"እንጨት" አዳምን ከቤቱ አባረረው!
"እንጨት" ኖህን ከጥፋት ውሃ አዳነው!
"እንጨት" ይስኅቅን ክመታረድ አዳነው!
"እንጨት" የኤርትራን ባህር ለሁለት ከፈለ!
"እንጨት" ለዳዊት ቅብአ ዘይት ሆነ!
"እንጨት" ለአሮን በትር ሆነ!
"እንጨት" የጽዮን ጽላት ሆነ!
"እንጨት" ኪሩቤል ሆነ!
"እንጨት" ሰይጣንን አሰረ!
"እንጨት" ሲኦልን ሰባበረ!
"እንጨት" ገነትን መርቆ ከፈተ!
"እንጨት" ፈያታዊን ወደ ገነት ሰደደ!
"እንጨት" አለምን ቀደሰ!
"እንጨት" ድንግልንና ዮሐንስን አማማለ!
"እንጨት" አዳምን ወደ ቀድሞ ክብሩ መለስው!
"እንጨት" ለአንካሶች ምርኩዛቸው ነው!
"እንጨት" ለእውራን ብርሃናቸው ነው!
"እንጨት" ለለምጻሞች መንጺያቸው ነው!
"እንጨት" ለተራቡት ምግባቸው ነው!
"እንጨት" ለነብያት ትንቢታቸው ነው!
"እንጨት" ለሐዋርያት ስብከታቸው ነው!
"እንጨት" ለሰማዕታት ሞገሳቸው ነው!
"እንጨት" ለክርስቲያኖች ሰላም ነው!
ስለዚህም "እንጨት" ፍቅር፡ ክብር፡ ስግደት ይገባዋል!!❤
"እንጨት" ኖህን ከጥፋት ውሃ አዳነው!
"እንጨት" ይስኅቅን ክመታረድ አዳነው!
"እንጨት" የኤርትራን ባህር ለሁለት ከፈለ!
"እንጨት" ለዳዊት ቅብአ ዘይት ሆነ!
"እንጨት" ለአሮን በትር ሆነ!
"እንጨት" የጽዮን ጽላት ሆነ!
"እንጨት" ኪሩቤል ሆነ!
"እንጨት" ሰይጣንን አሰረ!
"እንጨት" ሲኦልን ሰባበረ!
"እንጨት" ገነትን መርቆ ከፈተ!
"እንጨት" ፈያታዊን ወደ ገነት ሰደደ!
"እንጨት" አለምን ቀደሰ!
"እንጨት" ድንግልንና ዮሐንስን አማማለ!
"እንጨት" አዳምን ወደ ቀድሞ ክብሩ መለስው!
"እንጨት" ለአንካሶች ምርኩዛቸው ነው!
"እንጨት" ለእውራን ብርሃናቸው ነው!
"እንጨት" ለለምጻሞች መንጺያቸው ነው!
"እንጨት" ለተራቡት ምግባቸው ነው!
"እንጨት" ለነብያት ትንቢታቸው ነው!
"እንጨት" ለሐዋርያት ስብከታቸው ነው!
"እንጨት" ለሰማዕታት ሞገሳቸው ነው!
"እንጨት" ለክርስቲያኖች ሰላም ነው!
ስለዚህም "እንጨት" ፍቅር፡ ክብር፡ ስግደት ይገባዋል!!❤
አርጋኖን ተበልቶ ይጸለያል?
የአርጋኖን ጸሎት ተጀምሮ ሲቋረጥ ሰይጣን ይመታናል?
አርጋኖን ከተጀመረ አይቋረጥም?
ፀሎቱ በአጋንንት ላይ ያለው የበላይነት እና በአጋንንት ዘንድ ያለው መፈራት?
የፀሎቱ ጠቀሜታ ምንድን ነው?
በቀሲስ መ/ር ሄኖክ ወ/ማርያም
ሼር በማድረግ ላላወቁት አሳውቁ፣ለጥያቄያቸው መልስ ይሁኑ!
ተወዳጆች ሆይ ከፋሲካ በኃላ ባለው በዓለ ሃምሳ ብዙዎቻችን በጸሎት ሕይወታችን የምንዘናጋባት፣በጸሎት እንደ አጽዋማት ወቅት የማንበረታበት፣ጸሎታችንም ወጥ የማይሆንበት እና መቋረጥ የበዛበት ወይም የሚታጎልበት ወቅት ነው፡፡ ይህም የሚሆነው በፍስክ ወቅት የምንበላቸው ምግቦች ለሰውነት ከበድ የሚሉ ስለሆነ ጸሎታችንን ያዘናጉታል፡፡ እንዲሁም ጸሎትን እንደ ውዴታ እንጂ እንደ ግዴታ የማየት እና የመተግበር ልምዱ ስለሌለን ነው፡፡ ሌላው ድካማችንን፣ስንፍናችንን ተገን እያደረገ በየምክንያት ወደ ሕይወታችን ገባ ወጣ የሚለው ሰይጣን የሚያመጣብን ፈተና ነው፡፡ ያም ሆነ ይህ በዚህ ርዕስ ለብዙዎቻችን ጥያቄ የሚሆነውን ስለ አጋርኖን ጸሎት የማያዳግም ምላሽ ለመስጠት ነው፡፡
ወዳጆቼ ስለ አርጋኖን ጸሎት ጥያቄዎች ከመመለሳችን በፊት እስኪ ትንሽ ስለ ጸሎቱ ደራሲ ዘርዘር አደርገን እንይ፡፡ ምክንያቱም ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ ‹‹የደራሲውን መጽሐፍ ከማወቅህ በፊት ስለ ደራሲው ማንነት እወቅ›› ስለሚል ነው፡፡
ይህ ታላቅ የእመቤታችን የምስጋና ጸሎት የተደረሰው በኢትዮጲያዊው ቄርሎስ በአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ነው፡፡ አባታችን አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ጥቅምት 3 ቀን በ1357 ዓ.ም ተጸንሰው በዚያው ዓመት ሐምሌ 7 ቀን በእለተ ማክሰኞ ተወለዱ፡፡ ከመወለዳቸው አስቀድሞ ለእናት አባታቸው በወርኅ መስከረም ቅዱስ ዑራኤል በሰማእታት አለቃ በቅዱስ ጊዮርጊስ ስም የተሰየመ ልጅ እንደሚወልዱ ነግሯቸዋል፡፡
አባ ጊዮርጊስ እናትና አባታቸው ፈሪሃ እግዚአብሔርን እያስተማዋቸው በእውቀት እና በጥበብ አሳደጓቸው፡፡ ለአቅመ ትምህርት ሲደርሱ በጊዘው በኢትዮጲያ ታላቅ የትምህርት ማዕከል በነበረው በሐይቅ ደብረ ነጎድጓድ ገዳም ገብተው ከታላቁ ሊቅ ዐቃቤ ሰዓት አባ ሠረቀ ብርሃን ጋር እንዲማሩ ሰጥዋቸው፡፡
አባ ጊዮርጊስ ከማኅፀን የተመረጡና ሀብተ መንፈስ ቅዱስ ያደረባቸው ቢሆኑም ገዳሙንና አባቶችን በእውቀት ሳይሆን በጉልበት ነበር የሚያገለግሉት፡፡ ግን ሌሊት ሌሊት ከእመቤታችን ከድንግል ማርያም ስዕል ሥር አብዝተው በመስገድ ፈጣሪያቸውን ይማጸኑ ነበር፡፡ አባ ጊዮርጊስ ገዳሙንና አባቶችን በጉልበት ቢያገለግሉም ከአባ ሠረቀ ብርሃም የሚሰጣቸው ትምህርት ሊገባቸው አልቻለም፡፡ ትምህርት እንዳልገባቸው የተረዱት አባ ሠረቀ ብርሃን እንዳይወቀሱ የአባ ጊዮርጊስን አባት አስጠርተው ‹‹ይህ ልጅ ትምህርት ሊገባው አልቻለም ስለዚህ ሌላ ሙያ አስተምረው›› ብለው ለአባቱ ሰጡት፡፡ አባታቸውም መልሰው ‹‹ልጁን የወለድኩት በስዕለት ነውና ከዚህ ገዳምን እያገለገለና አባቶችን እየረዳ ይኑር›› ብለው እዛው ሐይቅ እስጢፋኖስ ገዳም ትተዋቸው ሄዱ፡፡
በዚያም ትምህርታቸውን እየተማሩ በቀን ዘጠኝ ዘጠኝ ቅርጫት እህል እየፈጩ ማገልገል ቢጀምሩም ቅን አገልግሎት የሚያበረክቱላቸው መነኮሳት ከማመስገን ይልቅ ‹‹ትምህርት የማይገባው›› እያሉ ይዘልፋቸውና ይሰድቧቸው ጀመር፡፡ አባ ጊዮርጊስም ጸጋ እግዚአብሔር ያደረባቸው ደግ ሰው ናቸውና እንደ ሰደቡኝ ልሳደብ፣እንደ ናቁኝ ልናቅ ሳይሉ የተለመደ አገልግሎታቸውን ሳያቋርጡ ከእመቤታችን ሥዕል ስር በግምባራቸው ተደፍተው ‹‹እመቤቴ ሆይ መነኮሳቱ በእኔ ላይ እየፈጸሙብኝ ያለውን ነቀፋ እና ዘለፋ ተመልክተሸ ትምህርቴን እንዲገልጽልኝ ከልጅሽ ከጌታችን ከመድኃኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ዘንድ አማልጂኝ›› እያሉ ሲያለቅሱና ሲማፀኑ፤እመቤታችን በገሃድ ተገልጻ ‹‹አይዞህ አታልቅስ ትምህርት ተከልክሎብህ ሳይሆን የምትጠቀምበት ጊዜው እስኪደርስ ነበር፤አሁን ግን ጊዜው ደርሷልና እስከ ሰባት ቀን በዚሁ በሱባዔው እንዳለህ ሆነህ ጠብቀኝ›› ብላቸው ተሰወረች፡፡
አባ ጊዮርጊስም በሱባዔ እንዳሉ በሰባተኛው ቀን እንደተለመደው በሥዕለ ማርያም ሥር ተደፍተው እያለቀሱ ሳሉ እመቤታችን ሊቀ መላእክት ቅዱስ ዑራኤልን አስከትላና ጽዋዓ እሳት አስይዛ መጥታ የሕይወት ጽዋዓ አጠጣቻቸው፡፡ አባ ጊዮርጊስም የሕይወት ጽዋዕን ከጠጡ በኃላ የሰማይና የምድር ምስጢር ሁሉ ተገለጠላቸው፡፡ በእግዚአብሔር ቅዱስ መንፈስ ተመልተው እግዚአብሔር በመዓልትና በሌሊት በዜማ የሚመሰገንባቸውን፣እመቤታችን በጸሎት የምትመሰገንበትንና ሌሎችንም የምስጋናና የጸሎት ቅዱሳት መጻሕፍትን ደርሰዋል፡፡
አስደናቂ ገድላቸው እንደሚነግረን የአባ ጊዮርጊስ የድርሰት ሥራዎች የሆኑት በተለይም የታወቁት አሥራ ሰባት ናቸው፡፡ እነሱም መጽሐፈ ብርሃን የመዓልትና የሌሊት ሰዓታት፣አርጋኖን፣ኆኅተ ብረሃን፣ውዳሴ መስቀል፣ዕንዚራ ስብሐት፣ሕይወተ ማርያም፣ተአምኆተ ብርሃን/ተአምኆተ ቅዱሳን/ ፣ውዳሴ ስብሐት፣ ውዳሴ ሐዋርያት፣ፍካሬ ሃይማኖት፣ጸሎተ ፈትቶ/በቅዳሴ ጊዜ የሚጸለይ/፣ መጽሐፈ ምስጢር፣መዓዛ ቅዳሴ፣ ቅዳሴ እግዚእ ካልእ፣ውዳሴ ማርያም ካልእ፣ጸሎት ዘቤት ውስተ ቤት እና መዝሙረ ድንግል ናቸው፡፡ ግን በገድሉ ውስጥ በቀጥታ ካልተጠቀሱት መካከል መልክአ ውዳሴ፣መልክአ ሥዕል፣ይዌድስዋ ማርያም/የሰዓታት ክፍል/ እና ሌሎችም ይገኙበታል፡፡ ወዳጆቼ ከእነዚህ የአባ ጊዮርጊስ የመንፈስ ቅዱስ ድርሰቶች ውስጥ ለርእሳችን የመረጥነውን አርጋኖን ስለተባለው የእመቤታችን ምስጋና እንመልከት፡፡
ነገረ አርጋኖን ፦
አባታችን አባ ጊዮርጊስ አንድ ቀን የድረሰት መጽሐፍ ሊጽፍ ወደደና ቀኑን ሙሉ ሲጽፋ ዋለ፡፡ በማግስቱም በዚያው ድረሰት ላይ ሊጨምር በወደደ ጊዜ የጻፈበት ጥራዝ ቀለሙ ጠፍቶ ነጭ ሆኖ አገኘው፡፡ በዚህም የተሰረቀ መስሎት በልቡ አዘነ፡፡ ጥራዞቹንም በቆጠራቸው ጊዜ ከቁጥር ሳይጎሉ አገኛቸው፡፡ ለሁለተኛ ጊዜ በድጋሜ ጻፈ፡፡ በማግስቱም እንደ መጀመሪያው ነጭ ሆኖ አገኘው፡፡ እስከ ሦስትና አራት ቀን ደጋግሞ ጻፈ ግን እንደ መጀመሪያው ሆነበት፡፡
ከዚህ በኃላ ወደ እመቤታችን ይማልል፣ይጸልይ ጀመረ፡፡ እመቤታችንንም ‹‹ይህ የሆነው በኃጢአቴ ነውን? ወይስ አይደለም? እባክሽ ግለጪልኝ›› አላት፡፡ አንድ ቀን አባ ጊዮርጊስ በሌሊት እኩሌታ ወደ ቤተ ክርስትያን ሲሄድ እመቤታችን በድንገት በማይነገር ክብር ተገለጸችላቸው፡፡ ከእሷም ጋር የቅዱሳን ማኅበር ሁሉ ነበሩ፡፡ እመቤታችንም በእጇ ከጸሐይ ከጨረቃ የበለጠ የሚያበራ መጽሐፍ ይዛ ነበር፤አባ ጊዮርጊስም እመቤታችንን ባየ ጊዜ ወደ መሬት ወደቀ፣እንደ በድንም ሆነ፡፡ እመቤታችንም አነሳችውና ‹‹ሳትጠይቀኝ መጽሐፌን ትጽፍ ዘንድ ለምን ደፈርህ›› አለችው፡፡ መልሳም ‹‹እኔ ወድጄህ ከእናትህ ማኅፀን መርጨህ ለጴጥሮስ፣ለጳውሎስና ለዮሐንስ አደራ ሰጥቼህ የለምን›› አለችው፡፡
አባ ጊዮርጊስም ‹‹እመቤቴ ሆይ ይቅር በይኝ፤ደስ የሚያሰኝሽ መስሎኝ ነውና ይህን ባለማወቅ ሠርቻለሁና›› አሏት፡፡ እመቤታችንም ‹‹ወዳጄ ሆይ ይቅር ብየሃለሁ፣ልትጽፍ የወደድከው መጽሐፍም እነሆ በእጄ አለ፤ከአሁን በኃላ የተወደደ ልጄ በአንደበትህ ሊገልጸው ወዷልና፡፡ ነገር ግን ከአርያም ከሰማይ ኅይልን እስክትላበስ ድረስ አትቸኩል›› ብላ ተሰወረችው፡፡
ያን ጊዜ የአባ ጊዮርጊስ ልቡ እንደ ፀሐይ በራ፣የመለኮትም ባሕር በኅሊናው አበራ፡፡ በመንፈስ ቅዱስም መስታወት የተሰወረውን ሁሉ አየ፡፡ እግዚአብሔርን በሚወድ በንጉሥ ዳዊት ዘመን አርጋኖንን ደረሰ፡፡ መጽሐፉንም በሦስት ስሞች ጠራው፡፡ እነሱም አርጋኖነ

ውዳሴ፣መሰንቆ መዝሙር፣ዕንዚራ ስብሐት ናቸው፡፡ እመቤታችንም አባ ጊዮርጊስ ስለ ደረሰው ስለ አርጋኖን የጸሎትና የምስጋና መጽሐፍ ክብሩን ስትገልጽለት አባ ጊዮርጊስም ‹‹ከደረስኳቸውና ከተናገርኳቸው ድርሳናት ሁሉ አርጋኖን ውዳሴ ይጣፍጣል፣ይበልጣል›› አለ፡፡ ተወዳጆች ሆይ ልብ በሉ ይህ ታላቅ የእመቤታችን የጸሎት እና የምስጋና መጽሐፍ ከሰማይ የተገለጠ እና ለአባ ጊዮርጊስ ከእመቤታችን እጅ የተሰጠ መጽሐፍ ነው፡፡
የአርጋኖን መጽሐፍ ይዘት በአጭሩ
የአርጋኖን መጽሐፍ ይዘት በሁለት ከፍለን ማየት እንችላለን፡፡ የመጀመርያው መጽሐፍ ስለ እመቤታችን ንጽህና፣ቅድስና፣ፍጹም ድንግልና አብዝቶና አምልቶ ያናገራል፡፡ የእመቤታችንን ወላዲተ አምላክነትን ይመሰክራል፡፡ እንዲሁም ስለ ክብራ በተለያዩ የከበሩ ማዕድናት እየመሰለ ያደንቃል፡፡ ሌላው ከዘፍጥረት እስከ ራዕይ ያለውን ምስጢራት በእሷ ይገልጻል፡፡
ሁለተኛው መጽሐፉ የእመቤታችን ምስጋና ቢሆን ስለ ተወዳጅ ልጅዋ በሰፊው ያትታል፡፡ በተለይ በእሷ ስም የጌታን ሕማም ስቃይ እያሳሰበ፤ጌታንም እያመሰገነ፣ሰማያዊ ክብሩም ይገጽልናል፡፡ እሷን ብቻ ሳይሆን ልጇንም አምልቶ እና አስፍቶ ያመሰግናል፡፡ ስለ አርጋኖን ይህንን ካልን ወደ ጥያቄያችን እንመለስ፡፡
አርጋኖን ተበልቶ ይጸለያል?
አርጋኖን ሳንበላም በልተንም የምንጸልየው ጸሎት ነው፡፡ ምክንያቱም ጸሎቱ ምስጋና ስለሆነ ነው፡፡ ምስጋና ደግሞ ከሆድ ሳይሆን ከልብ የሚገናኝ ነው፡፡ እመቤታችንን በአርጋኖን ጸሎት ማመስገን የፈለገ ሰው የበረታ ሌሊት ወይም ጠዋት መጸለይ፡፡ ካልሆነልንና ካልተመቸን በየትኛውም ሰዓት መጸለይ እንችላለን፡፡ ለምሳሌ በሥራና በተለያየ ምክንያት አርጋኖንን ሌሊት አልያም ጠዋት መጸለይ ያቃተው ሰው ማታ በጸሎት ሰዓቱ አርጋኖንን መጸለይ ይችላል፡፡
አርጋኖን ከሌሎቹ ጸሎቶት አንዱ የሚለይበት ጸሎቱ ረጅም በመሆኑ ነው፡፡ ስለዚህ አጋንንት የጸሎቱን ርዝመት እንደ ስንፍና ምክንያት ተጠቅሞ እንዳንጸልይ እንዳያረገን በላንም አልበላን በሚመቸን ሰዓት መጸለይ፡፡ በተለይ ሌሊት ወይም ጠዋት መጸለይ ያልቻልን ሰዎች ማታ ብንጸልይ ይመረጣል፡፡ በእመቤታችን ተባርከን ስለምንተኛ ቅዠቱም፣ፈተናውም ይርቅልናል፡፡ ሰናይ ሕልምም ያሳየናል፡፡
የአርጋኖን ጸሎት ተጀምሮ ሲቋረጥ ሰይጣን ይመታናል?
ወዳጆቼ እንኳን አርጋኖንን የሚያክል ታላቅ ጸሎት ቀርቶ ማንኛውም ጸሎት ባይቋረጥ ይመረጣል፡፡ ምክንያቱም ከላይ እንዳልኩት ለእኛ ለኦርቶዶክሶች ጸሎት ውዴታችን ሳይሆን ግዴታችን ነውና፡፡ ስለዚህ ጸሎት ማቋረጥ ለመንፈሳዊ ሕይወት መዳከም እና ለተለያዩ ፈተናዎች ይዳርገናል፡፡ ጌታችንም እያቋረጣችሁ ሳይሆን ተግታችሁ ጸልዩ ነው ያለን፡፡ ለሥጋችን በቀን ሁለት ሦስቴ በቋሚነት ምግብ እንደምንበላ ሁሉ ጸሎትም ነፍስ ምግብ ነውና ቢያስ በሃያ አራት ሰዓት ሁለቴ ጠዋት እና ማታ ልንጸልይ ይገባል ያስገድዳል፡፡
አርጋኖን ከጸሎት ባሻገር ምስጋና ስለሆነ ጸልየን ብናቋርጥ ሰይጣን አይመታንም፡፡ ከተቋረጠ ሰይጣን ይመታል የሚሉት አንድም ቀን ጸሎቱን ጸልየው የማይውቁት ሰዎች ናቸው፡፡ በመሠረቱ አንድ ሰው በለቅሶ፣በሠርግ፣በሕመምና በተለያዩ ማህበራዊ ገጠመኞች እና ችግሮች ጸሎትን የሚያቋርኝበት እና ጸሎቱም የሚታጎልበት ጊዜ ይኖረዋል፡፡ ስለዚህ በተቻለን አቅም ሳናቋርጥ ብንጸልይ እመቤታችን ትለመነናለች፣ችግራችንን ትፈታልናለች፣የአጋንንትን ፈተና ታስታግስልናለች፣ታርቅልናለች፡፡ እዚህ ላይ ልብ ልንለው የሚገባን ጸሎትን ለምሳሌ አርጋኖንን ስንጸልይ ሰይጣን የሚርቀን ስናቋርጥ የሚመታን ከሆነ የሚጠብቀን እግዚአብሔር ሳይሆን ጸሎታችን ነው ያሰኛል፡፡ ይህ ደግሞ ልክ አይደለም፡፡ እግዚአብሔር ስንጸልይም ሳንጸልይም ይጠብቀናል፡፡ ደግሞስ እስከ ዛሬ እራሳችንን የጠበቅነው በየትኛው ጸሎታችን ነው? ቂም በቋጠረው፣ይቅርታን እንቢኝ ባለው፣ኃጢአት በተጫነው፣ቅድስና በሌለው ማንነታችንና ጸሎታችን ነው የምንጠብቀው? ወይስ በቸርነቱ እና በጠባቂነቱ?
ስለዚህ አርጋኖንን ስንጸልይ ሰይጣንን የሚያርቅ ስናቋርጠው ሰይጣንን የሚያቀርብ አይደለም፡፡ ወዳጆቼ እስኪ አንድ ቀን እናመስግናት እና የሚሆነውን እንይ፡፡ ሰይጣን እናታችንን እንዳናመሰግናት፣አርጋኖን ጸልየን ነፍሳችንን የእመቤታችንን ፍቅር እንዳንመግባት የሚፈጥረው ሰይጣናዊ አሉባልታ እንጂ እውነታ የለውም፡፡ ሌላው መረሳት የሌለበት እመቤታችን ከምስጋናዎችዋ ሁሉ እጅጉን የምትወደው አርጋኖንን ነው፡፡ አባ ጊዮርጊስም ከደረስዋቸው ድርሰቶች ሁሉ አብልጠው የሚወዱት አርጋኖንን ነው፡፡
አርጋኖን ስንጸልይ ይረዝምብናል ለምንል እንዲህ እንጸልይ
ተወዳጆች ሆይ አርጋኖን ከሌሎቹ ጸሎቶች ለመጸለይ ምቹ የሚያደርገው በምዕራፍ በምዕራፍ መከፋፈሉ ነው፡፡ በምዕራፍ ሲከፋፈል የሐሳብ ፍሰት መቋረጥ እና መፋለስ የለውም፡፡ አንዱን ምዕራፍ ጨርሶ ወደ ሌላኛው ምዕራፍ ስንገባ በአዲስ ምስጋና ነው የሚጀምረው፡፡ ይህ ደግሞ ጊዜ ለሌለንና ጸሎቱ ረጅም ነው እያልን ላለመጸለይ ምክንያት ለምናቀርብ ሰዎች የቻልነውን ያህል አመስግነን ምዕራፉን ስንጨርስ በአባታችን ሆይ ዘግተን እመቤታችንን መማፀን እንችላለን፡፡ ልክ እንደ ዳዊት አንድም ሁለት ሦስትም ምዕራፍ መጸለይ እንችላለን፡፡
የዛሬ አሥር ዓመት አንድ የእመቤታችን ወዳጅ ሱባዔ ትገባና እመቤታችን አርጋኖን ብትጸልይ ብዙ በረከት እንደምታገኝ፣ብዙ ችግሯ እንደሚፈታና አርጋኖንን ብትጸልይ እመቤታችን አብልጣ እንደምትወዳት ትነግራታለች፡፡ ልጅትዋም ‹‹ጸሎቱ ረጅም ነው እንዴት አድርጌ ነው የምጸልየው?›› ስትላት እመቤታችንም የቻለችውን ያህል ጸልያ ምዕራፉ ላይ ማቆም እንደምትችል ነግራት እስከ ዛሬ ስትችል ሙሉውን ያልቻለች ቀን በምዕራፉ ላይ እያበቃች ትጸልያለች፡፡ ስለዚህ የእኛን ችግር ከእኛ የበለጠ የምታውቀው እመቤታችን ስለሆነች እንዳቅማችን በመጸለይ ከእመቤታችን ጸጋና በረከትን እናትርፍበት፡፡
አርጋኖን ከተጀመረ አይቋረጥም?
ከላይ እንዳየነው ማንኛውም ጸሎት ባይቋረጥ ይመከራል፡፡ ግን አርጋኖን መጸለይ ከተጀመረ አይቋረጥም የሚለው ሰይጣናዊ አሉባልታ ብዙዎችን ጸሎቱን እንዲወዱት ሳይሆን እንዲፈሩት አድርጓቸዋል፡፡ ሰይጣን ጸሎት የምናቋርጥበትን መቶ ምክንያቶችን እየደረደረ፣በጎን ደግሞ በሰዎች ላይ እያደረ ‹‹አርጋኖን ከተጀመረ አይቋረጥም›› እያስባለ ጸሎቱን እንደ ጸሎት እንድንወደው ሳይሆን እንድንፈራው አድርጎናል፡፡ ወዳጆቼ ከቻላችሁ በቋሚነት ካልቻላችሁ ባገኛችሁት አጋጣሚና ጊዜ እናትችሁን በአርጋኖን አመስግኗት ጸልዩበት እንጂ የሰይጣንን አሉባልታ እየሰማችሁ ከጸሎቱ በረከት ሳትሳተፉ እንዳትቀሩ፡፡ እኛ ጸሎቱን ከጀመርን እመቤታችን ስለምታበረታን ጸሎቱን መፍራት ሳይሆን መጸለይ ይገባል፡፡
ጸሎቱ በአጋንንት ላይ ያለው የበላይነት እና በአጋንንት ዘንድ ያለው መፈራት
ወዳጆቼ ለአጋንንት ሁሉም ጸሎቶች ቢያቃጥሉትም አርጋኖን ግን ለአጋንንት እሳት ከመሆኑም ባሻገር ጸሎቱ እጅጉን ይከብደዋል፡፡ አጋንንት ከማይቋቋመው ጸሎቶች አንዱ አርጋኖን ነው፡፡ ጸሎቱ በእመቤታችን ዘንድ እጅጉን ተወዳጅ ስለሆነ በአጋንንት ዘንድ ደግሞ ይጠላል፡፡ ስለዚህ አርጋኖንን ስትጸልዩ ጸሎቱ በራሱ ምልክት ያሳያቹኃል፡፡ በተለይ በውስጣችን አንዳች የሚፈትነን መንፈስ ካለ ገና ጸሎቱን ሳንጀምር እንጨናነቃለን፣ያስጠላናል፣ሰውነታንን ይከብደናል፡፡ ስንጀምረው ያስፋሽገናል፣ጸሎቱ አልገፋ ይለናል፣ተራራ መስሎ ይታየናል፡፡ እየጸለይነው ሰውነታን ይዝላል፣እሳት ይለቅብናል፣ያልበናል፣ወገባችን እግራችን ይብረከረካል ይንቀጠቀጣል፡፡ የምናውቀው አማረኛ

እየጠፋን አልነበብ ይለናል፣እንተባተባለን፡፡ መንጠራራት እና ጩኸ ጩኸ የሚል ስሜት ይሰማናል፡፡
ይህን ጸሎት በርትተን ከጸለይን የሚፈትነን መንፈስ ይያዝልናል፡፡ አባ ጊዮርጊስም አርጋኖንን ሰይጣን እንዴት እንደሚጠላው ሲገልጽ ‹‹ሰይፍ ነው አንገቱን ይቆርጠዋል፣መራጃ ነው ወገቡን ይሰብረዋል፣ሰይጣን ይህንን የምስጋና ጸሎት በሰማ ጊዜ ዓይኑ ይፈጣል ጥርሱ ይገጣል›› በማለት ገልጾታል፡፡ ስለዚህ አጋንንት ከሚጠላቸው እና ከሚረታባቸው ጸሎቶች ውስጥ አንዱ አርጋኖን ስለሆነ በርትተን እንጸልይ፡፡
የጸሎቱ ጠቀሜታ
ተወዳጆች ሆይ የአርጋኖን ጸሎት ጠቀሜታ ይህ ነው ተብሎ ለመግለጽ ቃላት ቢያጥርም ጸሎቱ በእመቤታችን ዘንድ ከፍተኛ መወድድንና ባለሟልነትን ያሰጣል፡፡ የእመቤታችን ጸጋና በረከት እንዲያድርብን ያደርጋል፡፡ የሚፈታተነንን አጋንንት ልምሾ ያደርጋል፡፡ ስለ እመቤታችን ቅድስናና ክብር በብዙ ያሳውቃል፡፡ በተለይ ብሉይ ኪዳንንና ሐዲስ ኪዳንን በሰፊው ስለሚዳስስ መንፈሳዊ እውቀታችንን ከፍ ያደርጋል፡፡ እንዲሁም በሱባዔ ወቅት ለምሳሌ በገና፣በዓብይና በፍልሰታ አጽዋማት ወቅት በርትተን ብንጸልየው ምስጢር ይገልጻል፣ጥያቄያችን እንዲመለስ ያደርጋል፣ችግራችንን እንዲፈታ ያግዛል፡፡ የጸሎቱ ኃይል አጋንንትን ይቀጠቅጣል እንደ ሰም ያቀልጣል፡፡ በዚህም ድል መንሳትን ያጎናጽፈናል፡፡ ፀሎቱ ለአጋንንት ሬት ለእኛ ወተት በመሆኑ የእመቤታችንን ፍቅር ያበዛልናል።
በመጨረሻ የአርጋኖን ጸሎት ቡራኬ ‹‹ይህንን መጽሐፍ የሚያነብ ሁሉ አንደበቱ በመንፈስ ቅዱስ ጨውነት የጣፈጠ ከማር ወለላና ከሱካር ምንጭ ይልቅ የጣፈጠ ይሁን፡፡ በዚህ ጸሎት የሚጸልይ ሁሉ የሕይወት እሳትን በሚዳስስ እጅሽ በረከት የተባረከ ይሁን፡፡ የመንፈስ ቅዱስ መዓዛም በተዋሃደው አንደበትሽ የተመረቀ ይሁን፡፡ ዓለምን በያዙ በሥላሴ እጅ የተባረከ ይሁን›› /አርጋኖን ዘሰኑይ ገጽ 11/
ተወዳጆች ሆይ ‹‹በዓለ ሃምሳ፣እጅ ታጥቦ ወደ ምሳ›› የሚባለውን የአጅሬን ተረት ተወት እድርገን እናታችንን በአርጋኖን እናመስግናት፣ጸልየን ለጥያቄያችን መልስ እናግኝባት፡፡
ሚያዝያ 27/8/11 ዓ.ም
አዲስ አበባ

የግእዝ ቁጥሮች በአኀዝና በፊደል
=====================
0. - አልቦ
1. ፩ አሐዱ
2. ፪ ክልኤቱ
3. ፫ ሠለስቱ
4. ፬ አርባዕቱ
5. ፭ ሐምስቱ
6. ፮ ስድስቱ
7. ፯ ስብዓቱ
8. ፰ ስመንቱ
9. ፱ ተሰዓቱ
10. ፲ አሠርቱ
11. ፲፩ አሠርቱ ወአሐዱ
12. ፲፪ አሠርቱ ወክልኤቱ
13. ፲፫ አሠርቱ ወሠለስቱ
14. ፲፬ አሠርቱ ወአርባዕቱ
15. ፲፭ አሠርቱ ወሐምስቱ
16. ፲፮ አሠርቱ ወስድስቱ
17. ፲፯ አሠርቱ ወሰብዓቱ
18. ፲፰ አሠርቱ ወስመንቱ
19. ፲፱ አሠርቱ ወተሰዓቱ
20. ፳ እስራ
21. ፳፩ እስራ ወአሐዱ
22. ፳፪ እስራ ወክልኤቱ
23. ፳፫ እስራ ወሠለስቱ
24. ፳፬ እስራ ወአርባዕቱ
25. ፳፭ እስራ ወሐምስቱ
26. ፳፮ እስራ ወስድስቱ
27. ፳፯ እስራ ወሰብዓቱ
28. ፳፰ እስራ ወሰመንቱ
29. ፳፱ እስራ ወተሰዓቱ
30. ፴ ሠላሳ
31. ፴፩ ሠላሳ ወአሐዱ
32. ፴፪ ሠላሳ ወክልኤቱ
33. ፴፫ ሠላሳ ወሠለስቱ
34. ፴፬ ሠላሳ ወአርባዕቱ
35. ፴፭ ሠላሳ ወሐምስቱ
36. ፴፮ ሠላሳ ወስድስቱ
37. ፴፯ ሠላሳ ወሰብዓቱ
38. ፴፰ ሠላሳ ወሰመንቱ
39. ፴፱ ሠላሳ ወተሰዓቱ
40. ፵ አርብዓ
50. ፶ ሃምሳ
60. ፷ ስድሳ
70. ፸ ሰብዓ
80. ፹ ሰማንያ
90. ፺ ተሰዓ
100. ፻ ምዕት
101. ፻፩ ምዕት ወአሐዱ
102. ፻፪ ምዕት ወክልኤቱ
103. ፻፫ ምዕት ወሠለስቱ
104. ፻፬ ምዕት ወአርባዕቱ
105. ፻፭ መዕት ወሐምስቱ
106. ፻፮ ምዕት ወስድስቱ
107. ፻፯ ምዕት ወሰብዓቱ
108. ፻፰ ምዕት ወስመንቱ
109. ፻፱ ምዕት ወተሰዓቱ
110. ፻፲ ምዕት ወአሠርቱ
111. ፻፲ወ፩ ምዕት አሠርቱ ወአሐዱ
112. ፻፲ወ፪ ምዕት አሠርቱ ወክልኤቱ
113. ፻፲ወ፫ ምዕት አሠርቱ ወሠለስቱ
114. ፻፲ወ፬ ምዕት አሠርቱ ወአርባዕቱ
115. ፻፲ወ፭ ምዕት አሠርቱ ወሐምስቱ
116. ፻፲ወ፮ ምዕት አሠርቱ ወስድስቱ
117. ፻፲ወ፯ ምዕት አሠርቱ ወሰብዓቱ
118. ፻፲ወ፰ ምዕት አሠርቱ ወስመንቱ
119. ፻፲ወ፱ ምዕት አሠርቱ ወተሰዓቱ
120. ፻፳ ምዕት ወእስራ
130. ፻፴ ምዕት ወሠላሳ
140. ፻፵ ምዕት ወአርብዓ
150. ፻፶ ምዕት ወሃምሳ
160. ፻፷ ምዕት ወስድሳ
170. ፻፸ ምዕት ወሰብዓ
180. ፻፹ ምዕት ወሰማንያ
190. ፻፺ ምዕት ወተሰዓ
200. ፪፻ ክልኤቱ ምዕት
201. ፪፻ወ፩ ክልኤቱ ምዕት ወአሐዱ
202. ፪፻ወ፪ ክልኤቱ ምዕት ወክልኤቱ
203. ፪፻ወ፫ ክልኤቱ ምዕት ወሠለስቱ
204. ፪፻ወ፬ ክልኤቱ ምዕት ወአርባዕቱ
205. ፪፻ወ፭ ክልኤቱ ምዕት ወሐምስቱ
206. ፪፻ወ፮ ክልኤቱ ምዕት ወስድስቱ
207. ፪፻ወ፯ ክልኤቱ ምዕት ወሰብዓቱ
208. ፪፻ወ፰ ክለኤቱ ምዕት ወስመንቱ
209. ፪፻ወ፱ ክልኤቱ ምዕት ወተሰዓቱ
210. ፪፻ወ፲ ክልኤቱ ምዕት ወአሠርቱ
211. ፪፻፲ወ፩ ክልኤቱ ምዕት አሠርቱ ወአሐዱ
212. ፪፻፲ወ፪ ክልኤቱ ምዕት አሠርቱ ወክልኤቱ
213. ፪፻፲ወ፫ ክልኤቱ ምዕት አሠርቱ ወሠልስቱ
214. ፪፻፲ወ፬ ክልኤቱ ምዕት አሠርቱ ወአርባቱ
215. ፪፻፲ወ፭ ክልኤቱ ምዕት አሠርቱ ወሐምስቱ
216. ፪፻፲ወ፮ ክልኤቱ ምዕት አሠርቱ ወስድስቱ
217. ፪፻፲ወ፯ ክልኤቱ ምዕት አሠርቱ ወሰብዓቱ
218. ፪፻፲ወ፰ ክልኤቱ ምዕት አሠርቱ ወሰመንቱ
219. ፪፻፲ወ፱ ክልኤቱ ምዕት አሠርቱ ወተሰዓቱ
220. ፪፻፳ ክልኤቱ ምዕት ወእስራ
230. ፪፻፴ ክልኤቱ ምሪዕት ወሠላሳ
240. ፪፻፵ ክልኤቱ ምዕት ወአርብዓ
250. ፪፻፶ ክልኤቱ ምዕት ወሃምሳ
260. ፪፻፷ ክልኤቱ ምዕት ወስድሳ
270. ፪፻፸ ክልኤቱ ምዕት ወሰብዓ
280. ፪፻፹ ክልኤቱ ምዕት ወሰማንያ
290. ፪፻፺ ክልኤቱ ምዕት ወተሰዓ
300. ፫፻ ሠለስቱ ምዕት
400. ፬፻ አርባዕቱ ምዕት
500. ፭፻ ሐምስቱ ምዕት
600. ፮፻ ስድስቱ ምዕት
700. ፯፻ ስብዓቱ ምዕት
800. ፰፻ ስመንቱ ምዕት
900. ፱፻ ተሰዓቱ ምዕት
1000. ፲፻ አሠርቱ ምዕት
2000. ፳፻ እስራ ምዕት
30
=====================
0. - አልቦ
1. ፩ አሐዱ
2. ፪ ክልኤቱ
3. ፫ ሠለስቱ
4. ፬ አርባዕቱ
5. ፭ ሐምስቱ
6. ፮ ስድስቱ
7. ፯ ስብዓቱ
8. ፰ ስመንቱ
9. ፱ ተሰዓቱ
10. ፲ አሠርቱ
11. ፲፩ አሠርቱ ወአሐዱ
12. ፲፪ አሠርቱ ወክልኤቱ
13. ፲፫ አሠርቱ ወሠለስቱ
14. ፲፬ አሠርቱ ወአርባዕቱ
15. ፲፭ አሠርቱ ወሐምስቱ
16. ፲፮ አሠርቱ ወስድስቱ
17. ፲፯ አሠርቱ ወሰብዓቱ
18. ፲፰ አሠርቱ ወስመንቱ
19. ፲፱ አሠርቱ ወተሰዓቱ
20. ፳ እስራ
21. ፳፩ እስራ ወአሐዱ
22. ፳፪ እስራ ወክልኤቱ
23. ፳፫ እስራ ወሠለስቱ
24. ፳፬ እስራ ወአርባዕቱ
25. ፳፭ እስራ ወሐምስቱ
26. ፳፮ እስራ ወስድስቱ
27. ፳፯ እስራ ወሰብዓቱ
28. ፳፰ እስራ ወሰመንቱ
29. ፳፱ እስራ ወተሰዓቱ
30. ፴ ሠላሳ
31. ፴፩ ሠላሳ ወአሐዱ
32. ፴፪ ሠላሳ ወክልኤቱ
33. ፴፫ ሠላሳ ወሠለስቱ
34. ፴፬ ሠላሳ ወአርባዕቱ
35. ፴፭ ሠላሳ ወሐምስቱ
36. ፴፮ ሠላሳ ወስድስቱ
37. ፴፯ ሠላሳ ወሰብዓቱ
38. ፴፰ ሠላሳ ወሰመንቱ
39. ፴፱ ሠላሳ ወተሰዓቱ
40. ፵ አርብዓ
50. ፶ ሃምሳ
60. ፷ ስድሳ
70. ፸ ሰብዓ
80. ፹ ሰማንያ
90. ፺ ተሰዓ
100. ፻ ምዕት
101. ፻፩ ምዕት ወአሐዱ
102. ፻፪ ምዕት ወክልኤቱ
103. ፻፫ ምዕት ወሠለስቱ
104. ፻፬ ምዕት ወአርባዕቱ
105. ፻፭ መዕት ወሐምስቱ
106. ፻፮ ምዕት ወስድስቱ
107. ፻፯ ምዕት ወሰብዓቱ
108. ፻፰ ምዕት ወስመንቱ
109. ፻፱ ምዕት ወተሰዓቱ
110. ፻፲ ምዕት ወአሠርቱ
111. ፻፲ወ፩ ምዕት አሠርቱ ወአሐዱ
112. ፻፲ወ፪ ምዕት አሠርቱ ወክልኤቱ
113. ፻፲ወ፫ ምዕት አሠርቱ ወሠለስቱ
114. ፻፲ወ፬ ምዕት አሠርቱ ወአርባዕቱ
115. ፻፲ወ፭ ምዕት አሠርቱ ወሐምስቱ
116. ፻፲ወ፮ ምዕት አሠርቱ ወስድስቱ
117. ፻፲ወ፯ ምዕት አሠርቱ ወሰብዓቱ
118. ፻፲ወ፰ ምዕት አሠርቱ ወስመንቱ
119. ፻፲ወ፱ ምዕት አሠርቱ ወተሰዓቱ
120. ፻፳ ምዕት ወእስራ
130. ፻፴ ምዕት ወሠላሳ
140. ፻፵ ምዕት ወአርብዓ
150. ፻፶ ምዕት ወሃምሳ
160. ፻፷ ምዕት ወስድሳ
170. ፻፸ ምዕት ወሰብዓ
180. ፻፹ ምዕት ወሰማንያ
190. ፻፺ ምዕት ወተሰዓ
200. ፪፻ ክልኤቱ ምዕት
201. ፪፻ወ፩ ክልኤቱ ምዕት ወአሐዱ
202. ፪፻ወ፪ ክልኤቱ ምዕት ወክልኤቱ
203. ፪፻ወ፫ ክልኤቱ ምዕት ወሠለስቱ
204. ፪፻ወ፬ ክልኤቱ ምዕት ወአርባዕቱ
205. ፪፻ወ፭ ክልኤቱ ምዕት ወሐምስቱ
206. ፪፻ወ፮ ክልኤቱ ምዕት ወስድስቱ
207. ፪፻ወ፯ ክልኤቱ ምዕት ወሰብዓቱ
208. ፪፻ወ፰ ክለኤቱ ምዕት ወስመንቱ
209. ፪፻ወ፱ ክልኤቱ ምዕት ወተሰዓቱ
210. ፪፻ወ፲ ክልኤቱ ምዕት ወአሠርቱ
211. ፪፻፲ወ፩ ክልኤቱ ምዕት አሠርቱ ወአሐዱ
212. ፪፻፲ወ፪ ክልኤቱ ምዕት አሠርቱ ወክልኤቱ
213. ፪፻፲ወ፫ ክልኤቱ ምዕት አሠርቱ ወሠልስቱ
214. ፪፻፲ወ፬ ክልኤቱ ምዕት አሠርቱ ወአርባቱ
215. ፪፻፲ወ፭ ክልኤቱ ምዕት አሠርቱ ወሐምስቱ
216. ፪፻፲ወ፮ ክልኤቱ ምዕት አሠርቱ ወስድስቱ
217. ፪፻፲ወ፯ ክልኤቱ ምዕት አሠርቱ ወሰብዓቱ
218. ፪፻፲ወ፰ ክልኤቱ ምዕት አሠርቱ ወሰመንቱ
219. ፪፻፲ወ፱ ክልኤቱ ምዕት አሠርቱ ወተሰዓቱ
220. ፪፻፳ ክልኤቱ ምዕት ወእስራ
230. ፪፻፴ ክልኤቱ ምሪዕት ወሠላሳ
240. ፪፻፵ ክልኤቱ ምዕት ወአርብዓ
250. ፪፻፶ ክልኤቱ ምዕት ወሃምሳ
260. ፪፻፷ ክልኤቱ ምዕት ወስድሳ
270. ፪፻፸ ክልኤቱ ምዕት ወሰብዓ
280. ፪፻፹ ክልኤቱ ምዕት ወሰማንያ
290. ፪፻፺ ክልኤቱ ምዕት ወተሰዓ
300. ፫፻ ሠለስቱ ምዕት
400. ፬፻ አርባዕቱ ምዕት
500. ፭፻ ሐምስቱ ምዕት
600. ፮፻ ስድስቱ ምዕት
700. ፯፻ ስብዓቱ ምዕት
800. ፰፻ ስመንቱ ምዕት
900. ፱፻ ተሰዓቱ ምዕት
1000. ፲፻ አሠርቱ ምዕት
2000. ፳፻ እስራ ምዕት
30
00. ፴፻ ሠላሳ ምዕት
4000. ፵፻ አርብዓ ምዕት
5000. ፶፻ ሃምሳ ምዕት
6000. ፷፻ ሳድስ ምዕት
7000. ፸፻ ሰብዓ ምዕት
8000. ፹፻ ሰማንያ ምዕት
9000. ፺፻ ተሰዓ ምዕት
10,000. ፻፻ እልፍ
20,000. ፪፻፻ ክልኤቱ እልፍ
30,000. ፫፻፻ ሠለስቱ እልፍ
40,000. ፬፻፻ አርባዕቱ እልፍ
50,000. ፭፻፻ ሐምስቱ እልፍ
60,000. ፮፻፻ ስድስቱ እልፍ
70,000. ፯፻፻ ሰብዓቱ እልፍ
80,000. ፰፻፻ ስመንቱ እልፍ
90,000. ፱፻፻ ተሰዓቱ እልፍ
100,000. ፲፻፻ አሠርቱ እልፍ
200,000. ፳፻፻ እስራ እልፍ
300,000. ፴፻፻ ሠላሳ እልፍ
400,000. ፵፻፻ አርብዓ እልፍ
500,000. ፶፻፻ ሃምሳ እልፍ
600,000. ፷፻፻ ስድሳ እልፍ
700,000. ፸፻፻ ሰብዓ እልፍ
800,000. ፹፻፻ ሰማንያ እልፍ
900,000 ፺፻፻ ተሰዓ እልፍ
1,000,000 ፻፻፻ አእላፋት
10,000,000 ፲፻፻፻ ትእልፊት
100,000,000. ፻፻፻፻ ትልፊታት
1,000,000,000. ፲፻፻፻፻ ምእልፊት
4000. ፵፻ አርብዓ ምዕት
5000. ፶፻ ሃምሳ ምዕት
6000. ፷፻ ሳድስ ምዕት
7000. ፸፻ ሰብዓ ምዕት
8000. ፹፻ ሰማንያ ምዕት
9000. ፺፻ ተሰዓ ምዕት
10,000. ፻፻ እልፍ
20,000. ፪፻፻ ክልኤቱ እልፍ
30,000. ፫፻፻ ሠለስቱ እልፍ
40,000. ፬፻፻ አርባዕቱ እልፍ
50,000. ፭፻፻ ሐምስቱ እልፍ
60,000. ፮፻፻ ስድስቱ እልፍ
70,000. ፯፻፻ ሰብዓቱ እልፍ
80,000. ፰፻፻ ስመንቱ እልፍ
90,000. ፱፻፻ ተሰዓቱ እልፍ
100,000. ፲፻፻ አሠርቱ እልፍ
200,000. ፳፻፻ እስራ እልፍ
300,000. ፴፻፻ ሠላሳ እልፍ
400,000. ፵፻፻ አርብዓ እልፍ
500,000. ፶፻፻ ሃምሳ እልፍ
600,000. ፷፻፻ ስድሳ እልፍ
700,000. ፸፻፻ ሰብዓ እልፍ
800,000. ፹፻፻ ሰማንያ እልፍ
900,000 ፺፻፻ ተሰዓ እልፍ
1,000,000 ፻፻፻ አእላፋት
10,000,000 ፲፻፻፻ ትእልፊት
100,000,000. ፻፻፻፻ ትልፊታት
1,000,000,000. ፲፻፻፻፻ ምእልፊት
👉🏻በመጀመሪያ የትዳር አጋርን ለመምረጥ ብዙ ሊደከም ይገባል
፡ ሊቁ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንዲህ ይላል አንድን ዕቃ ስንገዛ ስለሚሸጡልን ሰዎች መረጃ እንደምንሰበስብ የሚያዋጣን መኾኑን እንደምናመዛዝን ከሉ አንድ ኦርቶዶክሳዊ ወጣት የትዳር አጋሩን ሲመርጥ እጅግ ከፍ ያለ ጥንቃቄ ሊያደርግ ይገባዋል፡፡ ምክንያቱም የገዛነው ዕቃ የተበላሸ እንደ ሆነ ልንመልስ እንችላለን አንዴ ወደ ትዳር ከገባን በኋላ ግን የትዳር አጋራችንን መለወጥ አንችልም፡፡ ታዲያ መምረጥ የምንችለው
ሀ/👉🏻 ፍቃደ እግዚአብሔርን በመጠየቅ:-
ከምንም በፊት እግዚአብሔርን ልንጠይቅ ይገባል፡፡ ሊቁ አንዲህ ይላል ማግባት ስትፈልግ አስቀድመህ ጸልይ አሳብህን ለእግዚአብሔር ንገረው፡፡ እግዚአብሔር መርጦ እንዲሰጥህ ለምነው፡፡ ጭንቀትህን ሁሉ በእርሱ ልይ ጣለው፡፡ አንተ እንደዚህ እርሱ እንዲመርጥልህ የምታደርግ ከኾነም አክብረኸዋልና እርሱም ለአንተ በጎ የትዳር አጋርን በመስጠት ያከብርሃል፡፡ ታዲያ አስቀድመን እንዲህ ብናደርግ ወደ ትዳር ስንገባ ፍቺ አይገጥመንም ሚስት ወይ ባል ሌላ አይመኝም በሌላ በማንም እንዳንቀና ያደርገናል ጠብ ክርክር አይኖርም ከጠብ ይልቅ ታላቅ የኾነ ሰላምና ፍቅር በመካከል ይኖራል፡፡ እነዚህን ደግሞ በጎ ምግባራትን ትሩፋትን ለመፈጸም አንቸገርም፡፡
አንድ ሰው አይቶ ስለ ወደደ፤ ሃይማኖት ስላለው፤ በጎ ምግባርን ገንዘብ ስላደረገ ብቻ ይህን ማግባት አለብኝ ብሎ ሊወስን አይገባውም፡፡ ወደውሳኔ ከመምጣት በፊት ያሰብኩት አሰብ የማነው የእግዚአብሔር አሳብ ሊሆን ይችላል ወይ የራሴ ወይ ደግሞ የዲያብሎስ አሳብም ሊኾን ይችላል ብለን ቆም ብለን ማሰብ ይገባል፡፡ አስቀድመን የንሰሐ አባታችንን ማማከር በጸሎት ሊረዱን ከሚችሉ መንፈሳውያን አባቶች ወይም እናቶች ጋር ተመካክሮ የዓቅማቸንን ያህል ሱባኤ መያዝ ተገቢ ነው፡፡ በተቻለን አቅም ደግሞ ስናማክር የትዳር ተቀዳሚ ዓላማ ያልገባቸው ሰዎችን ለእርዳታ እና ለምክር ባንጠይቅ የተሸለ ነው፡፡ በሰዎች ምስቅልቅል ሕይወት የሚነግዱም ስላሉ፡፡ ከዚህ ሁሉ ይልቅ የእግዚአብሔርን እርዳታ መጠየቅ በናንተ መሃል ሽማግሌ ለመሆን አያፍርም፡፡ መንፈሳዊ ሕይወታችሁ ጽኑዕ የትዳራችሁ ዋና ግብም ጽድቅ እንዲሆን እግዚአብሔርን ጠይቁ፡፡ ይሄን አድርገን እግዚአብሔር መፍቀዱን በምን እናውቃለን ብንል እግዚአብሔር በራዕይ ወይ በድምጽ እንዲነግረን አንጠብቅ ፍቃዱ ከሆነ ያች በአቅማችን የያዝናት ሱባኤ የመረጥነው ሰው የእግዚአብሔር ፍቃድ ከኾነ ያለን መውደድ እየጨመረ ይሄዳል፡፡ አሳቡ የራሳችን ምኞት ወይ የዲያብሎስ ምክር አሳብ ከነበረ ግን ጸሎት የማያፈርሰው የጠላት አጥር የለምና ስለዛ ሰው የነበረን አሳብ ይጠፋል፡፡ የእግዚአብሔር ፈቃድ ካልሆነ ያ የጀመርነው ጓደኝነት በሆነ ምክንያት እግዚአብሔር ያስቀረዋል። ለዚህ ምሳሌ ሊሆን የሚችለው የአበ ብዙኀን የአብርሃም አገልጋይ ለይስሐቅ ሚስት ለማምጣት በተላከ ጊዜ ያደረገው ጸሎትና ርብቃን የለየበት መንገድ፡፡ ዘፍ 24፡12
ለ/ 👉🏻የትዳርን ዓላማን በደንብ መረዳት፡- የትዳር የመጀመሪያ ዓላም ጽድቅን መፈጸም ነው፡፡ ሌሎቹ ዓላማዎች በዚህ ስር ይጠቃለላሉ
ልጅን ለመውለድ ብቻ አስቦ ማግባት አይገባም የትዳር አንዱ ዓላማ ልጅ መውለድ ቢኾንም ቅሉ ላይወልድም ይችላልና ፡፡
ወጪውን ለመቀነስ ብሎም አያግባ ዓላማው ከዚህም ያልፋል
አንድ ለአንድ መወሰን ጥሩ በሚል ብቻም ማግባት የለበትም መልካም ቢሆንም በውስጡ ከዝሙት ተጠብቆ ጽድቅን ለመፈጸም ካልሆነ ምክንያቱም ከአሕዛብም የጽድቅ አሳብ ሳይኖራቸው የሚወሰኑ አሉና፡፡
መልኳም ወደድኹ ብሎም ማግባት ውበት ባይጠላም እርሱ ግን የትዳር ዓላማ አይደለም ይህንን አድንቆ ከገባ ከተወሰንኑ ቀናት በኋላ አይማርከውም ይለምደዋልና፡፡ ሌላም ቆንጆ ቢያይ ልሂድ ሊል ነው።
እነዚህ ዓላማ ሳያደርግ ግን ጽድቅን አስቦ የገባ ባይወልድ እንኳ አይፋታም፤ ሩካቤ ባያደርግ፤ ቢሰንፍ እንኳን እራሳቸውን ከዝሙት ተጠብቀውና ራሳቸውን ገዝተው የትዳር አጋራቸውንም እግዚአብሔርን በማመስገን ይኖራሉ እንጂ አይፈቱም፡፡ ጋብቻ ግቡ ይኼ ነውና፡፡ መገንዘብ ያለብን ጋብቻ ወደ ቅድስና የሚያደርስ እንጂ በራሱ ጽድቅ አለመኾኑን ነው፡፡ ጋብቻ በእምነት ያገኘነውን ልጅነት አጽንተን እንድንይዝ እግዚአብሔር ወደ መምሰል እንድናደርግ የሚያደርግ ከድንግልና ሕይወት ቀጥሎ ያለ አንድ የሕይወት መንገድ እንጂ በራሱ ቅድስናን የሚሰጥ አለመሆኑን ነው፡፡ ሰለዚህ የትዳር አጋራችን ስንመርጥ ወደምንፈልገው ግብ የሚያደርሰንና እርሱም አብሮን የሚደርስ ሊኾን ይገባዋል፡፡ ፍቃደ እግዚአብሔር አስቀድመን ስንጠይቅና እግዚአብሔርም ጸሎታችንን ሲሰማ የሚሰጠን የትዳር አጋር ለዚህ ተቀዳሚ ዓላማ የሚስማማንን ነው፡፡ ይሄ ባይሆን ግን የትዳር ዓላማ ሳይገባን የምንገባበት ከኾነ ግን የትዳር አጋራችን የቱንም ያህል መንፈሳዊ ቢኾንም እንኳን አስቸጋሪ ነው፡፡
አንድ ምሳሌ እንይ መንፈሳዊ ሕይወታቸውን ብቻ አይተው የሚያገቡ ሰዎች ስግብግብ ነጋዴዎችን ይመስላሉ ይላል ሊቁ ቅ/ዮሐንስ አፈወርቅ። ስግብግብ ነጋዴዎች መርከቦቻቸውን ከዓቅም በላይ ዕቃ ስለሚጭኑባቸው ማዕበሉን መቋቋም አይችሉም፡፡ ይሰጥማሉ የማይችሉትን ሸክም ለመሸከም የሚገቡ ሰዎችም እንደዚህ ናቸው፡፡ የማይችሉትን የትዳር አጋራቸውን ጠባይ ለመሸከም ይገደዳሉ፡፡ ይህን ለመሸከም ሲሉ ከዓቅማቸው በላይ ወደ ኾነ ተጋድሎ ይገባሉ፡፡ ተጋድሎው በራሱ መልካም ቢኾንም ከዓቅማቸው በላይ ስለሚኾን ይመረራሉ፡፡ አንዱ ብዙ እንጸልይ፤ ብዙ እንስገድ፤ እንጹም ሲል ሌላኛው ግን ከዓቅሙ በላይ ስለሚኾንበት በዚህ ይሰናከልበታል፡፡ ሲከፋም ወደ ውጭ ማየት ሊመጣ ይችላል፡፡ በዓቅማቸው የሚጋቡ ከሆነ ግን ሚስቶች የቱንም ያህል ክፉ ቢኾኑም እንኳን ባሎች፡- ክርስቶስ ደግሞ ቤተ ክርስቲያንን እንደ ወደዳት ሚቶቻችሁን ውደዱ የሚለውን ቃል እግዚአብሔር ለመፈጸም አይቸገሩም፡፡ ሚስቶቹም ባሎቻቸውን በጌታ ለመታዘዝ አይቸገሩም፡፡ እህቴ እኔም የምመክርሽ ፍቃደ እግዚአብሔርን ጠይቂ!!!

🌼አቃፊው -- አባት🌼
ሲሰድቡት ውለው_________ሲመርቅ ያድራል
ሊገድሉት ሲሹት............ከሞት ያድናል
እያስለቀሱት ..............እንባን ያብሳል
ሲገፈትሩት...............በፍቅር ያቅፋል
ለሚያሳድዱት.........እጅ ይዘረጋል
እውን እንዳንተ አባት ይገኛል?
ለጠወልግነው የሆንከን ታዛ
በፀጋህ ሀይል ገፃችን ወዛ
ምን ቢያስድዱህ ብትሆን ባይተዋር
ወደቁ ከእግርህ ዳኑ ከሞት ጣር
እንዲያ ሲሰድቡህ ሲያሳዱህ
ችለህ ማለፍህ ሳያንስብህ
በእጅህ ሊድኑ ከእግርህ ቢወድቁ
አቅፈህ ሳምካቸው ዳኑ ሊደምቁ
አባ ኑርልን ዘላለም አለም
ጠላትን አሳድ ከአለም አለም
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
ውድ የመምህር ግርማ ፍሬዎች እንኳን ለ፪ሺ፲፪ አዲስ አመት አደረሳችሁ
🌺🌸🌼🌼አዲሱ አመት🌼🌼🌺🌸
ንስሀየምንገባበት፣የምንቆርብበት፣የተጣላን የምንታረቅበት፣በሀገራችንም በሀይማኖታችንም ያንዣበብው መከራ የሚያልፍበት፣ ከክፉ መሰሪ ጥንተ ጠላታችን የምንላቀቅበት፣ሰው የምንሆንበት፣ ከምንም በላይ ከእማዋይሽ፣ ከወለላይቱ፣ ከፍቅር እናት፣ስለኛ ከማትደከመዋ፣ከአንድዬ እናት፣ሁሉ ለእርሷ ሁሉ ስለእርሷ ለተፈጠረላት፣የሰይጣንን ምርኮ ካራገፈችው፣ብንጠላት ከማትጠላን፣ብንተዋት ከማትተወን፣ ቅዱሳን ምስጋናዋን አላልቅ ቢላቸው በእንባ ከጨረሱላት፣መላእክት አምላካቸውን ካዩባት፣ ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም የምንጣበቅበት፣በረከቷን፣አማላጅነቷን፣ በገፍ የምናፍስበት አመት ያድርግልን
🌼አሜን🌼

ከነፍስ ስደት ታድነን ዘንድ እመቤታችንን እንማፀናት፡ ከክፉው ከአውሬው እጅ እንድታላቅቀን ሰግደን እንለምናት
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
መልአከ መንክራት መምህር ግርማ በአሜሪካ በካንሳስ የተናገሩት ድንቅ መልእክት
የአባታችንን ደስታ አይታችሁ ይህንን የ ቪዲዮ መልእክት ሼር በማድረግ ጠላታችንን ዲያቢሎስ አሳፍሩት እስኪ share Share share
ስጋ ወደሙ ውሰዱ የሚል ጠንቋይ እንዲህ ከሆነ አረ ሁላችሁም ጠንቋይ ሁኑ! እግዚአብሔር ይርዳችሁ የእግዚአብሔርን ስራ ከሰራን እንጠላለል
የእግዚአብሔርን ስራ ከሰራን እንሰደዳለን
ዝም ብላችሁ ከተቀመጣችሁ ቴሌቭዥን ነን ማለት ነው አይሆንም የእግዚአብሔርን ስራ መስራት አለብን የእግዚአብሔርን የስራ ውጤቱ ደግሞ በብዙ መከራ ውስጥ አሳልፎ ዛሬ እኔና እናንተን በአሜሪካ በቅድስት ቤተክርስቲያን አገናኝቶናል ።
በመቀጠልም በኮሎራዶ ካንሳስ እና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ አባታችን አቡነ ናትናኤል እንዲቀሩብን አንፈልግም ከእርሶ ተማሪ ጋር በመሆን በአሜሪካ ቤት ሰርቼ እጠብቆታለሁ በማለት ለ መልአከ መንክራት መምህር ግርማ ወንድሙ ቃል ገብተዋል ።
የበረከት ስራም ለቤተክርስቲያኑ በብዙ ሺህ የሚቆጠር ዶላር ገቢ ሆንዋል ።
ይህን ያደረገ እግዚአብሔር ይመስገን!
<<እንዳትሰናከሉ ይህን ተናግሬአችኋለሁ።
2፤ ከምኵራባቸው ያወጡአችኋል፤ ከዚህ በላይ ደግሞ የሚገድላችሁ ሁሉ እግዚአብሔርን እንደሚያገለግል የሚመስልበት ጊዜ ይመጣል። >> የዮሐንስ ወንጌል 16 ፤ 1

Forwarded from በማለዳ ንቁ ! (Natnael S. 🕆)
መሠረታዊ የአምልኮት ትምህርት.docx
399.8 KB
✞ መሠረታዊ የአምልኮት ትምህርት ✞
እድለኛ የሆነ፤ በጥሞና አንብቦ ወደ ምግባር ሲያወርደው በሕይወቱ የሚታይ መንፈሳዊውም ሥጋዊም ለውጥ ያመጣል፡፡
ለራሳችሁ ስትሉ ንቁ!
ከንቱነት ይብቃችሁ!

ሕዝቅኤል 7
¯¯¯¯¯"¯¯¯¯¯
¹⁹ ብራቸውን በጎዳናዎቹ ላይ ይጥላሉ ወርቃቸውም እንደ ጕድፍ ይሆናል፤ በእግዚአብሔር መዓት ቀን ብራቸውና ወርቃቸው ያድናቸው ዘንድ አይችልም። እርሱ የኃጢአታቸው ዕንቅፋት ሆኖአልና ሰውነታቸውን አያጠግቡም ሆዳቸውንም አይሞሉም።
…
²⁷ ንጉሡም ያለቅሳል፥ አለቃም ውርደትን ይለብሳል፥ የምድርም ሕዝብ እጅ ትንቀጠቀጣለች፤ እንደ መንገዳቸውም መጠን አደርግባቸዋለሁ፥ በፍርዳቸውም መጠን እፈርድባቸዋለሁ፤ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።

Forwarded from “ መምህር ግርማ ምን አስተማሩ “
የምሥራች
በ ቅርብ ቀን የሚለቀቅ የሚወደድ አዲስ ዝማሬ
በዲያቆን ኃይለመለኮት ግርማ ወንድሙ
( አትልፋ ጠላቴ )
ለቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አማኞች በሙሉ ምንም እንኳን በዚህ ዓመት በአስቸጋሪ እና በጭንቅ ውስጥ ሆነን ቢሆንም ስብሐተ እግዚአብሔርን ማቋረጥ የባሰ ጭንቅ ስለሆነ ጠላት ቢሮጥ እግዚአብሔር ከያዝን ምንም እንደማያመጣ የሚያስረዳ ወቅታዊ የመዝሙር ቪዲዮ ሲሆን
በ እንሳሮ ፊልም ED ፕሮዳክሽን በልዩ ሁኔታ የተቀረፀ ድንቅ የሚወደድ ዝማሬ ነው የተለየ ያማረና ፍሬያማ ሥራ እንዲሆን ደክመንበታል፡፡ በጣም በጣም ደክመንበታል፡፡ ጥሩ ነገር ለማቅረብ ለማድረግ የሚቻለውን አቅም ተጠቅመናል፡፡ ጊዜ ገንዘብ እና ጉልበታችንን ከ ሶስት ሳምንት በላይ በደንብ የፈተነ ሥራ ቢሆንም እግዚአብሔር ይመስገን ጨርሰን ልናቀርብላችሁ ተዘጋጅተናል፡፡
እንግዲህ የነፍሳችሁን መንገድ ሰማያዊ ለማድረግ ነው ጥረቱ፡፡ በየ ሥራ ቦታችሁ በሁሉ ቦታ ጠላት አንደማይጠፋ የተረጋገጠ ቢሆንም እውነትን ከያዝን የእግዚአብሔር ኃይል እንደሚበልጥ የሚገልጥ መዝሙር ነው የልፋታችን ውጤቱ እናንተ ናችሁ፡፡ እንግዲህ እኛ እዚህ ድረስ ስንታትር እናንተ ፍሬያማ በመሆን በከንቱ እንዳልደከምን በምግባረ አምልኮ ሕይወት ለሁሉም የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ምዕመናን በሙሉ ላልሰሙት በማሰማት በ Facebook በ YouTube በሁሉም ሚድያ በማስተላለፍ ይህን መዝሙር ለዓለም እናዳርስ ሁላችንም በየግል media ችን share በማድረግ ግዴታችንን እንወጣ!
በቅርብ ቀን ይጠብቁ!
ከዲያቆን ኃይለመለኮት ግርማ