አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.87K photos
25 videos
1.86K files
3.58K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
Africa is leading, Ethiopia is on top

The world’s 10 fastest growing airline brands for 2023:

1. Ethiopian Airlines 🇪🇹
2. Vueling (Spain) 🇪🇸
3. United Airlines
4. China Southern 🇨🇳
5. American Airlines 🇺🇸
6. Korean 🇰🇷
7. Turkish 🇹🇴
8. China Eastern 🇨🇳
9. Alaska 🇺🇸
10.Qatar 🇶🇦

Source: @BrandFinance

Follow National Belt
👍214👏2
Federal Income Tax Explanatory Notes.docx
321.9 KB
የኢትዮጵያ የገቢ ግብር ማብራሪያ ፅሁፍ
Ethiopian Federal Income Tax Explanatory Notes
👍5🔥2
Forwarded from አለሕግAleHig ️ (Lawyer and Consultant)
የማስረጃ ህግና ህገ-መንግስቱ.pdf
15 MB
👍111
The 1995 FDRE Constitution Minutes - Part One (2).pdf
26.3 MB
የህገመንግስት ኮሚሽን ከ1ኛ-88ኛ መደበኛ ስብሰባ ቃለ ጉባኤ ጥራዝ
  #አለ_ህግ #Ale_Hig #Lawsocieties
https://t.me/lawsocieties
The 1995 FDRE Constitution Minutes - Part Two (2).pdf
38.1 MB
የህገመንግስት ኮሚሽን ከ1ኛ-88ኛ መደበኛ ስብሰባ ቃለ ጉባኤ ጥራዝ
  #አለ_ህግ #Ale_Hig #Lawsocieties
https://t.me/lawsocieties
👍51
procurement_directive_english (1).pdf
416.3 KB
Share 'procurement_directive_english (1).pdf'
👍4
ጋብቻ በአንደኛው ተጋቢ ሞት ምክንያት በፈረሰ ጊዜ የጋራም ሆነ የግል ንብረት በምን ያህል ጊዜ ውስጥ መጠየቅ እንዳለበት

በፍ/ብ/ህ/ቁ. 1677 መሠረት በቁ. 1845 ላይ የተቀመጠው #የ10_ዓመት ይርጋ ተፈፃሚ ስለመሆኑ፣

የፍ/ብ/ህ/ቁ. 1677፣ 1845   * ቅፅ-4 መ/ቁ 17937

ጋብቻ ልዩ ባህርይ ቢኖረውም ከሁለቱም ተጋቢዎች ስምምነት የሚመነጭ መብትና ግዴታም የሚጥል በመሆኑ በቤተሰብ ሕግ ግልጽ ድንጋጌ ሣይኖር ሲቀር በውል ሕግ መርሆች ወይም ድንጋጌዎች ተፈፃሚ ማድረግ የውል ሕግ አንቀጽ 1677ም የሚፈቅደው ነው:: ይኸው ድንጋጌ «ግዱታዎቹ ከውል የተገኙ ባይሆኑም የዚህ አንቀፅ ደንቦች ይፈፀሙባቸዋል» በማለት ይደነግጋል፡፡ የባልና ሚስት የንብረት ክርክር የተለየ የይርጋ ጊዜ ስለሌለው በዚህ ድንጋጌ መሠረት የውል ሕግ የይርጋ ድንጋጌዎች እንዲገዛ ማድረግ ተገቢ ነው:: የውል ሕግ ይርጋ አጠቃላይ ድንጋጌ በአንቀፅ 1845 እንደተገለፀው በሌላ አኳኋን ካልተወሰነ በስተቀር 10 ዓመት ነው፡፡

አውራሽ/ሟች/ በህይወት እያለ ከይዞታ ቦታው ላይ ለሌላ ሠው ቤት እንዲሠራ ፈቅዶ ቢሰጠው ሟች በሚሞትበት ጊዜ በሟች ፈቃድ ቤት የሠራው የቤቱ ባለቤት እንደሚሆንና ከሌላው ቦታ ጋር ሆኖ የውርስ ክፍል የሚሆን ስላለመሆኑ፣ የፍ/ህ/ቁ. 826/2/ እና 1179/1/። ሰ/መ/ቁ-96628  ቅፅ-17.
በመሆኑም ፈቅዶ የሰጠው ሟች የቦታውን መብት ለባለ ሀብቱ እያስተላለፈ /እያጠ/ ስለሆነ በፍ/ብ/ህ/ቁ/826/2/ መሰረት አውራሻቸው የሌለው መብት ለወራሾች ሊተላለፍ የሚችልበት የሕግ መሠረት የለም፡፡በፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 1179(1) መሠረት ባለመብት የሚሆነው አውራሽ ሳይቃወመው በራሱ ወጭ በሠራቸው ቤቶችና ቤቶቹ በተሰሩበት ወይም ባረፉበት ቦታ ላይ ብቻ ይሆናል ።ይህ ቦታም የውርስ ሀብት ክፍል በሆኑ ንብረቶቹ ውስጥ ሊካተት አይችልም ።
  #አለ_ህግ #Ale_Hig #Lawsocieties
https://t.me/lawsocieties
👍13🔥21👏1
በግብይት_የተገኘ_ንብረት_የግል_ይባልልኝ.pdf
76.3 KB
ባልና ሚስት ከትዳር በፊት ያፈሯቸው ወይም ከትዳር በኋላ በውርስ ወይም በስጦታ ያገኟቸው ንብረቶች የግል ንብረታቸው ሆነው ይቀራሉ፡፡ እንዲሁም ባልና ሚስት ከተጋቡ በኋላ ከተጋቢዎች አንዱ የግል ሀብቱን ለውጦ፤ ንብረቱን ሸጦ ወይም በግል ገንዘቡ የሚያገኘው ገንዘብ ወይም ንብረት የግል ንብረቱ ይሆናል፡፡
ነገር ግን ከላይ በተገለጸው መልኩ በግብይት /ንብረት በመሸጥ፤ በመለወጥ ወይም በግል ገንዘብ በመግዛት/ የተገኘ ንብረት የግል ንብረት የሚሆነው ንብረቱን በግብይት ያገኘው ተጋቢ ይህ ንብረት የግል ይባልልኝ ብሎ ለፍርድ ቤት ጥያቄ ሲቀርብ እና ጥያቄው በፍርድ ቤት ውሳኔ መሠረት ተቀባይነት ሲያገኝ ብቻ ነው፡፡ ካልሆነ ይህ የግል ንብረት ይሆን የነበረው በግብይት የተገኘ ንብረት የጋራ ንብረት እንሆነ የሕግ ግምት ይወሰዳል፡፡
በግብይት የተገኘ ንብረት የግል ይባልልኝ በሚል የሚቀርብ ማመልከቻ ከዚህ በታች በተገለጸው ፎርም የሚቀርብ ሲሆን ጋብቻው በተፈጸመበት አከባቢ በሚገኘው ወይም በተጠሪ የመኖሪያ አድራሻ አከባቢ ለሚያስችለው ፍርድ ቤት ይቀርባል፡፡ አመልካች በግብይት የግል ንብረት ያፈራው ተጋቢ ሲሆን ተጠሪ ማለት ደግሞ ሌላኛው ተጋቢ ነው፡፡
https://t.me/lawsocieties
👍9
ሰ/መ/ቁጥር---228231 የካቲት 30 ቀን 2015 ዓ.ም
የተራ ዋስትና እና የአንድነት ዋስትና ልዩነት
በቅድሚያ ከባለዕዳው ተከራከር የማለት መብት ለመጠቀም መሟላት ያለባቸው ቅድመ ሁኔታዎች የፍ/ብ/ሕ/ቁ 1935(1) ዋሱ እንደ ተከሰሰ ወዲያውኑ ባለገንዘቡን ከባለዕዳው ጋር ተከራከር ካላለ በቀር ባለገንዘቡ ከዋናው ባለዕዳ ጋር ለመከራከር ግዴታ የለበትም በማለት ሲደነግግ የፍ/ብ/ሕ/ቁ 1936 ደግሞ በቅድሚያ ከባለዕዳው ተከራከር የሚለውን መብት ለመጠቀም እንደቅድመ ሁኔታ መሟላት ያለባቸው ነገሮች ያስቀመጠ ሲሆን ይኸውም ክርክሩን የሚጠይቀው ዋስ ለባለገንዘቡ የዋናውን ባለዕዳ ንብረቶች መምራትና ለዚሁም ክርክር የሚያስፈልገውን በቂ ወጪ አስቀድሞ ለባለገንዘቡ መስጠት አለበት በማለት አስቀምጧል።
ይህም የሚያስገነዝበን ዋሱ በቅድሚያ ከባለዕዳው ጋር ተከራከር የሚለውን መብት ለመጠቀም፥
አንደኛ ክሱ እንደቀረበበት ወዲያውኑ በቅድሚያ ከባለዕዳው ተከራከር በማለት ማንሳት አለበት፤
ሁለተኛ በደፈናው ባለዕዳው ንብረቶች ማለት ብቻ ሳይሆን ከክርክር ነጻ የሆኑ የባለዕዳው ንብረቶችን ቆጥሮ ወይም መርቶ ማሳየት አለበት፤
ሦስተኛ ለክርክር የሚያስፈልገውን በቂ ወጪ መዴቦ ለባለገንዘቡ መስጠት ይኖርበታል፡፡
ከእነዚህ ሦስት መስፈርቶች ውስጥ አንዱ እንኳ ካልተሟላ ባለገንዘቡን በቅድሚያ ከባለዕዳው ተከራከር የማለት መብቱን እንደሚያጣ በግልጽ ያሳያል፡፡ ይህ ማለት ደግሞ የክፍያው ጊዜ ደርሶ ገንዘቡ ያልተከፈለው ባለገንዘብ ቢፈልግ ባለዕዳውንና ዋሱን በአንድ ሊይ መክሰስ ወይም ባለዕዳውን ትቶ ዋሱን ብቻ መክሰስ የሚችል ሲሆን ተራ የሆነ ዋስትና ግዴታ የገባው ዋስ የአንድነት ዋስትና ከገባው ዋስ የሚለየው ከባለዕዳው ተከራከር የማለት መብቱን ቅድመ ሁኔታዎችን አሟልቶ በአግባቡ መጠቀም ሲችል ብቻ መሆኑን ነው፡፡
ቅድመ ሁኔታዎችን አሟልቶ ከባለዕዳው ጋር በቅድሚያ ተከራከር የማለት መብቱን ያልተጠቀመ ተራ ዋስ በተናጠልም ሆነ ከባለዕዳው ጋር በጋራ የዋስትና ግዴታ የገባውን ዕዳ አልከፍሌም ማለት የሚችልበት የሕግ አግባብ የለም፡፡
#Click Ethiopian Laws

👇👇👇👇👇👇
👍85
rights and benfit officals Proclamation 284..pdf
1.7 MB
አዋጅ ቁጥር 284/2014 ዓ.ም
የተሻሻለው ከኃላፊነት የተነሡ የአማራ
ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ የምክር ቤት አባላት፣ ዳኞችና ዓቃቤያነ ሕግ መብቶችና ጥቅሞችን መወሰኛ አዋጅ
Proclamation No. 284/2022
The Revised
......
https://t.me/lawsocieties
👍6