አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.87K photos
25 videos
1.87K files
3.58K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
Forwarded from Yideg
አወ በእውነቱ ኢንስቲትይውቱ ውሳኔውን እንደገና ማጤን አለበት፡፡ እንደተባለው ግቢ ገብተን ቢያንስ 3 ሳምንታት የመዘጋጃ ጊዜ ካላገኘን ብዙ ተማሪዎች ያለአግባብ እንደሚጎዱ ልብ ሊባል ይገባል፡፡

አለወችን እናመሰግናለን🙏
ይህን ቅሬታ ወደሚመለከተው አካል አድርሳቹ ምላሹን እንደምታሳውቁን ባለሙሉ ተስፋ ነኝ፡፡
መፈተን አለብን ምንም ምክንያት አያስፈልግም
ere twu?
Forwarded from Alush
ሰላም ወንድሜ

ከዚህ በፊት ለመውጫ ፈተና(exit exam) የወጣው ጊዜ ሰሌዳ (ህዳር 1-4) መራዘም አለበት። ግቢ መቼ እንደምንገባ ባልተረጋገጠበት ሁኔታ የፈተና ፕሮግራም ማስቀመጥ ተገቢ አይደለም። እናንተም በተቻላችሁ መጠን ግፊት አድርጉና ለተማሪ ምቹ በሆነ ሁኔታ ለማስደረግ ሞክሩ። ተማሪው አሁን አዳዲስ ነገሮች ናቸው የሚገጥሙት(registration, test, new environment)። ከደረሰበት ስነልቦናዊ ጉዳት ለማገገም እና እነዚህን አዳዲስ ቻሎንጆችን ለመላመድ ጊዜ ያስፈልገዋል። ከተቻለ ቢያንስ የአንድ ወር ጊዜ ቢሰጠን መልካም ነው።
ስለሁሉ ጊዜ ጥረታችሁ ከልብ አመሰግናለሁ

መቼ ነው ግቢ የምንገባው?
የአስተዳደር ሥነ-ሥርዓት አዋጅ በመንግስት ተቋማት እና በዜጎች መካከል መልካም ግንኙነትን ለማጠናከር ጠቃሚ መሆኑ ተገለፀ
****************************
የአስተዳደር ሥነ-ሥርዓት አዋጅ የመንግስት አሰራር ግልጽነት እና ተጠያቂነት የሰፈነበት በማድግ ዜጎች ዴሞክራሲያዊ መብታቸውን በተገቢው መንገድ እንዲጠቀሙ የሚያድርግ መሆኑን የፌደራል መንግስት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በተሰጠው ስልጠና ላይ ተገለጸ፡፡
የአስተዳደር ሥነ-ሥርዓት አዋጅ በመንግስት ተቋማት እና በዜጎች መካከል መልካም ግንኙነትን ለማጠናከር ጠቃሚ መሆኑ ተገለፀ
****************************
የአስተዳደር ሥነ-ሥርዓት አዋጅ የመንግስት አሰራር ግልጽነት እና ተጠያቂነት የሰፈነበት በማድግ ዜጎች ዴሞክራሲያዊ መብታቸውን በተገቢው መንገድ እንዲጠቀሙ የሚያድርግ መሆኑን የፌደራል መንግስት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በተሰጠው ስልጠና ላይ ተገለጸ፡፡
የአዋጁን አተገባበር እስመልክቶ ያነጋገርናቸው በኢፌዲሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የሕግ ጥናት ማርቀቅና ማጠቃለል ዳይሬክተር ጄኔራል የአስተዳደር ሥነ-ሥርዓት ህግ አስተባባሪ የሆኑት አቶ ጌታነህ ሀብታሙ እንደተናገሩት በአስተዳደር ሥነ-ሥርዓት አዋጅ መሰረት የመንግስት ተቋማት አሰራርና ተጠያቂነትን በመዘርጋት በሕግ የተሰጣቸውን ኃላፊነት በግልጸኝነት እንዲወጡ እና ዜጎች መብታቸውን በተገቢው መንገድ እንዲጠቀሙ እድል የሚሰጥ መሆኑን ተናግረዋል፡

አቶ ጌታነህ በገለጻቸው አዋጁ ዜጎች በሚወጡ መመሪያዎች ላይ ከቅድመ መመሪያ ረቂቅ ሂደት ጀምሮ መመሪያው ጸድቆ እስኪተገበር ድረስ ሙሉ ድርሻ እና ተሳትፎ እንዲኖራቸው ያስችላል ብለዋል፡፡ አክለውም የአስተዳደር ተቋማት ለዜጎች የሚሰጡትን አገልግሎት በሚያወጧቸው መመሪያዎች መሠረት እንደመሆኑ መጠን በመመሪያ አወጣጥ ሂደት ከማሳተፍ ባሻገር የወጡ ማንኛውም መመሪዎች ለጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ በአስተዳደር ሥነ-ሥርዓት አዋጁ በተሰጠው ሥልጣንና ኃላፊነት መሠረት የተላኩለትን የአስተዳደር ተቋማት ነባርና አዳዲስ መመሪያዎችን ሀገራዊ ቁጥር በመስጠት እየመዘገበና በተቋሙ ድህረ ገጽ ላይ የተጫነ መሆኑን ገልጸው የአስተዳደር ተቋማትም በራሳቸው ድህረ ገጽ ላይ እንዲጭኑና ለዜጎች ተደራሽ ማድረግ ስለሚገባቸው የአስተዳደር ሥነ-ሥርዓት ሕጉ መመሪያዎችን ለዜጎች ለማስተዋወቅ እና በዜጎች እና አገልግሎትን በሚያቀርቡ የመንግስት መስሪያ ቤት መካከል ያለውን ግንኙነት ግልጽነት ያለውና ሕጋዊነቱንም የጠበቀ ለማድረግ ይረዳል ብለዋል፡፡

አቶ ጌታነህ አክለውም የመንግስት የአስተዳደር ተቋማት በአዋጁ በተሰጠው ጊዜ መሰረት በስራቸው ያሉ ነባር መመሪያዎችን ለፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ በመላክ ማስመዝገብ እንደሚገባቸውና በአዋጁ መሰረት ያልተመዘገበ መመሪያ ሕጋዊነቱን እንደሚያጣም በማሳሰብ ያልተመዘገበ መመሪያ ለአስተዳደር ተቋማት ሥራ አስፈላጊ ቢሆን እንኳን እንደገና በአዲስ መልኩ የመመሪያ አወጣት ሥርዓትን ተከትሎ ማውጣት እንደሚገባቸው የአስተዳደር ሕጉ በግልፅ ያስቀመጠ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ማስታወቂያ (የተሻሻለ)

የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የቅድመ ምረቃ መደበኛ እና የማታ ፕሮግራም እጩ ተመራቂ ተማሪዎች
በኮረና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት የተቋረጠዉ የ2012 ዓ.ም የሁለተኛ ሰሚስተር ትምህርት ለማስጀመር የመልሶ ምዝገባ በሚከተለዉ መሠረት ይካሄዳል፡፡
✓ እጩ ተመራቂ የማታ ተማሪዎች ምዝገባ ጥቅምት 19 እና 20 2013 ዓ.ም
✓ እጩ ተመራቂ የመደበኛ ተማሪዎች ምዝገባ ጥቅምት 23 እና 24 2013 ዓ.ም ሲሆን
✓ ተመዝጋቢዎች ከኮሌጅ ሬጅስትራር ጽ/ቤቶች በመገኘት የኮርስ ምዝገባ ማካሄድ ይጠበቅባቸዋል፡፡
✓ የምዝገባ ወረቀቶቹ እንደ ተማሪ መታወቂያ ስለሚያገለግል በጥንቃቄ መያዝ ይኖርባችኋል፡፡
✓ ለመደበኛ ተማሪዎች ትምህርት መልሶ መከፈትን በተመለከተ እና ሊደረጉ ስለሚገቡ ጥንቃቄዎች ጥቅምት 25 ቀን 2013 ዓ.ም ገለፃ ይደረጋል፡፡
✓ ትምህርት የሚጀመረው ጥቅምት 26 ቀን 2013 ዓ.ም መሆኑን ያሳዉቃል
✓ ከምዝገባ በፊት ወይም በኋላ የሚመጡ ተማሪዎችን ዩኒቨርስቲዉ አያስተናግድም
✓ ዝርዝር መረጃዎችን ከዩኒቨርስቲዉ ድረ ገፅ  www.aau.edu.et ማግኘት ይቻላል፡፡
 
አ.አ.ዩ ሬጅስትራር
#ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቀረበው ረቂቅ የወንጀል ሕግ ሥነ ሥርዓት እንዳይፀድቅ ጥያቄ ቀረበ::#
ከግማሽ ምዕተ ዓመት በላይ በአገልግሎት ላይ የቆየውን ‹‹የወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕግ›› እንዲተካ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ይሁንታን አግኝቶ፣ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከሁለት ሳምንታት በፊት የቀረበው ‹‹የወንጀል ሕግ ሥነ ሥርዓት ረቂቅ›› እንዳይፀድቅ ጥያቄ ቀረበ፡፡

ጥያቄውን ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያቀረበው፣ የኢትዮጵያ የሕግ ባለሙያዎች ማኅበር ሲሆን፣ ረቂቁ እንዳይፀድቅ ጥያቄ ያቀረበው፣ በቀረበው ረቂቅ የወንጀል ሕግ ሥነ ሥርዓት ድንጋጌዎች ላይ መሻሻል፣ መስተካከልና እንደ አዲስ መካተት ያለባቸው ነጥቦች ስላሉ መሆኑን በመጥቀስ ነው፡፡ የማኅበሩ ፕሬዚዳንት ጠበቃ ፊሊጶስ ዓይናለም ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ እንደ ሕግ ባለሙያ ረቂቁን ሲፈትሹት ወይም ሲያነቡት ከላይ የተጠቀሱት ነጥቦች መስተካከል፣ መታረምና ያልተካተቱት መጨመር አለባቸው፡፡ ምክንያቱም ሕጉ ከፀደቀ በኋላ ለዘመናት የሚያገለግል መሆን ስላለበት መሆኑን አስረድተዋል፡፡

ረቂቁ ሕግ በ1954 ዓ.ም. ፀድቆ ከግማሽ ምዕተ ዓመት በላይ ለ58 ዓመታት ሲያገለግል የቆየና በማገልገል ላይ ያለን ሕግ የሚተካ መሆኑን የገለጹት አቶ ፊልጶስ፣ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቀረበው ረቂቅ ሕግ፣ ከአራት ጊዜ በላይ የተረቀቀና ለአሥር ዓመታት ውይይት ተደርጎበት የነበረ እንደነበር አስታውሰዋል፡፡

ከለውጥ በኋላ የተቋቋመው የሕግና ፍትሕ ማሻሻያ ምክር ቤት ከተቋቋመ በኋላ እንደገና ታይቶና ለውይይት ቀርቦ በጥሩ ሁኔታ የተዘጋጀ መሆኑንም አቶ ፊልጶስ ገልጸዋል፡፡ ነገር ግን በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 20 እና 21 ድንጋጌዎች ስለ የሕግ አማካዎች (ጠበቆች) ደንግጎ የሚገኝ ሆኖ ሳለ፣ አዲሱ ረቂቅ ሕግ ሥነ ሥርዓት ግን ስለጠበቆች ያለው ነገር እንደሌለ ተናግረዋል፡፡

ረቂቁ፣ ፍርድ ቤቶች፣ ዓቃቤ ሕግንና ፖሊስን አካቶ እያለ ለፍትሕ ሥርዓቱ ከፍተኛ ዕገዛና ድጋፍ የሚሰጠውን ጠበቃ ሳያካትት መቅረቱ ትክክል ስላልሆነ፣ ሊታረምና መካተት እንደሚገባውም አስረድተዋል፡፡

ረቂቁ በትርጉም ክፍሉ ስለ ተከላካይ ጠበቃ ትርጉም ሲሰጥ እንኳን ጠበቃን ዝም ብሎ ማለፉ፣ ‹‹ጠበቆች የፍትሕ አካሉ አይደሉም›› እንደማለት ስለሆነ፣ በደንብ ታይቶ ሊታረም እንደሚገባም ጠቁመዋል፡፡ ረቂቁ በጣም ብዙ በጎ ነገሮች እንዳሉት ጠቁመው፣ ለዓቃቤ ሕግና ለፖሊስ የሰጠው ሥልጣን ሰፊ ከመሆኑ አንፃር ግዴታም ሊጥልበት እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡ ከፍርድ ቤቶች ማቋቋሚያ አዋጅም ጋር ስለሚጋጭ በደንብ ሊታይ እንደሚገባ ጠቁመዋል፡፡

ፍርድ ቤት፣ ፖሊስና ዓቃቤ ሕግና በጋራ ዕቅድ አውጥተው እንዲሠሩ የሚደነግገው ክፍል፣ የፍርድ ቤቶችን ነፃነት የሚገፉ በመሆኑ ሊታሰብበትና በደንብ ሊታይ እንደሚገባም መክረዋል፡፡ በረቂቁ የተጠቀሱ ድንጋጌዎች እርስ በርሳቸውና ከሕገ መንግሥቱ ድንጋጌዎች ጋርም ስለሚጋጩ፣ የሕግ ባለሙያዎች ተወያይተውና ሙያዊ አስተያየቶቻቸውን ሳይሰጡ እንዳይፀድቅ፣ ምክር ቤቱ የውይይት መድረክ እንዲያዘጋጅላቸው በደብዳቤ መጠየቃቸውን አቶ ፊልጶስ ተናግረዋል፡፡ ጉዳዩ ከፍተኛ ጥንቃቄ የሚፈልግ መሆኑን ጠቁመው፣ ‹‹የፍትሕ ሥርዓት ማስከበር ከሕግ አወጣጥ ስለሚጀምር ረቂቁ በደንብ መፈተሽ አለበት፤›› ብለዋል፡፡

ለክልል በፌዴራል የሚሰጠው ሥልጣን፣ ስለባህላዊ የዕርቅ መፍቻ ዘዴዎች፣ ስለዋስትና መብት፣ ስለይግባኝና ሌሎችም በረቂቁ የተጠቀሱ ድንጋጌዎች ጥልቅ ውይይትና ዕይታ ስለሚፈልጉ፣ በተለይ የሕግ ባለሙያዎች ሳይወያዩበት እንዳይፀድቅ መጠየቃቸውን ፕሬዚዳንቱ ገልጸዋል፡፡ ምክር ቤቱ ከጉዳዩ አሳሳቢነት አንፃር ተመልክቶ ሐሳባቸውን እንደሚቀበላቸውም ያላቸውን እምነት ተናግረዋል፡፡ ምንጭ፡- ሪፖርተር ጋዜጣ ታምሩ ጽጌ እንደዘገበው
ዲ/ን ዳንኤል ክብረት

የታጠቁ ዘራፊዎች ወደ ባንክ ገብተው “አንድም ሰው እንዳይንቀሳቀስ! ገንዘቡ የመንግሥት ነው፤ ህይወታችሁ ግን የእናንተ ነው” ሲሉ ድምጻቸውን ከፍ አድርገው ተናገሩ፡፡
ሁሉም ሰው ወለሉ ላይ በደረቱ ተኛ፡፡ ይኼ “Mind Changing Concept” ይባላል፤ ከተለመደው ወጣ ባለ መልኩ የሰዎችን አስተሳሰብ መቀየር ነውና፡፡ ጠረጴዛ ላይ ተደፍታ የነበረች አንዲት ሴት የማጉረምረም ድምጽ ስታሰማ፣ ከዘራፊዎች አንዱ ቆጣ ብሎ፣ “እመቤት እንደሰለጠነ ሰው አስቢ እንጂ፡፡ ይህ እኮ ዘረፋ እንጂ አስገድዶ መድፈር አይደለም ” አላት፡፡ ፀጥ አለች፡፡ ይኼ “Being Professional” ነው፤ በሰለጠንክበት ጉዳይ ላይ ብቻ ትኩረት ታደርጋለህና፡፡
ዘራፊዎቹ ያለምንም ችግር ቤታቸው ገቡ፡፡ ከዘራፊዎቹ መካከል ልጅ እግሩ እና የMaster of Business Administration ተመራቂው የተዘረፈው ገንዘቡ እንዲቆጠር ሃሳብ አቀረበ፡፡ ነገር ግን በዕድሜ ታላቅ የሆነውና እስከስድስተኛ ክፍል ብቻ የተማረው ዘራፊ፣ በቁጣ “አንተ የማትረባ ደደብ! ይህን ሁሉ ገንዘብ ማን ይቆጥራል? ዛሬ ማታ በቴሌቪዥን ዜና ላይ ስንት እንደዘረፍን ይነግሩናል፡፡” ይኼ “Experience” ይባላል፡፡ ዛሬ ዛሬ በትምህርት ከሚገኝ ዕውቀት ይልቅ ‘ልምድ’ የበለጠ ዋጋ አለው፡፡
ዘረፋው ከተፈፀመ በኋላ፣ የባንኩ ማናጀር የባንኩን ሱፐርቫይዘር ጠርቶ በአስቸኳይ ፖሊስ እንዲጠራ ነገረው፡፡ ሱፐርቫይዘሩ ግን፣ “ቆይ ተረጋጋ! እየውልህ፣ መጀመሪያ ከካዘና 10 ሚሊየን አንስተን ለራሳችን እንውሰድ፡፡ ከዚያም ባለፉት ወራት የወሰድነውን 70 ሚሊየን እንጨምርበት፡፡ ለፖሊስ ሪፖርት ማድረግ ያለብን ይህን ገንዘብ ዛሬ ከተዘረፈው ጋር ደምረን ነው” አለው፡፡ ይኼ “Swim with the tide” ይባላል፡፡ የተፈጠረን አስቸጋሪ ሁኔታ ለራስ ጥቅም ማዋል እንደማለት፡፡ ሱፐርቫይዘሩም አለ፣ “በየወሩ ዘረፋ ቢካሄድብን እንዴት መልካም ነበር!”
በሚቀጥለው ቀን፡፡ ከባንኩ የተዘረፈው ገንዘብ 100 ሚሊየን እንደሆነ በቴሌቪዥን ዜና ተነገረ፡፡ ዘራፊዎች ደነገጡ፤ የዘረፉትንም መቁጠር ጀመሩ፤ ማመን አቃታቸው፤ ደግመው ቆጠሩ፤ ያው ነው፡፡ ትንሽ ቆይተው እንደገና መቁጠር ጀመሩ፤ ተመሳሳይ መጠን – 20 ሚሊየን ብቻ! በጣም ተናደዱ፣ “እኛ ህይወታችንን ለአደጋ አጋልጠን 20 ሚሊየን ብቻ ስናገኝ፣ የባንክ ማናጀሩ ቁጭ ብሎ 80 ሚሊየን እንዴት ያገኛል?” ከንፈራቸውን ነከሱ፣ ጠረጴዛውን በቡጢ ነረቱ፡፡ ሌባ ከመሆን መማር ይሻላል ማለት ይህ አይደል?i (Africa’s elites are lords of poverty! ያለው ማን ነበር?)
የማናጀሩ ፊት በፈገግታ እንደ ማለዳ ፀሐይ አብረቅርቋል፤ የደስታ ግምጃ አድምቆታል፡፡ በሽርክና ገበያው የተፈጠረበት ጉድለት ተሞልቶለታልና፡፡ ይኼንን “Seizing the opportunity” ይሉታል፡፡ ዋነኞቹ ዘራፊዎች እነማን ናቸው? የሚል ጥያቄ ማስቀመጥ ፈልጌ የነበረ ቢሆንም ከወቅቱ ጋር ላይሄድ ይችላል ብዬ በማሰብ ትቼዋለሁ፡፡
#ዲ/ን ዳንኤል ክብረት
21/10/2020

Legal Officer

 Bunna Insurance S.C. -Ethiopia

 

 Addis Ababa, Ethiopia

FULL_TIME Insurance Jobs in Ethiopia Legal Jobs in Ethiopia

Job Description

JOB REQUIREMENT

Qualification:- LLB Degree in Law

Experience: – 2 Years of Relevant Experience

Knowledge and Skill:- Excellent Communication Skill and Personality Written & Spoken Afaan Oromo Language is Advantageous

Place of work: – Addis Ababa, Head Office

Salary & Benefits: As per the salary scale of the Company with Other benefit packages.

HOW TO APPLY

Interested and qualified applicants fulfilling the above requirements can submit non returnable application letter, CV and copies of supporting credentials along with the original document in person to Human Resource Management Division located Around Sarbet behind Africa Union Bunna Insurance S.C Head Quarter within 5 working days of this announcement.

Human Resource Management Division

Bunna Insurance S.C

Tel. 011- 1- 57-60-54/011-1-56 57 78

About Bunna Insurance S.C. -Ethiopia
https://t.me/lawsocieties
Good morning law societies ‼️‼️‼️‼️
አለ ቻናላችን ዉስጥ በብዛት በአባልነት እየተሳተፉ ያሉ እካላትን ለማወቅ እና ሌሎች ስራዎችን መስራት ያስችለን ዘንድ አለ እነሆ ትብብርን ይጠይቃል። ከዚህ በታች በተዘረዘሩት መሰረት ሙሉልን ...........
public poll

📮fifth year (5) – 186
👍👍👍👍👍👍👍 42%

♨️LL.B – 79
👍👍👍 18%

🛎fourth year (4) – 50
👍👍 11%

💊third year (3) – 42
👍👍 9%

📕LL.M – 35
👍 8%

🩸second year (2) – 18
👍 4%

Re exam – 17
👍 4%

♥️other field graduate – 7
▫️ 2%

🧲First year (1) – 6
▫️ 1%

🔵Other field student – 4
▫️ 1%

👥 444 people voted so far. Poll closed.
1👍1
''የ5ኛ አመት የህግ ተማሪዎች የመዉጫ ፈተና(exit exam) ይራዘም ወይስ በታቀደለት ቀን ይሁን? ከታች ያሉትን ምርጫዎች click በማድረግ ድምፅ ይሥጡ እና የአብዛኛዉ ተማሪ ፍላጎት የትኛዉ እንደሆነ ለሚመለከተዉ አካል እናሣዉቅ‼️
public poll

❤️ይራዘም – 474
👍👍👍👍👍👍👍 80%

❤️እዳይራዘም – 87
👍 15%

consortium የሚወስነውን እንቀበላለን – 32
▫️ 5%

👥 593 people voted so far. Poll closed.
ለ5ኛ አመት Exit Exam ፈተና
የእናንተ ድምፅ ለቅዳሜው የ consortium ስብሰባ እና ውሳኔ ትልቅ ሚና ይኖረዋል ድምፅ ስጡ‼️‼️

ድምፅ እንዲሰጡ ❤️Share❤️ አድርጉ

https://t.me/lawsocieties
Forwarded from Lawyer Aschalew
ሰላም የተከበራችሁ አባላት! ከህዳር 1 - 4 ይሰጣል በተባለው የ exit exam ላይ ሀሳቤን ልስጥ።
በቅድሚያ፣ በግሩፑ ውስጥ በዚህ ጉዳይ ላይ የተንፀባረቁትን ሀሳቦች አይቻለሁ። አንዱ ይራዘም ሲል፣ ሌላው በተወሰነልን ግዜ እንፈተን ይላል! ለክርክሩ መነሻ የሆነውን መሰረታዊ ምክንያት ስንመረምር፣ ምክንያቱ የኮሮና ወደ ሀገራችን መግባትና መስፋፋት ሆኖ እናገኘዋለን። በዚህም ምክንያት፣ ግንቦት ላይ ሊሰጥ የታሰበው ፈተና የተለያዩ ምክረሀሳቦችን አልፎ በመጨረሻ ህዳር ላይ እንዲሆን መወሰኑን አውቀናል። ከምክረ ሀሳቦቹ አንዱ፣ በ2012 አ.ም በነሀሴ ወር ላይ ፈተናውን ለመስጠት ታስቦ እንደነበር አንዳንድ ምንጮች ተናግረዋል። ይህም የሆነው፣ ተመራቂዎች ሰኔ ወይም ሀምሌ ላይ ወደ ግቢ ይመለሳሉ፣ ለማንበብም ቢያንስ አንድ ወር ይኖራቸዋል በሚል ሀሳብ ነበር።
አሁንም፣ በህዳር እንዲሆን የተወሰነው፣ ተመራቂዎች በመስከረም ወር መጨረሻና በጥቅምት ወር መጀመርያ አከባቢ ወደ ግቢ ይመለሳሉ በሚል assumption እንደሆነ እናስባለን። ነገር ግን የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚንስቴር ወደ ግቢ የመመለሻ ቀኑን ከጥቅምት 23 - 30 በማድረጉ፣ የታሰበው የማንበቢያው ግዜ ሙሉ በሙሉ መክኗል፣ ባክኗል!
በግሩፑ የተነሱትን የሁለቱንም ወገን ተከራካሪዎች የመከራከሪያ ሀሳቦች እንደሚከተለው መዝነናል።
አንዱ ወገን፣ ፈተናው መራዘም አለበት በሚል አቋም የሚከተሉትን ምክንያቶች ዘርዝሯል።
1. ለሰባት ወራት ያህል ተፈታኞች ከlibrary ርቀው የትምህርት መፅሀፎች በሌሉበት፣ ኢንተርኔትና መብራት በሌለበት እልም ባለው የገጠሩ አከባቢ ስለሚኖሩ እነሱን ታሳቢ ማድረግ ያስፈልጋል። የተወሰነው ውሳኔ ግን ተፈታኞችን ያማከለ አይደለም።
2. ከተማ አከባቢ ሆነውም teaching materials በ soft copy ለማንበብ PC ወይም smart phone የሌላቸው ብዙ ተፈታኞችን ከግንዛቤ ውስጥ አላካተተም።
3. በጥቅምት 30 ገብተን ያለምንም ዝግጅትና orientation ህዳር አንድ መፈተን አስቸጋሪ ነው። የሚሉና ሌሎች ተያያዥነት ያላቸው የመከራከርያ ነጥቦች ተነስተዋል።
በሌላ በኩልም፣ ፈተናው መራዘም የለበትም የሚለውን አቋም የሚደግፉት ተከራካሪዎች፣ የሚከተሉትን የመከራከርያ ነጥቦች አንስተው ተከራክረዋል።
1. ለሰባት ወራት ያህል አንብበናል፣ ባናነብም ትምህርት አስጠልቶናል ቶሎ እንገላገል!
2. ገጠር ባሉ ተፈታኞች አታሳቡ፣ እነሱንም ወክላችሁ አትከራከሩ።
3. ምንም ምክንያት አያስፈልግም ዝም ብለን እንፈተን፣ ቀኑ ሲራዘም ፈተናው የሚቀር መሰላችሁ እንዴ?
3. ቀኑ በተራዘመ ቁጥር ያነበብነውን እንረሳዋለን። የሚሉና ይህን መሰል ሌሎች የመከራከሪያ ነጥቦችም ተነስተዋል።
እኛም፣ በሁለቱም ወገን የተነሱትን የመከራከሪያ ነጥቦች ካለው ተጨባጭ ሁኔታ አንፃር እንደሚከተለው መርምረናል።
ፈተናው እንዲራዘም የጠየቀው ወገን ያነሳቸው ነጥቦች በሙሉ አግባብነት ያለው መሆኑን አረጋግጠናል።
ነገር ግን፣ በሌላኛው ወገን የተነሳው ሀሳብ፣ 1. ገጠር የሚኖሩ ተመራቂዎችን መወከል አትችሉም ለሚለው፣ እነሱ ካልወከሏቸውና በእነሱ ቦታ ሆነው ካልተከራከሩላቸው፣ ገጠር ላሉ ተፈታኞች ማን ድምፅ ይሆናል? ምክንያቱም ኢንተርኔትም ሆነ መብራት ስለሌላቸው እንኳን ማጥናት አሁን የያዝነውን ክርክር እንኳ ለመካፈልና ድምፃቸውን ለማሰማት አልቻሉም። 2. ምንም ምክንያት አያስፈልግም ዝም ብለን እንፈተን ለሚለው ደሞ፣ ለሁሉም ነገር ምክንያት ያስፈልጋል። እንደውም እኛ የህግ ማህበረሰብ ውስጥ ያለነው ደሞ ከሌሎች በላይ በምክንያታዊነት ማመን ይጠበቅብናል! እንኳን እኛ፣ ከእያንዳንዱ የህግ አንቀፅና ንኡስ አንቀፅ ጀርባ ምክንያት ሊኖር ግድ ነው።
ኧረ ይብቃኝ አስለፈለፋችሁኝ!
ስለዚህ፣ ከላይ በጠቀስነው ምክንያት፣ የሚከተለውን ውሳኔ ሰጥተናል።
ውሳኔ;
1. ፈተናው መራዘም የለበትም ማለታችሁ ሳይሆን፣ ፈተናው እንዳይራዘም ያነሳችሁት የመከራከሪያ ሀሳቦች ተገቢነት የላቸውም ብለናል።
2. ከህዳር 1 - 4 እንዲሰጥ የተወሰነው ውሳኔ ተሽሮ የመፈተኛው ቀን እንዲራዘም የማዘዝ ድፍረት ስለሌለን፣ በትህትና ቀኑ እንዲራዘም እንጠይቃለን።

መዝገቡ አልተዘጋም።
የአስር ጣቶች የማይነበብ ፊርማ አለበት።
😂😂😂😂😂🤣🤣🤣🤣🤣🤣🤣🤣
የህግ የበላይነት ስንል ምን ማለታችን ነዉ?
*****

በዚህ አጭር ግንዛቤ የመስጫ ሰነድ ስለ የህግ የበላይነት ምንነት እና ለሀገራችን እና ለዜጎች ያለው ትርጉምና ከዚህ አንፃር ዜጎች ከሀገራቸው ምን እንደሚጠብቁ ወይም መብት እንዳላቸውና ከእነሱ የሚጠበቀውን ግዴታቸውን በመዳሰስ ግንዛቤ ለመስጠት ይሞክራል፡፡
........የህግ የበላይነት በጣም ሰፊና በርካታ መርሆችን ያቀፈ ፅንሰ ሀሳብ ነው፡፡ በአጭሩ እና ቀለል ባለ አገላለፅ የህግ የበላይነት ማለት በህግ መሠረት መግዛት እና መተዳደር ማለት ነው፡፡ በዚህ ውስጥ በርካታ ጉዳዮች ይኖራሉ፡፡ በህግ መሰረት መገዛት ሲባል በምን አይነት ህግ የሚለው የመጀመሪያ ጥያቄ ነው፡፡ ህግ ማለት በአንድ ሀገር የሚኖሩ ሰዎች መብትና ጥቅማቸው የሚረጋገጥበት አስገዳጅ በሁሉም ሊከበርና ሊፈፀም የሚገባ ስርአት ሲሆን ከህጎች ሁሉ የበላይ ከሆነው ህገ መንግስት ጀምሮ አዋጆችን፣ ደንቦችና መመሪያዎችን ያጠቃልላል፡፡

እነዚህ ህጎች የሚወጡት በአንድ ሀገር ባሉ ህዝቦች ፈቃድና ስምምነት መሰረት በቀጥታና በተወካዮቻቸው አማካኝነት በሚወስኑትና በሚደነግጉት መሰረት የሚወጣ ነው፡፡ በተጨማሪም ህጎቹ መሰረታዊ የህግ መርሆችን እና ሀገሪቷ የተቀበለቻቸውን አለማቀፍ አስገዳጅ ለሰው ልጆች የሚገቡ ሰብአዊ መብቶችን በተከተለ መንገድ እንዲሆን ይጠበቃል፡፡ እነዚህ ህጎች የህዝቡን እና በሀገሪቱ ውስጥ ያሉ ግንኙነቶችን የሚመለከቱ አጠቃላይ ጉዳዮችን የሚገዙ ናቸው፡፡ ከነዚህም ውስጥ ስርአተ መንግስትን፣ የመንግስት አስተዳደር ሁኔታን፣ ህዝቡ ራሱን በራሱ እና በተወካዮቹ አማካኝነት እንዴት እንደሚገዛ፣ እንደሚተዳደር፣ የምርጫ ስርአቱን፣ መብቶቹን፣ መብቶቹ የሚጥሱ ሰዎችም እንዴት በወንጀል እንደሚጠየቁ፣ ውሎች በምን መልኩ እንደሚገቡና እንደሚከበሩ፣ የንግድ ስርአቱ እንዴት እንደሚመራ፣ የቤተሰብና ጋብቻ ስርአት እንዴት እንደሚጠበቅ፣ ውዘተ የሚጠቀሱ ናቸው፡፡

የህግ የበላይነት ስንል በህግ መሰረት መገዛት ወይም መተዳደር ነው የሚለውን ካየን በኋላ ማን ባወጣው ህግ ነው የምንተዳደረው የሚለው ጥያቄ መታየት አለበት፡፡ የአንድ ሀገር ህዝብ የሚተዳደረው በተስማማበትና ራሱ በራሱ ሊሆነ ይገባል፡፡ ይህን ለማድረግ ደግሞ የአንድ ሀገር ህዝብ ሁሉም በአንድ ጊዜ እነዚህን ዝርዝር የአስተዳደር ህግጋት ላይ ለመስማማትም ሆነ ለማውጣት ስለማይችል ተወካዮችን መርጦ በተወካዮቹ አማካኝነት እና በዴሞክራሲያዊ መንገድ አብዛኛው በሚስማማበትና በተቻለ መጠን በክርከርና በድርድር በምክር ቤትና በጉባኤ መክሮና ዘክሮ ሁሉም የሚያማክል ህግ ይወጣል፡፡

በዚህ መልኩ በሚወጡ ህጎች የአንድ ሀገር ህዝቦች ይተዳደራሉ፡፡ በየደረጃው ያሉ ደንቦችና መመሪያዎችም በተመሳሳይ መልኩ በህዝብ ተወካዮች በሚሰጥ ፈቃድና ውክልና ወይም ስልጣን መሰረት በተቋማትና በአስፈፃሚዎች ይወጣል፡፡

የህግን ምንነት እና ህጉን ማን ያወጣዋል የሚለውን ጉዳዮች ካየን በኋላ የሚነሳው ጥያቄ ህጉን ማን ተግባራዊ ያደርገዋል እንዲሁም በህጉ መሰረት ዜጎችና ህዝቦች እየተዳደሩ መሆኑን ማን ያረጋግጣል ወይም በአጭሩ ማን በህጉ መሰረት ያስተዳድራል የሚለው ነጥብ መታየት አለበት፡፡ የህግ የበላይነት ሲባል የግለሰብ ወይም የንጉስ ወይም የሆነ ቡድን አስተዳደር ማለት አይደለም፡፡

ይልቁንም የህዝብ አስተዳደር ማለት ነው፡፡ ይህም የሚሆነው ህዝቡ የተስማማበት ወይም በተወካዮቹ አማካኝነት ባወጣው ህግ መሰረት አስተዳደር እንዴት እንደሚመረጥ፣ ለምን ያህል ጊዜ እንደሚያስተዳድር፣ እንዴት እንደሚያስተዳድር፣ ስልጣኑ ምን እንደሆነ፣ ሀላፊነቱ ምን እንደሆነ በተደነገገው መሰረት የሚመራ ነው፡፡ በዚህም መሰረት የህግ የበላይነት የሚረጋገጠው በህግ መሰረት በሚመረጥ የህዝብ ወኪል በመሆነ አስተዳደር በወጠለት ህግ መሰረት ሲያስተዳድር የህግ የበላይነት ተረጋገጠ ለማለት ይቻላል፡፡

ከዚህ መሰረታዊና ቀለል ባለ መልኩ ከቀረበው አጠቃላይ ሀሳብ በማስከተል በህግ ይዘት ውስጥ፣ በህግ አወጣጥ ሂደት እና በህጉ አተገባበር ወይም አፈፃፀም ረገድ ስላሉ የህግ መርሆች እንደሚከተለው በአጭሩ ይገለፃል፡፡

ህዝብ የሚተዳደርበት ህግ የበላይ የሆነው እና የበለጠ የሰፊው ህዝብ ተሳትፎና ቅቡልነት ያለው ህገ መንግስት የበላይነት መሆኑ ሊረጋገጥ ይገባል፡፡ አንድም በህገ መንግስቱ ባራሱ የህጎች ሁሉ የበላይ መሆኑ በማወጅና በተግባርም እርሱን የሚጣረሱ ሌሎች ህጎችና አፈፃፀሞች ወይም ተግባራት ውድቅ እንዲሆኑ የሚደረግበት ስርአት መኖር ይህን ያረጋግጣል፡፡ ከዚህ በተጓዳኝ ለሰብአዊ መብቶች ከፍ ባለ ደረጃ በህግ እውቅና መሰጠቱ እና ተጥሰው ሲገኙም መፍትሄ የሚሰጥበት ስርአት እና የዚህም ውጤታማ አፈፃፀም መኖር የህግ የበላይነት መኖር ማሳያ ነው፡፡

በተመሳሳይ እኩልነት እና ፍትሀዊነት ለህግ የበለይነት መኖር አስፈላጊ መርሆች ናቸው፡፡ ህግ ለሁሉም በእኩል የሚየገለግል መሆኑ እና ሁሉም ከህግ በታች መሆኑ ብሎም ህጉ በሁሉም ላይ በእኩል ሲፈፀም የህግ የበላይነት መኖሩን ያመለክታል፡፡ ህጉ በሚፈፀምበት ወቅትም በፍትሀዊነት እና ሰብአዊነት በተላበሰ መለኩ በርትእ በመተሳሰብና በወንድማማችነት ሲፈፀም የበለጠ ፍትሀዊ ይሆናል፡፡

በሌላ በኩል የህዝብ ተሳትፎ የሚረጋገጥበት የዴሞክራሲ ስርአት ማለትም የምርጫና የህዝብ በመንግስት አስተዳደር የሚኖረው ተሳትፎ የተረገጋገጠና የተከበረ መሆኑ ሌላው ማሳያ ነው፡፡ የመንግስት አስተዳደርም በግልፅነትና ህዝብን በማሳተፍ መከወኑ በአንፃሩም ስህተትና ጥፋት ሲያጋጥምም የተጠያቂነት ስርአት መኖሩ ስርአቱ የተደላደለና የዘፈቀደ አለመሆኑ ተቋማዊ መሆኑን ጥሩ ማሳያ ይሆናል፡፡
ይህን ተጠያቂነት ለማጠናከርም ስልጣን በአንድ አካል ላይ እንዳይከማች የመንግስት ስልጣንን የሚከፋፍል የህግ ስርአት መዘርጋቱ የህግ የበላይነትን የበለጠ ለማረጋገጥ ያግዛል፡፡ የተከማቸ ስልጣን ለቁጥጥርና ተጠያቂነት አመቺ ባለመሆኑ አስተዳደሩ በህግ አውጪ፣ አስፈፃሚና ተርጓሚ ወይም ዳኝነት አካላት መከፋፈሉ አንዱ የሰራውን ሌላው ለመከታተልና ለማረም እድል በመስጠት የተጠናከረ የህግ የበላይነትን ያሰፍናል፡፡ ከዚህ አንፃር ሌላው በህግ የበላይነት ውስጥ ተግባራ ሆኖ ሊታይ የሚገባው መርህ የዳኝነት ነፃነት ነው፡፡

የዳኝነት አካሉ ከአስፈፃሚው ውጭ ሆኖ ዜጎች ከመንግስትም ሆነ ከሌሎች ግለሰቦች በደል ወይም የመብት መጓደል ሲደርስባቸው ጥያቄያቸውን አቀርበው መፍትሄ የሚያገኙበትን ዋስትና የሚሰጥ ይሆናል፡፡ በመጨረሻም ከዚሁ ጋር በተያያዘ የሚነሳው መርህ የመሰማት መብት ወይም (ዲዩ ፕሮሰስ) ስርአት ሊኖር ይገባል፡፡ በህግ መሰረት የዜጎችን መብትና ጥቅም የሚነካ እርምጃ ወይም ውሳኔ ሊወሰድ ሲል የሚመለከታቸውን ሰዎች የማስታወቅ ቅሬታም ካላቸው እንዲያቀርቡ እና በፍትሀዊነት ውሳኔ የሚሰጥበት ስርአት መኖሩ የህግ የበላይነትን የሚያረጋግጥ ይሆናል፡፡

በአጠቃላይ የህግ የበላይነት ለመልካም አስተዳደር፣ ለእድገት እና ለሰላም ከፍተኛ ጠቀሜታ ያለው ትልቅ እሴት ነው፡፡ ለህግ የበላይነት መረጋገጥ ደግሞ ከላይ እንደተመለከተው እያንዳንዱ ዜጋም ሆነ የመንግስት አካልና ተቋማት ትልቅ ድርሻና ሀላፊነት እነዳለባቸው በግልፅ የሚያመለክት ነው፡፡ ይህም ሲባል መንግስት እና ሀላፊዎች በህግ መሰረት ብቻ በግልፅነትና ህዝብን በማሳተፍ ስራቸውን ማከናወን፣ ህግ አውጪዎች ምክንያታዊና ፍትሀዊ ህጎችን እንዲሁም የተሟሉ የህግ ስርአቶችን መዘርጋት፣ የዳኝነት አካሉ የዜጎችን የመሰማት መብት ጠብቆ በነፃነት ፍትሀዊ ውሳኔዎችን መስጠት
፣ ዜጎች ደግሞ አንዱ የሌላውን በህግ የተሰጠ መብት ማክበር፣ በመንግስት አስተዳደር ተሳትፎ ማድረግ፣ ጥያቄዎችን እና መብትን በህግ ስርአት መሰረት ማስፈፀምይጠበቅባቸዋል፡፡
በመሆኑም ዜጎች እና የህዝብ አገልጋዮች ይህን ሰፊ የህግ የበላይነት ማእቀፍ መረዳትና መብትና ግዴታን ማወቅ ለህግ የበላይነት መስፈን...
🙏1
እና መረጋገጥ እንዲሁም መጠናከር አስፈላጊና ወሳኝ ነው፡፡
አለ ቻናላችን ዉስጥ በብዛት በአባልነት እየተሳተፉ ያሉ እካላትን ለማወቅ እና ሌሎች ስራዎችን መስራት ያስችለን ዘንድ አለ እነሆ ትብብርን ይጠይቃል። ከዚህ በታች በተዘረዘሩት መሰረት ሙሉልን ...........
public poll

📮fifth year (5) – 186
👍👍👍👍👍👍👍 42%

♨️LL.B – 79
👍👍👍 18%

🛎fourth year (4) – 50
👍👍 11%

💊third year (3) – 42
👍👍 9%

📕LL.M – 35
👍 8%

🩸second year (2) – 18
👍 4%

Re exam – 17
👍 4%

♥️other field graduate – 7
▫️ 2%

🧲First year (1) – 6
▫️ 1%

🔵Other field student – 4
▫️ 1%

👥 444 people voted so far. Poll closed.