቢያ ላይ የደረሰ አደጋ ነው ቦታው ከርቭ ላይ ሥለሆነ በጨለማ አይታይም ቶሎ ካልተነሣም ተጨማሪ አደጋ ያስከትላል ጥንቃቄ እናድርግ
17/09/2016
አፋልጉን

ይሄ በፎቶ የምታዮት ወንድማችን ዳዊት አስናቀ ይባላል ተወልዶ ያደገዉ እዚሁ አዲስ አበባ ነው ሆኖም ግን ከ3 ቀን በፊት የጠፋ እሰካሁን አልተመለሰም። በጊዜው ኮድ 2-B65248 ኮሮላ መኪና እያሽከረከረ ነበር።

ሰልኩም አይሰራም። በምን ሆኔታ ላይም እንዳለ አናውቅም
በቻላቹሁት አቅም ሁሉ ሸር በማድርግ ወንድማችንን አፋልጉን

ስልክ
:- 0918706526
፡-0913412564
:-0911609294
👍1
ወደ ክፍያ መንገዱ በሚገቡ ተሽከርካሪዎች የቴክኒክ ፍተሻ
============================================
ኢክመኢ / ETRE [ግንቦት-18-2016ዓ.ም]

ኢንተርፕራይዙ የቴክኒክ ደረጃቸውን ያልጠበቁ ተሸከርካሪዎች በፍጥነት መንገዱ አደጋ እንዳያደርሱ የቅድመ አደጋ መከላከል ስራ በአዲስ - አዳማ የክፍያ መንገድ በቱሉ ዲምቱ እና በአዳማ ዋና የክፍያ ጣቢያ የውጫዊ የተሸከርካሪዎች የቴክኒክ ፍትሻ አደረገ፡፡

በተጨማሪም አሽከርካሪዎች በክፍያ መንገዱ ውስጥ ሲያሽከረክሩ ለደህንነታቸው ሊያደርጓቸው የሚገባቸውን ተግባራት ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎችን መስራት ተችሏል፡፡

የቴክኒክ ደረጃቸውን ያልጠበቁ ተሽከርካሪዎች ወደ ክፍያ መንገዱ ክልል እንዳይገቡ የማድረግ ስራ እና በትራፊክ ህግ መሰረት እንዲታረሙ ማድረግ ተችሏል፡፡

የቴክኒክ ፍተሻው በዋነኝነት ትኩረት ተደርጎ የተሰራው
🚑 የጎማ ጥራት
🚑 የዝናብ መጥረጊያ
🚑 መብራቶች
🚑 ሶስት ማዕዘን አንፀባራቂ ናቸው፡፡

ኢንተርፕራይዙ ለመንገድ ተጠቃሚዎች የቴክኒክ ደረጃውን ያልጠበቀ ተሸከርካሪ ባለማሽከርከር እና ወደ ክፍያ መንገዱ ከመግባታቸው በፊት የቅድመ ጉዞ ፍተሻ በማድረግ አደጋን በጋራ እንከላከል እያለ ጥሪውን ያቀርባል፡፡

የኢትዮጵያ የክፍያ መንገዶች ኢንተርፕራይዝ
ደህንነትዎ የክብር ስማችን ነው!

☎️ 0114171717 /00/13
ሰሞኑን ሹፌሮች በየቀኑ እስከመኪናቸው እየጠፉ ነው

ሼር እድርጉት 🙏

እዮብ አንዳርጌ ይባላል በ14/9/16 ከቤት እንደወጣ አልተመለሰም በወቅቱ ኮድ1 አ አ ያሪስ 30805 ታርጋ ቢጫ ቀለም ያላት ይዞ ነበር እባካችሁ እዮብን ያየ ወይም ያለበትን የሚያውቅ በፈጣሪ ስም ያሳውቀን

ፈላጊ ቤተሰቦቹ
0913577424
0911116275
0910479302
0945576477
1👍1