Forwarded from Ministry of education ®
13 ድሮኖችን የሠራው የዩኒቨርሲቲ መምህር
ወጣት አማኑኤል ባልቻ ከአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በሜካኒካል ምህንድስና የተመረቀ ሲሆን አሁን ላይ በደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ በመምህር እያገለገለ ነው።
በርካታ በአይነታቸው የሚለያዩ ድሮኖችን ሠርቶ የሙከራ በረራም አድርጓል።
የቡራዩ የልዩ ተሰጥኦ ትምህርት ቤት በቅርቡ ሲመረቅ የሠራቸው ከ13 በላይ ድሮኖችን ለዕይታ አቅርቧል።
ወጣት አማኑኤል በመንግስታዊ እና የግል ተቋማት ድጋፍ ሁሉንም አይነት ድሮኖች የሚመረቱበት ትልቅ የድሮን ኩባንያ መክፈት እንደሚፈልግ ይናገራል።
ኩባንያው የድሮን ስልጠናዎችን የሚሰጥ እና ልዩ ፍላጎት ያላቸው ህጻናት ስለ ድሮን የሚማሩበት ማዕከል እንደሚሆን ይገልጻል።
በተጨማሪም ማዕከሉ በትዕዛዝ ለተቋማት ድሮኖች የሚሠሩበት ይሆናል ብሏል።
ወደፊት እንዳደጉት አገራት እንደነቱርክ ግዙፍ ድሮኖች በኢትዮጵያ የመሥራት ተስፋ መሰነቁን ወጣት አማኑኤል ይናገራል።
@Temhert_Minister