Genius Tutorial Service
142 subscribers
191 photos
5 videos
51 links
Empowering Genius Mind
Download Telegram
#ZENA
#ATTENTION
#እንድታውቁት

መስከረም 30 ቀን 2015 ዓ.ም. ለሚጀምረው የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ አገር አቀፍ ፈተና የመጀመሪያ ዙር የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች መስከረም 26-28 ተጠቃለው በመግባት መስከረም 29 ስለፈተናውና ተያያዥ ጉዳዮች በየተመደቡባቸው ዩኒቨርስቲዎች ገለጻ የሚደረግበት ዕለት መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቆ ነበር።

ሆኖም የእስልምና እምነት ተከታዮች መስከረም 28 የመዉሊድ በዓል አክብረዉ መስከረም 29/2015 ዓም እሁድ ጠዋት መግባት እንዲችሉ በልዩ ሁኔታ የተፈቀደላቸዉ መሆኑን ሚኒስቴሩ ገልጿል።

የፈተና እና ተያያዥ ጉዳዮች ገለጻ /Orientation/ ይህንን ታሳቢ ባደረገ መልኩ እሁድ ከሰዓት በኋላ እንዲሰጥ የተደረገ ሲሆን የእምነቱ ተከታይ ተማሪዎችም ይህንን አውቀው በተጠቀሰዉ ሰዓት በመገኘት ገለጻ /Orientation/ እንዲከታተሉ ትምህርት ሚኒስቴር አሳስቧል።

Source-@tikvahethiopia