አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.87K photos
25 videos
1.86K files
3.58K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
በተከራካሪው የተወከለው ጠበቃ ሌል ችሎት ስለተደረበበት ክርክሩ በሚሰማበት ቀን መቅረብ ባለመቻሉ መዝገቡ ከተዘጋ እንደነገሩ ሁኔታ በቂ ምክንያት በመሆኑ የተዘጋው መዝገብ ሊከፈት ይገባል።

ሰ.መ.ቁ. 182136 ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም

በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.74 [2] ደንጋጌ መሰረት “በቂ ሆኖ የሚገመት እክል” ምን እንደሆነ የተመለከተ ባይሆንም አመልካች ቀጠሮ ለመቅረት የቻለዉ በምን ምክንያት እንደሆነ አጠቃላይ ሁኔታዉን መመርመር የሚያስፈልግ ሆኖ፣ አመልካች በራሱ ጉድለት ወይም ቸልተኛነት ቀጠሮዉን ሳይከታተል ቀርቶ ካልሆነ በስተቀር፣ ፍትሕ የማግኘትና የመከራከር መብት ከግምት በማስገባት አመልካችን የገጠመዉ እክል እንደበቂ ምክንያት በመውሰድ ለተጠሪ [መዝገቡ የተዘጋው በክልል ሰበር ችሎት በነበረው ክርክር ነው] ተገቢ ኪሳራና ወጪ በማስከፈል፣ የተዘጋዉ መዝገብ ተከፍቶ ክርክሩ እንዲሰማ መድረጉ አግባብ ነዉ። በመሆኑም አመልካች ክርክሩን በጠበቃ ለማካሄድ ወስኖ በሕጉ አግባብ ተገቢዉን ዉክልና ሰጥቶ እያለ ጠበቃዉ ችሎት በሚሰጠዉ ቀነ ቀጠሮ ተገኝቶ አመልካችን ወክሎ ተገቢዉን ክርክር የማቅረብ ኃላፊነት ይኖርበታል። ነገር ግን ጠበቃ የተለያዩ ደንበኞች ሊኖሩት ስለሚችል ፍ/ቤት በሚሰጠዉ ቀነ ቀጠሮ በተቻለ መጠን ለደንበኞቹ ተገቢዉን የጥብቅና አገልግሎት መስጠት በሚያስችለዉ አግባብ አጀንዳዉን አስማምቶ ቀጠሮ እንዲያዝለት ለፍ/ቤቱ ማመልከት ይጠበቅበታል። ይህም ሆኖ ቀጠሮ ተደራርቦበት በአንድ ጊዜ በተለያዩ ችሎቶች የሚቀርበበትን እድል በማዛባቱ ምክንያት የባለጉዳዩ መዝገብ ከፍ ሲል በተጠቀሰዉ የህጉ ድንጋጌ መሰረት ተዘግቶ እንደሆነ፣ አጠቃላይ የነገሩን ሁኔታ በመመርመር፣ የአመልካች የመከራከርና ፍትሕ የማግኘት መብት ታሳቢ በማድረግ መዝገቡ ተከፍቶ ክርክሩ እንዲሰማ ማድረጉ ተገቢ ነዉ።

#ጠበቃ #አብርሀምዮሀንስ

ይህ ለጠቅላላ እውቀት ብቻ ነው።
ለበለጠ መረጃ ህግ ባለሙያ ያማክሩ!

Alternative legal enlightenment(ALE)#አለሕግ Affordable&Accessible Legal Expertise አማራጭ የሕግ እውቀት፣ ነፃ የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ የሕግ ማብራርያ አለ፣ መሰረታዊ የሕግ እውቀት ያገኛሉ።

#አለሕግ #Alehig

👉Telegram Channel 👈
https://t.me/lawsocieties

👉Facebook Page
https://www.facebook.com/lawsocieties/

👉YouTube 👈
https://www.youtube.com/@Ale_Hig
👍14🔥2