አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.87K photos
25 videos
1.86K files
3.58K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
የፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ:
ሁከት ሲባል ምን ማለት ነው? በፍትሐብሔር ሕጎች ያለው
ገጽታ እና ሁከት ተፈጥሯል የሚባልባቸው ሁኔታዎች
ምንድን ናቸው?
__________________
የሕግ የበላይነት የዓለም ሁሉ የትልቅነት መለኪያ እና
ራዕይ በመሆን ላይ ይገኛል፡፡ ህዝብ፣ መንግስት እና
በዓለም ላይ የሚገኙ ድርጅቶች ይደግፉታል፡፡ የሀገር
ውስጥ የአስተዳደራዊ እና የሕግ ሥርዓቶች የማዕዘን ራስ
ነው ተብሎ በስፋት ይታመናል፡፡
በዓለም ሆነ በሀገር አቀፍ ሕግጋት እውቅና ተሰጥቷቸው
ጥበቃ ከሚደረግላቸው መብቶች አንዱ የግል ነጻነት
መብት ነው፡፡ የግል ነጻነት መብት ሲባል በግለሰቦች
አካልም ሆነ ንብረት ወይም የይዞታ መብት ላይ
የሚደረግን አግባብነት የሌለው ጣልቃ ገብነት ለማስከበር
ሲባል የተቀመጠ መብት ነው፡፡
በዛሬ ዝግጅታችን ሁከት ማለት ምን ማለት ነው? ከሕግ
አኳያ እንዴት ይታያል? በሚል ርዕሰ ጉዳይ ለግንዛቤ ይረዳ
ዘንድ ይዘን ቀርበናል፡፡በግለሰቦች ወይም በይዞታዎቻቸውና
በንብረቶቻቸው ላይ የሚደረግ አግባብነት የሌለው ጣልቃ
ገብነት ሁከት የሚባል ሲሆን ከዚህ በመነሳት ሁከት
በማንኛውም ሕጋዊ ሰብአዊ ወይም ኢኮኖሚያዊ መብት
ላይ የሚደረግ ወረራ ወይም አግባብነት የሌለው
ያልተፈቀደ ጣልቃ-ገብነት ነው ብሎ ማስቀመጥ ይቻላል፡፡
በኢ.ፌ.ድ.ሪ ሕገ-መንግስት እና ሀገሪቱ በተቀበለቻቸው
ዓለም አቀፍ ስምምነቶች በተለይም በዓለም አቀፉ
የኢኮኖሚ፣ የማህበራዊና የባሕል መብቶች ስምምነት
ሁከት ወይም በይዞታ ላይ የሚደረግ ወረራን መከላከልና
ማስከበር ጥበቃ የተደረገለት ከመሰረታዊ ሰብአዊ
መብቶችና ነፃነቶች አንዱ ነው፡፡
ሁከት በወንጀልና በፍትሐብሔር ጉዳዮች ላይ የተለያዬ
ገጽታ ያለው ቢሆንም በመሰረታዊነት ጥበቃ በሚደረግለት
መብት ባሕርይ ግን ተመሳሳይነት አላቸው፡፡ ከወንጀል ሕጉ
አንቀጽ 686 መገንዘብ እንደሚቻለው ሁከት በሌላ ሰው
ሰላማዊ ይዞታ ላይ በኃይል ድርጊት፣ በዛቻ፣ በመሳሪያ
በቡድን ሊፈጸም የሚችል በመሆኑ ነው፡፡
በጥቅሉ ሲታይ ሁከት በሚንቀሳቀሱ ወይም
በማይንቀሳቀሱ ንብረቶቸ ወይም ይዞታዎች ላይ
የሚደረግ ጣልቃ ገብነት ነው፡፡
የጣልቃ ገብነቱ አይነትም የንብረቱን ሁኔታ ወይም ይዘት
በመለወጥ፣ ንብረቱን በኃይል በመያዝና በመድፈር፣
ያለሕግ ወይም ያለፈቃድ በመውረርና በመቆጣጠር፣
ከሕጋዊው ባለመብት ወይም ባለይዞታ ላይ በመንጠቅና
በመሰወር ወዘተ … ሊፈጸም ይችላል፡፡
የሁከት ተግባር በማይንቀሳቀሱ ንበረቶች ላይ (ለምሳሌ
እንደ መኖሪያ ቤት፣አጥር ግቢ፣ መሬት፣ ጀልባ፣ መስሪያ
ቤት፣ ድርጅት፣ ሕንጻ፣ ቢሮዎች፣ መጋዘን ወይም ግምጃ
ቤት የመሳሰሉ የተከለሉና የተጠበቁ ቦታዎች ላይ) ወይም
በተንቀሳቃሽና በልዩ ተንቀሳቃሽ የንብረት ጥቅሞች ላይ
ሊፈጸም ይችላል፡፡
በተጠበቁና በተከለሉ ቦታዎች ላይ ዛቻና ማስፈራራትን፣
መሳሪያን ወይም ሌላ ማንኛውንም ኃይል በመጠቀም
የሚደረግ የሁከት ተግባር የፍትሐብሔር ብቻ ሳይሆን
የወንጀልም ኃላፊነት ሊያመጣ ይችላል፡፡
በፍትሐብሔር ጉዳዮች ላይ ሁከት ተፈጥሯል
የሚባልባቸው ሁኔታዎች መካከል አንደኛ ጣልቃ-ገብነቱ
በማያሻማ ወይም በማያጠራጥር የሌላ ሰው ይዞታ ላይ
የተደረገ ሲሆን፡-አንድ ይዞታ የማያሻማ ወይም
የማያጠራጥር ነው የሚባለው በስውር ወይም በድብቅ
የተያዘ ይዞታ ሲሆን ነው (የፍ/ብ/ሕ/ቁ 1146 (1)፡፡
ንብረቱን በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ መንገድ በእጅ ይዞ
የሚገኘው ሰው በያዘው ንብረት ላይ አንዳች መብት
እንደሌለው ለማሳሰብ በሚያስችል ሁኔታ ባለይዞታነቱን
የደበቀ እንደሆነ ወይም ንብረቱን እጅ አድርጎ
የሚጠቀመው ሰው ንብረቱ ወይም ነገሩ የእርሱ
ስለመሆኑ በአካባቢያዊ ሁኔታዎች ተመዝኖ የሚያጠራጥር
ሆኖ ሲገኝ ወይም ንብረቱን የያዘው ስለሌላ ሰው እንደሆነ
መሆኑን የፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 1146 (2)፣ (3)
ይደነግጋል፡፡
አንድን ንብረት ስለሌላ ሰው ሆኖ የያዘ ሰው እንደንብረት
ጠባቂ እንጅ እንደባለይዞታ ሆኖ በየፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1147
(1) አይቆጠርም፡፡ እዚህ ላይ ግን ይዞታን በጠባቂ
አማካኝነት መያዝ አይቻልም ለማለት ሳይሆን ክርክር
ባጋጠመ ጊዜ እውነተኛ ባለይዞታው ጠባቂው ሳይሆን
የይዞታ መብቱን በጠባቂው አማካኝነት የሚፈጽመው ሰው
መሆኑን ለማመልከት ነው፡፡
በሁለተኛ ሁከቱ የተፈጠረው ጉድለት በሌለበትና
ባለይዞታው በእውነት በሚያዝበት ይዞታ ላይ ሲሆን፡-ይዞታ
ጉድለት የሌለበት የሚባለው በኃይል ወይም በሌላ
ሕገወጥ ተግባር ያልተገኘና የማያጠራጥር ወይም
የማያሻማ እንዲሁም ለረዥም ጊዜ ያልተቋረጠ ወይም
ያልቀረ ሲሆን ነው፡፡ አንድ ይዞታ ሕጋዊ ነው የሚባለው
በሰላማዊ ሁኔታ የተያዘ ሲሆን ነው፡፡
የይዞታን እውነተኛነት በተመለከተም ባለይዞታው ይዞታውን
በእጁ ማድረጉ እንደተበቀ ሆኖ አያያዙም በተረጋገጠና
ባልተጭበረበረ መንገድ ወይም በማናቸውም ሁኔታ
ሕገወጥ ባልሆነ መንገድ ያልተያዘ መሆን ይኖርበታል፡፡
የሕጉ ዓላማና መንፈስ የሚያሳየው ባለቤትነት ስላለ ብቻ
አንድን ሕጋዊ ባለይዞታ በሁከት ይወገድልኝ ጥያቄ ወይም
በኃይል ማስለቀቅ እንደማይችል ነው፡፡
ሁከት ተፈጠረብኝ የሚል አካል ይዞታውን ያገኘበት ሕጋዊ
አግባብና በእውነት የሚያዝበት መሆኑ ግንዛቤ መወሰድ
እንዳለበት ያስገድዳል፡፡
በመጨረሻም በሰዎች ግላዊና የኢኮኖሚ መብቶች ላይ
የሚደረግ ሕጋዊ አግባብነት የሌለው ጣልቃ ገብነት
ወይም ወረራ ወይም ሁከት በፍትሐብሔርና በወንጀል
ጉዳዮች ላይ የሚኖረውን ገጽታና ልዩነት እንዲሁም
የሁከት ምንነት፣ ሁከት ተፈጠረ የሚባልበት ሁኔታና ጊዜ፣
ሁከት የሚወገድባቸው መንገዶች፣ መብትና በግዴታን
አውቆ የሕግ የበላይነትን በማክበርና በማስከበር ይገባል
እያልን በተጣይ ዝግጂታችን በወንጀል ጉዳይ ሁከት
ተፈጥሯል ስለሚባልባቸው ሁኔታዎች ይዘን እንቀርባለን፡፡
ሰላም!
👍2
Hi Ale Society
How are you? Hopefully u all are Fine
Am Amanuel
I want Short notes on 2nd Year First semester , PPT PDF, Words
Please Send me
የፌዴራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ፕሬዝደንት ክብርት ወ/ሮ መዓዛ አሸናፊ የዓመቱን የስራ ጊዜ መገባደድ አስመልክቶ ለዳኞች የምስጋና መግለጫ ልከዋል፡፡ የመግለጫው ሙሉ ይዘት እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡

የዓመቱን የስራ ጊዜ መገባደድ አስመልክቶ ከጠቅላይ ፍ/ቤት ፕሬዝደንት
ለዳኞች የተላከ የምስጋና መግለጫ

ሐምሌ 30 ቀን 2011 ዓ.ም

የጠቅላይ ፍ/ቤት ፕሬዝደንት ሆኜ ከተሾምኩበት ከጥቅምት 22/2011 ዓ.ም ጀምሮ ዳኞቻችን በከፍተኛ የሃላፊነት ስሜት፣ ትጋት እና የሙያ ፍቅር ሃላፊነታቸውን በመወጣት ላይ መሆናችሁን ተገንዝቤአለሁ፡፡ ለዚህም ጠለቅ ያለ የዓመቱ ምስጋና ይገባችኋል፡፡
እኔና ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ሰለሞን አረዳ የስራ ሃላፊነት ተቀብለን ወደ ጠ/ፍ/ቤት ከመጣንበት ጊዜ ጀምሮ በምናስበው መንገድ ሃላፊነታችንን እንድንወጣ ያደረጋችሁልን በጎ አቀባበል እና ድጋፍ የሚደነቅ ነው፡፡

እንደምትገነዘቡት የፍ/ቤታችን አዲስ አመራር የተቃኘው አዎንታዊ አመራር ወይንም Positive Leadership በሚባለው የአመራር አቅጣጫ ነው፡፡ ይህ አይነት አመራር በግልጽነት፣ በመተማመን፣ የጋራ ራዕይ በመፍጠር የሚያምን፣ በአዎንታዊ እና በበጎ ጎኖች ላይ የሚገነባ አበረታች የአመራር ዘዴ ነው:: በሌላ በኩል የምንከተለው የአመራር አቅጣጫ ቴክኒካዊ ብቻ ሳይሆን ፈር ቀዳጅ ይሆናል፡፡ ባለፉት ወራት ፍ/ቤቶቻችን ነጻ፣ ገለልተኛ፣ ውጤታማ እና ቀልጣፋ እንዲሆኑ በርካታ የስልጠና፣ የሕዝብ ግንኙነት፣ የአስተዳደር ወዘተ ስራዎች ተሰርተዋል፡፡

የጀመርነውን የፍ/ቤቶች ማሻሻያ ስራ የበለጠ ቅርጽ ለማስያዝ የሶስት ዓመት የስራ ዕቅድ ነድፈን ተወያይተን ተስማምተንባቸዋል፡፡ ዕቅዱን ለማስፈጸም መንግስት ከመደበልን በጀት በተጨማሪ የሀብት ማሰባሰብ ተግባር ቀጣዩ ስራችን ነው፡፡

ውድ ዳኞች
ከተጀመሩት የማሻሻያ /Reform/ ስራዎች ጥቂቱን ላስታውሳችሁ፡-
• ፌደራል ፍ/ቤት ራሱን የማስተዳደር አቅም እንዲጠነክር፣ በአባላቱ ጥንቅርም ሆነ በስልጣን ወሰን የተጠናከረ የዳኝነት አስተዳደር ጉባኤ እንዲቋቋም ረቂቅ የሕግ ማሻሻያ ተዘጋጅቷል፤
• ፍ/ቤቶቻችን የሚመለከቷቸው ጉዳዮች ፍሰት አስተዳደርን ውጤታማ ለማድረግ የፍ/ቤታችንን አደረጃጀት እና ስልጣን የሚወስነውን አዋጅ 25/88 እና ተከታታይ ማሻሻያዎችን በአዲስ መልክ ለማሻሻል የተጠቃለለ ረቂቅ አዋጅ ተዘጋጅቷል፤
• ‘’FITH” (ፍትህ) በመባል ተሰይሞ በUSAID /አሜሪካን የልማት ድርጅት/ አጋርነት የሚከናወነው ፕሮጀክት በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ያተኩራል፡፡ በአሁኑ ጊዜ በዳኞች ስነምግባር ደንብ እና በዳኞች የስራ አፈጻጸም ምዘና ላይ ትኩረት በማድረግ በመስራት ላይ እንገኛለን፡፡ የሚዘጋጁት ደንቦች እና መመሪያዎች የሀገራችንን የቆየ የዳኝነት አስተዳደር እና ዓለምአቀፍ መመዘኛዎችን ቀምረው የሚዘጋጁ ሲሆኑ ተጠናቀው ወደ ስራ ሲተረጉሙ ለተቋማችን ጥንካሬ ከፍተኛ አስተዋፆ ያደርጋሉ፡፡

ውድ ዳኞች
እየተደረጉ ያሉት የሕግ ማሻሻያ ስራዎች በፍ/ቤቱ በተሰየመ የከፍተኛ የህግ ባለሞያዎች ቡድን የሚታገዝ ነው፡፡ ባለሙያዎቹ ከፍተኛ የሞያ ታማኝነት እና የአገልግሎት መንፈስ አሳይተዋል፡፡

ክቡራን ዳኞች
በምሳሌነት የተጠቀሱት እርምጃዎች ላቀድናቸው የፍ/ቤቱ የሪፎርም ስራዎች መሠረት የሚሆኑ ናቸው፡፡ በረቂቅ ህጎች /ደንቦች/ መመሪያዎች ላይ የዳኞችን አስተያየት የማሰባሰቡ ስራ ይቀጥላል፡፡ የተጠቀሱት የህግ ማዕቀፎች ከጸደቁ በኋላ አስፈላጊ ስልጠናዎች ተደርገው የሪፎርም ስራውን በሰፊው እናራምዳለን፡፡

ውድ ዳኞች
የዳኝነት ሃላፊነት ከባድ መሆኑን ሕዝቡ እንዲገነዘበው ማድረጉ አንዱ ሃላፊነታችን ነው፡፡ ሕዝቡ ከፍርድ ቤቶቻችን ሚዛናዊ ብቻ ሳይሆን የተቀላጠፈና መብት አክባሪ የፍትህ አገልግሎት ይጠብቃል፡፡ በአንጻሩ የጉዳዩች ፍሰት ብዛት፣ የአቅርቦት ውስንነት እና ሌሎች እጥረቶች ስራችንን ፈታኝ ያደርጉታል፡፡

የዳኝነት የስራ ጫና ለመቀነስ በቅርቡ ከ150 በላይ የረዳት ዳኞች ቅጥር በማከናወን ላይ እንገኛለን፣ በሂደት ግባችን እያንዳንዱ ዳኛ ማለትም 354ቱም ዳኞች ረዳቶች እንዲኖሯቸው ነው፡፡

በዚህ ዓመት ካከናወናቸው ስራዎች አንዱ 16 ተጨማሪ የጠ/ፍ/ቤት ዳኞች በፓርላማ መሾማቸው ነው፡፡ ከተሾሙት ዳኞች 40 በመቶ የሚጠጉት ሴቶች መሆናቸው እንደ ትልቅ ዜና መታየት አለበት ፡፡

ክቡራን ዳኞች
በተለይ በወንጀል ጉዳይ ከሌሎች የፍትህ አካላት ጋር መነጋገር የሚገቡን ጉዳዮች ስላሉ ²አብይ ኮሚቴ² በተባለው መድረክ ላይ ገንቢ ሚና በመጫወት ላይ ነን፡፡ በወንጀል ጉዳይ የተጠረጠሩ ሰዎች በማረሚያ ቤት እንዲቆዩ የሚያደርጉ ዋና ጉዳዮች ተለይተው ችግሩን ለመፍታት እርምጃዎች መወሰድ አለባቸው፡፡ ይሄ ለነገ የሚባል ስራ አይደለም፡፡

ውድ ዳኞች
ሃላፊነታችን የየዕለት የመዝገብ ስራ ሳይስተጓጎል እንዲከናወን ማድረግ ብቻ ሳይሆን የዳኝነት ዘርፍ እንደ ሶስተኛ የመንግስት አካል ሚናው ምን እንደሆነ ለሕዝብ ብቻ ሳይሆን ለሌሎች የመንግስት አካላት በአዲስ መልክ የማስገንዘብ ስራንም ይጨምራል፡፡ በዚህ ዓመት የፍ/ቤቱን በጀት በቀጥታ ለፓርላማ አቅርበን ማስወሰናችን አንደኛው የፍ/ቤቱ ተቋማዊ ነጻነት እርምጃ ማረጋገጫ ሆኖ ይታያል፡፡ በብሄራዊም ሆነ በዓለም አቀፍ ደረጃ የፍ/ቤታችን ገጽታ እያደገ ነው፡፡ በመሆኑም እንድናከናውናቸው የሚጠበቁ ዓላማዎች በርካቶች ናቸው፡፡

ውድ ዳኞች
ነጻ፣ ገለልተኛ፣ ቀልጣፋ እና ውጤታማ ፍ/ቤት በመገንባት ሀገራችን ወደ ዲሞክራሲ እና ልማት ለመሸጋገር አስተዋፆ ለማድረግ የታሪክ አጋጣሚ መፈጠሩ አስደሳች ነው፡፡ ለአንድ የሕግ ባለሞያ ከዚህ የተሻለውን የእርካታ እድል ሊፈጥር የሚችል ምን አጋጣሚ ይገኛል? በተባበረ መንፈስ ጠንክረን በመስራት ይሄንን እድል ለማሳካት እንችላለን፡፡

ውድ ዳኞች
ከዳኝነት የሚጠበቀውን ከፍ ያለ የሙያም ሆነ የጨዋነት/ (integrity) ደረጃ የማያሟሉ ዳኞች በስልጠና ወደ መስመር እንዲገቡ ጥረት ይደረጋል:: ከዚያ የሚሰፉ ችግሮችም በሕጋዊ ስርዓት የሚታዩ ይሆናል፡፡

ወድ ዳኞች
በመደበኛ ቀጠሮዎች ከሚታዩት መዝገቦች ሌላ ከ2009 ዓ.ም በፊት ተከፍተው እንደ ውዝፍ መዝገብ /Backlog/ የፈረጅናቸውን መዝገቦች ለመወሰን ከፍተኛ ትጋት አሳይታችኋል፡፡ በዚህ ረገድ በሶስቱም ፍ/ቤቶቻችን 7,663 መዝገቦች እልባት አግኝተዋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በእረፍት ጊዜአችሁ ቀሪ የዘገዩ መዝገቦችን ለመወሰን አብዛኞቻችሁ ፍቃደኞች መሆናቸሁ ሌላ የሚያስመሰግን ተግባር ነው፡፡

ወድ ዳኞች በመጨረሻም
በከፊል ስራ ላይ ብትሆኑም ከዛሬ ሐምሌ 30/2011 ዓ.ም ጀምሮ ፍ/ቤቶቻችን ዝግ በመሆናቸው መልካም የእረፍት እና የቤተሰብ ጊዜ እመኛለሁ፡፡ መስከረም ሲጠባ በመጪው የስራ ዘመን አቅጣጫ ላይ ለመወያየት የዓዲስ አመት ጉባኤ ይጠራል፡፡ ይህን የምስጋና መግለጫ በአንድ የወታደር ጥቅስ መዝጋት እፈልጋለሁ፡፡
“በሰላምና እና በነጻነት ጊዜ የምንኖርባትን ሀገር በችግር ጊዜም ልንቆምላት ይገባናል"

መዓዛ አሸናፊ መንግስቱ
የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት
WORBREEZY GOLDBERG:
Pls inform us..about oromia Judicial center
........Rewrting ........:
ሙስሊም ወንድም እና እህቶች መልካም የአረፋ ዐዓል እንዲሆንላችሁ ከልብ ተመኘው🙏🙏🙏🙏
addisu:
pls send me constitutional law short note
ALE Law Society is the independent professional body for all law societies @lawsocieties @lawsocieties @lawsocieties @lawsocieties @lawsocieties @lawsocieties @lawsocieties @lawsocieties
We are the voice of all law societies, drive excellence in the profession and safeguard the rule of law.
Kal:
Can u please send second year first semester courses
Ale 🔴Thank you Andy ye Henu: for sending us ....
Second year first semester course
Vip Vip:
Please Ale oromia region honew oromigna lemyichilu ye hig temariwoch le training endet memezgeb endemichilu merega yiseten please?