የኢትዮጵያ አየር መንገድ በግማሽ ዓመቱ 4.1ሚሊዮን ደንበኞችን አጓጓዘ። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የስድስት ወር የስራ አፈፃፀም በገንዘብ ሚኒስቴርና በመንግስት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር በሂልተን ሆቴል በዛሬው ዕለት በተገመገመበት ወቅት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ምክትል ዋና ስራ አሰፈፃሚ አቶ ኢሳያስ ወልደ ማሪያም እንደገለፁት አየር መንገዱ ከመሰል ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪ ድርጅቶች አንጻር በተለያዩ መመዘኛዎች ሲታይ የላቀ ዕድገት አሳይቷል፤ ትርፋማነቱ በዚህ አስቸጋሪ ወቅትም ቀጥሏል።
የገንዘብ ሚኒስቴር ሚንስትር ክቡር አቶ አህመድ ሺዴ በአሁኑ ጊዜ በርካታ የአየር መንገዶች በአስቸጋሪ ወቅት ላይ ቢሆኑም የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ባሳየው ትርፋማነት፣ በወጪ ቅነሳ ረገድ ውጤት ማስመዝገቡና በተለይ በዕቃ ማጓጓዝ አገልግሎት ያሳየው አመርቂ አፈፃፀም የሚደነቅ መሆኑን ገልፀዋል።
የገንዘብ ሚኒስቴር ሚንስትር ክቡር አቶ አህመድ ሺዴ በአሁኑ ጊዜ በርካታ የአየር መንገዶች በአስቸጋሪ ወቅት ላይ ቢሆኑም የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ባሳየው ትርፋማነት፣ በወጪ ቅነሳ ረገድ ውጤት ማስመዝገቡና በተለይ በዕቃ ማጓጓዝ አገልግሎት ያሳየው አመርቂ አፈፃፀም የሚደነቅ መሆኑን ገልፀዋል።
👍1
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አራተኛው ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ በማረፋቸው የተሰማንን ጥልቅ ሀዘን እየገለፅን ለወዳጅ ዘመዶቻቸዉ እና ለመላው የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች መፅናናትን እንመኛለን። #የኢትዮጵያአየርመንገድ
👍1
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦይንግ 777-8 Freighter የተሰኘውን አዲስ የጭነት ማጓጓዣ አውሮፕላን ምርት ለመግዛት የሚያስችለውን የመግባቢያ ስምምነት ከቦይንግ አውሮፕላን አምራች ካምፓኒ ጋር ተፈራረመ።
ስምምነቱ አየር መንገዱ በዓለም አቀፍ ደረጃ እያደገ ከመጣው የካርጎ ጭነት አገልግሎት ፍላጎት ይበልጥ ተጠቃሚ የሚያደርገው ሲሆን እያስመዘገበ የሚገኘውንም ዕድገት ቀጣይነት የሚያረጋግጥ ነው።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ተወልደ ገብረማርያም ስምምነቱን አስመልክተው “በአፍሪካ አቪየሽን መስክ ቀዳሚ አየር መንገድ እንደመሆናችን መጠን ይህንን አዲስ ፣ ዘመናዊና ነዳጅ ቆጣቢ የጭነት አውሮፕላን ከቦይንግ ካምፓኒ ለመግዛት የመግባቢያ ስምምነት በመፈራረማችን ደስታ ይሰማናል” ያሉ ሲሆን “ይህ አዲሱ ቦይንግ777-8F የጭነት አውሮፕላን እያደገ የመጣውን የአየር መንገዱን የካርጎ ጭነት አገልግሎት በማስፋፋት አሁን ያሉትን 66 ዓለም አቀፍ መዳረሻዎች ለማሳደግ በእጅጉ ይረዳዋል” ብለዋል።
ለተጨማሪ ንባብ ማስፈንጠሪያውን ይጫኑ
https://corporate.ethiopianairlines.com/Press-release-open-page/ethiopian-airlines-and-boeing-sign-memorandum-of-understanding-for-new-777-8-freighter

ብሩህ እና ስኬታማ ሳምንት ተመኘንላችሁ!
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
መልካም ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን። #የኢትዮጵያአየርመንገድ #March8
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የባህርና አየር የተቀናጀ ትራንስፖርት አገልግሎት (sea-air multimodal transportation) ለመስጠት የሚያስችለውን የጋራ ስምምነት ከጅቡቲ አለም አቀፍ የኢንዱስትሪ ፓርኮች አገልግሎት (IDIPO) እና ከጅቡቲ ኤር ጋር ተፈራረመ። ስምምነቱ ከቻይና በባህር ወደ ጅቡቲ የሚመጡ ጭነቶችን የአየር መንገዱን ሰፊና ዘመናዊ የካርጎ ጭነት አገልግሎት አቅም በመጠቀም ከጅቡቲ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ወደተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት በአየር ለማጓጓዝ የሚያስችል ነው።
ከ መጋቢት 20 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ዳሬሰላም፣ታንዛንኒያ የምናደርገውን እለታዊ በረራ ወደ ሁለት ከፍ የምናደርግ መሆኑን ስንገልፅ ደስታ ይሰማናል።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
የዛሬውን #የመስኮትምልከታ ያጋሩን @ Tabor ናቸው ፤ እናመሰግናለን። እርስዎም ከእኛ ጋር ሲበሩ ያነሱትን ምስሎች በመልዕክት መቀበያ ሳጥን ይላኩልን፤መልሰን እናጋራዎታለን።#የኢትዮጵያአየርመንገድ
❤1
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የአውሮፕላን ጥገና ክፍል የዘርፉን ብቁ ባለሙያዎች የያዘ እና በአቪዬሽን የጥገና መስክ በተሰማሩ አለም አቀፍ ተቆጣጣሪ አካላት ስለ አስተማማኝነቱ የተመሰከረለት ምርጥ የአውሮፕላን ጥገና ማዕከል ነው።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
📸 #HilenaTafesse
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
📸 #HilenaTafesse
👍3
ምቾትዎን ጠብቀን እርስዎን በብቃት ማገልገላችን የሁልግዜም ኩራታችን ነው!
#የኢትዮጵያአየርመንገድ
#የኢትዮጵያአየርመንገድ