የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ጉባዔ 5ኛ ዓመታዊ ጉባዔ የአቋም መግለጫ
****************************
ነሐሴ 30 ቀን 2012 ዓ.ም
የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ጉባዔ በፌዴራል ፍ/ቤቶች አዋጅ 25/88 ከአንቀጽ 31-34 በተደነገገው መሰረት የተቋቋመና በዳኝነት ሥራ አስተዳደር ረገድ በሚያጋጥሙ ችግሮች ላይ ተወያይቶ መፍትሔ የመስጠት፤ የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የዳኝነት አሰራርን ለማሻሻል የሚረዱ መመሪያዎችና ውሳኔዎችን የማሳለፍ፤ አዳዲስ ሕጎች እንዲወጡ ወይም ነባር ሕጎች እንዲሻሻሉ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሃሰብ የማቅረብ፤ የዳኝነት ስራ አካሄድን ለማቀላጠፍና ለማጠናከር የሚረዱ ሌሎች ተግባራትን የማከናውን እና ለጉባዔው ስራ አፈጻጸም አስፈላጊውን ደንብ የማውጣት ስልጣንና ተግባር የተሰጠው ጉባዔ ነው፡፡ በዚህም መሰረት የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ጉባዔ 5ኛውን ዓመታዊ ጉባዔ ዛሬ ነሐሴ 30 ቀን 2012 ዓ.ም በፌዴራልና በክልል ፍርድ ቤቶች ተቋማዊና ዳኝነታዊ ነጻነት ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ውይይት አካሂዷል፡፡
ጉባዔው ባካሄደው ውይይት የፌዴራልና የክልል ፍርድ ቤቶች በነጻነትና በገለልተኝነት ዳኝነት የመስጠት ህገመንግስታዊ ሃላፊነት የተሰጣቸው ተቋማት መሆናቸው በውይይቱ ተገልጿል፡፡ የዳኝነት ተጠያቂነት የዳኝነት ነጻነት ዋስትና መሆኑንም ስምምነት የተደረሰበት ጉዳይ ነው፡፡ በሃገራችን ከመጣው የለውጥ እንቅስቃሴ በኋላ በፌዴራልና በክልል ፍርድ ቤቶች የተጀመሩ የለውጥ እንቅስቀሴዎች መኖራቸውንና የተወሰኑትም ቢሆኑ ተግባራዊ መሆን መጀመራቸውን መገንዘብ ተችሏል፡፡
የዳኝነት ነጻነትን ለማረጋገጥ ከተሰሩ ስራዎች መካከልም የፍርድ ቤቶች አደረጃጀትና የዳኞች አስተዳደር ጉባዔ አዋጆችን የማሻሻል ስራዎች በሂደት ላይ መሆናቸው፤ በዚህም አስተዳደራዊ እና የበጀት ነጻነት መጎናጸፍ የሚያስችሉ ድንጋጌዎች መካተታቸው፤ እንዲሁም የዳኞችን ግለሰባዊ ነጻነት ለማስጠበቅም ያለመከሰስ መብት የህግ ድጋፍ እንዲኖረው መደረጉ፤ ከዚህ ጎን ለጎን የዳኝነት ነጻነት ዋስትና የሆነው የዳንነት ተጠያቂነት ስርዓት መዘርጋት የሚያስችሉ አንቀጾች እንዲገቡ ተደርጓል፡፡
የዳኞችን ግለሰባዊ ነጻነት ከሚያስጠብቁ ጉዳዮች መካከልም በፌዴራልና በተወሰኑ ክልሎች የደሞዝ ማሻሻያ መደረጉ፡፡ በፌዴራል ፍርድ ቤቶች ዳኞች የመኖሪያ ቤት እንዲያገኙ መደረጉ እና ሌሎች ጥቅማ ጥቅሞች እንዲጠበቁላቸው ጥረቶች መደረጉ ታይቷል፡፡
ይሁን እንጂ ዳኞች ከህግ አውጪውም ሆነ ከአስፈጻሚው አካል ሊደርስ ከሚችል ተጽእኖ ነጻ መሆን ይጠበቅባቸዋል፡፡ ፍርድ ቤቶች የሚሰጧቸው ውሳኔዎችም መከበርና መፈጻም አለባቸው፡፡ ዳኞች ከሚሰጣቸው ውሳኔዎች ጋር ተያይዞ ከማንኛውም ስጋት ነጻ መሆን ይጠበቅባቸዋል፡፡ ከዚህ አንጻር በአንዳንድ ክልሎች ፍርድ ቤቶች የበጀት፤ የድጋፍ ሰጪ ሰራተኞችን ከማስተዳደር አንጻር ችግሮች ያሉባቸው መሆኑ ተነስቷል፡፡ በምክር ቤቱ የተፈቀደ በጀትን የመከልከል ችግሮችም እንዳሉ ተነግሯል፡፡ በተወሰኑ ክልሎች ደግሞ በበጀት እጥረት ምክንያት የደሞዝ ማሻሻያ አለመደረጉ እና ተመጣጣኝ ክፍያ መርህን ያልተከተለ የደሞዝ ማስተካከያ መደረጉም ከተነሱ ችግሮች መካከል ይጠቀሳሉ፡፡
ከዳኞች ግለሰባዊ ነጻነት ጋርም ተያይዞ በተወሰኑ ክልሎች ዳኞች በሰጡት ውሳኔ በፖሊስ የመታሰር፤ ባልታወቁ ሰዎች የመደብደብ፤ በመኖሪያ ቤታቸው አካባቢ ተኩስ በመክፈት ጫና ለማሳደር መሞከር፤ በማህበራዊ ሚዲያ ዳኞች ከህግ ውጪ እንዲወስኑ በተለያዩ ግለሰቦችና ኢ-መደበኛ ቡድኖች ጫና ማሳደር እና የመሳሰሉት ሁኔታዎች ተስተውለዋል፡፡ እነዚህን በፈጸሙ ግለሰቦች እና ቡድኖች ላይ ተገቢውን ህጋዊ ምርመራ አድርጎ ወደ ህግ በማቅረብ በኩል ክፍተቶች ታይተዋል፡፡
በተጨማሪም ቁጥጥር ሊደረግባቸው የማይችሉ ሚዲያዎች የሚያሰራጯቸው አሉታዊ ይዘት ያላቸው መረጃዎች በፍርድ ቤትና በዳኞች ላይ ተጽዕኖ መፍጠራቸውም እንደዚሁ ተጠቁሟል፡፡
ከዚህ በመነሳት የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ጉባዔ 5ኛ ዓመታዊ ጉባዔ የሚከተለውን የአቋም መግለጫ በማውጣትም ስብሰባውን አጠናቋል፡፡
1. የዳኝነት ነጻነት መኖር በህግ ማዕቀፍ ብቻ የሚረጋገጥ ባለመሆኑ የዳኝነት ነጻነት መከበር በተግባርም ጭምር መታየት ይኖርበታል፡፡ ለዚህም የህግ አውጪውም ሆነ የአስፈጻሚው አካል በህገ መንግስትና ተያያዥ ህጎች መሰረት ለዳኝነት ነጻነት መረጋገጥ እና አገልግሎት መሻሻል አስቻይ የሆነ በጀት የሃገሪቱ አቅም በሚፈቅደው መጠን መመደብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
2. የዳኝነት ነፃነትን ማስጠበቅ በዋነኝነት የዳኞች ኃላፊነት ቢሆንም የመንግስት አስፋፃሚ አካል፤ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች፤ ሲቪል ማህበራት እና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ለሃገሪቱ ሰላምና መረጋጋትን ለማምጣት፤ የህግ የበላይነትን ለማስከበርና የመንግስትን ቀጠይነት ለማረጋገጥ እንዲያስችል የዳኝነት ነጻነት እንዲከበር የበኩላቸውን ሚና ሊጫወቱ ይገባል፡፡
3. የዳኝነት ነጻነት በዳኞች የሚሰጡ ውሳኔዎች በህገመንግስቱ ከተቋቋመ የመንግስት ተቋም የሚሰጡ ውሳኔዎች በመሆናቸው ትእዛዛቸውና ውሳኔያቸው መከበርን ግድ ይላል፡፡ የዳኝነት ነጻነትን የተመለከቱ የህግ ማዕቀፎች መኖር አስፈላጊነት እንደተጠበቀ ሆኖ የመንግስት አካላትን ጨምሮ ሌሎች ወገኖች በፍርድ ቤት የሚሰጡ ውሳኔዎችን በማንኛውም አካል ምርመራ ሳይደረግባቸውና ሳይሸራረፉ ማክበር እና ተግባራዊ ማድረግም ይኖርባቸዋል፡፡
4. በህገመንግስታችን መግቢያ እንደተገለጸው በሃገራችን አንድ የኢኮኖሚ እና የፖለቲካ ማህበረሰብ ለመመስረት የፌዴራልና የክልል ፍርድ ቤቶች ወሳኝ ድልድዮች ናቸው፡፡ በስራ ረገድም በበርካታ ሁኔታዎች ይገናኛሉ፡፡ የሚመሩበት የሙያ መርህና የስራ ባህሪያቸውም እጅግ ተመሳሳይ በመሆኑ የዳኞችን ግለሰባዊ ነጻነት ለማረጋገጥ የሚደረጉ የደመወዝ እና የጥቅማጥቅም ፓኬጆች ምክንያታዊና ነባራዊ ሁኔታውን ከግምት ያስገባ እንዲሆኑ አመራሩ በቀጣይነት በልዩ ትኩረት የሚሰራበት ጉዳይ ይሆናል፡፡
5. የዳኝነት እና የዳኞች ነጻነት የህግ የበላይነት ቁልፍ ማዕዘን ነው፡፡ በየትኛውም ቦታ የሚያገለግሉ ዳኞች የስራ ነጸነት መከበር አለበት፡፡ በዚህ ረገድ ዳኞች ሁሉ በጋራ መቆምና ሙያዊ መደጋገፍን ማሳየት ሃላፊነታችን ነው፡፡ የዳኞች በባለጉዳይም ሆነ በመንግስት አካላት መደፈር በፍጹም ተቀባይነት የሌለው ተግባር ነው፡፡ መንግስት የዳኝነት ነጻነትን ለማረጋገጥ ያለውን ፍላጎትና ቀርጠኝት በተለያየ ሁኔታ ቢያሳይም በመንግስት የታችኛው መዋቅር ያሉ ግሰቦች የተሰጣቸውን ኃላፊነት ባልተገባ መንገድ በመጠቀም በዳኝነት ነጻነት ላይ የሚያሳድሩትን አሉታዊ ተጽእኖ በጋራ የምንታገለው ይሆናል፡፡ መንግስትም በህግ የበላይነት መከበር ላይ እየተስተዋሉ ያሉ ችግሮች እየተስፋፉ እንዳይሄዱ ከላይ በተጠቀሱትና መሰል ተግባራት ላይ የተሰማሩ ግለሰቦችን ምርመራ በማድረግ ለይቶ ወደ ህግ በማቅረብ አስፈላጊውን ህጋዊ እርምጃ እንዲወስድ እንጠይቃለን፡፡

👍1
6. የዳኝነት ተጠያቂነት የዳኝነት ነጻነት ዋስትና ነው፡፡ ዳኞች ስህተት ሊሰሩ ይችላሉ፡፡ ነገር ግን ውሳኔያቸው በይግባኝ ሊሻር ይችላል፡፡ ከዚህ አልፎ የተሰጣቸውን የዳኝነት ስልጣን ባልተገባ መልኩ በመጠቀም የዲሲፕሊን ጥፋት የሚፈጽሙ ዳኞች ተጠያቂ የሚሆኑበት ስርዓት አለ፡፡ የዳኝነት ነጻነትን ሚዛን መጠበቅ የሚያስችል የተጠያቂነት ስርዓት መዘርጋት በፍርድ ቤቶች በልዩ ትኩረት ሊሰራ እንደሚገባም በአንድ ሃሳብ የተቀበልነው ጉዳይ ነው፡፡ ዓለም አቀፍ ደረጃንና መስፈርትን የጠበቀ የዳኝነት ተጠያቂነት ስርዓት ለመዘርጋት የጀመርናቸውን ጥረቶች አጠናክረን የምንቀጥል ይሆናል፡፡
7. የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ያስከተለው ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጫና ይታወቃል፡፡ መንግስት ወረርሽኙን ለመቆጣጠር የሚወስዳቸው ሌሎች እርምጃዎች እንደተጠበቁ ሆነው በፍርድ ቤቶች በኩል ወረርሽኙ ያለመገታቱን በመገንዘብ የተጀመሩትን የጥንቃቄ እርምጃዎች መቀጠል ይኖርብናል፡፡
8. ጉባዔው የፌዴራልና የክልል ፍርድ ቤቶችን የዳኝነት አሰራር ለማሻሻል የሚረዱ መመሪያዎችና ውሳኔዎችን እንዲያሳልፍ የተሰጠውን ስልጣን ተግባራዊ ለማድግ በፌዴራልና በክልል ፍርድ ቤቶች ያሉትን የጋራ ችግር በመለየትና ምክረ ሃሳብ በማቅረብ ድጋፍ የሚያደርግ ኮሚቴ ተቋቁመዋል፡፡
የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ጉባዔ
5ኛ ዓመታዊ ጉባዔ
ነሐሴ 30 ቀን 2012 ዓ.ም.

Hi ale is there any new info about exit exam of 2012 years graduation
Hi endat nachehu sil exist exam addis neger lemaggnet tirt bitadergu.....
ALE (Alternative Legal Education) All in one, All Law Societies. federal & regional Judges, Prosecutors, Advocates, consultants & law school heads, instructors, deans, Law graduates, Students & other NGO and PLC employees..
etc.
Contact Us Via @Alemwaza
https://t.me/lawsocieties
etc.
Contact Us Via @Alemwaza
https://t.me/lawsocieties
Telegram
ሕግ ቤት
ሕግ ቤት Access legal information
ጠበቃ እና የሕግ አማካሪ ያማክሩ
@HigBet #ሕግ_ቤት
lawsocieties@gmail.com
https://www.facebook.com/Ethiopianlegalinfo/

A student enrolled in a legal education should engage with bigger questions such as:
❓“Who am I?”
❓“What do I believe in?”
❓“What is important to me?”
❓“What will I do to make this world and my nation a better place?”
❓“How will I be remembered?”
@lawsocieties

#ALE
#ALE
የተልያዩ የህግ materials ጥቆማ እናደርጋለን።
#ALE
⚫️ህግ ነክ ትኩስ መረጃዎች
⚫️ህግ ነክ ነገሮች እና ችግሮች
⚫️ህግ ነክ መጣጥፎች
⚫️መፃፎች
⚫️short notes
⚫️Exit exams
⚫️proclamations
⚫️regulations
etc..
ALE (Alternative Legal Education) አለ for All Ethiopian Law Families.
አስተያየት እና መረጃ ለመስጠት inbox via
@Alemwaza
#please share to your friends ‼️‼️
#ALE
@lawsocieties @lawsocieties

Forwarded from 🇪🇹የሕግ ጉዳይ (Alemwaza)
ፍየል ወዲህ ቅዝምዝም ወዲያ
የፌደረሽን ምክርቤት ሊሰበሰብ ነው ሲባል ለኢትዮጵያ ክብር የሚመጥን ውሳኔ ሊወስን የተጠራ መስሎን ነበር። የትግራይ ክልላዊ መንግስት አዋጆች ህጋዊነት ግምገማ ሪፖርት ስሰማ ግን እጢዬ ዱብ አለ። ጆሮዬም ማመን አቅቶን ህገመንግስቱን አገላበጥኩ። የፌደሬሽን ምክርቤት ህግ ይተረጉማል የሚል አንቀፅ ፈልጌ አጣሁ። ምናልባት ሌላ ህገመንግስት ይኖር ይሆን ብዬም አሰብኩ። እንደገናም ጠየቅሁ፤ ህገመንግስት ይተረጉማል ማለት ህግ ይተረጉማል ማለት ነው? አጥጋቢ መልስ ሳጣ ፌደሬሽኑ በከንቱ እንደተሰበሰበ ገባኝ።
እንደውነቱ ከሆነ የፌደሬሽኑ አጀንዳ መሆን የነበረበት ጉዳይ ግልፅ ነው። የህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ የሚያደርገው እንቅስቃሴ ህገመንግስቱን የጣሰ ስለሆነ ፌደሬሽኑ በህገመንግስቱ መሰረት ምን ማድረግ አለበት የሚለው ነበር። ህገመንግስቱም በዚህ ጥያቄ ላይ ግልፅ ነው። አንቀፅ 51 (1ን) እና 62 (9ን) መመልከት በቂ ነው። ፌደሬሽኑ የሰጠው የህግ ትርጉምና ትንተና በህገመንግስቱ አንቀፅ 62 በተሰጠው ስልጣን ዝርዝር ውስጥ የለም። ህገመንግስቱን ይተረጉማል ከሚለው አንቀፅ 62 (2) ውጪ ህግ ይተረጉማል፤ይተነትናል የሚል አንቀፅም ሆነ ንኡስ አንቀፅ አይገኝም። ለፌደራል መንግስት የህግ አስተያየት ወይም ምክር ይሰጣል የሚልም የለም። ባጠቃላይ የፌደሬሽኑ ውሳኔ ፍየል ወዲህ ቅዝምዝም ወዲያ አይነት ነው።
የትግራይ ክልላዊ መንግስት ህጎች ከህገመንግስቱ ጋር ይጋጫሉ ወይስ አይጋጩም የሚለውን ጥያቄ ለመመለስ ከፍተኛ ስልጣን ያለውን ምክርቤት ክተት አውጆ አቧራ ማስነሳት አስፈላጊ አልነበረም። ይልቁንም የክቡር ጠቅላይ ሚንስትሩ የህግ አማካሪዎች በግማሽ ገፅ አስተያየት የሚጨርሱት ቀላል የህግ ጉዳይ ነበር። በመሆኑም የፌደሬሽኑ ምክርቤት በማይመለከተው የጥብቅናወይም የህግ ምክር አገልግሎት ስራ ውስጥ በመግባት ህገመንግስቱን የጣሰ ስለሆነ የሱን ውሳኔ ህጋዊነት የሚገመግም ሌላ ምክርቤት መጠራት ሳይኖርበት አይቀርም። ያም ሆነ ይህ ተሸውደናል።
ከዚህ ይልቅ የተሰጠውን ህገመንግስታዊ ስልጣን በመጠቀም ሀገራችንንና የትግራይን ህዝብ ማዳን ነበረበት። ምክርቤቱ ከገጠመን ችግር ጋር የማይመጣጠንና የማይመሳሰል ውሳኔ ወስኖ በመነሳቱ ከክልሉ መንግስት ለደረጃው የማይመጥን መልስ አግኝቷል፤ ፥ከማንም እውቅና አንፈልግም የሚል።፥ ከዚህ በላይ የሚጠበቅ ህገመንግስታዊ ውድቀት የለም። ሀገራችንንና የምንወደውን የትግራይ ህዝ ከመከራ ያድናል ተብሎ ተስፋ የተጣለበት የፌደሬሽን ምክርቤት የውል ክርክር ላይ የሚሰጥ ዳኝነት የሚመስል ውሳኔ ሰጥቶ በመነሳቱ ህዋህት ከጥቂት ቀናት በኋላ አዲስ መንግስት ይሆናል። የትግራይም ህዝብ እንደኤርትራ ህዝብ ያለፍላጎቱ ከእናት ሀገሩ የሚለይበት ጊዜ ቀርቧል። እኛም ወንድምና እህቶቻችንን ከህግ ውጪ እንደቀልድ ልናጣቸው ነው። ምርጫ የሚመስል ህዝበውሳኔ እየተካሄደ ስለሆነ የትግራይ መገንጠል ጉዳይ ሟርት ሳይሆን እውነት እየሆነ ነው። የቅዳሜውም የፌደሬሽን ምክርቤት የህግ ትንተና ይህን አደጋ የማቆም አቅም የለውም። ህገመንግስግ የሚከበረው ህገመንግስት በደነገገው መንገድ ነው። የኢትዮጵያ ህዝባዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፓብሊክ ህገመንግስት አንቀፅ 51 (1) እና አንቀፅ 62 (9))።
በካሳሁን ይበልጣል።
at Face book Kassahun Yibeltal

Hi mikysha endet nehe sele exit exam temariwoch eyeteyeku nw ena professor abeben swerechew nbr already le exit exam hetemete kifeya tekefluale gn temert minister meche universitywoche endemikefetu alasawekem ena demo fekad alsetem selezi consortiumu wesane lay mederes alchalem gn as soon as temert endetejemere lihon yechelale selezi eyanebebu yetebeku teblual
👍1
🇪🇹የሕግ ጉዳይ
ፍየል ወዲህ ቅዝምዝም ወዲያ የፌደረሽን ምክርቤት ሊሰበሰብ ነው ሲባል ለኢትዮጵያ ክብር የሚመጥን ውሳኔ ሊወስን የተጠራ መስሎን ነበር። የትግራይ ክልላዊ መንግስት አዋጆች ህጋዊነት ግምገማ ሪፖርት ስሰማ ግን እጢዬ ዱብ አለ። ጆሮዬም ማመን አቅቶን ህገመንግስቱን አገላበጥኩ። የፌደሬሽን ምክርቤት ህግ ይተረጉማል የሚል አንቀፅ ፈልጌ አጣሁ። ምናልባት ሌላ ህገመንግስት ይኖር ይሆን ብዬም አሰብኩ። እንደገናም…
It is laughable to see someone who is may be calling himself 'a lawyer' and telling us that a constitution is not a legal document.
Sisay Degaga
Sisay Degaga
🇪🇹የሕግ ጉዳይ
ፍየል ወዲህ ቅዝምዝም ወዲያ የፌደረሽን ምክርቤት ሊሰበሰብ ነው ሲባል ለኢትዮጵያ ክብር የሚመጥን ውሳኔ ሊወስን የተጠራ መስሎን ነበር። የትግራይ ክልላዊ መንግስት አዋጆች ህጋዊነት ግምገማ ሪፖርት ስሰማ ግን እጢዬ ዱብ አለ። ጆሮዬም ማመን አቅቶን ህገመንግስቱን አገላበጥኩ። የፌደሬሽን ምክርቤት ህግ ይተረጉማል የሚል አንቀፅ ፈልጌ አጣሁ። ምናልባት ሌላ ህገመንግስት ይኖር ይሆን ብዬም አሰብኩ። እንደገናም…
ጉማዬ😷:
ለዚ በቂ መልስ በቀድሞ የአ.አ ዩኒቨርስቲ የህገ መንስት አስተማሪ
ስለ (ትግራይ) ምርጫ ሕገ-መንግሥታዊነት እንደገና
(26 August 2020)
=======
1. ምርጫ ማካሄድ፣ ሕገ-መንግሥታዊ ግዴታን በተገቢው መንገድ መወጣት ነው። ምርጫን በተቀመጠለት የጊዜ ሰሌዳ መሠረት ማካሄድ፣ የአንድን ሕዝብ የዴሞክራሲ መብት (ማለትም፣ ሕዝቦች መንግሥታቸውን የማቆም፣ የመቆጣጠርና፣ ካልፈለጉትም የመሻር ሥልጣንን) ማክበር ነው።
የሕዝቦች የዴሞክራሲ መብት (the right of people to democracy)፣ ሥልጣን በመሠረቱ የመንግሥት ሳይሆን የሕዝብ መሆኑን ታሳቢ ያደረገ ነው። ይህ እሳቤ፣ መንግሥት ሥልጣንን የሚጠቀመው ሕዝብን ወክሎ ብቻ መሆኑን አስምሮበት ይነሳል። በመሆኑም፣ አንድ ሰው፣ ወይም አንድ ቡድን፣ መንግሥት ለመሆንና እንደ መንግሥትም ሥልጣንን ለመጠቀም እንዲችል፣ በቅድሚያ፣ በግልጽ በህዝብ መወከል አለበት። ይሄ የሕዝብ ውክልና ደሞ የሚረጋገጠው በምርጫ ብቻ ነው።
ያለ ምርጫ፣ ሕዝብን ወክሎ ሥልጣን መያዝም፣ መጠቀምም፣ የሥልጣን ዘመንን ማስረዘምም አይቻልም። ሕጋዊ መሠረትም፣ ፖለቲካዊ ቅቡልነትም አይኖረውም።
በኢትዮጵያ ሕገመንግሥት በአንቀጽ 8 የተደነገገውም፣ ይህንኑ መርህ በግልጽ የሚያጸና ነው። ሥልጣን (መሠረታዊው የሉዓላዊነት ሥልጣን) የብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች መሆኑን፣ ይሄ ሥልጣንም መገለጫው ሕገ-መንግሥቱ መሆኑን፣ ሕገ-መንግሥቱ ከሚደነግገው አግባብ ውጪ በሌላ መንገድ ሥልጣን መያዝ የማይቻል መሆኑንም በግልጽ ይደነግጋል። ይሄ ከሕገ-መንግሥቱ መሠረታዊ መርሆዎች አንዱና የመጀመሪያው ነው።
ሕገ-መንግሥቱ፣ በዝርዝር ድንጋጌዎቹም፣ ኢትዮጵያ የውክልና ዴሞክራሲ ሥርዓት እንደምትከተል፣ ይሄንንም ለመተግበር፣ የሕዝብ ተወካዮች በየአምስት ዓመቱ በሕዝብ እንደሚመረጡ፣ እነዚህ በህዝብ የተመረጡ ተወካዮች (ማለትም የፓርላማ አባላት)፣ መንግስት (የሥራ አስፈጻሚውን አካል) እንደሚያቋቁሙ፣ የፓርላማው (እና በፓርላማው የተቋቋመው መንግሥትም) የሥልጣን ዘመን አምስት ዓመት ብቻ እንደሆነ፣ በግልጽ ያስቀምጣል (አንቀጽ 50፣ 54፣ 56፣ እና 58)።
2. የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት (በፌደራሉም ሆነ በክልሎች ደረጃ) የሥልጣን ዘመን፣ 5 ዓመት መሆኑ በግልጽ ተደንግጓል። ይሄ በክልሎቹ ሕገ-መንግሥታት ውስጥም በግልጽ የተቀመጠ ድንጋጌ ነው።
ከዚህም የተነሳ፣ ምርጫ፣ ይህ የሥልጣን ዘመን ከማለፉ (ወይም 5ቱ ዓመታት ከማለቃቸው)(አንድ ወር) በፊት ተካሂዶ መጠናቀቅ አለበት።
ምርጫ ባልተካሄደበት ሁኔታ፣ ሥልጣን ማስረዘም የሚቻልበት አንዳችም ክፍተት የለም።
ያለ ምርጫ ሥልጣንን ለማራዘም ሲባል ብቻ የሚደረግ የትርጉም ፍለጋ ተግባርም ትክክል አይደለም፤ ምንም ሕጋዊ መሠረት የለውም።
3. በኮረና ምክንያት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የታወጀ በመሆኑ ምርጫ ለማድረግ ይቻል ወይም አይቻል እንደሆነ ለማወቅ ሕገ-መንግሥታዊ ትርጉም መጠየቁም፣ ያስፈልጋል ተብሎ መበየኑም፣ ፍጹም ሕጋዊነትም ሆነ ሕገ-መንግሥታዊነት ያለው አካሄድ አይደለም። ሕጉ በግልጽ "ምርጫ በየአምስት ዓመቱ ይካሄዳል" ካለ፣ እና ይሄን ተላልፈን ሥልጣን ማራዘም አለብን ከተባለ፣ ብቸኛው መንገድ፣ ሕገ-መንግሥቱን ማሻሻል ነው እንጂ፣ የሕገ-መንግሥት ትርጉም መጠየቅ አይደለም። ሕግ ግልጽ በሆነ ጊዜ የሚያስፈልገው መተርጎም ሳይሆን፣ መተግበር ብቻ ነው።
4. ይሄም ሆኖ፣ ጉዳዩ ለሕገ-መንግሥት አጣሪ ጉባኤ ሲመራ፣ መጀመሪያ ሊወሰን የሚገባው ጭብጥ፣ "ትርጉም ያስፈልጋል ወይስ አያስፈልግም?" የሚለው ሆኖ ሳለ፣ ይሄንን በማለፍ ወደ "ትርጉም" ሥራ ተገባ። ለመተርጎምም እንዲቻል፣ የህገ-መንግሥት ሕግ ባለሙያዎች፣ የሕገ-መንግሥቱ አርቃቂዎች፣ ወዘተ የትርጉም ሃሳብ እንዲያቀርቡ ተጠየቀ። አጣሪ ጉባኤው፣ እራሱ በሕገመንግሥት ትርጉም ጉዳይ የመጨረሻው የሕግ ባለሙያዎች አካል ተደርጎ የሚወሰድ ቅድመ-ግምት (presumption) መኖሩን ባለመገንዘብ፣ ከሌላ አካል የሕገ-መንግሥት ትርጉም ሃሳብ መጠየቁ ስህተት ነበር። ይሄ ተግባሩ፣ በኢትዮጵያ የሕግ ሥርዓት ታሪክ ውስጥ አሳፋሪ ሆኖ ሲታወስ ይኖራል።
የሕገ-መንግሥት ትርጉም የሚያስፈልገው አንቀጽ ኖሮ፣ ትርጉም ያስፈልጋል ቢባል እንኳን፣ ከጉዳዩ ጋር የፍሬ ነገር ተያያዥነት ስላለው መሰማት ያለበት የሙያ ምስክርነት፣ የጤና ባለሙያዎችና የምርጫ ባለሙያዎች ሙያዊ የምስክርነት ቃል ብቻ ነበር።
የጤና ሚኒስቴር እና የምርጫ ቦርድ ሹመኞች ቀርበው የሰጡት ምስክርነት፣ ሕገ-መንግሥታዊ ትርጉም የሚያስፈልገው አንቀጽ የነበረ ቢሆን ኖሮ፣ ትክክለኛ የሆነ፣ የፍሬ ነገር ጭብጥ ለማስረዳት የሚጠቅም፣ ምስክርነት ነበር። በእነሱ ምስክርነት መሠረት፣ "ምርጫ ለማድረግ አይቻልም" የሚል መደምደሚያ ላይ ከተደረሰም፣ ትክክለኛው ቀጣይ ውሳኔ መሆን የነበረበት፣ የሕገ-መንግሥት ማሻሻያ እንዲደረግ ሃሳብ ማቅረብ ነበር እንጂ፣ ያለ ምርጫ የሥልጣን ዘመንን ማራዘም አልነበረም።
5. አጣሪ ገባኤው፣ ያለ ሥልጣኑ ኢ-ሕገመንግሥታዊ በሆነ መንገድ የአብይን መንግሥት የሥልጣን ዘመን ለማራዘም ያቀረበው የውሳኔ ሃሳብ ለፌደሬሽን ምክር ቤት ሲቀርብ፣ የወቅቱ የፌደሬሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ፣ የውሳኔ ሃሳቡን፣ ሕገ-መንግሥታዊ ስላልሆነ አለመቀበላቸውን በይፋ ገልጸዋል። በዚህም፣ የሕገ-መንግሥት ትርጉም ሥራን በሚመለከት የመጨረሻ ሥልጣን ያለውና የሕገ-መንግሥቱ ባለአደራ የሆነው የፌደሬሽን ምክር ቤት፣ ውሳኔውን ውድቅ እንዳደረገው ግልጽ ሆነ።
ይሄንን የውሳኔ ሃሳብ፣ አብይ በጉልበትና በድርጅታዊ ሴራ በምክር ቤቱ ላይ ለመጫን ጥረት ሲያደርግም፣ አፈ-ጉባኤዋ፣ ለሕገ-መንግሥቱ፣ ለፌደሬሽኑና ለሕዝቦቹ፣ እንዲሁም ለህሊናቸው ተገዢነታቸውን በመግለጽ፣ ከስልጣናቸው እራሳቸውን አግልለዋል። ይሄም፣ ውሳኔው ተቀባይነት እንዳጣ፣ ሕገ-መንግሥታዊና ተቋማዊ መሠረትም እንዳላገኘ፣ ግልጽ ያደረገ ክስተት ነበር።
ጥልቅ የሆነ የሕገ-መንግሥት ቀውስ ሁኔታ በገሃድ የተከሰተበት ወቅትም ይሄ ወቅት ነበር። (በነገራችን ላይ፣ የመከላከያ ሠራዊት ጣልቃ በመግባት ሕገ-መንግሥታዊ ሥርዓቱን የመታደግ ሥራ መሥራት ከነበረበት ወቅቶች አንዱ ይሄ ወቅት ነበር። የሕገ-መንግሥቱ ባላደራ የሆነው ተቋም በኢ-ሕገመንስታዊ መንገድ፣ ለኢሕገመንግሥታዊ ዓላማ ተብሎ በሥራ አስፈጻሚው አካል ሲጠቃና ሥልጣኑ ሳይከበር ሲቀር፣ ሠራዊቱ፣ የተቋምና የሥርዓት መናድን እያየ ዝም ማለቱ ተገቢ አልነበረም።)
6. መንግሥታዊ ሕገ-ወጥነቱ ቀጥሎ፣ በይፋ ሕገ-መንግሥታዊ ሥርዓቱን ከሥሩ መሸርሸሩ እየተስፋፋ፣ አፈ-ጉባኤዋ በተቃውሞ የለቀቁትን የፌደሬሽን ምክር ቤቱን በመጠቀም፣ የአብይ መንግሥት የፌደራሉን ብቻ ሳይሆን የክልሎችን ምርጫም ላልተወሰነ ጊዜ አስተላለፈ፤ ያለ ምርጫም የአብይን መንግሥት የሥልጣን ዘመን አራዘመ። ባልቀረበለት የክልሎች ሕገ-መንግሥታት ላይም "የትርጉም" ሥልጣን ያለው ይመስል በማይመለከተው ጉዳይ ገብቶ የክልሎቹን ምክር ቤቶች የሥልጣን ዘመን አራዘምኩ አለ።
ይሄን ተከትሎም፣ ለወትሮውም ቢሆን ምርጫ እንዳይካሄድ ሲወተውት የነበረው ምርጫ ቦርድ፣ በአብይ ትዕዛዝ፣ "ክልሎች ካለ እኔ ፈቃድ ምርጫ ማካሄድ አይችሉም፤ ምርጫ ማድረግ፣ ሕገ-መንግሥታዊ ሥርዓቱን አደጋ ውስጥ ስለሚከት፣ ክልሎች ምርጫ ለማድረግ ከተነሱም፣ የፌደራል ጣልቃ-ገብነት ትዕዛዝ በማውጣት አስቆማለሁ" ሲል ፎከረ።
7. በመሠረቱ፣
ሀ) ምርጫ ቦርድ፣ በአንቀጽ 102 መሠረት፣ ምርጫ የማስፈጸም ሥልጣንና ኃላፊነት (ግዴ

ታ) አለው/አለበት እንጂ፣ ምርጫ የመከልከል ሥልጣን የለውም።
ለ)ምርጫ ቦርድ
በአዋጅ፣ "ጠቅላላ ምርጫ" (ማለትም ለፌደራልና ለክልል ምክር ቤት አባልነት የሚካሄዱ ምርጫዎችን) የማስፈጸም ስልጣንና ግዴታ አለበት።
ሐ) ክልሎች፣ የትግራይ ክልል እንዳደረገው፣ ምርጫ እንዲያስፈጽምላቸው ሲጠይቁ፣ "አልችልም" ብሎ ከኃላፊነት መሸሹ የሚያስጠይቅ ነው። በምንም ምክንያት ይሁን "አልችልም ወይም አልፈልግም" ካለ ግን፣ ክልሎች ምርጫ እንዳያካሄዱ እንቅፋት መሆን አይገባውም፣ አይችልምም። ምርጫን ማደናቀፍ በወንጀል ያስጠይቃልና።
መ) ምርጫ ቦርድ፣ ምርጫ የማስፈጸም ሥልጣን አለው ማለት፣ በአገሪቱ ውስጥ ብቸኛው የምርጫ አስፈጻሚ ተቋም እርሱ ነው ማለት አይደለም። ምርጫን የሚመለከት ጉዳይ የሚመለከተው እርሱን ብቻ ነው ማለት አይደለም።
ሠ) 'የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ'፣ ምርጫ የማስፈጸም ሥልጣን አለው ማለት፣ ምርጫ የማስፈጸም ሥልጣን የፌደራል መንግሥት ሥልጣን ሥር ይወድቃል ማለት አይደለም። ሕገ-መንግሥቱ፣ የትም ቦታ፣ ምርጫን የማካሄድ ሥልጣን የፌደራል መንግሥት ሥልጣን መሆኑን አይደነግግም። ምርጫ ቦርድ፣ ሕገ-መንግሥቱን ጥሶና ሕገ-መንግሥታዊ ግዴታውን ገፍቶ (ሥልጣኑን abdicate አድርጎ)፣ ምርጫ እንዳይካሄድ ስለወሰነ ብቻ፣ ክልሎቹ ምርጫ እንዳያደርጉ መከልከል ይችላል ማለት አይደለም። ክልሎች እንዲህ ያለውን ኢ-ሕገመንግሥታዊ የምርጫ ቦርድ ደብዳቤ በመቃወማቸው፣ "ፌደራል መንግሥቱን አላከበሩም" (አንቀጽ 50(8)) አያስብልም። ምክንያቱም፣ 'ብሔራዊ' ምርጫ ቦርድ፣ እራሱን የቻለ ሕገ-መንግሥታዊ ተቋም ነው እንጂ፣ የፌደራል መንግሥቱ አካል (ወይም ተቀጥላ) አይደለምና። የፌደራል መንግሥቱ፣ በምርጫ ጉዳይ ላይ (በተለይ በክልሎች ውስጥ በሚካሄድ ምርጫ ጉዳይ ላይ) አንዳችም ሥልጣን የለውም።
ረ) 'ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ'፣ እራሱን የቻለ ሕገ-መንግሥታዊ ተቋም ነው እንጂ፣ የፌደራል መንግሥት ተቋም አይደለም። የፌደራል መንግሥቱ ተላላኪ፣ የመንግሥቱ ሥራ አስፈጻሚ፣ ነው ማለት አይደለም። በአገሪቱ ክልሎች ውስጥ ምርጫ የማስፈጸም ግዴታውን ስለገፋ ብቻም፣ ክልሎች ምርጫ እንዳያደርጉ የማስገደድ አለው ማለት አይደለም።
ሰ)ክልሎች በሕገ-መንግሥቱ በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ ምርጫ ማካሄዳቸው (አሁን የትግራይ ክልል እያደረገ እንዳለው)፣ ሕገ-መንግሥቱን ያጸናል፣ ያስከብራል፣ እንጂ፣ በየትኛውም መስፈርት፣ ሕገ-መንግሥቱን አይጥስም፤ ወይም ሥርዓቱን ለአደጋ አያጋልጥም።
ሕገ-መንግሥቱን በመጣስ፣ ሕገ-መንግሥታዊ ሥርዓቱን ለአደጋ የሚያጋልጠው፣ በተጨባጭም እያጋለጠ ያለው፣ ምርጫን አለማድረግ ነው እንጂ፣ ምርጫን ማካሄድ አይደለም።
ምርጫን አላደርግም ያለው ሕገወጥ ቡድን፣ ምርጫን ለማካሄድ የሚንቀሳቀሱ ሕጋውያንን ለማስጠንቀቅ መሞከሩ፣ የኢፍትሓዊነት ጥግ ላይ መደረሱን ያረጋግጣል። It's a travesty of justice, pure and simple.
ተፃፈ በዶ/ር ፀጋዬ
የላከልን ጉማዬ ነው

አለሕግAleHig ️
ጉማዬ😷: ለዚ በቂ መልስ በቀድሞ የአ.አ ዩኒቨርስቲ የህገ መንስት አስተማሪ ስለ (ትግራይ) ምርጫ ሕገ-መንግሥታዊነት እንደገና (26 August 2020) ======= 1. ምርጫ ማካሄድ፣ ሕገ-መንግሥታዊ ግዴታን በተገቢው መንገድ መወጣት ነው። ምርጫን በተቀመጠለት የጊዜ ሰሌዳ መሠረት ማካሄድ፣ የአንድን ሕዝብ የዴሞክራሲ መብት (ማለትም፣ ሕዝቦች መንግሥታቸውን የማቆም፣ የመቆጣጠርና፣ ካልፈለጉትም የመሻር…
ይሄንን ጽሑፍ የጻፉት የህገ-መንግስት አስተማሪ ናቸው መባሉ በራሱ ያሳፍራል። የፖለቲካውን ወሬ ትተን የምናወራው ስለ ህግ ከሆነ እነዚህ የህገ መንግሥት አንቀጾች በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ወቅት ምርጫን ማራዘም እንደሚቻል ያስረዳናል። የመጀመሪያው አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለማወጅ የሚያበቃ ምክንያት መኖሩ ሁላችንንም የሚያስማማን ነገር እንደሆነ አምናለሁ። በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ወቅት የሚንስትሮች ምክር ቤት የዜጎችን መሠረታዊ የፖለቲካና የዲሞክራሲ መብቶችን አዋጁን ለማሳወጅ ምክንያት የሆነውን ጉዳይ ለማስወገድ ተፈላጊ ሆኖ በተገኘው ደረጃ ማገድ እንደሚችል በህገ መንግስቱ አንቀጽ 93 (4) (ለ) በግልጽ ተቀምጦ ይገኛል። ምርጫ የዜጎች መሰረታዊ የፖለቲካ መብት ስለሆነ ሊታገድ እንደሚችል ግልጽ ነው። ሰዎች እንኩዋን እነዚህን መብቶችን መጠቀም ቀርቶ ከፈጣሪያቸው ጋርም በቤተ እምነታቸው እንዳይገናኙ ታግደዋል። እንግዲህ ህግ ሲቀረጽ መርህ(principle) ብቻ ሳይሆን exception (አሁን አቻ የአማርኛ ትርጉም ስላጣሁለት ነው) አብሮ እንደሆነ እንኩአን ለህግ አስተማሪ ለሌላው ዜጋም ብዙም ውስብስብ ነገር አይደለም። ምርጫ ዜጎች ያላቸውን ሉአላዊ የሆነ ስልጣን በውክልና ለመንግስት የሚያስተላልፉበት መንገድ ነው። ህገ መንግስት ደግሞ በመንግስት እና በህዝብ መካከል ያለውን ግንኙነት የሚያሳይ ሰነድ ነው ማለት እንችላለን። እንግዲህ በየ አምስት አመቱ ምርጫ መካሄድ አለበት ብሎ የደነገገው ህገ መንግስቱ (መርህ/principle) በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ደግሞ የዜጎችን ህገ መንግስታዊ የሆኑ መብቶችን ማገድ እንደሚቻል (exception) ራሱ ህገመንግስቱ እንደሚደነግግ አይተናል።
ከዚህም አልፎ ህገ መንግስቱ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ወቅትም ጭምር ሊሻሩ የማይችሉትን መብቶች ግልፅ በሆነ መልኩ በህገ መንግስቱ አንቀጽ 93 (4) (ሐ) ላይ አስቀምጧል። እነዚህም አንቀፅ 1፣18፣25፣39(1) (2) መሆኑን ገልጿል። እነዚህ አንቀጾች ደግሞ ምርጫን ከማድረግ ጋር ሚገናኙ አይደሉም። ስለዚህም ህገ መንግስቱ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ወቅት የዜጎችን መሰረታዊ የፖለቲካ መብቶች መገደብ እንደሚችል ከመደንገጉም በላይ ምርጫ ህገ መንግሥቱ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ወቅት ሊገደቡ አይችሉም ካላቸው አንቀጾች ውጪ በመሆኑ ህገ መንግሥቱ ምርጫን በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ሊገድበው እንደሚችል ግልፅ ነው።
እኔ ፖለቲከኛ አይደለሁም። በወልቂጤ ዩኒቨርስቲ ተመራቂ የህግ ተማሪ ነኝ። ይህንን ሃሳብ ህግን መሰረት ባደረገ መልኩ የምትቃረኑ ከሆነ እኔም የተሻለ መረዳት እንዲኖረኝ እይታችሁን አካፍሉኝ።
በደሳለኝ ንዳ ተጻፈ

ታ) አለው/አለበት እንጂ፣ ምርጫ የመከልከል ሥልጣን የለውም። ለ)ምርጫ ቦርድ በአዋጅ፣ "ጠቅላላ ምርጫ" (ማለትም ለፌደራልና ለክልል ምክር ቤት አባልነት የሚካሄዱ ምርጫዎችን) የማስፈጸም ስልጣንና ግዴታ አለበት። ሐ) ክልሎች፣ የትግራይ ክልል እንዳደረገው፣ ምርጫ እንዲያስፈጽምላቸው ሲጠይቁ፣ "አልችልም" ብሎ ከኃላፊነት መሸሹ የሚያስጠይቅ ነው። በምንም ምክንያት ይሁን "አልችልም ወይም አልፈልግም" ካለ…
These guys have completely forgotten the very objective of election in which people ascertain their democratic rights and bring to power those who care for their human rights issues including their rights to life. Elections should not be lifeless and mechanical and if it is expected to be carried out by the expense of the lives of the poor for the sake of putting some 'artful politicians in power', then that's what traversy of justice is all about since the so called politicians will have no one to represent and rule. Being written by a 'doctor' does not make an article always credible.
Sisay Degaga
Sisay Degaga
ስንሽከረከር እንዳንውል ለነገሩ ጭብጥ መኖሩ አግባብ መሆኑን አምናለሁ። በመሆኑም
1 ምርጫ የዜጎች ዴሞክራሲያዊ መብት መሆኑ
2 በአንቀፅ 93 ስር ከማይታገዱ የዜጎች መብት ስር አለመካተቱ
ለዚህ የምርጫ ጉዳይ በቂ ጭብጥ ነው የሚል እምነት አለኝ።
ሌላው የሚያሳዝነው ጉዳይ መንግስት በክልሎች ጉዳይ ጣልቃ ከሚገባባቸዉ ጉዳዮች
1 ህገመንግስታዊ ሥርዐቱን አደጋ ላይ የሚጥል ጉዳይ ሲኖር
2 የህዝብን ጤንነት አደጋ ላይ የሚጥል ሁኔታ ሲኖር ነው
እናም አሁን ያሳዘነኝ ጉዳይ የህዝብ ጤንነት አደጋ ላይ የሚጥል ይህ ሁኔታ ተከስቶ ሳለ ምርጫ እንዲካሄድ በዝምታ ወይም ህጋዊ እውቅና የሌለው ምርጫ የሚል ውሳኔ በጣም አሳዛኝ ነው።
የክልከለው አላማ የህዝቡን ጤና እንዲጠበቅ ማስቻል በመሆኑ ነው። እናም የጤናቸው ጉዳይ አያሳስበኝም ስልጣኔን ግን አላስነካም ማለት ያስተዛዝባል።
የፌደራሉ መንግሰት ለህዝብ ቢቆም ኖሮ ይህንን ምርጫ ያስቆም ነበር።
ስለሆነም ከአዋጁ አላማ ውጭ ፖለቲካዊ ጉዳዩን ብቻ ማታየቱ ያሳዝነኛል።
እዚህ ላይ የፌደራል መንግስት በክልሎች ጉዳይ የሚገባበት ሁኔታ በአዋጅ መውጣቱን መገንዘብ ያሻል።
በ ∞

ህገ-መንግስት እንዲያኗኑረን እንጅ ለዕለት ህይወታችን ሆነ ለጥቅል ማህበራዊ ስሪታችን ጠንቅ እንዲሆን የተከተበ ሰነድ እንዳይደለ ጠንቅቀን እናውቃለን፡፡ህገ-መንግስት የተቀመጠው የማህበረሰባችን ህይወት ሰበቃ ቀንሶ አብሮ መኖራችንን በመደላድል እንዲያመቻምች እንጅ ከድጡ ወደማጡ እንዲከት አይደለም፡፡የማህበረሰብ ህይወትን በህግ መሰረት ቃኝቶ ለማጽናት የተቀረጸው ይኸው ሰነድ ባለቤቱ የሆነው ህዝብ ያልተገመተ ፈተና ሲገጥመው በልሂቃን እየዳበረ ጊዜውን እየመጠነ የሚሄድ እንጅ ቆሞ ቀር መሆንም የለበትም፡፡
የህግ ምሁራን የፖለቲከኞች ቀላጤ ሲሆኑ የህግ ሥርዓቱ በጥልቅ ቀውስ ውስጥ እንደሚገኝ ለመገንዘብ አያዳግትም፡፡ በመቀሌ ዩኒቨርሲቲ የህግ መምህርም ይኸው መሰለኝ እየተደረገ ያለው፡፡ የህግ ልሂቃን በተቻላቸው በራሳቸው ተፈጭተው ፣ተከራክረው እና ተሟግተው ለማህበረሰብ መተላለፊያ መንገድ ሊያበጁ ሲገባ ጎራ ለይተው ከመርህም ሆነ ከሞራል ባፈነገጠ አኳኋን ወገንተኛ የሆነ እና በፖለቲካ የታጀለ የህግ ትንተና ሲያቀርቡ ለህግ ስርዓታችን መጎልበት ምን ያህል ጠንቅ ሊሆን እንደሚችል መረዳት ይኖርብናል፡፡
ለመቀሌው ዩኒቨርሲቲ መምህር የማቀርበው
1. በዜጎች ጤናቸው ተጠብቆ የመኖር መብትን በተመለከተ ምን አስተያየት ይኖራቸው ይሆን?
2. ለህግ የበላይነት ያላቸው ምልከታስ እንዴት ይገለጽ ይሆን?
3. በፌዴሬሽን በአንድ ተጣምሮ የሚገኝ በባለ ሁለት ደረጃ መንግስታዊ አስተዳድር መርሆዎችና የስልጣን እና ተግባር ድልድሎችስ ላይ ምን ይነግሩናል?
4. የፍርድ ቤት ውሳኔ ሲጣፍጥ የሚከበር ሲመር ግን ወደ ጎን የሚደረግ ነው ወይ?
ህግ ስርዓታችንን በተመለከተ ብዙ ህጸጾች መዘርዘር አይደለም ለባለሙያ ለሰፊው ህዝብም የሚከብድ እንዳልሆነ እናውቃለን፡፡አሁን ደግሞ ከትላንት ዛሬ ከተደፋበት ለመቀናት ደንበር ገተር በሚልበት ወቅት እንዲህ ያለ ህግን እና ፖለቲካን ክፉኛ የደባለቀ ትንተና ለነገ ስምም አይበጅም፡፡ ያፈጠጠውን ለመከለለ እንዲህ የቃላት ድሪቶ ማድራት ነገ በትምህርት ክፍል የአሉታ ማጣቀሻ ከመሆን ያለፈ ሚና ይኖረዋል የሚል እምነት የለኝም፡፡
ቀና ቀናውን ያመላክተን፡፡
አንገት ከሚሰበር ……. እንዲል አቀንቃኙ ብኩርናን ለምስር ዳርጎት መለወጥ ነውር ነው በሉልኝ፡፡
በ ካbtaAmu