Genius Tutorial Service
141 subscribers
191 photos
5 videos
51 links
Empowering Genius Mind
Download Telegram
#zena
#ATTENTION
#NationalExam

የ2014 የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና ከነገ መስከረም 30 ጀምሮ መሰጠት ይጀምራል።

ነገ ፈተናቸውን የሚፈተኑት በመጀመሪያ ዙር ወደ መፈተኛ ማዕከላት / ዩኒቨርሲቲ የገቡ የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ናቸው።

ተማሪዎቹ ስለፈተናው አጠቃላይ (ኦረንቴሽን) ገለፃ ተደርጎላቸዋል።

በፈተና ወቅት መከተል ስላለባቸው የስነምግባር መርሆች፣ የሰዓት አከባበርን በተመለከተ ፣ የተብራራላቸው ሲሆን የመፈተኛ ጣቢያ እና ክፍላቸውን ለይተውም እንዲያውቁ መደረጉን ሰምተናል።

ከተፈታኝ ተማሪዎች በተጨማፊ ፈታኞች፣ ለፈተና ጣቢያ ኃላፊዎች፣ ለሱፐርቫይዘሮች፣ ማየት ለተሳናቸው ተፈታኝ አንባቢዎችና ለመልስ ወረቀት ቆጣሪዎች ገለፃ (ኦረንቴሽን) ተሰጥቷቸዋል።

የማህበራዊ ሳይንስ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከነገ ጥዋት ጀምሮ እስከ ጥቅምት 2 ድረስ ይሰጣል፤ ከጥቅምት 3 - ጥቅምት 4 ተፈታኞች ወደየአካባቢያቸው ይመለሳሉ።

የ12ኛ መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተናው ጥብቅ በሆነ ዲሲፕሊን እንደሚመራ ተገልጾልናል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ለተፈታኞች በሙሉ መልካም ፈታናን ይመለኛል!

Source- @tikvahethiopia