December 17, 2022
December 17, 2022
December 19, 2022
December 20, 2022
December 21, 2022
Forwarded from Ministry of Education Ethiopia
መምህራን ቴክኖሎጂን በአግባቡ በመጠቀም የተሻለች አገር የሚፈጥር ብቁና ተወዳዳሪ ዜጋ ማነጽ እንደሚጠበቅባቸው ተገለጸ
....................................................................................
ታህሳስ 13/2015ዓም (ትምህርት ሚኒስቴር) ከአንድ ሺ ለሚበልጡ የ2ኛ ደረጃ መምህራን በቴክኖሎጁ አጠቃቀም ዙሪያ ስልጠና ተሰጥቷል።
የመምህራንና የትምህርት አመራር ልማትና አስተዳደር ዴስክ ኃላፊ ወ/ሮ አሰገድ ምሬሳ በስልጠናው ወቅት እንደገለጹት የጊዜውን ቴክኖሎጂ ተጠቅሞ አገሩን የሚገነባ ትውልድ መፍጠር ከመምህራን የሚጠበቅ ተግባር ነው።
በመሆኑም መምህራን የቴክኖሎጂ አቅማቸውን በማሳደግ በስርዓተ ትምህርቱ ላይ የተቀመጡ ዓላማዎችን ተማሪዎች በቀላሉና በተሻለ እንዲረዱ ማስቻል እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።
የመምህራንና የትምህርት አመራር ልማትና አስተዳደር ዴስክ ከፍተኛ የድጋፍና ክትትል ባለሙያ አቶ አለሙ ተስፋዬ በበኩላቸው የስልጠናው ዓላማ መምህራን ቴክኖሎጁን አማራጭ የትምህርት መረጃ መሳሪያ በማድረግ የመማር ማስተማር ስራውን ለማጠናከር ነው ብለዋል።
ስልጠናው መምህራን የቴክኖሎጂ ክህሎታቸውን በማሳደግ አዳዲስ ዕውቀቶችን እንዳያብሩና በአንድ ጊዜ ብዙ ተማሪዎችን ለመድረስ እንደሚያስችላቸውም አቶ አለሙ ተናግረዋል።
ከሁሉም ክልሎች ለተመለመሉ የ2ኛ ደረጃ መምህራን በ11 የስልጠና ማዕከላት በተሰጠው በዚህ ስልጠና ከአንድ ሺ አንድ መቶ የሚበልጡ ተሳታፊዎች መገኘታቸውንም ተናግረዋል።
በሌላ በኩል ከሁሉም ክልሎች ለተውጣጡ 3ሺ 12 የትምህርት ቤት አመራሮች አቅም ለማጎልበት ልዩ የአንድ ዓመት የስራ ላይ ስልጠና እየተሰጠ መሆኑን የመምህራንና የትምህርት አመራር ልማትና አስተዳደር ዴስክ ኃላፊ ወ/ሮ አሰገድ ምሬሳ ገልጸዋል።

December 23, 2022
December 23, 2022
December 24, 2022
December 26, 2022
December 27, 2022
December 27, 2022
December 28, 2022
December 29, 2022