አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.87K photos
25 videos
1.86K files
3.58K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
#Ethiopia : በኮቪድ-19 ሕይወቷ ላለፈው ኢትዮጵያዊት ቤተሰብ እና ወዳጆች ከልቤ መጽናናትን እመኛለሁ። ነፍሷ ዘላለማዊ ረፍትን ታግኝ።

ዜናውን የሰማችሁ ሁሉ #እንድትረጋጉ እና የወጡትን መመሪያዎች በጥብቅ እንድትከተሉ አሳስባለሁ።

የሚገጥመንን ሁኔታ በጋራ ለማስተናገድ በምንዘጋጅበት በዚህ ጊዜ፣ በእምነት ጸንተን ቫይረሱ በማኅበረሰባችን መካከል እንዳይሠራጭ በትጋት ልንሠራ ያስፈልጋል።

አካላዊ ርቀታችሁን ጠብቁ። እጆቻችሁን በሚገባ ታጠቡ። በምትችሉት መንገድ ሁሉ ለሌሎች ድጋፍ አድርጉ።

(የኢፌዴሪ ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ አሊ)
አለሕግAleHig ️
Video
The Federal Supreme Court of Ethiopia:
በፍርድ ቤቶች እተደረጉ ያሉ ማሻሻያዎችን በተመለከተ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት ክብርት ወ/ሮ መዓዛ አሸናፊ ለቀረበላቸው ጥያቄ የሰጡት መልስ ፋና ብሮድካስቲንግ እነደዘገበው፡፡
የሟች ቁጥር ሁለት (2) ብለናል።
@lawsocieties

የግሌ ኮሮና ደብዛሽ የጠፋብኝ፤
እራሴን ያመመኝ ትኩሳት የሆንሽኝ፤
ጉሮሮየን ፍቀሽ እዳልቀምስ ያረገሽኝ፤
ሰውነቴ እስኪዝል በደረቁ አስሎኝ፤
ነፍሴ ልትወጣ ነው ፍቅርሽ አስነጥሶኝ
አየርም ያጥረኛል መተንፈስ ቸገረኝ፤
አርቴፍሻል አፍሽን ልተንፍስ ላኪልኝ፤
ትዝታ ገዳይ ነው ነይና አገግሚኝ።

🔝አለ ትዝታ🛑
@lawsocieties @lawsocieties
https://telegram.me/lawsocieties
COVID-19 underscores the critical (and often unmet) need for protective equipment for nurses/midwives, which enables them to safely provide care and reduce the rate of infection in emergency settings.

On this #WorldHealthDay we join the World Health Organization (WHO) showing our gratitude to them.
This is the final version of the proclamation on Hate Speech. It can help others, please share it.
የዓለም የጤና ድርጅት ‘‘ክትባቱ በአፍሪካውያን ይሞከር’’ የሚለውን የተመራማሪዎች ሐሳብ አወገዘ፡፡
https://amharaweb.com/የዓለም-የጤና-ድርጅት-ክትባቱ-በአፍሪ/
ባሕር ዳር፡ መጋቢት 29/2012 ዓ.ም (አብመድ) የዓለም ጤና ድርጅት የኮኖና ቫይረስ ክትባት በአፍሪካውን እንዲሞከር ከሰሞኑ ተመራማሪዎች ያቀረቡንት ሐሳብ አውግዟል፡፡

ሁለት የፈረንሳይ የሕክምና ሳይንስ ተመራማሪዎች የኮሮና ቫይረስ በአፍሪካውን ላይ እንዲሞከር ሐሳብ ማቅረባቸው አፍሪካውያንን አስቆጥቷል፡፡ በኋላም አንደኛው ዶክተር ይቅርታ መጠየቃቸው ይታወሳል፡፡

የዓለም የጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም የኮሮና ወረርሽኝን በተመለከተ በሰጡት መግለጫ ላይ ጉዳዩን በተመለከተ ሐሳብ ሰጥተዋል፡፡ ዶክተር ቴዎድሮስ ይህንን…

https://telegram.me/lawsocieties
አለሕግAleHig ️
cassation decision 189201.pdf
የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችሎት ጉዲፈቻን አስመልክቶ የህግ ትርጉም ሰጠ

የፌዴራል ጠቅላይፍረድ ቤት 1ኛ ሰበር ችሎት መጋቢት 02 ቀን 2012 ዓ.ም በዋለው ችሎት የውጭ ሃገር ጉዲፈቻን በተመለከተ የቀድሞ የቤተሰብ ህግ ደንጋጌን ያሻሻለው አዋጅ ቁጥር 1070/2012 ላይ በመዝገብ ቁጥር 189201 አስገዳጅ የህግ ትርጉም ሰጥቷል፡፡ ለዝርዝሩ ከዚህ መልዕክት ጋር የተያያዘውን የችሎት ውሳኔ ግልባጭ ያንብቡ፡፡
በችሎቶች የተሰጡ ውሳኔዎች Table.pdf
160.7 KB
የፌደራል ፍርድ ቤቶች የኮሮና ቫይረስ ወረርሽንን ለመከላከል በከፊል ዝግ ሆነው በቆዩባቸው ጊዜያት በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከመጋቢት 11 - 28/2012 ዓ.ም ድረስ በተለያዩ ችሎቶች በቀረቡ መዝገቦች ላይ የተሰጡ ውሳኔዎች እንደሚከተለው ቀርበዋል፡፡
Article 93
Declaration of State of Emergency
1. (a) The Council of Ministers of the Federal Government shall have the
power to decree a state of emergency, should an external invasion, a break
down of law and order which endangers the Constitutional order and
which cannot be controlled by the regular law enforcement agencies and
personnel, a natural disaster, or an epidemic occur.
(b) Sate executives can decree a State-Wide state of emergency should a
natural disaster or an epidemic occur. Particulars shall be determined in
State Constitutions to be promulgated in conformity with this Constitution.
2. A state of emergency declared in accordance with sub-Article 1(a) of this
Article:
(a) If declared when the House of Peoples’ Representatives is in session,
the decree shall be submitted to the House within forty-eight hours of
its declaration. The decree, if not approved by a two-thirds majority
vote of members of the House of Peoples' Representatives, shall be
repealed forthwith.
(b) Subject to the required vote of approval set out in (a) of this subArticle, the decree declaring a state of emergency when the House ofPeoples’ Representatives is not in session shall be submitted to it
within fifteen days of its adoption.
3. A state of emergency decreed by the Council of Ministers, if approved by
the House of Peoples’ Representatives, can remain in effect up to six
months. The House of Peoples’ Representatives may, by a two-thirds
majority vote, allow the state of emergency proclamation to be renewed
every four months successively.
4. (a) When a state of emergency is declared, the Council of Ministers shall,
in accordance with regulations it issues, have all necessary power to
protect the country’s peace and sovereignty, and to maintain public
security, law and order.
(b) The Council of Ministers shall have the power to suspend such political
and democratic rights contained in this Constitution to the extent necessary
to avert the conditions that required the declaration of a state of
emergency.
(c) In the exercise of its emergency powers the Council of Ministers can
not, however, suspend or limit the rights provided for in Articles 1, 18, 25,
and sub-Articles 1 and 2 of Article 39 of this Constitution.
5. The House of Peoples’ Representatives, while declaring a state of
emergency, shall simultaneously establish a State of Emergency Inquiry
Board, comprising of seven persons to be chosen and assigned by the
House from among its members and from legal experts.
6. The State of Emergency Inquiry Board shall have the following powers
and responsibilities:
(a) To make public within one month the names of all individuals arrested
on account of the state of emergency together with the reasons for their
arrest.
(b) To inspect and follow up that no measure taken during the state of
emergency is inhumane.
(c) To recommend to the Prime Minister or to the Council of Ministers
corrective measures if it finds and case of inhumane treatment.
(d) To ensure the prosecution of perpetrators of inhumane acts.
(e) To submit its views to the House of Peoples’ Representatives on a
request to extend the duration of the state of emergency.
via y2y
From tomorrow onwards there are new communication regulations.

All calls are recorded

All phone call recordings saved

WhatsApp is monitored

Twitter is monitored

Facebook is monitored

All social media and forums are monitored

Inform those who do not know.

Your devices are connected to ministry systems.

Take care not to send unnecessary messages

Inform your children, Relatives and friends about this to take care

​​Don't forward any posts or videos etc., you receive regarding politics/present situation about Government/PM etc.​​

Police have put out a notification termed ..Cyber Crime ... and action will be taken...just don't delete ...

Inform your friends & others too.

Writing or forwarding any msg on any political & religious debate is an offence now....arrest without warrant...

This is very serious, plz let it be known to all our groups and individual members as group admin can b in deep trouble.

Take care not to send unnecessary messages.
Inform everyone about this to take care.

Please share it; it's very much true. Groups please be careful.
👍1
አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ምን ማለት ነው? 🇪🇹

አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማለት መንግስት በ መደበኛው ስርአት ለማከናወን የማይችላቸውን ነገሮች እንዲያከናውን ጉልበት የሚሰጠው ህገመንግስታዊ መሳሪያ ነው ፡፡ በአሁኑ ሰአት በርካታ ሀገራት በ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ስር ነዉ ያሉት : ለምሳሌ ዩናይትድ ስቴትስ : ጃፖን : ሀንጋሪ : ቡልጋሪያ : ስሎቫኪያን መመልከት ይቻላል ::

በኢፌዴሪ ህገ መንግስት አንቀፅ 93 መሰረት ፡የውጭ ወረራ ሲያጋጥም ወይም ሕገ መንግስታዊ ስርአቱን አደጋ ላይ የሚጥል ሁኔታ ሲከሰትና በተለመደው የሕግ ማስከበር ሥርአት ለመቋቋም የማይቻል ሲሆን ፡ ማናቸውም የተፈጥሮ አደጋ ሲያጋጥም ወይም የህዝብን ጤንነት አደጋ ላይ የሚጥል በሽታ ሲከሰት ፡ የፌደራሉ መንግስት ፡ የሚኒስትሮች ምክር ቤት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የሚደነግግ ይሆናል ፡፡ ስለሆነም አሁን በተከሰተው ወረርሽኝ የተነሳ ዛሬ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ታውጇል ፡፡

የሚኒስትሮች ምክር ቤት ፡ በዚህ ሰአት ትልቅ ሚና የሚጫወት ሲሆን ስልጣኑም በህገ መንግስቱ የተቀመጡትን መሰረታዊ የፓለቲካና የዴሞክራሲ መብቶችን ፡ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ለማወጅ ምክንያት የሆነውን ጉዳይ ለማስወገድ ተፈላጊ ሆኖ በተገኘ ደረጃ እስከ ማገድ ሊደርስ የሚችል ነው ፡፡ ቢሆን ግን የሚኒስትሮች ምክር ቤት የሚወስዳቸው እርምጃዎች በማናቸውም ረገድ የማይገድባቸው መብቶች ተብለው በህገ መንግስቱ የተቀመጡት 1) የኢትዮጵያ መንግስት ስያሜ ፡ ማለትም ኢፌዴሪ የሚለውን 2) ኢሰብአዊ አያያዝ መከልከሉን 3) የእኩልነት መብትን እና 4) የብሄሮች ፡ ብሄረሰቦች ፡ ህዝቦች መብት ነው ፡፡ እነዚህ ከላይ ያሉት አራቱ መብቶች መቼም ቢሆን በሚኒስትሮች ምክር ቤት እርምጃ የማይገደቡ መብቶች ሲሆኑ ቀጥሎ ሊገደቡ የሚችሉ መብቶችን እናያለን ፡፡

በቀጣይ ጊዜያት መንግስት የሚያወጣቸዉ ዝርዝር መመሪያዎች እንደተጠበቁ ሆነዉ : በህገ መንግስቱ የተዘረዘሩትን ሊገደቡ የሚችሉ የፓለቲካና የዴሞክራሲ መብቶችን ለመጥቀስ ያህል 1) የአመለካከት እና ሐሳብን በነፃነት የመያዝና የመግለፅ መብት፡ 2) የመሰብሰብ ፡ ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ ነፃነት 3) የመደራጀት መብት 4) የመዘዋወር ነፃነት 5) የመምረጥ እና የመመረጥ መብቶች ፡ እያለ ይቀጥላል ፡፡ ባጭሩ አሁን የተከሰተውን ወረርሺኝ ለመግታት፡ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማወጅ ታውጃል ፡ ይህ ማለት ደግሞ ፡ በህገ መንግስቱ የተረጋገጡት የፓለቲካና የዴሞክራሲ መብቶች ለጊዜው ወረርሽኙን ለመግታት ሲባል እንደ አስፈላጊነቱ ሊገደቡ ይችላሉ ማለት ነው ፡፡

ስለሆነም በዚህ ሰአት መንግስት በቀጣይ የሚያወጣቸዉን መመሪያዎች ማክበር እና ከፀጥታ አካላት ጋር ተናቦ በቅንጅት መንቀሳቀስ ያስፈልጋል እንጂ መብቴ ነዉ ብሎ መድረቅ አያስፈልግም ምክንያቱም መብቶች ሊገደቡ ስለሚችሉ ::

በተረፈ እግዚአብሄር ሁላችንንም ይርዳን ::

ምንጭ;
ከህግ አገልግሎት /legal service ተገኘ
https://telegram.me/lawsocieties
ጉዳት ለመቀነስ የወጣ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በተመለከተ የኢፌዲሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የፅሁፍ ማብራሪያ ሰጥቷል።

የማብራሪያው ሙሉ ቃል እንደሚከለው ቀርቧል፦

1) የአዋጁ አስፈላጊነት እና አላማ
🔴🔴🔴የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ 🔴🔴

የኮቪድ-19 ሥርጭትን ለመከላከል፣ ለመቆጣጠር እና የሚያስከትለውን ጉዳት ለመቀነስ የወጣ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በተመለከተ የኢፌዲሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የፅሁፍ ማብራሪያ ሰጥቷል።

የማብራሪያው ሙሉ ቃል እንደሚከለው ቀርቧል፦

1) የአዋጁ አስፈላጊነት እና አላማ

#Ethiopia : የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ሕገ-መንግሥት ለሃገር እና ለህዝብ አደጋ የሆኑ ሁኔታዎች ሲያጋጥሙ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በማወጅ የሚተዳደርበትን ሥርዓት በአንቀጽ 93 ላይ አስቀምጧል። በአንቀጽ 93 (1) (ሀ) መሰረት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዲታወጅ መነሻ ከሚሆኑ ሁኔታዎች አንዱ “የሕዝብን ጤንነት አደጋ ላይ የሚጥል በሽታ ሲከሰት” የሚል ነው።የኮቪድ-19 የሕዝብን ጤንነት በከፍተኛ ደረጃ አደጋ ላይ የሚጥል በሽታ እንደሆነ ዕሙን ነው።

ይህን ወረርሽኝ ለመከላከል፣ ለመቆጣጠር እና የሚያስከትለውን ጉዳት ለመቀነስ የሚወሰዱ እርምጃዎችን ለማሳለጥ እና ውጤታማ ለማድረግ ደግሞ ከተለመደው አሠራር እና ሕገ-መንግሥታዊ ማዕቀፍ ወጥቶ በልዩ ሁኔታ መንቀሳቀስ ይጠይቃል። አዋጁ መንግሥት የቫይረሱን ስርጭት ለመከላከል አስፈላጊ የሆኑ እርምጃዎችን በሚወስድበት ጊዜ የተሻለ ነጻነት እና አቅም እንዲኖረው፣ የመንግስት ሥልጣን ላይ ያሉ ገደቦች ወይም የሰብዓዊ መብት ድንጋጌዎች በተለየ ሁኔታ ለጊዜው ተፈጻሚነታቸው ቀርቶ በሙሉ ኃይል፣ በተቀላጠፈ እና በተቀናጀ መልኩ ለወረርሽኙ ምላሽ መስጠት እንዲቻል በማሰብ ይህ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ታውጆዋል።

ወረርሽኙን ለመከላከል የሚወሰዱ እርምጃዎችን ለማሳለጥ እና ከሕግ አንጻር አስቻይ ሁኔታን ከመፍጠር ባለፈ፤ የዚህ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አላማ፣ ከቫይረሱ ስርጭት ጋር ተያይዘው የሚመጡ ተጓዳኝ ተግዳሮቶችን በተመለከተ አስፈላጊውን እርምጃዎች የመደንገግ ስልጣን ለስራ አስፈጻሚው የመንግስት አካል መስጠት ነው። እነዚህ አላማዎች ያሉት የኮቪድ-19 ሥርጭትን ለመከላከል፣ ለመቆጣጠር እና የሚያስከትለውን ጉዳት ለመቀነስ የወጣ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በዛሬው እለት በሚኒስትሮች ምክር ቤት ጸድቆዋል።

2) የአዋጁይዘት

የአዋጁ አንኳር ይዘት በአዋጁ አንቀጽ 4(1) የተለፀው፤ የሚኒስትሮች ምክር ቤት የወረርሽኙ ሥርጭት እያስከተለ ያለውንና ሊያስከትል የሚችለውን ሰብዓዊ፣ ማኅበራዊ ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ጉዳቶች ለመቀነስ እና ለመከላከል ይህንን አዋጅ ለማስፈጸም በሚያወጣቸው ደንቦች የመብት እገዳዎችንና፣ እርምጃዎችን በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 93 (4) (ሀ)እና (ለ) መሰረት ለመደንገግ የተሰጠው ስልጣን ነው። ይህም ማለት የወረርሽኙ ሥርጭት የሚያስከትለውን ጉዳት ለመቀነስ ወይም ለመከላከል እንደሁኔታው እና እንደአስፈላጊነቱ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ በማወጣት የመብት እገዳዎችን ማድረግ እና እርምጃዎችን መውሰድ ይችላል።

እነዚህን የመብት ገደቦች እና እርምጃዎች በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ወስጥ ዘርዝሮ ማስቀመጥ ያልተቻለው አስፈላጊ የሚሆኑት ገደቦች እና እርምጃዎች ከጊዜ ጊዜ እና በሃገሪቱ ውስጥ ከቦታ ቦታም ሊለያዩ ስለሚችሉ ነው። እንደወረርሽኙ ስርጭት የስፋት አድማስ፣ እንደሚያስከትለው ጉዳት አስፈላጊ የሆኑት ገደቦች እና እርምጃዎች ሊለዋወጡ ይችላሉ።

አዋጁ ተፈጻሚ በሚሆንበት ጊዜ ውስጥ ሁሉ የሚያስፈልጉት ክልከላዎች እና መወሰድ ያለባቸው እርምጃዎች ተለዋዋጭነት ሊኖራቸው ስለሚችል፣ ይህን ከግንዛቤ በማስገባት፣ በየጊዜው ያለውን ሁኔታ በመገምገም እና ስለቫይረሱ ስርጭትም ሆነ ባህሪ የሚገኙ ሳይንሳዊ መረጃዎችን፣ የህዝብ ጤና ባለሞያዎችን ምክር ከግምት በማስገባት የመብት እገዳዎችን እና እርምጃዎችን ተግባራዊ ማድረግ ያስልፈጋል። ይህን ለማድረግ ይቻል ዘንድ ዝርዝር እና ቋሚ የመብት እገዳዎችን እና እርምጃዎችን ከመዘርዘር ይልቅ እንዳስፈላጊነቱ ተለዋዋጭ (flexible) በሆነ ሁኔታ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ በማውጣት እገዳዎችን እና እርምጃዎችን እንዲደነግግ አዋጁ ስልጣን ይሰጠዋል። አዋጁ በዚህ መልክ የተቀረፀው አስፈላጊ የሆኑ የመብት እገዳዎች እና እርምጃዎች ዝርዝር ሁኔታ ከጊዜ ጊዜ፣ ከቦታ ቦታ ሊለዋወጥ እንደሚችል ታሳቢ በማድረግ ፣ ተጨባጭ ሁኔታውን ከግምት በማስገባት፣ አስፈላጊ እና ተመጣጣኝ የሆነ እገዳ ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችል አሠራር ለመዘርጋት ነው። ይህ አይነት አካሄድ የቫይረሱን ሥርጭት ለመከላከል የሚወሰዱ እርምጃዎች የተሻለ ውጤታማ እንዲሆኑ እና በሕገ-መንግሥታዊ መብቶችም ላይ ሊደርስ የሚችለውን አሉታዊ ተጽዕኖ አስፈላጊ ከሆነው መጠን ያላለፈ እንዲሆን ለማድረግ ይረዳል። በደፈናው ከሚጣሉ ገደቦች ይልቅ፣ በየጊዜው ያለውን ሁኔታ እና ስጋት ከግምት በማስገባት፣ አስፈላጊውን እርምጃ ለመውሰድ እንዲህ ያለ ማዕቀፍ ተመራጭ ነው።

የሚኒስትሮች ምክር ቤት የሚያወጣቸው ደንቦችና የሚወስዳቸው እርምጃዎች በማንኛውም ሁኔታ በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 93 (4) (ሐ) ልዩ ጥበቃ የተደረገላቸውን ድንጋጌዎች የሚገድቡ ሊሆኑ አይችሉም። ከዚህ በተጨማሪ በአለም አቀፍ ህግ እና አስቸኳይ ጊዜ አዋጅን በተመለከተ በተለመደው አሰራር መሰረት ሰፊ ተቀባይነት ያላቸው የ “አስፈላጊነት” እና “ተመጣጣኝነት” መርሆዎችም የሚንስትሮች ምክር ቤትን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ስልጣን የሚገድቡ አጠቅላይ መርህዎች ተደርገው በታሳቢነት የሚወሰዱ ናቸው።

• አዋጁ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን የማስፈጸም ኃላፊነትን በተመለከት የመብት እገዳዎቹና እርምጃዎቹ ዝርዝር ሁኔታ በየጊዜው በሚኒስትሮች ምክር ቤት ወይም የሚኒስትሮች ምክር ቤት ለዚሁ ዓላማ በሚያቋቁመው የሚኒስትሮች ኮሚቴ እየተወሰነ ለሕዝብ ይፋ እንደሚደረግያመላክታል።

• አዋጁ ማንኛውም ሰው በዚህ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መሠረት በሕግ አስከባሪ አካላት ወይም ሌላ በሕግ ሥልጣን ባለው አካል የሚሠጥ ሕጋዊ ትዕዛዝ እና መመሪያን የመፈጸም ግዴታ እንዳለበት ይደነግጋል። እንዲሁም የፌደራል፣ የክልል የሕግ አስከባሪ ተቋማት እና ሌሎች በሕግ ሥልጣን የተሰጣቸው አካላት ተመጣጣኝ ኃይል በመጠቀም በአዋጁ አንቀጽ 5 ንዑስ አንቀጽ 1 መሰረት ይፋ የተደረጉ የመብት እገዳዎችን እና እርምጃዎችን የማስፈጸም ስልጣን እንደሚኖራቸው ይደነግጋል።

• አንቀጽ 6 በወንጀል ሕግ የተካተቱ አግባብነት ያላቸው የወንጀል ድንጋጌዎች እንደተጠበቁ ሆኖ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ መሠረት የተደነገጉ የመብት እገዳዎችን፣ እርምጃዎችን፣ የተሰጠ መመሪያ ወይም ትዕዛዝን ሆን ብሎ የጣሰ ማንኛውም ሰው እስከ ሶስት ዓመት በሚደርስ ቀላል እስራት ወይም ከአንድ ሺ ብር እስከ ሁለት መቶ ሺ ብር በሚደርስ የገንዘብ መቀጮ ሊቀጣ እንደሚችል ያስቀምጣል።

• አስቸኳይ ጊዜ አዋጁ አንቀጽ 7 በአቸኳይ ጊዜ አዋጁ መሠረት የሚደነገጉ የመብት እገዳዎችና እርምጃዎች ዝርዝር ሁኔታ በጠቅላይ ሚኒስቴር ጽሕፈት ቤት እና ሕግ የማስረፅ ሃላፊነት በተጣለበት በጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ በስፋት ለሕዝብ ተደራሽ በሆኑ የመገናኛ ብዙሃን መገለጽ እንዳለባቸው ይደነግጋል። የፌደራልም ሆነ የክልል፣ እንዲሁም የግል ሚድያዎች ከዚህ ጋር የሚሰጡ ማብራሪያ እና ገለጻዎችን በተለያዩ ቁንቋዎች ለህዝብ የማድረስ ሃላፊነት እና ግዴታ አለባቸው።

• አዋጁ በመላው ሃገሪቱ ተፈጻሚ የሚሆን ሲሆን፣ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ከፀደቀበት ጊዜ ጀምሮ ለአምስት ወራት ተፈጻሚ ይሆናል።
https://telegram.me/lawsocieties