Ethiopian Airlines የኢትዮጵያ አየር መንገድ
82.3K subscribers
2.27K photos
90 videos
2 files
295 links
ይህ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ይፋዊ የቴሌግራም ገፅ ነው።
Download Telegram
በዓለም አቀፉ ጥምረት አማካኝነት የእንግሊዝ መንግስት ለኢትዮጵያ የለገሰውን 499,200 ዶዝ የአስትራ ዜኒካ ክትባት አጓጉዘን ለጤና ሚኒስቴር በማስረከባችን ደስታ ተሰምቶናል።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
የዛሬውን #የመስኮትምልከታ ያጋሩን አቶ ሞሀመድ ኦኩር ናቸው ፤ እናመሰግናለን። #የኢትዮጵያአየርመንገድ
የእቃ ጭነት አገልግሎታችን የጥንካሬአችን ቁልፍ መገለጫ ነው። #የኢትዮጵያአየርመንገድ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የ ቦይንግ 767  የመንገደኛ አውሮፕላኖችን ሙሉ በሙሉ ወደ እቃ ጭነት ለመቀየር የሚያስችል ማእከል ከ እስራኤሉ ኤሮስፔስ ኢንዱስትሪ ጋር በመተባበር አቋቋመ። ማእከሉ የአየር መንገዱን አውሮፕላኖች ብቻ ሳይሆን የሌላ ሀገር አየር መንገድ አውሮፕላኖችንም ከመንገደኛ አውሮፕላኖች ወደ እቃ ጭነት የመቀየር  አገልግሎት የሚሰጥ ሲሆን በቅርቡ ስራ የሚጀምር ይሆናል።
ከኮቪድ 19 ወረርሽኝ መነሻ ጀምሮ የተተገበሩ ፈጣንና የፈጠራ ክሕሎት የታከለባቸው እንቅስቃሴዎቻችን ወረርሽኙ በአቪየሽን ኢንዱስትሪ ላይ ያደረሰውን ተፅዕኖ እንድንቋቋም ረድቶናል። ከራዕይ 2025 ጎን ለጎን የዕቃ ጭነት አገልግሎታችንን በአውሮፕላን ብዛት፣ በካርጎ መሰረተ ልማት እና መዳረሻ ብዛት አንፃር ለማዘመንና እድገት ለማስመዝገብ በትጋት እየሰራን ነው።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
ምቾቶን ጠብቀው የኢትዮጵያ ኩራት በሆነው አየር መንገዳችን በደስታ ይብረሩ፡፡ #የኢትዮጵያአየርመንገድ
በረራዎን ከእኛ ጋር በማድረግ የማይረሳ ጊዜ ያሳልፉ፡፡የዛሬውን የአውሮፐላን ምስል ያጋሩን Hilena Tafesse ናቸው ፤ እናመሰግናለን። #የኢትዮጵያአየርመንገድ
'የኢትዮጵያ አየር መንገድ አስደናቂ እድገት' በ Simple Flying ሚዲያ የተፃፈ ዘገባ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ባለፉት አስር አመታት ውስጥ በፍጥነት እያደገ የመጣ አየር መንገድ ነው።
አየር መንገዱ ከሌሎች አየር መንገዶች የተሻለ ስኬት ማስመዝገብ የቻለው በዋናነት በ 2010 ባዘጋጀው ጠንካራ የስራ ዕቅድ ነው።
ለተጨማሪ ንባብ ሊንኩን ይጫኑ። simpleflying.com/rise-of-ethiopian-airlines/
የአፍሪካ ቁጥር 1 አየር መንገድ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሰራተኞችን ሳይቀንስ እንዲሁም ሳይከስር የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ያስከተለውን ቀውስ እንዴት መቋቋም ቻለ?

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ተወልደ ገብረማርያም ከአሜሪካው ሚድያ The Points Guy ጋር ያደረጉትን ቃለ ምልልስ ሊንኩን ተጭነው እንዲያነቡ ጋብዘኖታል።
https://thepointsguy.com/.../ethiopian-airlines-layoffs.../
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦይንግ-767 የመንገደኛ አውሮፕላኖችን እ.ኤ.አ ከ 1980ዎቹ ጀምሮ ተረክቦ በማብረር በአፍሪካ ምድር ላይ ቀዳሚው አየር መንገድ ነው። በቅርቡም የእነዚህ አውሮፕላን ሞዴሎች ሙሉ ለሙሉ የእቃ ጭነት አገልግሎት እንዲሰጡ የማደረግ ስራ (Conversion) በአየር መንገዱ የአውሮፕላን ጥገና ክፍል ይከናወናል።
የዛሬውን #የመስኮትምልከታ ያጋሩን አቶ አብደላ ገባኒ ናቸው ፤ እናመሰግናለን። እርስዎም ከእኛ ጋር ሲበሩ ያነሱትን ምስሎች በመልዕክት መቀበያ ሳጥን ይላኩልን፤መልሰን እናጋራዎታለን። #የኢትዮጵያአየርመንገድ
"ኮቪድ 19 ያስከተላቸውን ተግዳሮቶች ወደ ጥሩ የንግድ እድል ከለወጡ ጥቂት አየር መንገዶች አንዱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ነው። አመራሩ እና ታታሪ ሰራተኞቹ አየር መንገዱ በሚታወቅበት ጠንካራ የስራ ባህል ታግዘው አስቸጋሪውን ወቅት ተቋቁመውና ስኬት አስመዝግበው ማለፍ ችለዋል።"

በ Nortgern-Tip Aviation Consulting የተፃፈውን ፅሁፍ ከታች ያለውን ሊንክ ተጭነው እንዲያነቡ ጋብዘኖታል።
https://www.northerntipaviation.no/post/is-ethiopian-airlines-the-champion-of-the-covid-time
እርስዎን ከዓለም ጋር ለማገናኘት ተግተን እንሰራለን። #የኢትዮጵያአየርመንገድ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ኤርባስ A350-900 አውሮፕላን ፍራንክፈርት አውሮፕላን ማረፊያ ሲቃረብ ፡፡
ምስል በ @hessenflyer
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ እና የቦይንግ ካምፓኒ ኢትዮጵያን የአፍሪካ አቪየሽን ማዕከል የሚያደርገውን ስትራተጂካዊ የጋራ ስምምነት ሰነድ /MoU/ ተፈራረሙ። ስምምነቱ ሁለቱ ካምፓኒዎች ለ70 ዓመታት በአቪየሽን መስክ የገነቡት የዳበረ ግንኙነት /partnership/ ታሪክ አካል ሲሆን፣ኢትዮጵያን የአፍሪካ አቪየሽን መናኸሪያ በማድረግ ሀገሪቱ በአፍሪካ አህጉር የምትጫወተውን ሁላቀፍ ሚና ወደላቀ ደረጃ እንደሚያሸጋግር ታምኖበታል።
ለተጨማሪ መረጃ የሚከተለውን ሊንክ ይጫኑ
https://corporate.ethiopianairlines.com/.../ethiopian...
ከእኛ ጋር ይብረሩ፣ በዓለም ዙሪያ መልካም ትውስታን ያኑሩ። የበረራ ምዝገባዎትን ከቤትዎ ሆነው በቀላሉ ይያዙ።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
https://www.ethiopianairlines.com/aa
የኢትዮጵያ አየር መንገድ “My Sheba Space”’ የተሰኘ የኢኮኖሚ ትኬት ያላቸው መንገደኞች በረራቸው 72 ሰዓት ሲቀረው ጀምሮ ለአንድ ተጨማሪ ወንበር በመክፈል በበለጠ ምቾት እና ነፃነት እንዲጓዙ የሚያደርግ በዲጂታል ቴክኖሎጂ የታገዘ አሰራር አስተዋወቀ። ለተጨማሪ ንባብ ሊንኩን ይጫኑ ።
https://bit.ly/3mO2aF7
ተቋርጦ የነበረውን የኢ-ቪዛ አገልግሎት መስጠት ተጀምሯል። ኢ-ቪዛዎን በሚከተለው አድራሻ ማግኘት ይችላሉ።
www.evisa.gov.et