የኢትዮጵያ አየር መንገድ የአውሮፕላን ጥገና ክፍል ከእስራኤል ኤሮስፔስ ኢንደስትሪስ (IAI) ጋር በጥምረት ቦይንግ 767 የመንገደኛ አውሮፕላንን ሙሉ በሙሉ ወደ እቃ ጭነት አውሮፕላን የመቀየር ስራ በተሳካ ሁኔታ አገባድዷል። በቀጣይ ሁለት ወራት አውሮፕላኑን ሙሉ በሙሉ ወደ እቃ ጭነት የመቀየሩ ተግባር ሲጠናቀቅ የአየር መንገዱ የጥገና ክፍል በአፍሪካ ደረጃ የመንገደኛ አውሮፕላንን ሙሉ በሙሉ ወደ እቃ ጭነት አውሮፕላን የቀየረ የመጀመሪያው የጥገና ማዕከል ያደርገዋል። ይህንን ስኬታማ ክንውን አስመልክቶ በተዘጋጀው ፕሮግራም ላይ በኢትዮጵያ የእስራኤል አምባሳደር ክቡር አምባሳደር አለልኝ አድማሱ ፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው እና ሌሎች ተጋባዥ እንግዶች ተገኝተዋል።
👍4
በአፍሪካ ቀዳሚ በሆነው ፣ በሚሰጠው እጅግ ዘመናዊና አለም ዓቀፋዊ እውቅና ያለው የአቪዬሽን ስልጠና ብዙ ሺዎችን ባፈራው የኢትዮጵያ አየር መንገድ አቪዬሽን አካዳሚ ገብተው ይሰልጥኑ!
corporate.ethiopianairlines.com/eaa/training-schools
#የኢትዮጵያአቪዬሽንአካዳሚ
#የአቪዬሽንልሕቀትማዕከል
corporate.ethiopianairlines.com/eaa/training-schools
#የኢትዮጵያአቪዬሽንአካዳሚ
#የአቪዬሽንልሕቀትማዕከል
👍2
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ሙምባይ፣ ህንድ ያደረገውን የ50 አመታት ያልተቋረጠ አገልግሎት በድምቀት አከበረ።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች መልካም የኢድ አልፈጥር በአል እንዲሆንላችሁ እንመኛለን። ኢድ ሙባረክ!
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
@ lucieory ይህን ማራኪ ምስል ስለላኩልን እናመሰግናለን። እርስዎም በኢትዮጵያ አየር መንገድ ሲበሩ ያነሱትን ምስል በመልዕክት ሳጥን መቀበያችን በኩል ይላኩልን መልሰን እናጋራዎታለን።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
ሳምንትዎን ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር ይጀምሩ። ጥራት ያለው አገልግሎታችን ተጠቃሚ ይሁኑ። #የኢትዮጵያአየርመንገድ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ አቪዬሽን አካዳሚ አሜሪካ ከሚገኘው ሚሲሲፒ ዪኒቨርሲቲ ጋር እ.ኤ.አ በ 2018 ዓ. ም በተፈራረመው የመግባቢያ ስምምነት መሰረት በ Integrated Marketing Communication የሁለተኛ ዲግሪ ፕሮግራም ትምህርታቸውን የተከታተሉ 17 የኢትዮጵያ አየር መንገድ ማኔጅመንት አባላት ተመረቁ።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
https://www.youtube.com/watch?v=fVE8Q4FCQvQ
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
https://www.youtube.com/watch?v=fVE8Q4FCQvQ
👍2
በአፍሪካ ትልቁ የካርጎ ኦፕሬተር የሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለእናቶች ቀን 100 ሚሊዮን የአበባ ዘለላ ከአዲስ አበባ፣ ናይሮቢ፣ ቦጎታ እና ኪቶ ወደ አሜሪካ እና አውሮፓ አጓጓዘ።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
#የኢትዮጵያአየርመንገድ