አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.87K photos
25 videos
1.87K files
3.58K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
የውጭ ባንኮች የኢትዮጵያን ገበያ መቀላቀላቸውን አስመልክቶ የተለያዩ የድጋፍም ሆነ የተቃውሞ ሐሳቦች እየተንጸባረቁ ነው።

በዝርዝር ለመተቸትም ሆነ ለመደገፍ ፖሊሲዎች የአፈጻጸም መመሪያዎች እስኪወጡ መጠበቅ ተገቢ ስለሆነ፣ ለዛሬው ጥቅል ሐሳቦችንና ትኩረት የሚሹ ነጥቦች ብቻ በጨረፍታ አቀርባለሁ።

የዓለም አቀፍ ገበያ ድርጅትን (WTO) ለመቀላቀል አንዱ መስፈርት የሆነው ባንክና ቴሌን የመሳሰሉ ተቋማትን ለውጭ ኢንቨስተሮች ክፍት ማድረግ ነው። በዚህ ምክንያትም የውጭ ሀገር ባንኮች የሀገራችንን የባንኪንግ ኢንደስትሪ የመቀላቀላቸው ጉዳይ የጊዜ ጉዳይ እንጂ አይቀሬ እንደነበር የሚታወቅ ነው።

አሁን ሊያወያየን የሚችለው ጉዳይ ባንኮቹ ገበያውን እንዲቀላቀሉ የተፈቀደበት ወቅት ተገቢ ነበር ወይ? የመንግስት፣ የብሔራዊ ባንክና ሀገር በቀል ባንኮች አቅምና ቅደም ዝግጅታቸውስ ምን ይመስላል? የገበያችንን ስርዓት ( Market Structure ) ምን ያህል ሕጋዊነትን የተከተለና ለወንጀልና ወንጀለኞች ያልተጋለጠ ነው። የግብር አከፋፈል፣ የመረጃ አሰባሰብና የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂያችን ምን ያህል ጥብቅና ለውንብድናና ለጠለፋ ( Hacking ) ያልተጋለጡ ናቸው የሚሉትና መሰል ጉዳዮች ይሆናሉ

የውጭ ሀገር ባንኮች ወደ ሀገራችን የሚመጡት ገበያ፣ ነባርና አዲስ ደንበኛና ትርፍ ፍለጋ ስለሆነ ስለ ሀገር እድገት በተለይ የሚጨነቁና የማይጠበቡ ልማታዊ እሳቤም የሌላቸው እንደሆነ የሚታወቅ ነው። የሚቀላቀሉት ገበያ ያለበት ሀገርም ሀገራቸው ስላልሆነ ትርፍ እስካገኙ ድረስ በማንኛውም መንገድ ከማትረፍ ወደኃላ የማይሉና የሕግ አስገዳጅነት እንጂ የሞራል ጥያቄ እምብዛም የማይገዳቸው ሊሆኑ እንደሚችሉ ታሳቢ መሆን አለበት። በተቃራኒው ደግሞ ሀገር በቀል ባንኮች ከትርፍ ባሻገር የሀገራቸው፣ የመንግስትና የልማታቸው አጋር ስለሆኑ ከሕግ ባሻገር በርካታ የውዴታ ግዴታና የሞራል ፈተና ስላለባቸው ውድድሩ የተለየ ጫና  ሊያሳድርባቸው ይችላል።

የውጭ ሀገር ባንኮች  በርካታ የውጭ ምንዛሬ ያመጣሉ የሚለውም እሳቤ የተጋነና በአብዛኛው የተሳሳተ መረጃ ነው። የውጭ ባንኮች የውጭ ምንዛሪ በገፍ ይዘው መጥተው በብር የመለወጥ ፍላጎት አይኖራቸውም። በአብዛኛውም ያለችውን ገበያና የውጭ ምንዛሪ መቀራመት ላይ እንደሚያተኩሩ ከሌሎች ሀገራት ተሞክሮ ይታወቃል።

ትርፋቸውንም በውጭ ምንዛሪ ከሀገር የማውጣት እድላቸው ጠባብ ስለሆነና ዋና መስርያ ቤታቸውን እንዲገነቡ ለሚሰበስቡት ብር ተመጣጣኝና ኃላፊነትና ግዴታ (Risk) እንዲወስዱ ካልተገደዱ በስተቀር ዘርፉ ቅርንጫፍ ተከራይቶ ቁሳቁስ በማሟላትና ገንዘብ በመሰብሰብ በትንሽ ኢንቨስትመንት የሚሰራ ስለሆነ ኢንቨስትመንታቸውንም ውስን በማድረግ ያለ በቂ ኃላፊነት፣ ስጋትና መተማመኛ ሊነግዱ ይችላሉ።

ሌላው ሀገር በቀል ባንኮች ከተደራሽነትና ሕዝብን ከማገልገል አኳያ ትርፍ ኖረም አልኖረ እንደ አቅማቸው ሁሉም ቦታ ቅርንጫፍ ይከፍታሉ። የውጭ ባንኮች ግን ሀብትና ኢኮኖሚያዊ አቅም በስፋት የሚታይባቸው አካባቢዎች ላይ ብቻ አትኩረው ሊሰሩ ስለሚችሉ አቅም ባለበት ቦታ ላይ ብቻ የሚኖረው ውድድሩ በሚፈጥረው ሽሚያ  በሚፈጠረው አቅም መዳከም ምክንያት ቀሪው አካባቢና ማህበረሰብ የባንክ አገልግሎት ላያገኝ ይችላል።

ሌላው ሀገራችን ውስጥ የሚገኙ ከፍተኛ አስቀማጭና ተበዳሪዎች በጥቂት መቶዎች የሚቆጠሩ ሰለሆኑ እነዚህን ደንበኞችና ገበያ (Niche Market) ላይ ብቻ በማተኮር ወይም ከፍተኛ እጥረት ያለበት የውጭ ምንዛሪ አቅርቦትን በማባበያነት በመጠቀም፣ የኢንዱስትሪውን አቅም ከ70 በመቶ በላይ በቀላሉ ለመቆጣጠር ይችላሉ። ይህ ደግሞ የተዛባና ወደ አንድ ጎን ያጋደለ (Economic imbalance) ፣ ኢ-ፍትሐዊ ወይም ሚዛናዊ ያልሆነ ውድድር (Unfair Competition) ሊፈጥሩ ይችላሉ።

በዚህ መንገድ ከሞላ ጎደል ገበያውን መሉ ለሙሉ ለመቆጣጠር ስለሚችሉም የፈለጉትን የአገልግሎት ዋጋ በመጣል፣ ወለድ በመተማንና ለፈቀዱለትና ለሚመስላቸው ዘርፍ ብቻ በማበደር ኢኮኖሚውን ወደ ፈለጉበት በመጠምዘዝ ልማታዊ እድሎችን እስከማደናቀፍ ሊደርሱ ይችላሉ። የውጭ ምንዛሪ ሲፈቅዱ የሀገራቸው ምርት ብቻ እንዲገባ በማድረግም ሀገሪቱን የሸቀጥ ማራገፊያ ( Damping ground) ሊያደርገት ይችላሉ። እንደዚህ ዓይነት አካሄዶች በማደግ ላይ ባሉ በርካታ ሀገራት ላይ ያጋጠመ ፈተናና ችግር ነው። በአንዳድ ሀገራትም አንዴ ባንኮቹ ጡንቻ ካፈረጠሙ በኃላ ለተለያዮ ኃይሎች የፖለቲካ መሳርያ በመሆን የመንግስትን እጅ እስከ መጠምዘዝ የደረሱበት ሁኔታም ታይቷል።

የውጭ ባንኮች ወድ ሀገር ውስጥ መግባታቸው በጠንካራ ጎንነት ሊወሳ የሚችለው የቴክኖሎጂ ሽግግር፣ ዘመናዊ የባንክ ሙያና እውቀት ስርጸት፣ አዳዲስ የማኔጅመንትና የአመራር ጥበብ ሽግግር የመሳሰሉት ይጠቀሳሉ። ከዚህም በላይ ለነባርና ብቃት ላላቸው የባንክ ሰራተኞችን ጨምሮ ለአዳዲስ ስራተኞችም የስራ እድል ይፈጥራል።

የውጭ ባንኮቹ ሀገር ውስጥ መኖራቸው በወጭና በገቢ ንግድ ላይ የነበረውን የተንዛዛ አሰራርና ተደራራቢ የክፍያ ስርዓት ሊቀንስ ይችላል። ኢንደስትሪው በስርዓትና በሕግ ከተመራም የዘመነና ጤናማ ውድድርን ሊያስከትል ይችላል። በአጠቃላይ ዘመናዊ አሰራር በማስተዋወቅ አዲስ ሃብት ከውጭ ወደ ሀገር ውስጥ በማሸጋገርና በማበልጸግ የተቀማጭም ሆነ የውጭ ምንዛሪ ይበልጥ እንዲሳለጥና Economics of Scale ከፍ እንዲል ሊያግዝ ይችላል።
Mushe Semu
https://t.me/lawsocieties
👍7
👍6
Traffic Rules
👍3
Tsehay Insurance S.C በሚከተሉት የስራ መደቦች በርካታ ሰራተኞችን አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል።

Position:-
1: Underwriting Officer II
2: Auditor II
3: Claims Officer II
4: Legal Officer I

📚የትምህርት ዓይነት እና ደረጃ
BA/BSc Degree in Management, Accounting, Economics, Computer Science or Law,related fields.


🇪🇹 የስራቦታ:- Addis Ababa

🧭የምዝገባ ጊዜ ፡ እስከ መስከረም
4/2015 ዓ.ም

🔔ስለ ስራው ሙሉ መረጃ ለማየት እና ለማመልከት ቀጣዩን ሊንክ ይጠቀሙ

https://jobs.amazonethiopia.com/job/tsehay-insurance-s-c-5/
👍11😁2
#United Insurance Company#

▪️1: Trainee Underwriting/Trainee Claims Officer
▪️2: Property Administration Officer
▪️3: Human Resource Officer/Personnel Officer
▪️4: Attorney
▪️5: Driver II/CEO Driver
▪️Find More Details here
💧💧💧💧💧
https://bit.ly/3KNs5qg

▪️Deadline - September 11/22
👍3
#Enat Bank SC#

▪️1: Business Development Officer
▪️2: Legal Aid
▪️3: Senior Business Research Management Officer
▪️4: Senior IS Auditor
▪️5: Branch Manager Grade B
▪️Find More Details here
💧💧💧💧💧
https://bit.ly/3TWvw2j

▪️Deadline - September 10/22
2👍1😁1
NBE Directive (1).pdf
1.8 MB
New directive Alert📍📍📍The National Bank of Ethiopia isused a directive that requires every person residing in Ethiopia (includes Ethiopians and foreigners having a permanent or temporary residence permit) to convert all of their foreign currency into Birr within 30 days of their entry in to Ethiopia. Those acquiring #forex through gift or donation before September 5 are also required to convert the same within 30 days as of today. The directive entered into force as of today.
👍7
Religious Radio and TV Licensing Directive_899.pdf
437.2 KB
የሃይማኖት ሬዲዮና ቴሌቪዥን ፈቃድ አሰጣጥ መመሪያ ቁጥር 899/2014
ለባንክ በመያዣ የተሰጡ ንብረቶች
***

* ለባንክ በመያዣ የተሰጡ ንብረቶችን በተመለከተ በተወሰኑ የፍትሐ ብሔር እና የንግድ ሕጉ ድንጋጌዎች ላይ ማሻሻያ ተደርጓል።

* የመጀመሪያውን ማሻሻያ ያደረገው አዋጅ ቁጥር 65/89 ነው።
* ይህ አዋጅ በፍ/ሕ/ቁ 2851 እና 3ዐ6ዐ ላይ ማሻሻያ አድርጎባቸዋል።
* ማሻሻያው የሚመለከተው ባንክ በመያዣ የተያዙ ንብረቶች አሻሻጥ ሥርዓትን ነው።
* ባንክ በመያዣ የያዘውን ንብረት ወደ ፍ/ቤት መምጣት ሳያስፈልገው ራሱ እንዲሸጥ።
* የሚያደርገ ስምምነት ሕጋዊ ውጤት እንዲኖረው ተደርጓል።
* አዋጅ ቁጥር 97/9ዐ ከፍ ሲል የተጠቀሰውን አዋጅ ሽሮታል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ለባንክ በመያዣ የተሰጠ የንግድ መደብርን በተመለከተ አዋጅ ቁጥር 98/98 በቀድሞው የንግድ ሕጉ ላይ ማሻሻያ አድርጓል።
* እነዚህ አዋጆች ባንክ በመያዣ የያዛቸውን ንብረቶች ራሱ የውል ጊዜው ተጠናቆ ብድር ካልተመለሰ እንዲሸጥ የሚያደርገውን ስምምነት ህጋዊነት ይቀበላሉ።
* አዋጆቹ ከመውጣታቸው በፊት እና በኋላ በመያዣ በተሰጡ ንብረቶች ላይ ልዩነት አድርገዋል።
* አዋጆቹ ከመውጣታቸው በፊት ለባንክ በመያዣ የተሰጡ ንብረቶችን በተመለከተ ባንኩ የተዋዋዮቹ ስምምነት ሳያስፈልገው ንብረቶቹን ራሱ ለመሸጥ ህጉ መብት ሰጥቶታል።
* አዋጆቹ ከወጡ በኋላ በመያዣ የተሰጡ ንብረቶችን በተመለከተ ራሱ ለመሸጥ ግን ስምምነት ያስፈልገዋል።
* ባንኩ ንብረቶቹን ራሱ ለመሸጥ ስምምነት ካላደረገ የፍትሐብሔር ህጉ ድንጋጌዎች ተፈፃሚ ይሆናሉ።
* በአሻሻጥ ሥርዓቱ ላይ ከተደረገው ለውጥ በቀር የፍትሐብሔር ህጉ ሆነ የንግድ ህጉ ድንጋጌዎች ተፈፃሚነት ይኖራቸዋል።
* በአዲሱ የንግድ ሕግ በአንቀጽ 654 ሥር የተቀመጡ ድንጋጌዎች ንግድ ባንኮች በአዋጁ የተሰጠንን መብት የሚሸረሽር ነው በሚል ቅሬታ እያቀረቡበት ነው ።
📌* በዚህ አንቀጽ ሥር የተቀመጠው መሠረታዊ ድንዳጌ፣ ‹‹…የማይንቀሳቀስ ንብረት መያዣ፣ የንብረት ዋስትና ያላቸውን፣ የቅድሚያ መብት ያላቸውን፣ እንዲሁም ባለሀብትነታቸው እንደተጠበቀ ሆኖ የተደረጉ የሽያጭ ውሎች ያሏቸው ገንዘብ ጠያቂዎችን ጨምሮ፣ በማናቸውም ገንዘብ ጠያቂዎች ክፍያ ለማስፈጸም በተናጠል የሚደረጉ ክርክሮች፣ በሙሉ ባለ ዕዳው ወይም በመልሶ የማደራጀት ኃላፊው በተናጠል ክፍያ ለማስፈጸም የሚደረጉ ክርክሮች እንዲቋረጡላቸው ጥያቄ ማቅረብ ሳያስፈልጋቸው በመጠባበቂያ ጊዜው ወቅት በሕግ ተቋርጠው ይቆያሉ፤›› የሚል ነው፡፡
📌* በዚህ የአዲሱ ህግ ድንጋጌ እና በጠቅላላው ምዕራፍ 3 ላይ የተካተቱ ድንጋጌዎች መሰረት አንድ ተበዳሪ ያለበት ብድር ተበላሽቷል ( bad debit) ሆኗል ከመባሉ አስቀድሞ ብድሩን ሊከፍል የሚችልበት አማራጭ እድል ይሰጠዋል።
📌* ይህም በብዙዎች ኢ- ህገመንግስታዊ እና ኢ-ፍትሃዊ ነው ተብሎ ከተረቀቀበት ጊዜ አንስቶ ሲተች የነበረውን አዋጅ ቁ. 90/97 እና አዋጅ ቁጥር 98/98 የማሻሻል የህግ ውጤት ስላላቸው የንግድ ህጉ አካሄድ ይበል እሚባል ነው ።

💼#ዳንኤል ፍቃዱ (ጠበቃና የህግ አማካሪ)
https://t.me/lawsocieties
👍8
የመድን ህግ -ቅሪት ሰ/መ/ቁጥር 204256

በመኪና ላይ ለደረሰ ጉዳት ለማስጠገኛ ወጪ ክፍያ የሚቀበል የመኪና ባለቤት ከጥገና የሚቀሩ ቅሪቶችን በዓይነት ወይም ግምታቸውን በገንዘብ ለመድን ሰጪው ድርጅት ሊመልስ ይገባል፡፡

የጉዳት ካሳ የመክፈል ሀላፊነት ያለበት የመድን ድርጅት ከጉዳት የተረፉ ቅሪቶች በዓይነት እንዲሰጠው ወይም በዋጋቸው ልክ ከሚከፍለው ላይ እንዲቀነስለት ለመጠየቅ የተከሳሽ ከሳሽነት ክስ ማቅረብ ሳይኖርበት በመከላከያ መልሱ ላይ ጥያቄውን ማቅረብ ይችላል፡፡
#Abrham_Yohanes
👍21👏1
የአዲስ አበባ የህግ ምሩቃንን ያገለለው የስልጠና እና ስራ ዕድል
የኢትዮጵያ ፍትህ ስርዓት አዳዲስ የህግ ምሩቃንን በዳኝት እና በዐቃቤ ህግነት አሰልጥኖ የሚቀጥር ነው።


የዚህ ስልጠና ዋና ዓላማ ሰልጣኞች በቀጥታ የፍትህ ስርዓቱን ከመቀላቀላቸው በፊት የተግባር ልምምድ እንዲያገኙ ማስቻል ነው። 

የ አዲስ አበባ ነዋሪ የሆኑ ተመራቂዎች  “በአዲስ አበባ የፍትህ አካላት የቅድመ ስራ ስልጠና ተቋም ባለመኖሩ ዓቃቤ ህግ ወይም ዳኛ ሆነው ለመሥራት መቸገራቸውን ይናገራሉ። ወደ ክልልሎች ሲሄዱም ስልጠና ለማግኘት የነዋሪነት መታወቂያና ቋንቋ እንደ ቅድመ ሁኔታ በመቀመጡ ስልጠናውን ማግኘት ሳይችሉ ይቀራሉ የአዲስ አበባ ነዋሪ የሆኑ የህግ ተመራቂ ተማሪዎች በየአከባቢያቸው የመሰልጠንና የመስራት ህገመንግስታዊ መብታቸው ተገፎ በማያውቁት አከባቢ ተገደው ሄደው እንዲሰለጥኑ እና እንዲሰሩ ሆኗል በዚህም ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ቀውስ እየገጠው ይገኛል ተማሪዎቹም በየአከባቢአቸው ስልጠናውና የስራ እድል እንዲሰጣቸው ይጠይቃል ።
የአዲስ አበባ ነዋሪ የህግ ተመራቂ ተማሪዎች!!
Justice for addis ababa dweller law graduate student!!
Via Santa
#share for Justice
ፍትህ እንድናገኝ ሼር በማድረግ ድምፅ ይሁኑን🙏🙏
👍89👏16😁1
#መረጃ

"ለግል መገልገያ እንዲውሉ ወደ ሀገር የሚገቡ/የሚወጡ ዕቃዎች ሁኔታን የሚወስነው በሥራ ላይ ያለው መመሪያ (መመሪያ ቁጥር 51/2010) ለሕገ ወጥ ንግድ በር የከፈተ እና አገልግሎት አሰጣጡ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ያሳደረ በመሆኑ ዓለምአቀፍ አሠራሮችን በተከተለ አኳኋን መመሪያውን አሻሽል ማውጣት በማስፈለጉ" በሚል ምክንያት ለግል መገልገያ እንዲውሉ ወደ አገር የሚገቡ ወይም ከአገር የሚወጡ ዕቃዎችን ለመወሰን መመሪያ ቁጥር 923/2014 ከነሀሴ 12/2014 ጀምሮ ተፈፃሚ እንዲሆን በገንዘብ ሚኒስቴር የተሻሻለው መመሪያ ይፋ ወጥቷል፡፡

በቀደመው መመሪያ በርካታ የቁሳቁስ አይነቶች ወደ ሀገር ውስጥ ከቀረጥ ነጻ ለማስገባት የሚፈቅደው መመሪያ በተሻሻለው አዲሱ መመሪያ መጠኑን ወደሚከተለው ሰንጠረዥ አሳጥሯል፡፡ ሙሉ መመሪያውን ማንበብ ለምትፈልጉ ከታች ይመለከቱ 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
👍5
የኪራይ ቤቶችን ዋጋ ለመወሰን የተዘጋጀው ረቂቅ አዋጅ በዚህ አመት ይፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል!

ለኪራይ የሚዘጋጁ ቤቶችን ዋጋ ደረጃ ለመወሰን የተዘጋጀው ረቂቅ አዋጅ በዚህ አመት ይጸድቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትር ወይዘሮ ጫልቱ ሳኒ ተናገሩ።በተለይ በከተሞች ያለው የመኖሪያ ቤት ከራይ መወደድና የአከራይና ተከራይ ጭቅጭቅ መላ ሊበጅለት እንደሚገባ በርካቶች ያምናሉ።

ለችግሩ እልባት ለመስጠት ተዘጋጅቶ ሚኒስትሮች ምክር ቤት የደረሰው ረቂቅ አዋጅ፥ የኪራይ ውል ጊዜን ከመወሰን ባለፈ ለኪራይ የሚዘጋጁ ቤቶች ሊያሟሏቸው የሚገቧቸውን መሰረተ ልማቶች በግልጽ ያስቀምጣል ብለዋል።በረቂቅ አዋጁ እንደተቀመጠውም አከራዮች የኪራይ ዋጋ መጨመር ሲፈልጉ በምን ያህል ጊዜና ምን ያህል የሚለውም ተለይቷል።ተከራዮችም በኪራይ የወሰዷቸውን ቤቶች በአግባቡ መያዝ እንደሚገባቸውና ሌሎች ግዴታዎቻቸውንም አስፍሯል ነው የተባለው።

ረቂቅ አዋጁ በደላሎች የሚዘወረውን የኪራይ ቤቶች ዋጋና አቅርቦት በማስተካከል አከራይንና ተከራይን ከማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጫናዎች ይታደጋልም ተብሎ ታምኖበታል።የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትሯ ወይዘሮ ጫልቱ ሳኒም ረቂቅ አዋጁ በዚህ አመት ፀድቆ ወደ ስራ ይገባል ተብሎ እንደሚጠበቅ ነው የተናገሩት።
Via #EthiopiaBusinessDaily
👍12
ቂሙን በፍየሎቹ ላይ የተወጣው ግለሰብ።

አንድ ግለሰብ ከወንድሙ ሚስት ጋር በመጣላቱ የተነሳ በፖሊስ ተይዞ ይታሰራል። ነገር ግን ግለሰቡ ለካ ለምን ታሰርኩ ብሎ ቂም በመያዝ በዋስ ከተፈታ በኋላ በመገስገስ ወደ ወንድሙ ሚስት ቤት ይሄዳል።

ሲደርስ ያጣታል፥ ይበሳጭና በሰፈር ውስጥ ታስረው ይግጡ የነበሩትን ንብረትነቱ ተጣላኋት ያላት የወንድም ሚስት የሆኑትን ሁለት ፍየሎች አርዶ ሄዷል።

ድርጊቱ የተፈጸመው በሀረር ከተማ ሶፊ ወረዳ ተብሎ በሚጠራው ስፍራ መሆኑንና ግለሰቡም በድጋሚ በህግ ቁጥጥር ስር መዋሉን የወረዳው አዛዥ ምክትል ኮማንደር መሀመድ ሳፊ ገልጸዋል።
#tikvahethmagazine
https://t.me/lawsocieties
👍31
የቤት ኪራይ ሕግ ሊወጣ ነው ሲባል ሰማሁ!  ሕጉ ምን ምን መያዝ እንዳለበት ሁላችንም ሐሳብ እንስጥበት፦

የእኔን እነሆ!
                ===
1. ለምሳሌ ቤቱን ተከራይተህ ምግብ መሸጥ ትጀምርና ቤትህ ታዋቂ ይሆናል። ባለቤት ሆዬ ውጣ ይልህና አንተ ባመጣኸው ዝና good will ይነግዳል። ውጣ ብሎ ካስወጣህ በዚያ ተመሳሳይ  ሥራ ቢያንስ ለሁለት ዓመታት መሥራት የለበትም።

2. ኪራይም ተመን ሊኖረው ይገባል። አንድ ቤድ ሩም፣ ሁለት ቤድ ሩም፣ ሶስት ቤድ ሩም እና ሊፍት ያለው የሌለው እንዲሁም አካባቢው አንደኛ ሁለተኛ ደረጃ ተብሎ የመነሻ እና የመዳረሻ Range ተመን ሊወጣለት ይገባል።

3. ባለፎቆች ገንዘብ ስላላቸው ለዓመታት ቤቱ ባይከራይ ጉዳያቸው አይደለም። ከሦስት ወራት በላይ ባልተከራየ ቤት እንደተከራየ ተደርጎ ግብር የሚከፍሉበት ሥርዓት ቢኖር መልካም ነው።

4. ኪራይ በዶላር መተመን በሕግ መከልከል አለበት።

5. ለረጅም ጊዜ ኪራይ ላልጨመሩ፣ የተጋነነ ኪራይ ላልጠየቁ፣ ከተሰጣቸው range በሚኒመም ላከራዩ፣ ለብዙ ዓመታት አንድ ቤተስብ ተከራይ ያላስወጡ ኢንሴንቲቭ ሊሰጣቸው ይገባል።

5. በአከራዮች ላይ የሚጣለው ግብር ገቢያቸው ከፍ ሲል የግብር መጠኑ ከፍ የሚልበት Marginal progressive taxation system ቢሆን፣ አንዳንዴም ከአነስተኛው እርከን ያገኘውን በታክስ የሚወስድበት ቢሆን መልካም ነው።

6. የመንግሥት መኖርያ ቤት ጠቅላላውን ለመንግሥት ሰራተኞችና ለጡረተኞች ብቻ ቢከራይ፣ የግል ፎቆች ላይ ነጋዴ ቢሆን ያስኬዳል፤  ነጋዴ ለነጋዴ ብቻ እርስ በርሱ ይሞሸላለቃል።

7. የራሳቸውን ቤት አከራይተው በመንግሥት ቤት የሚኖሩ ተለቅመው ሊነጠቁ ይገባል።

8. የመንግሥት መ/ቤቶች ለሠራተኞቻቸው መጠነኛ ኪራይ አስከፍለው የሚያከራዩት ቤት ቢኖራቸው ይደገፋል። አ.አ.ዩ አራት ኪሎ ሁለት ፎቅ ይዞ ቤት ለሌላቸው መምህራን ያከራያል።

9. ውል ለማቋረጥ ተከራይ ማስጠንቀቂያ መስጠት አያስፈልገውም። አከራይ ግን ለአንድ ዓመት ውል ሁለት ወር፣ ለሁለት ዓመት ውል አራት ወር፣ ለሶስት ዓመት ውል ስድስት ወር ቢሆን ከዚያ በላይ ላለው ስድስት ወር ቢሆን መልካም ነው።

10. የንግድ ቤት የኪራይ ውል ተከራይ በማናቸውም ጊዜ በማስጠንቀቂያ የማቋረጥ መብቱ ተጠብቆ ትንሹ የኪራይ ዘመን አምስት ዓመት መሆን አለበት።

11. ቤት ሲለቀቅ በጥንቃቄ ጉድለት የተበላሸ እንጂ እርጅና ብልሽት የማስተካከል ግዴታ መኖር የለበትም።

12. አከራይ ከተከራይ ጋር አንድ ግቢ የሚኖር ከሆነ የኪራይ ተመኑ ዝቅ ማለት አለበት።

13. የመንግስት ቤት የተከራዩ በኪራይ ማዳበል ቢፈቀድላቸው እጥረት ይቀርፋል።

14. ማናቸውም ቀጣሪ የግልም የመንግስትም ለሰራተኞቻቸው የኪራዩን እስከ 25% የኪራይ አበል መክፈል አለባቸው።

15. ቤት ለሌላቸው መንግስት መ/ቤት ላገለገሉ ጡረተኞች እንደ አገልግሎታቸው መጠን የቤት ኪራይ አበል ሊከፈላቸው ይገባል። ጡረተኛ እንደ ውዳቂ የማየት በመለስ ዜናዊ ለጡረተኛ ብር መስጠት ጉቶ ውኃ ማጠጣት ነው የሚለው የዱርዬ ፖሊሲ መሻር አለበት።
Guagule Teshager J
👍17👏6👎21🔥1🥰1😁1
#Ministry of Finance

የታክሲ ተሽከርካሪዎች ከቀረጥና ታክስ ነጻ በሚመለከት የተሰጠ ማብራሪያ


መስከረም 4/ 2015 ዓ.ም - መንግስት የትራንስፖርት ዘርፉን ለማዘመን እንዲሁም ለረጅም ጊዜ አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኙ በተለምዶ ላዳ ታክሲ በመባል የሚታወቁ ተሸከርካሪዎች በአዲስ ተሸከርካሪዎች የሚተኩበት መመሪያ ቁጥር 70/2013 አውጥቶ ስራ ላይ ማዋሉ ይታወሳል፡፡

ያገለገሉ ላዳ ታክሲዎችን የሚተኩ አዳዲስ ተሽከርካሪዎች ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል ተበትነው ወደ ሀገር ገብተውና በአገር ውስጥ ተገጣጥመው ለዚሁ ዓላማ ሲቀርቡ እንዲሁም አዲስ የታክሲ ማህበራት በሚመለከት ሙሉ ለሙሉ ተበትነው የገቡና በሀገር ውስጥ የተገጣጠሙ ሲሆን ከቀረጥና ታክስ ነጻ እንዲሆኑ መደረጉን በገንዘብ ሚኒስቴር ማብራሪያ ተሰጥቷል፡፡

ሚኒስቴሩ በሰጠው ማብራሪያ በአዲስ አበባ ከተማ ለረጅም ዓመታት በማገልገል ላይ የሚገኙ በተለምዶ የላዳ ታክሲዎች በመባል የሚታወቁ ተሽከርካሪዎች በአዲስ እንዲተኩ በማድረግ ባለንብረቶቹን በተሸከርካሪዎቹ እርጅና ምክንያት ከሚደርስባቸው ከፍተኛ የነዳጅና የመለዋወጫ ወጪ ለማዳን፣ በገበያ ላይ ተወዳዳሪ ሆነው በመስራት ይበልጥ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማስቻል፣ የአከባቢ ብክለትን ለመቀነስ፣ የከተማዋን ገፅታ ለማሻሻል እንዲሁም የከተማዋን የትራንስፖርት ዘርፍ ለማዘመን ሲባል ያገለገሉ ላዳዎችን የሚተኩ አዳዲስ ተሽከርካሪዎች ከቀረጥና ታክስ ነጻ እንዲሆኑ መደረጉ ተገልጽዋል፡፡

ይህን ተጨማሪ ማብራሪያ መስጠት ያስፈለገው የታክሲ ተሽከርካሪዎች የቀረጥና ታክስ ነጻ ጥያቄዎች አቀራረብና አፈቃቀድ በተመለከተ የወጣውን መመሪያ በአግባቡ የመገንዘብ ችግር ስላለ መሆኑን በመጥቀስ በመመሪያ 70/2013 በተደነገገው መሠረት የታክሲ ተሽከርካሪዎች ቀረጥና ታክስ ነጻ ጥያቄዎች የሚስተናገዱት ያገለገሉ ላዳ ታክሲዎችን የሚተኩት ተሽከርካሪዎች ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል ተበትነው ወደ ሀገር ገብተው በአገር ውስጥ ተገጣጥመው ሲቀርቡ ብቻ ሲሆን አዲስ የታክሲ ማህበራትን በሚመለከት ትኩረት የሚያደርገውም የትራንስፖርት ዘርፉን ፍላጎት ሆኖ የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር በሚያዘጋጀው ሀገር-አቀፍ የትራንስፖርት ፖሊሲና ስትራቴጂ ብቻ የሚወሰን መሆኑንም አስረድቷል፡፡

በዚህም መሰረት የሚቀርቡ ጥያቄዎች የሚስተናገዱት ለዚሁ ዓላማ በወጣው መመሪያ ቁጥር 70/2013 መሰረት በማድረግ ብቻ ሲሆን በዚህ መመሪያ ግልፅ የጥያቄ አቀራረብና የአፈቃቀድ ስርዓት መደንገጉንና በተለይም በመመሪያው አንቀፅ 10 መሰረት ለታክሲ አገልግሎት የሚውሉ የተሽከርካሪ ቀረጥና ታክስ ነጻ ጥያቄዎች መቅረብ የሚችሉት በሚከተለው መንገድ ብቻ ማለትም ፡-

የክልል መንግስታት፣ የከተማ አስተዳደሮች እና የፌዴራልና የመንግስት መ/ቤቶች ለታክሲ አገልግሎት የሚውሉ ተሸከርካሪዎች ከቀረጥና ታክስ ነፃ የሚገዙትን ተሽከርካሪዎች የሚፈልጉ የታክሲ አገልግሎት ሰጪ ማህበራት ጥያቄ ከድጋፍ ደብዳቤ ጋር ለትራንስፖርት እና ሎጀስቲክስ ሚኒስቴር ሲላክ፤

የትራንስፖርት እና ሎጀስቲክስ ሚኒስቴር የታክሲ ማህበሩን የግብር ከፋይ መለያ፣ የንግድ ምዝገባ ሰርፊኬት፣ የተሽከርካሪዎቹን ሊብሬ እና ሌሎች አስፈላጊ መረጃዎችን በማያያዝ ለገንዘብ ሚኒሰቴር ሲልክ፤

የገንዘብ ሚኒሰቴርም የቀረበውን ጥያቄ አግባብነት እና ማስረጃዎች ከመረመረ በኋላ የቀረጥ ነፃ መብቱን በመስጠት ለጉምሩክ ኮሚሽን ሲልክ መሆኑን ተብራርቷል፡፡

ከዚህ መመሪያ ውጭ የሚቀርቡ ጥያቄዎች የህግ መሰረት የሌላቸው በመሆኑ ተቀባይነት የሌላቸውና ከመመሪያው ውጪ የሚቀርቡ የታክሲ ተሽከርካሪ ቀረጥና ታክስ ነጻ ጥያቄዎች ከገንዘብ ሚኒስቴር እውቅና ውጭ መሆናቸውን በማወቅ ህብረተሰቡ ከተጠቀሰው ህጋዊ አሰራር ውጪ ማህበር እናደራጃለን፣ ቀረጥና ታክስ ነጻ አስፈቅደናል ወይም እናስፈቅዳለን ከሚሉ አካላት ራሱን መጠበቅ እንዳለበት የገንዘብ ሚኒስቴር ያሳስባል፡፡
👍7🥰2