አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.87K photos
25 videos
1.86K files
3.58K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
Forwarded from አለሕግAleHig ️ (Lawyer Mike 🔊የህግ ባለሙያ)
👉የቀብሩን ሥነ-ሥርዓት የሚመለከቱትን ትዕዛዞች ለመስጠት
 እያንዳንዱ ውርስ ከአምስት መቶ የኢትዮጵያ ብር የማይበልጥ የኑዛዜ ስጦታ ለማድረግ፣
 አካለ መጠን ላላደረሱ ልጆቹ አስተዳዳሪን ወይም ሞግዚትን የሚመለከቱ ውሳኔዎችን ለመስጠት ነው፡፡

በቃል የሚደረግ ኑዛዜ ውስጥ ከብር አምስት መቶ በላይ ኑዛዜ ተደርጎ ከሆነ ከአምስት መቶ ብር በላይ ያለው ተቀናሽ ይሆናል፡፡ በቃል የተደረገ ኑዛዜ ከተደረገበት ከሶስት ወር በኋላ ተናዛዡ በህይወት የቆየ እንደሆነ ኑዛዜው ተፈፃሚ አይሆንም ወይም ፈራሽ ይሆናል፡፡ ምክንያቱም ተናዛዡ ያንያህል ጊዜ ሳይሞት ከቆየ በግልጽ የሚደረግ ኑዛዜን ወይም በተናዛዡ ፅሁፍ የሚደረግ ኑዛዜን ለማድረግ እድል አለው ተብሎ ይገመታል፡፡

በሌላ በኩል ብዙ ኑዛዜዎች ካሉ አብሮ ተፈፃሚ ሊሆኑ በሚችሉበት መጠን ልዩ ልዩ ኑዛዜዎች አብረው ተፈጻሚ ይሆናሉ፡፡ ነገር ግን የሁለት ኑዛዜዎች ቃላት ሁለቱም ሊፈፀሙ ያልቻሉ ወይም የተቃረኑ እንደሆነ በኋላ የተደረገው ኑዛዜ ቅድሚያ ይሰጠዋል፡፡

በአጠቃላይ ንብረቱን በኑዛዜ ማስተላለፍ የሚፈልግ ሰው ሶስቱን የኑዛዜ አይነቶች ፎርማሊቲያቸውን በሟሟላት እንደየሁኔታው ሊጠቀምባቸው ይችላል፡፡ ኑዛዜ አድራጊው የኑዛዜ ቃላት ተፈፃሚነት እንዲያገኙ በህጉ የተቀመጡትን መስፈርቶች በጥንቃቄ መከተል አለበት፡፡ ይህ ካልሆነ ኑዛዜው ውድቅ ስለሚሆን የተናዛዡ ፍላጎት ተፈፃሚ አይሆንም ማለት ነው፡፡

 የኑዛዜ ማስረጃ ወይም ማረጋገጫ

በኑዛዜው የሰፈረውን ቃልና ኑዛዜው መኖሩን ማስረዳት ያለበት በዚህ ኑዛዜ ተጠቃሚ ነኝ የሚለው ሰው ነው፡፡ በግልፅ የሚደረግ ኑዛዜ ወይም በተናዛዡ ፅሁፍ የተደረገ ኑዛዜ መኖር የሚረጋገጠው የኑዛዜውን ፅሁፍ ዋናውን በማቅረብ ወይም ለማዋውል ስልጣን በተሰጠው ሰው ዘንድ ወይም ፍርድ መዝገብ ቤት ሹም ተክክለኛ ሆኖ የተመሰከረ አንድ ግልባጭ በማቅረብ ነው፡፡ ኑዛዜዎቹን ለማስፈፀም በማናቸውም ሌላ መንገድ ለማስረዳት አይቻልም፡፡ ነገር ግን በጥፋት ወይም በቸልተኝነት ኑዛዜው እንዲጠፋ ካደረገ ሰው የጉዳት ኪሳራ ለማግኘት ከሆነ በማናቸውም አይነት መንገድ ኑዛዜዎችን ማስረዳት ይቻላል፡፡

በአጠቃላይ በአንድ ኑዛዜ ተጠቃሚ ነኝ የሚል ሰው ሁለት ነገሮችን በመሰረታዊነት ማስረዳት ያለበት ሲሆን እነሱም በተናዛዡ የተደረገውን ኑዛዜ በማቅረብ የኑዛዜን መኖር እና የኑዛዜውን ይዘት በማስረዳት ማለትም እሱ የኑዛዜው ተጠቃሚ (beneficiary) መሆኑን ማስረዳት ናቸው፡፡

በንቃተ ህግ ትምህርትና ስልተጠና ዳይሬክቶሬት የተዘጋጀ
https://t.me/alehig
https://t.me/lawsocieties
#አለሕግ #ህግ  #AleLaw #አለጠበቃ #አለሕግአማካሪ #አለሕግ ነገረፈጅ #አለShare #lawsocieties
ይህ ለጠቅላላ እውቀት ብቻ ነው።
ለበለጠ መረጃ ህግ ባለሙያ ያማክሩ!
#አለሕግ #AleHig
ሼር ለወዳጅ ዘመድ ጓደኛ።
👍202
ክፍት የሥራ ቦታ ማስታወቂያ
👆👆👆👆👆👆👆👆👆
የኢፌዲሪ ፍትሕ ሚኒስቴር

ተወዳዳሪዎችን በመጋበዝ በዐቃቤ ሕግ ደረጃ-II እና በዐቃቤ ሕግ ደረጃ-I መደብ አወዳድሮ ለመቅጠር በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ማስታወቂያ ማውጣቱ ይታወቃል። 

በማስታወቂያው የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተወዳዳሪዎች ይህን ሊንክ  https://forms.gle/gsVXMso8EnAsPEvc9 ተጭናችሁ በተገቢው በመሙላት ባላችሁበት ሆናችሁ መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።
የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ፍትሕ ሚኒስቴር


👉Facebook Page 👈

👉Telegram Channel 👈


Website
http://alehig.wordpress.com
👍32
በተከራካሪው የተወከለው ጠበቃ ሌል ችሎት ስለተደረበበት ክርክሩ በሚሰማበት ቀን መቅረብ ባለመቻሉ መዝገቡ ከተዘጋ እንደነገሩ ሁኔታ በቂ ምክንያት በመሆኑ የተዘጋው መዝገብ ሊከፈት ይገባል።

ሰ.መ.ቁ. 182136 ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም

በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.74 [2] ደንጋጌ መሰረት “በቂ ሆኖ የሚገመት እክል” ምን እንደሆነ የተመለከተ ባይሆንም አመልካች ቀጠሮ ለመቅረት የቻለዉ በምን ምክንያት እንደሆነ አጠቃላይ ሁኔታዉን መመርመር የሚያስፈልግ ሆኖ፣ አመልካች በራሱ ጉድለት ወይም ቸልተኛነት ቀጠሮዉን ሳይከታተል ቀርቶ ካልሆነ በስተቀር፣ ፍትሕ የማግኘትና የመከራከር መብት ከግምት በማስገባት አመልካችን የገጠመዉ እክል እንደበቂ ምክንያት በመውሰድ ለተጠሪ [መዝገቡ የተዘጋው በክልል ሰበር ችሎት በነበረው ክርክር ነው] ተገቢ ኪሳራና ወጪ በማስከፈል፣ የተዘጋዉ መዝገብ ተከፍቶ ክርክሩ እንዲሰማ መድረጉ አግባብ ነዉ። በመሆኑም አመልካች ክርክሩን በጠበቃ ለማካሄድ ወስኖ በሕጉ አግባብ ተገቢዉን ዉክልና ሰጥቶ እያለ ጠበቃዉ ችሎት በሚሰጠዉ ቀነ ቀጠሮ ተገኝቶ አመልካችን ወክሎ ተገቢዉን ክርክር የማቅረብ ኃላፊነት ይኖርበታል። ነገር ግን ጠበቃ የተለያዩ ደንበኞች ሊኖሩት ስለሚችል ፍ/ቤት በሚሰጠዉ ቀነ ቀጠሮ በተቻለ መጠን ለደንበኞቹ ተገቢዉን የጥብቅና አገልግሎት መስጠት በሚያስችለዉ አግባብ አጀንዳዉን አስማምቶ ቀጠሮ እንዲያዝለት ለፍ/ቤቱ ማመልከት ይጠበቅበታል። ይህም ሆኖ ቀጠሮ ተደራርቦበት በአንድ ጊዜ በተለያዩ ችሎቶች የሚቀርበበትን እድል በማዛባቱ ምክንያት የባለጉዳዩ መዝገብ ከፍ ሲል በተጠቀሰዉ የህጉ ድንጋጌ መሰረት ተዘግቶ እንደሆነ፣ አጠቃላይ የነገሩን ሁኔታ በመመርመር፣ የአመልካች የመከራከርና ፍትሕ የማግኘት መብት ታሳቢ በማድረግ መዝገቡ ተከፍቶ ክርክሩ እንዲሰማ ማድረጉ ተገቢ ነዉ።

#ጠበቃ #አብርሀምዮሀንስ

ይህ ለጠቅላላ እውቀት ብቻ ነው።
ለበለጠ መረጃ ህግ ባለሙያ ያማክሩ!

Alternative legal enlightenment(ALE)#አለሕግ Affordable&Accessible Legal Expertise አማራጭ የሕግ እውቀት፣ ነፃ የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ የሕግ ማብራርያ አለ፣ መሰረታዊ የሕግ እውቀት ያገኛሉ።

#አለሕግ #Alehig

👉Telegram Channel 👈
https://t.me/lawsocieties

👉Facebook Page
https://www.facebook.com/lawsocieties/

👉YouTube 👈
https://www.youtube.com/@Ale_Hig
👍14🔥2
Breaking News .......

The former Ethiopian Investment commission deputy commisioner and the current Ethio post CEO, Mrs. Hana Arayaselassie, become the new Head of the Ethiopian Investment commission .


Alternative legal enlightenment(ALE)#አለሕግ Affordable&Accessible Legal Expertise

#አለሕግ #Alehig

👉Telegram Channel 👈
https://t.me/lawsocieties

👉Facebook Page
https://www.facebook.com/lawsocieties/

👉YouTube 👈
https://www.youtube.com/@Ale_Hig
9👍6👎2
ሰበር መዝገብ ቁጥር 93501 መጋቢት 12 ቀን 2006 ዓ/ም

አንድ አውራሽ ኑዛዜ ትቶ በሞተና ኑዛዜው ወራሾች በተገኙበት ጊዜ ተነቦ ሲገኝ በኑዛዜው ላይ ተቃውሞ ያለው ወራሽ ተቃውሞውን ሊያነሳ የሚችልበት የጊዜ ገደብ 
የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 973 እና 974 ድንጋጌዎች ከውርስ ንብረት ድልድል ጋር ተያይዞ ኑዛዜው የማይፀናበትን ሁኔታ በሚመለከቱ ጉዳዮችን መሰረት በማድረግ በሚቀርቡት ተቃውሞች ላይ ተግባራዊ መሆን ያለባቸውን የይርጋ ጊዜያትን የሚያሳዩ እንጂ በሕግ ጥበቃ የተደረጉትን ከኑዛዜ አደራረግ ስርዓትና ከውርስ የመነቀል ጉዳዮች ጋር እንዲሁም
ይህ ችሎት የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 973  እና 974 ድንጋጌዎች በኑዛዜው መነበብ ጊዜ  የነበሩና ያልነበሩ ሰዎች ኑዛዜው ላይ  የሚቀርቡትን መቃወሚያ በምን ያህል ጊዜ ማቅረብ እንደአለባቸው በመለየት የሚያስቀምጡ ድንጋጌዎች  መሆናቸውን፣ ከድንጋጌዎች ይዘትና መንፈስ ምላሽ የሚያስፈልገው አቢይ ጥያቄ ግን በኑዛዜው ላይ ሊቀርብ የሚችለው መቃወሚያ አይነት ምን እንደሆነ ግን ግልፅ የሆኑ ምክንያቶችን  እንደማያስቀምጥ፣ነገር ግን የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 973(1)  ይዘት ሲታይ መቃወሚያው መሰረት ማድረግ ያለበት ኑዛዜው አይጸናም ወይም አንዱ በኑዛዜው የተነገረ ቃል አይፀናም በማለት መቃወሚያ ማቅረብ እንደሚችሉ ጥቅል በሆኑ አገላለፅ ያስቀመጠ ሲሆን አንድ ኑዛዜ አይፀናም ወይም በኑዛዜው ላይ የተነገረ ቃል አይፀናም የሚባልባቸውን ሕጋዊ ምክንያቶችን ዝርዝር በሆነ ወይም አመላካች በሆነ ሁኔታ አላማስቀመጡን፣እንዲህ መሆኑ ግን የድንጋጌውን ትክክለኛ ተፈፃሚነት ለመለየት ሌሎች የውርስ ህግ ድንጋጌዎችን በማስተሳሰርና ተገቢውን የሕግ አተረጋጎም በመከተል በድንጋጌ ስር የሰፈረውን የሕግ አውጪውን ሐሳብ ለመየት አይቻልም ወደሚለው ድምዳሜ የማያደርስ መሆኑን፣ አንድ ኑዛዜ አይጸናም የሚባልባቸውን ሕጋዊ ምክንያቶች ምን ምን እንደሆኑ በቅድሚያ ማየቱ ተገቢ መሆኑን፣ የኑዛዜ በህግ ፊት ያለመፅናትን የሚያስከትሉ ምክንያቶች የኑዛዜው በሕግ ፊት ውድቅ የሆነ መሆን ወይም የኑዛዜ መሻር መሆናቸውን ስለኑዛዜ አደራረግ ፎርማሊቲ የሚያወሱትንና ስለኑዛዜ መሻር የሚደነግጉትን በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 881 እና 898  ተከታይ ድንጋጌዎች ስር ያሉትን ቁጥሮች በማየት የምንረዳው ጉዳይ ስለመሆኑ፣ድንጋጌዎቹ አንድ ኑዛዜ በሕግ ፊት የሚፀናው በሕጉ አግባብ በተዘረጋው ስርዓት ተደርጎ የተገኘ ከሆነ እና በሕጉ አግባብ ያልተሻረ መሆኑ ሲረጋገጥ መሆኑን እንደሚያሳዩ፣ ኑዛዜው በሕግ ፊት የሚጸናው ሕጉን ተቃራኒ ሆኖ እስካልተገኘ ድረስ መሆኑን፣ኑዛዜው በህግ የተቀመጠውን የአጻጻፍ ስርዓት ተከትሎ መከናወን ያለበት ከመሆኑም በላይ ሕጉ ለተናዛዡ የሠጠውን የመብት አድማስ ሳያልፍ በወራሽ መብት ላይም ተፈፃሚ እንዲሆን በሚያስችል መልኩ ተደርጎ መገኘት እንደአለበት፣አውራሽ ኑዛዜ ማድረግ የራሱ የግሉ ስራ እና መብቱ ስለመሆኑ ሕጉ በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 857 ያስቀመጠው በሕጉ ገደብ የተደረገባቸውን ሁኔታዎችን ሳያልፍ እንዲደረግ በማሰብ መሆኑን የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 857 ድንጋጌውን ስለኑዛዜ አደራረግ ስርዓትና ከውርስ ስለመነቀል ከሚደነግጉነት ድንጋጌዎችና ሌሎች በአውራሹ ገደብ የሚያደርጉት የውርስ ህግ ድንጋጌዎችን በአንድ ላይ በማንበብ የምንገነዘበው ጉዳይ ስለመሆኑ ዘርዝሮ በሕግ የተከለከለን ነገር አንድ አውራሽ በኑዛዜ አስፍሮ ቢገኝና በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 973 እና 974 ድንጋጌዎች አግባብ ኑዛዜው ሲነበብ ቢኖር ወይም ባይኖር ተቃውሞ ማቅረብ የግድ የሚል ነው ወይስ? በሕጉ ጥበቃ የተደረገለትን መብት ለማስከበር የሚችልበት ሁኔታ እንዳለ በማመን በሌሎች በውርስ ሕጉ በተመለከቱት የይርጋ ሕግ ድንጋጌዎች መሰረት ጥያቄውን ማቅረብ ይችላል? የሚለውን  የሕግ ጥያቄ አንስቶ በመጨረሻም ላይ በሕጉ ጥበቃ የተደረለትን መብት የሚጎዳ ተግባር ተፈፅሞ ሲገኝ ተቃውሞ መቅረብ ያለበት ሕጉ በግልጽ ተቃውሞው መቅረብ ያለበትን የጊዜ ገደብ አስቀምጦ ሲገኝ እንደሆነና ተቃውሞ አቅራቢ ለተቃውሞው አቀራረብ በሕጉ የተደረገ የጊዜ ገደብ መኖሩን ሊያውቅ  እንደሚገባ እንዲሁም ሕጉ ስለተቃውሞ አቀራረብ በግልጽ ባላስቀመጠበትና ሕጉ መብቱን በጠበቀበት ሁኔታ ግን በሕግ የተከለከለ ተግባር የፈጸመ ሰው ወይም የዚሁን ሰው ተግባር እንዲያጣራ በሕጉ አግባብ ኃላፊነትና ተግባር የተሰጠው ሰው ተግባሩን ለባለመብቱ ከገለፀበት ጊዜ ጀምሮ በሚቆጠርና ለሌላ ህጋዊ ምክንያት የተቀመጠውን የይርጋ ጊዜ መሰረት አድርጎ በባለመብቱ ላይ ክርክር ሊያቀርብ የሚችልበት የይርጋ ሕግ ጽንሰ ሃሳብ  አለመኖሩን በአቢይ ምክንያትነት ይዞ የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 973 እና 974 ድንጋጌዎች ከውርስ ንብረት ድልድል ጋር ተያይዞ ኑዛዜው የማይፀናበትን ሁኔታ በሚመለከቱ ጉዳዮችን መሰረት በማድረግ በሚቀርቡት ተቃውሞች ላይ ተግባራዊ መሆን ያለባቸውን የይርጋ ጊዜያትን የሚያሳዩ እንጂ በሕግ ጥበቃ የተደረጉትን ከኑዛዜ አደራረግ ስርዓትና ከውርስ የመነቀል ጉዳዮች ጋር እንዲሁም በሌላ ሰው ንብረት ላይ ኑዛዜ ተደርጎ ሲገኝ በንብረቱ ላይ መብት አለን የሚሉት ሰዎች የሚያነሱትን ጥያቄ ሁሉ የሚሸፍኑ አይደለም በማለት ደምደሞ ስለ ድንጋጌዎች አፈጻጸም በአዋጅ ቁጥር 454/1997 አንቀጽ 2(1)  በየትኛውም እርከን የሚገኝ ፍርድ ቤት የሚያስገድድ የህግ ትርጉም በሰ/መ/ቁጥር 70292 መጋቢት 13 ቀን 2005 ዓ/ም በዋለው ችሎት ሰጥቶአል፡፡
    ከዚህ አንፃር ጉዳዩን ስንመለከተው የተጠሪ የዳኝነት ጥያቄ ሟች እናታቸው ያደረጉት ኑዛዜ በተዘዋዋሪ ያለምክንያት ከውርስ የነቀላቸውና የጎዳቸው መሆኑን የሚጠቅስና ከፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 938 እና 939 ድንጋጌዎች ይዘትና መንፈስ ታይቶ የሚወሰን በመሆኑ ለጉዳዩ አግባብነት ያለው የይርጋ ድንጋጌ በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 973 እና 974 ድንጋጌዎች ስር የተመለከተው ሁኖ አልተገኘም፡፡ ይሁን እንጂ የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 973 እና 974 ስር የተመለከቱተት ድንጋጌዎች ለጉዳዩ አግባብነት የላቸውም ማለት ግን በሌላ ድንጋጌ አግባብ የይርጋው ክርክር አይታይም ማለት አይደለም፡፡ጥያቄው የይርጋ ጊዜ ገደብ የለውም ሊባል የሚችልበት ምክንያት የለም፡፡ክርክሩ የሚካሄደው በአባትም ሆነ በእናት በሚገናኙና የሁሉቱንም መብትና ግዴታ ለመውረስ በሚችሉ የመጀመሪያ ደረጃ ወራሾች መካከል ነው፡፡ በመሆኑም የወራሽነት ጥያቄ አንድ ወራሽ በሌላ በወራሽነት የውርስ ሀብት በያዘ ሰው ላይ ክስ ሲያቀርብ ተፈፃሚነት ባላቸው የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1000 (1) እና (2) ደንጋጌዎች ስር በተመለከቱት ደንቦች መሰረት የሚገደብ ነው፡፡በዚህም መሰረት የውርስ ንብረት ይገባኛል ጥያቄ መጠየቅ ያለበት ንብረቱ በሌላ ወራሽ መያዙ ከታወቀበት ጊዜ ጀምሮ በሦስት አመት ጊዜ መሆኑን እና በማናቸውም ጊዜ ግን ከአስራ አምስት አመት በኋላ ሊቀርብ የማይገባ መሆኑን ነው፡፡እነዚህ ድንጋጌዎች ተፈጻሚነት ያላቸው በወራሾች መካከል ስለመሆኑም ይህ ችሎት አግባብነት የላቸውን የውርስ ሕግ ድንጋጌዎችን በመመርመር በአዋጅ ቁጥር 454/97 መሰረት በየትኛውም እርከን የሚገኝ ፍርድ ቤት የሚያስገድድ የሕግ ትርጉም በመ/ቁጥር 15974 እና በሌሎች በርካታ መዛግብት ሰጥቶበታል፡፡ለጉዳዩ አግባብነት ያለው ድንጋጌ የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1000 መሆኑን ተገንዝበናል፡፡ለዚህ ጉዳይም ተፈፃሚነት ያለው በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1000 ስር የተመለከተው የይርጋ ጊዜ ነው፡፡
አብርሀም ዮሀንስ
https://t.me/lawsocieties
http://alehig.wordpress.com
https://t.me/alehig
👍112🔥1
Public #Access To #Legal #Information In Ethiopia
🎙Key Note Speaker: Mikias Melak
Public access to legal information in Ethiopia encompasses the availability and accessibility of legal resources like laws, cases, policies, and institutions for the general populace. It plays a crucial role in advancing the rule of law, human rights, democracy, and good governance in the country.

Despite Ethiopia's ratification of various international and regional human rights instruments affirming citizens' right to access justice and information, barriers exist. These hurdles include poverty, illiteracy, language disparities, geographical distance, corruption, discrimination, and lack of awareness.
👍152
አለሕግAleHig ️
Public #Access To #Legal #Information In Ethiopia 🎙Key Note Speaker: Mikias Melak Public access to legal information in Ethiopia encompasses the availability and accessibility of legal resources like laws, cases, policies, and institutions for the general…
To overcome these challenges, diverse initiatives by the government, civil society, and development partners aim to enhance public access to legal information. The Ethiopian Institutions of Ombudsman (EIO) leads the implementation of the 2008 Freedom of Expression and Access to Information Proclamation, monitoring progress and ongoing efforts. Additionally, Public Information Noble (PIN) Ethiopia collaborates with IEYA ongoing advocacy to ATI focuses on training, manuals, procedures, and awareness campaigns to address both demand and supply aspects of access to information.

The Alehig/አለሕግ platform is set to contribute significantly by providing searchable databases of Ethiopian laws, cases, and legal resources. It also includes audio files tailored for lawyers with visual impairments, ensuring inclusivity in legal information access.
Mikias Melak Birhanie
Attorney & consultant at law
https://t.me/lawsocieties
👍142
Screenshot_20240120-183542.png
763.9 KB
ማስታወቂያ

የምስራቅ ጉራጌ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ንዑስ የዳኞች አስተዳደር ጉባኤ ቀጥሎ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ እጩ ዳኞችን መልምሎ ማሾም ይፈልጋል።

https://t.me/lawsocieties
👍5
በአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 መሰረት የሚደረግ
የሰራተኞች ቅነሳ እና ውጤቱ
አንድ ሀገር በኢኮኖሚ እድገት የሚያሳየው፣ ዜጎች በትጋት ምርታማ (productive) ሆነው ስራቸውን መስራት ሲችሉ እና በአንፃሩ መብትና ጥቅማቸው በህግ አግባብ መከበር ሲችል ነው። በአሰሪና ሰራተኞች መካከል ያለውን የስራ ግንኙነት ለማስተዳደር ሁለቱንም አካል ሊገዛ የሚችል ህግ መውጣት እንዳለበት እሙን ነው። ሠራተኞችና አሠሪዎች የየራሳቸውን መብትና ጥቅም ለማስጠበቅና ግዴታዎቻቸውን በአግባቡ ለመወጣት እንዲያስችላቸው የኅብረት ስምምነት ድርድር በማድረግ፤ በመካከላቸው የሚነሱ የወልም ሆነ የግል የሥራ ክርክሮች፣ የማኅበራዊ ምክክር ሥርዓትን ጨምሮ በተጨማሪ አማራጭ መድረኮች በተቀላጠፈ ሁኔታ መፍትሔ እንዲያገኙ የሚያስችል ሥርዓት መዘርጋት አስፈላጊ ነው። በመሆኑም መሠረታዊ የሥራ ላይ መብቶችንና ግዴታዎችን ለመጠበቅ እንዲቻል የአሰሪና ሰራተኛ ህግ በኢትዮጵያ ወጥቶ ተግባራዊ ሆኗል፡፡
በዚህ አጭር ጽሁፍም በግል በተቋቋሙ ድርጅቶችና መንግስታዊ በሆኑ የልማት ድርጅቶች ተቀጥረው በሚሰሩ ሰራተኞች ላይ ተፈጻሚነት ባለው የአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 ላይ ተደንግጎ የሚገኘውን የሰራተኞች ቅነሳ እና ውጤቱን እንመለከታለን።
የሰራተኞች ቅነሳ መቼ ይደረጋል?
የሰራተኞች ቅነሳ በአንድ ድርጅት ውስጥ ሊደረግ የሚችለው የድርጅቱን ድርጅታዊ አቋም ወይም የሥራ እንቅስቃሴ በሚመለከት በሚከተሉት ምክንያቶች የሥራ ውል ሲቋረጥ ነው:-
👍112
አለሕግAleHig ️
በአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 መሰረት የሚደረግ የሰራተኞች ቅነሳ እና ውጤቱ አንድ ሀገር በኢኮኖሚ እድገት የሚያሳየው፣ ዜጎች በትጋት ምርታማ (productive) ሆነው ስራቸውን መስራት ሲችሉ እና በአንፃሩ መብትና ጥቅማቸው በህግ አግባብ መከበር ሲችል ነው። በአሰሪና ሰራተኞች መካከል ያለውን የስራ ግንኙነት ለማስተዳደር ሁለቱንም አካል ሊገዛ የሚችል ህግ መውጣት እንዳለበት እሙን ነው።…
በአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 መሰረት የሚደረግ
የሰራተኞች ቅነሳ እና ውጤቱ
አንድ ሀገር በኢኮኖሚ እድገት የሚያሳየው፣ ዜጎች በትጋት ምርታማ (productive) ሆነው ስራቸውን መስራት ሲችሉ እና በአንፃሩ መብትና ጥቅማቸው በህግ አግባብ መከበር ሲችል ነው። በአሰሪና ሰራተኞች መካከል ያለውን የስራ ግንኙነት ለማስተዳደር ሁለቱንም አካል ሊገዛ የሚችል ህግ መውጣት እንዳለበት እሙን ነው። ሠራተኞችና አሠሪዎች የየራሳቸውን መብትና ጥቅም ለማስጠበቅና ግዴታዎቻቸውን በአግባቡ ለመወጣት እንዲያስችላቸው የኅብረት ስምምነት ድርድር በማድረግ፤ በመካከላቸው የሚነሱ የወልም ሆነ የግል የሥራ ክርክሮች፣ የማኅበራዊ ምክክር ሥርዓትን ጨምሮ በተጨማሪ አማራጭ መድረኮች በተቀላጠፈ ሁኔታ መፍትሔ እንዲያገኙ የሚያስችል ሥርዓት መዘርጋት አስፈላጊ ነው። በመሆኑም መሠረታዊ የሥራ ላይ መብቶችንና ግዴታዎችን ለመጠበቅ እንዲቻል የአሰሪና ሰራተኛ ህግ በኢትዮጵያ ወጥቶ ተግባራዊ ሆኗል፡፡
በዚህ አጭር ጽሁፍም በግል በተቋቋሙ ድርጅቶችና መንግስታዊ በሆኑ የልማት ድርጅቶች ተቀጥረው በሚሰሩ ሰራተኞች ላይ ተፈጻሚነት ባለው የአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 ላይ ተደንግጎ የሚገኘውን የሰራተኞች ቅነሳ እና ውጤቱን እንመለከታለን።
የሰራተኞች ቅነሳ መቼ ይደረጋል?
የሰራተኞች ቅነሳ በአንድ ድርጅት ውስጥ ሊደረግ የሚችለው የድርጅቱን ድርጅታዊ አቋም ወይም የሥራ እንቅስቃሴ በሚመለከት በሚከተሉት ምክንያቶች የሥራ ውል ሲቋረጥ ነው:-
• ሠራተኞች የተሰማሩባቸው ሥራዎች በከፊልም ሆነ በሙሉ በቀጥታና ለዘለቄታው የሚያስቆም የሥራ ውል መቋረጥ የሚያስከትል ሁኔታ ሲከሰት፤
• በአዋጁ አንቀጽ 18(5) እና (6) ላይ የተቀመጡት ከስራ ውል የሚመነጩ መብቶችና ግዴታዎች ለጊዜያዊ የሚታገዱበት ሁኔታ እንደተጠበቀ ሆኖ አሠሪው በሚያመርታቸው ምርቶች ወይም በሚሰጣቸው አገልግሎቶች ተፈላጊነት መቀነስ ምክንያት የድርጅቱ የሥራ እንቅስቃሴ በመቀዝቀዙ ወይም ትርፍ እየቀነሰ በመሄዱ የሥራ ውል ማቋረጥ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ፤
• የድርጅቱን ምርታማነት ለማሳደግ የአሠራር ዘዴዎችን ለመለወጥ ወይም በአዲስ ቴክኖሎጂ ለመጠቀም ሲባል የሚደረግ የሥራ ውል መቋረጥ የሚያስከትል ውሣኔ ናቸው፡፡
የሰራተኞች ቅነሳ ነው ሊያስብል የሚችለው ከላይ በተጠቀሱት ምክንያቶች ቁጥራቸው ከድርጅቱ ሠራተኞች ቢያንስ ከመቶ አሥር የሚያህለውን ወይም የሠራተኞች ቁጥር (የአንድ አመት አማካኝ የሰራተኞች ቁጥር) ከሀያ እስከ ሀምሳ በሆነበት ድርጅት ቢያንስ አምስት ሠራተኞችን የሚመለከት ከአሥር ተከታታይ ቀናት ላላነሰ ጊዜ የሚቆይ የሥራ ውል መቋረጥ ሲከሰት እንደሆነ በአስሪና ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 አንቀጽ 29 ላይ በግልጽ ተደንግጎ ይገኛል፡፡
የሰራተኞች ቅነሳ ሂደት
በአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ መሰረት የሰራተኞች ቅነሳ ሲደረግ አሰሪ በራሱ ጊዜ የፈለገውን ሰራተኛ መቀነስ የማይችል ሲሆን ከላይ በተዘረዘሩት ምክንያቶች የሰራተኞች ቅነሳ ሲደረግ በመጀመሪያ አሠሪው ከሠራተኞች ማኅበር ወይም ተወካይ ጋር በመመካከር የሥራ ችሎታ ያላቸውና ከፍተኛ የምርት ውጤት የሚያሳዩ ሠራተኞች በሥራቸው ላይ እንዲቆዩ ያደርጋል ወይም ከማይቀነሱ ሰራተኞች መካከል ይሆናሉ፡፡ ነገር ግን በድርጅቱ ውስጥ ተመሳሳይ የሥራ ችሎታ ያላቸውና ተመሳሳይ የምርት ውጤት የሚያመርቱ ሠራተኞች በሚኖሩ ጊዜ የሰራተኞች ቅነሳ የሚደረገው በሚከተለው ቅደም ተከተል መሠረት ይሆናል:-
1. በድርጅቱ ውስጥ ለአጭር ጊዜ ያገለገሉ ሠራተኞች፤
2. አነስተኛ ቁጥር የሆነ ጥገኞች ያሏቸው ሠራተኞች፤
3. ከተራ ቁጥረ (4) እስከ (7) ከተዘረዘሩት የሠራተኛ ክፍሎች ውጭ የሆኑ ሠራተኞች ቅነሳው በመጀመሪያ ደረጃ የሚመለከታቸው ይሆናል፤
4. አካል ጉዳተኛ የሆኑ ሠራተኞች፤
5. በድርጅቱ ሳሉ በሥራ ምክንያት ጉዳት የደረሰባቸው ሠራተኞች፤
6. የሠራተኞች ተጠሪዎች፤
7. ነፍሰጡር ሠራተኞች ወይም ከወለዱ እስከ 4 ወር ድረስ የሆናቸው ሴት ሠራተኞች ናቸው፡፡
በልዩ ሁኔታ የኮንስትራክሽን ስራ ማለትም ሕንጻ፣ መንገድ፣ የባቡር ሐዲድ፣ የባሕር ወደብ፣ የውሃ ግድብ፣ ድልድይ፣ የመሣሪያ ተከላና ሌላም ተመሳሳይ ሥራ የመሥራት የመለወጥ፣ የማስፋፋት፣ የማደስና የመጠገን ሥራ ተከታታይነት እያለቀ ሲሄድ የሥራው መጠን በመቀነሱ ምክንያት ተቀጥረው በሚሰሩ ሠራተኞች ላይ ቅነሳ ሲደረግ አሠሪው በዚህ ከላይ የተመለከቱትን የሠራተኞች ቅነሳ ሥነ ሥርዓት መከተል አይጠበቅበትም፡፡ ነገር ግን ሰራተኞች የተቀጠሩበት ሥራ ከማለቁ በፊት ከሆነ የሰራተኛ ቅነሳ ሲደረግ በአዋጁ ላይ የተገለጸውን ሥነ-ሥርአት መከተል የግድ ይለዋል። በተጨማሪም ቅነሳ ለማካሄድ አሰሪው የሁለት ወር ቅድመ ማስጠንቀቂያ ለሚቀነሱት ሰራተኞች የመስጠት ግዴታ አለበት (አንቀፅ 35/1/መ)፡፡ እንዲሁም ድርጅቱ የሚወስደው እርምጃ፣ ከሰራተኞች ጋር የህብረት ስምምነት ካለው ይህንኑ እና የስራና ክህሎት ሚኒስቴር በዚህ ረገድ የሚያወጣውን መመሪያ ያከበረ መሆን አለበት፡፡
የሰራተኞች ቅነሳ ያለው ውጤት
አንድ ሰራተኛ በአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ አንቀጽ 29 መሰረት በሰራተኞች ቅነሳ ምክንያት የስራ ውሉ ሲቋረጥ የስራ ስንብት ክፍያ የማግኘት መብት አለው። የስራ ስንብት ክፍያ መጠንን በተመለከተ ለመጀመሪያው የአንድ ዓመት አገልግሎት የሠራተኛው ማለትም የተቀነሰው ሰራተኛ የመጨረሻ ሣምንት አማካይ የቀን ደመወዙ በ30 ተባዝቶ ይከፈለዋል፡ከአንድ ዓመት በታች አግልግሎ ለተቀነሰ ሰራተኛ ግን እንደአገልግሎት ጊዜው እየተተመነ ተመጣጣኝ ክፍያ ያገኛል፡፡ ከአንድ ዓመት በላይ አገልግሎ በሰራተኛ ቅነሳ ምክንያት የስራ ውሉ የተቋረጠበት ሠራተኛ ከላይ በተጠቀሰው ክፍያ ላይ ለእያንዳንዱ ተጨማሪ የአገልግሎት ዓመት ከላይ የተጠቀሰው ክፍያ አንድ ሦስተኛ እየታከለ የስራ ስንብት ክፍያው ይከፈለዋል፡፡ ነገር ግን ጠቅላላው ክፍያ ከሠራተኛው የ12 ወራት ደመወዝ መብለጥ የለበትም፡፡
በሰራተኞች ቅነሳ ምክንያት የስራ ውሉ ተቋርጦ ከስራ የተሰናበተ ሰራተኛ ከላይ ከተጠቀሰው የስራ ስንብት ክፍያ በተጨማሪ የሠራተኛው የመጨረሻ ሣምንት አማካይ የቀን ደመወዝ በ60 ተባዝቶ እንደሚከፈለው በአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ አንቀጽ 40 ላይ ተደንግጎ ይገኛል፡፡ ከዚህ ባለፈ አለመግባባት የሚፈጠር ከሆነ ሰላማዊ የኢንዱስትሪ ሰላም ለመፍጠር፣ ምርታማነትን ለማሻሻል ብሎም የሰራተኞች ህጋዊ መብቶች ለማስክበር በስራና ክህሎ ሚኒስቴር በሚመደብ አስማሚ ችግሩ እንዲፈታ መመልከት ወይም ይህን መሰል ጉዳይ የወል ስራ ክርክር በመሆኑ ለአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ ወሳኝ ቦርድ ዳኝነት መጠየቅ ይቻላል፡፡
Federal Justice and Law Institute
Alternative legal enlightenment (ALE)አለ
አማራጭ የሕግ እውቀት፣
ነፃ የሕግ ምክርና ድጋፍ ሰጪ ሕግ ባለሙያዎች፣ የተለያዩ የሕግ ማብራርያ ያገኛሉ 🔴

https://alehig.wordpress.com/blog-2/
#አለሕግ #Alehig

👉Telegram Channel 👈
https://t.me/lawsocieties

👉Facebook Page 👈
https://www.facebook.com/lawsocieties/

👉YouTube 👈
https://www.youtube.com/@Ale_Hig
👍243👎1🥰1
Forwarded from አለሕግAleHig ️ (Alemwaza)
🛑በጡረታ መገለል🛑
👆👆👆👆👆👆👆👆

ዋቢ ህጎች

የአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 1156/2011

የግል ድርጅት ሠራተኞች ጡረታ አዋጅ አዋጅ ቁጥር 715/2003

የመንግሥት የሠራተኞች ጡረታ አዋጅ ቁጥር 714/2003

የአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 አንቀፅ 243/ በሕግ በተደነገገው መሠረት የሥራ ውልን ስለማቋረጥ ብሎ በጡረታ መገለልን እንደ አንድ ውል የሚቋረጥበት መንገድ ያስቀምጠዋል፡፡ 24(3) ሠራተኛው አግባብ ባለው ሕግ መሠረት በጡረታ ሲገለል፤

በጡረታ መገለል
👇👇👇👇
የመንግሥት የሠራተኞች ጡረታ አዋጅ ቁጥር 714/2003 አንቀፅ 18(1) /ሐ መሰረት የጡረታ መውጫ ዕድሜ 60 ዓመት ነው፡፡ የመንግስት ሰራተኞች የጡረታ መውጫ ዕድሜ (በእንግሊዝኛው ቅጂ ላይ retirement age) ስድሳ ዓመት እንዲሆን ተወስኗል፡፡ ጡረታ መውጣት ማለት በህጉ የተወሰነው የስድሳ ዓመት እድሜ ላይ መድረስ ማለት ነው፡፡

በህግ የተቀመጠው የጡረታ ዕድሜ 60 ዓመት ሲሆን የሚሰላውም ሠራተኛው ለመጀመሪያ ጊዜ ሲቀጠር በቅድሚያ የመዘገበውን የልደት ዘመን መሠረት በማድረግ ነው፡፡ ሠራተኛው በህግ የተወሰነው የ60 ዓመት የጡረታ መውጫ እድሜ ላይ ሲደርስ የሥራ ውሉን ያቋረጠው ህግ እንጂ አሠሪው ባለመሆኑ የሥራ ውሌ ከህግ ውጪ ተቋርጧል በሚል የሚያነሳው ጥያቄ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
“ሠራተኛው አግባብ ባለው ህግ መሠረት በጡረታ ሲገለል” የሥራ ውሉ በሕግ በተደነገገው መሰረት ይቋረጣል፡፡
ሠራተኛው የጡረታ እድሜ ላይ ደርሶ ከተቀጣሪነት ወደ ተጧሪነት ሲሸጋገር የሥራ ውሉም ያለ ተጨማሪ ቅድመ ሁኔታ ወዲያውኑ ያበቃለታል፡፡ ያ ማለት ግን ከጡረታ በኋላ እንደገና በአዲስ መልክ ተቀጣሪ ለመሆን አይችልም ማለት አይደለም፡፡ ጡረተኛው ካካበተው የረጅም ጊዜ የሥራ ልምድ እና ተሞክሮ አንጻር በተለይ በአንዳንድ የሥራ መስኮች ላይ ተፈላጊነቱ ይጨምራል፡፡ ሆኖም በቋሚነት (ላልተወሰነ) ጊዜ የመቀጠር እድል የለውም፡፡
በአዲሱ አዋጅ ቁ.714/2003 ብሎም በግል ድርጅት ሠራተኞች የጡረታ አዋጅ 715/2003 አንድ ሠራተኛ የጡረታ መውጫ ዕድሜው ከመድረሱ በፊት ጡረታ የሚወጣበት ወይም በጡረታ የሚገለልበት ስርዓት የለም፡፡ ሆኖም ዕድሜው ለጡረታ ሳይደርስ የጡረታ አበል ባለመብትና ተጠቃሚ ሊሆን ይችላል፡፡ በአዋጅ ቁ. 345/1995 አንቀጽ 12(2) እንደተደነገገው ቢያንስ 20 ዓመት አገልግሎት ያለው የመንግስት ሠራተኛ በራሱ ፈቃድ ወይም በአዋጁ ከተጠቀሱት ውጪ በሆነ ምክንያት አገልግሎት ካቋረጠ የጡረታ መውጫ ዕድሜው ሲደርስ የአገልግሎት ጡረታ አበል እስከ ዕድሜ ልኩ ይከፈለዋል፡፡ ድንጋጌው ሠራተኛውን የጡረታ አበል ተጠቃሚ ወይም ተከፋይ ሳይሆን የጡረታ ባለመብት ያደርገዋል፡ በዚህ መልኩ የሚገኝ የጡረታ ባለመብትነት በአዋጅ ቁ 714/2003 እና በአዋጅ 715/2003 ላይም በተመሳሳይ መልኩ ተደንግጓል፡፡ ሆኖም የሥራ ውሉ የተቋረጠው ሃያ አምስት ዓመት አገልግሎት ከሰጠ በኋላ ከሆነ የጡረታ መውጫ ዕድሜው ሊደርስ አምስት ዓመት ሲቀረው የጡረታ አበል ተጠቃሚነት ወይም ተከፋይነት መብት ይኖረዋል፡፡

https://telegram.me/lawsocieties
Alternative legal enlightenment (ALE)አለ Provided by Legal Experts.
አማራጭ የሕግ እውቀት፣
ነፃ የሕግ ምክርና ድጋፍ ሰጪ ሕግ ባለሙያዎች፣ የተለያዩ የሕግ ማብራርያ ያገኛሉ 🔴

#አለሕግ #Alehig

👉Telegram Channel 👈
https://t.me/lawsocieties

👉Facebook Page 👈
https://www.facebook.com/lawsocieties/

👉YouTube 👈
https://youtube.com/@Lawsocieties
👍15
Hello AleHig family I need your help on finding a case of defamation in civil and Criminal case which held for the public interst (defamation took place over a public interst).
I hope you'll show me your support I'll compensate.
@Hubu_alnafs or 0945614343.
👍3👎1
Vacancy Notice for 16 Round Training.pdf
11.8 MB
Amhara  regional state judicial training vacancy 2024
👍2