አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.87K photos
25 videos
1.86K files
3.58K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
Forwarded from ⒻⒾⓇⒶ😉
Hige mengist zendiro taqayere new weyis teterogeme new linil minichilew?
Forwarded from 🇪🇹የሕግ ጉዳይ (Alemwaza)
07/09/2020

LEGAL AIDE

 Tsehay Insurance

 Addis Ababa, Ethiopia

FULL_TIME Insurance Jobs in Ethiopia Legal Jobs in Ethiopia

Job Description

JOB REQUIREMENT

Qualification: College Diploma in relevant field

Work Experience: 4 years of relevant experience

Place of Work: Head Office

HOW TO APPLY

Salary: As per the scale of the company with other benefit packages

Interested applicants, who fulfill the minimum requirements, can send their non-returnable application with CV and copies of relevant documents within 7 working days from the first date of this announcement to:

Tsehay Insurance S.C.

Manager, HR & Property Administration

P.O.Box 56144

Addis Ababa

@Ethiopian_Legal_Advocate
@Ethiopian_Legal_Advocate
ለውድ የ #ALE # አለ የመገናኛ አውታር ተከታዮች 🌼🌼🌼እንኳን ለ2013ዓ.ም አደረሳችሁ🌼🌼🌼🌼

🌼🌼🌼Happy New Year🌼🌼🌼
@lawsocieties

ባለፉት ዓመታት በALE (Alternative Legal Education) የቴሌግራም የመገናኛ አውታር ስንሰጣችሁ በነበረው ግልጋሎት እና ከአዲሱ ዓመት ጀምሮ አገልግሎታችንን በምን መልኩ እናድርገው በሚለው ነጥብ ላይ በማተኮር ያላችሁን ገንቢ አስተያየት ብትሰጡን አስተያየታችሁ ወደፊት የተሻለ አገልግሎት ለመስጠት ይረዳናል፡፡

አስተያየት ለመስጠት

@Alemwaza

ወይም

@Asratm27

አድራሻዎች ይጠቀሙ፡፡

🌻🌻🌻Happy New Year🌻🌻🌻
@lawsocieties
ሌሎች ወዳጆቻችሁንም የእዚህ የቴሌግራም አውታር ቤተሰብ እንዲሆኑ ይጋብዙ፡፡
🙏🏻🙏🏻🙏🏻እናመሰግናለን🙏🏻🙏🏻🙏🏻
አዲሱን ዓመት ፈጣሪ ወረርሽኙን አጥፍቶ ፤በተረጋጋ መንፈስና ስሜት የዘረኝነት አስተሳሰብ አስወግዶ ፤ በሰውነት መስፈርት ብቻ በቀደመው ኢትዮጵያዊ ማንነታችን ተከባብረን፣ በመተሳሰብ ፣በመደጋገፍ የምንኖርበት የተባረከ ዓመት ያድርግልን፡፡
🌼🌼🌼🌻🌻Happy New Year🌻🌻🌼🌼🌼

https://t.me/lawsocieties
@lawsocieties @lawsocieties
@lawsocieties @lawsocieties

🌼🌼🌼Happy New Year🌼🌼🌼
BERHANU. W:
ALE law Program?

ALE(አለ) የህግና ተያያዥ ጉዳዬች የሚቀርብበት በይነ መረብ የእስካሁን አቀራረብና ጥረት ታላቅ ምስጋና:ክብር እየሰጨሁ፣ቀጣይ መሆን ያለበት በዚህ ቀጥሎ መሻሻል አለበት እሚለውን አንተ ብጨምር።አንተን መረጃ እንድንጠይቅህ ብዙ ሳንደክም ቴሌግራም ቢኖርህ:ጥያቄውን ቶሎ ብታየው?በ2012 የት ጠፋህ?መረጃህ ቀንሶ ከረመ።በኮረና ይሆናል።ግን አይብዛ መጥፋት።አለን ሳላይ መረጃ ሳጣ በጣም እበሳጫለሁ።አንባቢ ነኝ።ህግ ነው የተማርኩት።ብሄር:ፖለቲካ: ገለመሌ አልወድም።አይመቼኝም።አመሠግናለሁ።(ብርሃኑ ወርቄ ወሎ ደሴ ኢትዮጵያ።)
Forwarded from abyssinialaw.com
የመንግሥት ሠራተኞች ደሞዝ መቁረጥ እና ሕጋዊነቱ

በ፡-አቤል ዘውዱ

ለዚህ ጽሑፍ መነሻ የሆነው ገበታ ለሃገር መርሃግብር የመንግሥት ሠራተኞች የወር ደሞዛቸውን ለገሱ የምትል ዜና በተደጋጋሚ በመስማቴ እና እውነት በዚህ የኑሮ ውድነት እነዚህ የመንግሥት ሠራተኞች ደሞዛቸውን የሚለግሱት ጎርጎራ፣ ወንጪ አሊያም ኮይሻ ላይ ሆቴል መሰራቱ ከጊዚያዊ ችግሮቻችን ይበልጣል ብለው አምነው ወይስ በአለቆቻቸው ተፅዕኖ ሥር በመሆናቸው ተገድደው የሚለው ጥያቄ በተደጋጋሚ ውስጤ ሲመላለስ በመቆየቱ ነው፡፡

መልካም ንባብ

https://www.abyssinialaw.com/blog-posts/item/1954-the-legality-of-cutting-civil-servant-salary
ALE ዎች እንዴት ከረማችሁ ከሁሉም በማሰቀደም እንኳን ለ2013 የዘመን መለወጫ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፡፡

የዚህ ቻናል አባል ከሆንኩበት ቅፅበት አንስቶ አያሌ ሕግ ሕግ የሚሸቱ ሰነዶችን፣ መረጃዎችን፣ እና ለህጉ ማህበረሰብ እሚጠቅሙ የተለያዩ ሀሳቦችን ስታካፍሉንና ስታሳትፉን ቆይታችዋል፤ በእውነቱ በርቱ ማለትን ፈልጋለው፡፡
በዚህ ላይ ማለት እምፈልገው የተለያዩ የህግ ሙህራን፣ የሕግ ትምህርት ቤቶች አመራሮች እንዲሁም ተማሪዎች እንደመኖራቸው መጠን በቀጣዩ አመት ሁሉም በሃላፊነት ቀለል ባለ አቀራረብ እውቀቱን ማካፈል ቢችልና በሳል የሆኑ ህግ ነክ ጉዳዮችን ማብላላት እሚቻለበት መደረክ አልያም መማማሪያ አይነት ነገር ማድረግ ቢቻል እና በዚህም ሁሉም መሳተፍ ቢችል በሃላፊነት ስሜት!!

ሌላኛው የተለያዩ ጥናቶችን፣ አርቲክሎችን፣ መፃህፍትን እና የህግ ሰነዶችን ማቅርብ ቢቻል በብዛትና ጥራት፡፡

የመጨረሻው ወቅታዊ የሆኑ ህግ ነክ መረጃዎችን እጅግ በፈጠነ መልኩ ማጋራት እምችሉበት ከበፊቱ በተሻለ ማቅርብ ብትሞክሩ፡፡

አመሰግናለሁ መልካም አዲስ ዓመት!!
(AN, ADAMA ETHIOPIA )
ይደግ እባላለሁ 5ኛ አመት የህግ ተማሪ ነኝ፡፡
በጣም ጥሩ እየተንቀሳቀሳቹ ነው፡፡ በርቱ፡፡
መረጃወችን በትኩስ በትኩሱ ተከታትላቹ ብታቀርቡልን፡ አንዳንድ መነበብ አለባቸው ምትሏቸውን ከአማርኛም ሆነ ከእንግሊዝኛ ስራወች(articles,books,journals, decisions) ብታካፍሉን እንዲሁም አንዳንድ ወሳኝ የህግ ጥያቄ የሚያስነሱ ጉዳዮችን ለክርክር እና ውይይት ብታቀርቡ እላለሁ፡፡
አመሰግናለሁ፡ እግዚአብሔር ይባርካቹህ
🌼🌼🌻🌼🌼🌼🌻እንቁጣጣሽ‼️
@lawsocieties
Forwarded from 🇪🇹የሕግ ጉዳይ (Alemwaza)
የፌዴራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ፕሬዝደንት ክብርት ወ/ሮ መዓዛ አሸናፊ የ2012 ዓ.ም የዳኝነት የስራ ዓመት መገባደድ እና የ2013 አዲስ ዓመት መባቻን አስመልክቶ ለዳኞች የምስጋና መግለጫ ልከዋል፡፡ የመግለጫው ሙሉ ይዘት እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡

ክቡራንና ክቡራት ዳኞች

ባሳለፍነው የዳኝነት ዘመን በፍርድ ቤቶች ለተስተዋለው የአገልግሎት አሰጣጥ መሻሻል ያሳያነው የዳኝነት ኃላፊነት ስሜት፤ የሙያ ስነምግባርና ክብር የሚመሰገን ነው፡፡ ለተገኘው ውጤትም በፍርድ ቤቱ ከፍተኛ አመራር አካላት በኩል ለተፈጠረው የጋራ ራዕይ፣ ግልጽነት፣ የመተማመን መንፈስ እና የስራ ትጋር ያለኝን አድናቆት እገልጻለሁ!!

የዳኝነት ዘርፉን በተሟላ ቅርጽና ይዘት የማሻሻል አቅም የሚፈጥሩና የማዕዘን ድንጋይ ተደርገው ሊወሰዱ የሚችሉ የፌዴራሉ መንግስት የዳኝነት አካል ራሱን በሙሉ ነጻነት ማስተዳደር የሚያስችል እና የፍርድ ቤቶችን አደረጃጀትና ስልጣን የሚወስነውን አዋጅ በአዲስ መልክ የሚያሻሽል ረቂቅ አዋጆች ተዘጋጅተው ለምክር ቤቱ ቀርበዋል፡፡ ምክር ቤቱም ላቀረባቸው የማብራሪያ ጥያቄዎች ዝረዝር ማብራሪያ በመስጠት በኮቪድ ምክንያት በሙሉ ዓቅሙ ስራ እንዳይሰራ ከማድረጉ በፊት የመጽደቅ የመጨረሻ ምዕራፍ ላይ ማድረስ ተችሏል፡፡

ሌላው በዚህ ዓመት ከተከናወኑት ዓበይት ስራዎች መካከል በዓለማችን እንዲሁም በሃገራችን በተከሰተውና እስከአሁንም መፍትሄ ባልተገኘለት የኮቪድ 19 ወርሽኝ ምክንያት የዜጎችን የዳኝነት መብት እና በጤና በህይወት የመኖር መብት በአንድ ላይ ለማረጋገጥ ከገባንበት አጣብቂኝ ውስጥ ለመውጣት የሰራነው ስራ አንዱ ነው፡፡

ፍርድ ቤቶቻችን የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ማሰራጫ ማዕከል እንዳይሆኑ ለማድረግ በተወሰደው አስተዳደራዊ እርምጃ ፍ/ቤቶች ከመጋቢት እስከ ሐምሌ አጋማሽ በከፊል ዝግ እንዲሆኑ ተደርገዋል፡፡ በዚሀም ምክንያት ወደ ፍርድ ቤቶቻችን ሊመጣ የሚችል የመዛግብት ፍሰት የቀነሰ ቢሆንም ዳኞች በቤታችሁና በቢሯችሁ ለምርመራ ለደረሱ መዛግብት እልባት ለመስጠት ጊዜያችሁን በመጠቀማችሁ በፌዴራል ፍ/ቤቶች ደረጃ 140 ሺህ ለሚሆኑ መዛግበት እልባት መስጠት ተችሏል፡፡

በወረርሽኙ ምክንያት ፍ/ቤቶቸ በከፊል ዝግ ሆነው እንዲቆዩ በተደረጉበት ተመሳሳይ ጊዜ አስቸኳይነት ያላቸውን ጉዳዮች በተረኛ ችሎት በማስተናገድ ለ7 ሺህ መዛግብት እልባት ተሰጥቷል፡፡ ይህም በአጣዳፊ ሁኔታ ዳኝነት ለሚሹ ወገኖቻችን ከራሳችሁ ደህንነት ይልቅ የእነርሱን በማስቀደም አወንታዊ ምላሽ ለመስጠት ያገኛችሁትን እድል በአግባቡ የተጠቀማችሁበት ለመሆኑ ያሳያችሁበት ነው ለማለት ያስችላል፡፡

የዳኝነት የስራ ጫና ለመቀነስ ከ150 በላይ የረዳት ዳኞች ቅጥር በማከናወን የዳኞችን የስራ ሸክም ለማቃለልም ተችሏል፡፡ የሬጂስትራር ባለሙያዎቸን በበቂ ቁጥር በመሾምና የሙያ ብቃታቸውን የሚያጎለብት ስልጠና ተሰጥቷል፤ የአሰራር ለውጥ ተደርጓል፡፡ ከተገልጋዮቻችን ያገኘነው ግብረመልስ የሬጂስትራር አገልግሎት አሰጣጥ ቅልጥፍናም መጨመሩን ጠቁሞናል፡፡
የተወደዳችሁ ዳኞች

የዳኝነት አንዱ መገለጫ ባህሪው ግልጽነት ነው፡፡ ዳኝነትን በግልጽ ችሎት ለመስጠት የማያስችሉ፤ ለዳኞችና ለተገልጋይ ምቾት የሌላቸውን ምድብ ችሎቶችን በመለየት የተሻለ አገልግሎት መስጠት የሚያስችሉ ህንጻዎችን በመከራየት ችግሩን ለመፍታት የተደረገው ጥረትም አበረታች ነው፡፡ ከዚህ አንጻር ከመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የመናገሻ እና የአራዳ ምድብ ችሎቶች እንዲሁም ከከፍተኛ ፍ/ቤት ጦሃይሎች ምድብ ችሎት ለአብነት የሚጠቀሱ ናቸው፡፡

እንደምትገነዘቡት የዳኝነት ነጻነትን ከማስጠበቅ አንጻር ያስመዘገብንባቸው አኩሪ እና ፈር ቀዳጅ ውጤቶችም አሉ፡፡ የዳኝነት አካሉን የበጀት ነጻነት ለማስጠበቅ በተሰራው ስራ በህገመንግስቱ በተቀመጠው ድንጋጌ መሰረት የፍርድ ቤትን በጀት ለመጀመሪያ ጊዜ በቀጥታ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤቱ በማቅረብ በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ምኒስቴር ከተቀመጠው የበጀት ጣሪያ በላይ በማስፈቀድ በጀቱን በውጤታማነት ጥቅም ላይ ማዋል ተችሏል፡፡

ከዚህ ጎን ለጎን የዳኞችን ግለሰባዊ ነጻነትና መብት አስከብሮ ገለልተኛ የዳኝነት አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችሉ ምቹ ሁኔታችን ለመፍጠር በተደረጉ ጥረቶች ዳኞች ያለባቸው የስራ ሃላፊነትና ጫና እነዲሁም የሃገሪቱን ኢኮኖሚ ከግንዛቤ ያስገባ የደመወዝ ማስተካከያም መደረጉ ይታወቃል፡፡ በእቅድ ከተያዘለት ጊዜ በላይ የወሰደው የዳኞች የጋራ መኖሪያ ሕንጻ ግንባታ እንዲጠናቀቅ ከመንግስትና ከተቋራጩ ድርጅት ጋር በተደረጉ ያልተቋረጠ ክትትልና የአስተዳደር ድጋፍ ስራችን ፍሬ አፍርቶ ግንባታውን ለማጠናቀቅ ችለናል፡፡ ዳኞች በቤት ኪራይ ሲደርስባቸው ከነበረው እንግልት የሚያወጣቸውና መኖሪያ ብቻ ሳይሆን እንደቢሮም የሚገለገሉባቸው 140 ባለ ሶስት እና 138 ባለ ሁለት መኝታ ክፍል ቤቶች ተጠናቀው ለአገልግሎት ዝግጁ ሆነዋል፡፡

ከላይ የጠቀስናቸው አመርቂ ውጤቶች ቢኖሩም አሁንም ያልተሸገርናቸውና ጉዳዮች አሉ፡፡ በጀመርነው አዲስ የዳኝነት ዓመት (2013 ዓ.ም) የጉዳዮች ፍሰት አስተዳደር ስርዓታችን እንዱ በልዩ ትኩረት ልንሰራበት የሚገባ ዘርፍ ነው፡፡ በጀምር ላይ ያለውና የመደበኛ ፍርድ ቤቶቻችንን ጫና ለመቀነስ የሚያስችል ፍርድ ቤት መር የአስማሚነት አገልግሎት ተጠናክሮ የሚቀጥልበት ሁኔታን ማመቻቸት ያስፈልገናል፡፡

የምንሰጠው ዳኝነት ከቅልጥፍና አንጻር መልካም ደረጃ ላይ ደርሷል ሊባል የሚችል ቢሆንም ከምንሰጠው ዳኝነት ጥራት አኳያ ውስንነቶች እንዳሉ በተለያየ መንገድ የሚደርሱን መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ የዳኝነት ነጻነት ሚዛን መጠበቂያ የሆነው የዳኝነት ተጠያቂነት ስርዓታችንንም እንደዚሁ የምንፈትሽና በረቂቅ ደረጃ የተዘጋጀን የዲሲፕሊንና ስነምግባር መመሪያ እንዲሁም የአፈጻጸም ምዘና መመሪያን በማጽደቅ ስራ ላይ የምናውል ይሆናል፡፡

ፍርድ ቤቶቻችን ለአራት ወራት በከፊል ዝግ ሆነው በመቆቀታቸው በወቅቱ ሊታዩ የሚገባቸው ጉዳዮች ሳይታዩና መዝገብ ሳይከፈትላቸው በመቆየታቸው በጀመርነው አዲስ አመት የመዝገብ ፍሰቱ መጨመሩ የማይቀር ነው፡፡ ለዚህም በተባበረ መንፈስ ጠንክረን በመስራት በፍርድ ቤቶቻችን እየታየ ያለውን ለውጥ በማስቀጠል አምና ያገኘነውን የሚያስመሰግን ውጤት ከፍ ባለ ደረጃ እንድንደግመው በጋራ ራዕያችን ላይ በጽናት እንድንቆም በዚሁ አጋጣሚ ልጠይቃችሁ አፈልጋለሁ፡፡

የአዲሱ አመት የመጀመሪያው ወር የእረፍት ጊዜያችሁ አንዲሆን መወሰኑ ይታወቃል፡፡ ነገር ግን በፍርድ ቤቶቻችን የተለመደ አሰራር አብዛኛዎቻችሁ ውዝፍ መዛግብትን በማጥራት ስራ ላይ በፈቃዳችሁ የምትቆዩ መሆናችሁ የሚያስመሰግናችሁ ነው፡፡

ወድ ዳኞች በመጨረሻም

መጪው አዲስ ዘመን ቃል የገባንለት ህጋዊና ፍትሃዊ ዳኝነት የመስጠት ተልዕኳችንን በእውቀትና በሙያ፤ በገለልተኝነትና በሐቀኝት፤ በቅልጥፍናና በጥራት፤ በነጻነትና በተጠያቂነት የምንወጣበት፤ ህብረተሰቡ በፍርድ ቤቶቻችን ላይ ያለው ዓመኔታ ከፍ የሚልበት እና ለሌላ ተጨማሪ ስኬት የምንበቃበት ዘመን እንዲሆንልን እመኛለሁ!!

ክብርት ወ/ሮ መዓዛ አሸናፊ መንግስቱ
የፌዴራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ፕሬዝደንት
ጷጉሜ 3 ቀን 2012 ዓ.ም

🎤የተከበራችሁ ክቡራት እና ክቡረን የ ALE channel ቤቸሰቦች ስላማችሁ ይብዛ በያላችሁበት ።

አህመድ እንድሪስ እባላለው በ ወሎ ዩኒቨርሲቲ የህግ ት/ቤት የ 4ኛ ዓመት ተማሪ ነኝ።

1⃣በቅድሚያ እንኳን (ለ ሀበሻዎች የዘመን መለወጫ ለሆነው)ለ ዓዲሱ ዓመት 2013 ዓ.ም በስላም አደረሳችሁ አደረስን።

2⃣በመቀጠል ይህ ቻናል(channel) ከተከፈተበት ቀን አንሰቶ እሰካሁን ደረስ ጥሩና የወሳኝ የሆኑ ሕግ ነክ መረጃዎችን: አጋዥ ማቴሪያሎችን እና ሌሎች ተዛመጅነት ያላቸው ጠቃሚ መረጃዎችን እያደረሰን ይገኛል።
↪️ስለሆነም መስጋናችን በጣም የላቀ ነው አሁንም ትብብረዎን እንሻለን መለገሰዎን ቢቀጥሉ።

🔵አዲሱን ዓመት የሰላም የፍቅር የደግነት የብሩህ ተሰፋ የጤና ያደርግልን ዘንድ ትልቅ ምኞቴ ነው ።

❤️❤️❤️❤️❤️❤️Happy new year 2013 EC.

@wulsu
እንኳን ለዘመን መለወጫ በዓል አደረሳችሁ!
አዲሱ 2013 ዓመት የሰላም፣ የጤና እና የደስታ እንዲሆንልን የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ለመላው ኢትዮጵያውያን ይመኛል!
የፌደራል ፍርድ ቤቶች በመስከረም ወር በከፊል ዝግ ሆነው ይቆያሉ
********************
የፌዴራል ፍርድ ቤቶች በመስከረም ወር 2013 ዓ.ም በከፊል ዝግ ሆነው እንደሚቆዩ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት አስታወቀ፡፡
ይህም ፍርድ ቤቶች የኮቪድ 19 ወረርሽኝን ለመከላከል ከመጋቢት 10 - እስከ ሐምሌ 10 ቀን 2012 ዓ.ም በከፊል ዝግ ሆነው ከቆዩብ ሁኔታ ለመውጣትና ተቋርጦው የነበሩት አገልግሎቶችን ደረጃ በደረጃ ለማስጀመር ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ሐምሌ 10 ቀን 2012 ዓ.ም ባወጣው መመሪያ መሰረት ዳኞች በመስከረም ወር እረፍት አንዲያደርጉ በመወሰኑ ነው ተብሏል፡፡
ዳኞች ዓመታዊ እረፍታቸውን በነሃሴ እና በመስከረም ወር የሚወስዱ በመሆኑ የፌዴራል ፍርድ ቤቶች አስቸኳይነት ያላቸውን ጉዳዮች ብቻ በተረኛ ችሎቶች በማስተናገድ በከፊል ዝግ ሆነው እንደሚቆዩ ማድረግ የተለመደ አሰራር መሆኑን ያስታወሰው ጠቅላይ ፍርድ ቤት፤ በዚህ ዓመት ዳኞች አጭር የእረፍት ጊዜ እንደሚኖራቸው ገልጿል፡፡
ፍርድ ቤቶቹ በከፊል ዝግ ሆነው በሚቆዩባቸው የመስከረም ወር 20 የስራ ቀናት አስቸኳይና ጊዜ የማይሰጡ ከዜጎች መሰረታዊ መብቶች እንዲሁም ከአገር ሰላምና ፀጥታ ጋር ግንኙነት ያላቸውን ጉዳዮች እንደሚመለከቱ ተገልጿል፡፡
ለአብነትም እንደ የጊዜ ቀጠሮ፣ የዋስትናና የዕግድ ጥያቄዎች፣ የመያዣና የብርበራ ትዕዛዞች፣ በተፋጠነ ስነ-ስርዓት የሚታዩ የእጅ ከፍንጅ ወንጀሎች እንዲሁም ከቤተሰብና ከሕፃናት ቀለብና አስተዳደግ ጋር የተያያዙ አጣዳፊ መሰረታዊ ጉዳዮች በተረኛ ችሎቶች የሚስተናገዱ መሆኑ ተነግሯል፡፡
የአዲሱ ዓመት የመጀመሪያው ወር ለዳኞች የእረፍት ጊዜያቸው አንዲሆን የተወሰነ ቢሆን በፍርድ ቤቶች የተለመደ አሰራር አብዛኛዎቹ ዳኞች በፈቃዳቸው ውዝፍ መዛግብትን በማጥራት ስራ ላይ የሚቆዩ መሆናቸውን ከፕሬዝደንት ጽ/ቤት ከተገኘው መረጃ ለመረዳት ተችሏል፡፡
የፌዴራል ጠቅላይ ፍ/ቤ ፕሬዝደንት ክብርት ወ/ሮ መዓዛ አሸናፊ ለዳኞች በስተላለፉት የምስጋና መግለጫ “መጪው አዲስ ዘመን ቃል የገባንለት ህጋዊና ፍትሃዊ ዳኝነት የመስጠት ተልዕኳችንን በእውቀትና በሙያ፤ በገለልተኝነትና በሐቀኝት፤ በቅልጥፍናና በጥራት፤ በነጻነትና በተጠያቂነት የምንወጣበት፤ ህብረተሰቡ በፍርድ ቤቶቻችን ላይ ያለው ዓመኔታ ከፍ የሚልበት እና ለሌላ ተጨማሪ ስኬት የምንበቃበት ዘመን እንዲሆንልን እመኛለሁ!!” ብለዋል፡፡
የፌ/ጠ/ፍ/ቤት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት
Legal Expert
#ethiopian_national_accreditation_office
#legal_services
#law
#legal_expert
Addis Ababa
LLB in Law with relevant work experience in related legal service
Minimum Years Of Experience: #6_years
Deadline: September 16, 2020
How To Apply: In person to the following address: Bole sub city Ethiopian National Accreditation Office 3rd floor to the HR office no. 304. Tel: 011667- 0994/011833-3770
Forwarded from ...
Selam ye robert allen sadler "Ethiopian civil procedure law" yemilew metsihaf pdf kale share bitareguln .Thank you in advance.