#የአፍሪካ_አመራር_ልህቀት_አካዳሚ እና #የሴቶች_እና_ማሕበራዊ_ጉዳይ_ሚኒስቴር በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራረሙ።
ስምምነቱን የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ፕሬዚደንት አቶ ዛዲግ አብርሃ እና የሴቶች እና ማሕበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ክብርት ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር) ተፈራርመዋል።
የኢትዮጵያንና የአፍሪካን ሴቶች፤ ወጣቶችና አካል ጉዳተኞችን የአመራር አቅም ለማጎልበት በሚያስችሉ ዘርፎች ላይ በጋራ ለመስራት ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ እና አካዳሚው ከስምምነት ላይ እንደደረሱም በፊርማው ስነ-ስርዓት ላይ ተገልጿል።
የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ፕሬዚደንት አቶ ዛዲግ አብርሃ በስምምነቱ ላይ እንደገለጹት አካዳሚው በለውጥ፤ ማስፋት እና ሽግግር ሂደት ውስጥ እንደሚገኝ ጠቁመው፤ ሴቶች በሀገራችን ማህበራዊ፤ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ እንቅስቃሴዎች ውስጥ ያላቸውን ቁልፍ ሚና በመረዳትና በመገንዘብ በሁሉም መስክ ተሳታፊና ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማድረግ እየተሰራ እንደሆነና አካዳሚው ከቢል እና ሜሊንዳ ጌትስ ፋውንዴሽን ጋር በመሆን የሴቶች የአመራር ልማት ፕሮግራም ፕሮጀክት ቀርጾ ከሁሉም የፌዴራል መንግስት እና ከከተማ አስተዳደሮች ተቋማት የተውጣጡ መካከለኛ ሴት አመራሮችን አቅም እየገነባ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

👍1

አቶ ዛዲግ አያይዘውም ፊንላንድ ሄልሲንኪ ከሚገኘው Global Center for Gender Equality ከተሰኘ ዓለምአቀፍ ተቋም ጋር በPublic Leadership for Gender Equality የአመራር ልማት ፕሮግራም ማዕቀፍ በመንግስት ተቋማት ውስጥ ያሉ የሴት አመራሮችንና ባለሙያዎችን የጾታ እኩልነት ለማረጋገጥ የሚሰራ ፐሮጀክት በአምስት ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር በጀት እንደታቀደ እና በቅርቡ ይፋ እንደሚደረግ ገልጸዋል።
በአካዳሚው ከሴቶች የአመራር ልማት ፕሮግራም ጋር በተያያዘም ከሁሉም የአፍሪካ ሀገራት ሁለት ሁለት ሴት አመራሮችን በመምረጥ ለስድስት ወራት ያህል በአመራር ልማት ፕሮግራም ውስጥ እንዲያልፉ የሚያስችል ፕሮጀክት ተቀርጾ ወደ ስራ ለመግባት እንደተቻለም ፕሬዚደንቱ ተናግረዋል።
በሀገራችን ያለውን የሴቶች፤ ወጣቶችና አካል ጉዳተኞች ችግር ለመቅረፍ በትብብር መስራቱ ከፍተኛ ሚና እንደሚኖረውም አቶ ዛዲግ አስታውሰው፤ ከሚኒስቴር መስሪኣ ቤቱ ጋርም በአራት ዋና ዋና ጉዳዮች በአመራር ልማት ፕሮግራም፤ በሴቶች የአመራር ልህቀት ሽልማት፤ በአፍሪካ የሴቶች ሽግግር ማዕከል እና በጋራ ጥናትና ምርምር ማድረግ በሚያስችሉ ስራዎች ላይ በትብብር ለመስራት ስምምነት ላይ መደረሱን ተናግረዋል።
የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትሯ ክብርት ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር) በበኩላቸው ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የሴቶች፣ ወጣቶችና አካል ጉዳተኛ ዜጎችን መብት ለማስከበር፣ በየዘርፉ ያላቸውን እኩል ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እና በየደረጃው ለማብቃት ከተለያዩ ባለድርሻና አጋር አካላት ጋር እየሰራ ይገኛል ብለዋል።
ሚኒስቴሩ ከዚህ ቀደም ከአካዳሚው ጋር በጋራ በፌዴራልና በክልል የሚገኙ ሴት አመራሮችን ውሳኔ ሰጪነት ሚና ለማሳደግ የአቅም ግንባታ ፕሮግራሞችን በመቅረፅ ተግባራዊ ሲያደርግ መቆየቱን ገልፀዋል።
ስምምነቱ የአስፈጻሚ አካላትን አቅም በመገንባት የአፍሪካ የብልፅግና ተምሳሌት የሆነች ኢትዮጵያን ለመፍጠር በሚደረገው ጥረት ውስጥ የአመራር ብቃት ያላቸውና የመሪነት ሚና የሚጫወቱ ሴቶች፣ ወጣቶችና አካል ጉዳተኛ ዜጎችን ለማፍራት ያለመ መሆኑን ተናግረዋል።
አካዳሚው ከኢትዮጵያ ባለፈ ለአፍሪካ ሀገራት ተምሳሌት ሊሆን የሚችል ትልቅ ስራ እየሰራ እንደሚገኝ ገልፀው ስምምነቱ ወደ ተግባር እንዲሸጋገር እና ስኬታማ እንዲሆን ትኩረት ሰጥቶ በቅንጅት ይሰራል ብለዋል።

👍3